➕➕ የማድያት እውነታዎች➕➕
🖲ማድያትን ለመለየት ቀላል ቢሆንም ነገርግን ፊት ላይ የሚወጣ ጥቁረት ሁሉ ማድያት አይደለም።
🖲ማድያትን በወጣበት ቦታ እና በያዘው የቆዳ ክፍል መሰረት ይከፋፈላል።
🖲አብዛኛውን ግዜ ከህክምና በኋላ እየተመላለሰ የመለያስቸግረው ማድያት የስረኛውን የቆዳ ክፍል የያዘ ከሆነ ነው።
🖲ማድያት የያዘው የቆዳ ክፍልን ለመለየት በቆዳ ሀኪም መታየት ያስፈልጋል።
🖲ማድያት የሚመጣበት አንድ ብቻ ምክኒያት የለውም፣ የተለያዩ ምክኒያቶች ማለትም፣
👉በተፈጥሮ
👉ለፀሀይ ጨረር መጋለጥ
👉ባለ ሁለት ሆርሞን የእርግዝና መከላከያ
👉እርግዝና
👉ከታይሮይድ ሆርሞን ማነስ እና ምክኒያቱ በማይታወቅ ሁኔታም ሊመጣ ይችላል።
🖲በእርግዝና ምክኒያት የመጣ ማድያት ከወሊድ በኋላ እየደበዘዘ ይጠፋል፣ ነገር ግን ከ ወሊድ በኋላ ከ 8 ወር በላይ ከቆየ እና እየሰፋ ከመጣ ህክምና ያስፈልገዋል።
🖲ማድያትን ሙሉ በሙሉ እንዳይመለስ አድርጎ የሚያጠፋ አንድ ብቻ የሆነ የሚቀባ መዳኒት የለም።
🖲ነገር ግን በተለያየ መንገድ የማድያት ጥቁረትን የሚያጠፉ፣ በሚቀባ መልክ የተዘጋጁ መዳኒቶች በሀኪም ትእዛዝ ይሰጣሉ።
🖲በዚህ መልኩ ማድያቱ ሲጠፋ፣ ተመልሶ እንዳይመጣ እና በህክምና ግዜ የሚሰጡ መዳኒቶች የቆዳ ቁጣ እንዳያስከትሉ ረዘም ላለ ግዜ ክትትልን ይፈልጋል።
🖲 ተጨማሪ መረጃ በ YouTube ላይ አስቀምጫለሁ ፣ አመሰግናለሁ ።
👇👇👇👇👇
https://youtu.be/KXS9zzDVH-g

YouTube
ማድያት እየተባሉ በስህተት የሚታዩ የፊት ቆዳ ጥቁረቶች እና ማድያት | Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ
👍201❤125🥰41🤔18😱5👏4
➕➕ ለማድያት እና ለጥቋቁር ነጠብጣቦች ➕➕
🖲ማድያት እየተመላለሰ የሚታስቸግረው የስረኛውን የቆዳ ክፍል የያዘ ከሆነና ከህክምና በኋላ ማድያትን ለሚያስከትሉ እና ለሚያባብሱ ምክኒያቶች ተጋላጭነት ከቀጠለ ነው።
🖲እነዚህ ምክኒያቶች
👉ምግብ ከማብሰል ጋር ተያይዞ እና በተለያዩ ምክኒያቶች ለከፍተኛ ሙቀት መጋለጥ
👉የፀሀይ መከላከያዎች ባግባቡ ባለመጠቀም እና፣ ለፀሀይ ጨረር መጋለጥ
👉ጭንቀት እና ድባቴ መኖር እና ቆዳ ላይ ቁጣ ሊያስከትሉ የሚችሉ ቅባቶችን ወይም በቤት የሚዘጋጁ ቅመሞችን በመጠቀም
🖲ማድያት ሊባባስ እንዲሁም ሊመላለስ ይችላል።
🖲ይህ እንዳይሆን ታድያ፣ በህክምና ማድያቱ ከጠፋም በኋላ፣ ከሀኪም ትእዛዝ ውጪ በቅባት መልክ የሚገኙ የጥቁረት ማደብዘዣዎችን እና የፀሀይ መከላከያዎችን አዘውትሮ በመቀም ማድያቱ እንዳይመለስ ይረዳል።
🖲ከዛ ውጪም በብጉር እና በአንዳንድ የቆዳ ቁጣዎች ምክኒያት የሚመጣን ጥቋቁር ነጠብጣብ ማደብዘዝም ያስችላል።
🖲እነዚህን የጥቁረት ማደብዘዣ ቅባቶችን እና የፀሀይ መከላከያ አይነቶችን፣ በ youtube ላይ አስቀምጫለሁ።
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/KDy5sHrAhfA

👍213❤84🥰21🤔13😱5🙏3😢2
➕➕የፊት መታጠቢያዎች➕➕
🖲ከደረቅ ሳሙና ይልቅ የፊት ቆዳን ለማፅዳት የተዘጋጁ ብዙ አይነት መታጠቢያዎች አሉ።
🖲በጠቅላላው Cleanser ተብለው ይጠራሉ፣ አይነታቸው እና አሰራራቸው፣ እንደታሰበላቸው አላማ ይለያያሉ። ለምሳሌ፣
👉ቆሻሻን ለማስለቀቅ
👉የፊት ወዝን ለመቀነስ
👉የብጉር ጥቃቅን ሽፍታን ለመቀነስ
👉የቆዳ ቅርፊትን ለማንሳት
👉ሜካፕን ለማስለቀቅ ፣ እንደ ቆዳው ይዘት ተቀምመው ለገበያ ይቀርባሉ።
🖲ከነዚህም ውስጥ በብዛት የሚታወቁት የ መታጠቢያ አይነቶች
👉ባለ አረፋ መታጠቢያ ( Foaming Cleanser )
👉ዘይት አዘል መታጠቢያ (Oil based Cleanser)
👉የቆዳ ቅርፊት ማንሻ ( Scrub )
👉ውሀ የማያስፈልገው የፊት ማፅጃ ( Milk Cleanser, Toner)
👉ደረቅ እና እርጥብ የፊት መጥረጊያ ጨርቆች ( Substrate Cleansers) በመባል ይታወቃሉ።
🖲ከነዚህ ውስጥ፣ ለወዛም ቆዳ ተስማሚ የሚሆኑት መታጠቢያዎች፣ ባለ አረፋ እና በውስጣቸው Salicylic Acid የሚይዙ ቢሆኑ ተመራጭ ነው።
🖲ለደረቅ እና ለሚቆጣ ቆዳ ደሞ፣ ውሀ የማያስፈልገው የፊት ማፅጃ (Milk Cleanser) በውስጡ የሚይዛቸው ንጥረ ነገሮች፣ ለቆዳ ተስማሚ ናቸው።
🖲ስለ ሁሉም የክሊንዘር አይነቶች በሰፊው ማብራሪያ YouTube ላይ አስቀምጫለሁ። አመሰግናለሁ።
👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/pLn8A8ynlxI

ለየትኛው ቆዳ ይሻላል | የፊት መታጠቢያ አይነቶች | Cleansers
👍265❤96🥰32👏5😍1
➕➕ተደጋጋሚ የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን➕➕
🖲 የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን በግብረስጋ ግንኙነት አይተላለፍም፣ ነገር ግን፣ በአንድ ጓደኛ ያልተወሰነ እና ተደጋጋሚ የግብረስጋ ግንኙነት፣ ለሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን አጋላጭ ነው።
🖲በአመት ሶስት ግዜ እና ከዛ በላይ የሚመጣ የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን፣ በተደጋጋሚ ግዜ የሚመጣ የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን ወይም በህክምናው (Recurrent UTI) ይባላል።
🖲ከ 50 እስከ 80 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች በህይወት ዘመናቸው አንድ ግዜ የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን ያጋጥማቸዋል። ከነዚህም ውስጥ ከ 20 እስከ 30 በመቶ የሚሆኑት ደሞ በድጋሚ ሊታመሙ ይችላሉ።
🖲ከወንዶች ይልቅ በሴቶች ላይ አብዝቶ ይከሰታል፣ ነገር ግን ከ 50 አመት የእድሜ ክልል በኋላ በወንድም በሴትም እኩል ሊከሰት ይችላል።
🖲አንድ ሴት ለመጀመሪያ ግዜ የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽ የታመመችው ከ 15 አመቷ በፊት ከሆነ፣ በቀጣይ እድሜዋ ተደጋጋሚ የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን ሊያጋጥማት ይችላል።
❌ከግንኙነት በኋላ ቶሎ ሽንት አለመሽናት
❌መሀፀን በሚታጠብበት ግዜ ውሀ እና ሳሙናን እንዲሁም ጣትን ወደውስጥ አስገብቶ መታጠብ
❌ሽንት በመጣ ግዜ ቶሎ አለመሽናት
❌ጥብቅ ያሉ ልብሶችን ማዘውተር
❌የመታጠቢያ ገንዳ ውስጥ ለረጅም ሰአት መዘፍዘፍ
❌ሴቶች ሰገራ ከተቀመጡ በኋላ ከኋላ ወደፊት ማፅዳት የመሳሰሉት ድርጊቶች
🛑 ለሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን አጋላጭ ምክኒያቶች ናቸው።
🖲የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን ሲኖር ጥብቅ ክትትል እና የህክምና ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባ ሰዎች፣
👉እርጉዝ ሴቶች
👉የስኳር በሽታ ያለባቸው፣
👉የስተሮክ እና በአደጋ ወይም በበሽታ ምክኒያት የማይንቀሳቀሱ ታካሚዎች፣
👉የHIV እና የካንሰር ታካሚዎች እና እድሜ ጠገብ አዛውንቶች ናቸው።
ሙሉ መረጃውን በ YouTube ቻናሌ ላይ አስቀምጫለሁ።
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/Add7eDCFq50

በቤት ውስጥ ለመከላከል የሚረዱ መንገዶች | ተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን | Dr. Seife
👍332❤94🥰15👏13😱7
➕➕ቆዳ ማርጠቢያ (Moisturizers ) ➕➕
🖲ጥርት ያለ እርጥብ ገፅታ ያለው ቆዳ እንዲኖር እንጂ የቆዳው ቀለም መቅላቱ ግዴታ አይደለም
🖲አንድ ሰው ያለው የቆዳ ይዘት እንጂ፣ የተፈጥሮ ቆዳ ቀለም የቆዳውን ጤንነት አይወስነውም።
🖲የቆዳን ጤንነት ለመጠበቅ ሶስት መሰረታዊ የቆዳ ጤንነት አጠባበቅ መንገዶች ያስፈልጋሉ
👉የቆዳ ንፅህናን መጠበቅ
👉ቆዳን ከፀሀይ ጨረር መከላከል እና
👉የቆዳን እርጥበት በጠበቅ ናቸው።
🖲ቆዳ ሁሌ የሚደርቅ ከሆነ፣ የቆዳው ጤንነት ይዛባል እንዲሁም ከእድሜ በፊት ቶሎ ያረጃል።
🖲የቆዳን እርጥበት ለመጠበቅ የሚያስፈልጉት ዋነኛ ተግባሮች ውስጥ፣
👉በቂ ውሀ መጠጣት
👉ሲጋራ አለማጨስ
👉ሰውነትን በቀን ውስጥ በተደጋጋሚ ግዜ አለመታጠብ
👉የልብስ ሳሙናን ለቆዳ ንፅህና አለመጠቀም
👉ከታጠቡ በኋላ የቆዳ ማርጠቢያዎችን መጠቀም የመሳሰሉት ይገኙበታል።
🖲የቆዳ ማርጠቢያ ቅባቶች በ 4 አይነት መልኩ ይገለፃሉ፣ ዝርዝራቸውን በቪዲዮው ላይ አስቀምጫለሁ።
🖲ለማንኛውም ግሊስሪንን የሚይዙ የቆዳ ማርጠቢያዎች ፣ እንዲሁም በውስጣቸው የፀሀይ መከላከያ እና ቪታሚን E የሚይዙ የቆዳ ማርጠቢያዎች፣ ለሁሉም አይነት የቆዳ ይዘት ተስማሚ ናቸው።
🖲ስለነዚህ ምርቶች አይነት በዝርዝር YouTube ላይ አስቀምጫለሁ ። አመሰግናለሁ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/3PSI8aAaWKQ

የፊት ክሬም | የቆዳ ማርጠቢያዎች | Face cream | Moisturizers | Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ #drseife #medical #habesha
👍202❤194👏41🥰34
➕➕ያልተፈለገ ቦታ ላይ ፀጉር ሲበቅል ➕➕
🖲ሴቶች ልክ እንደ ወንዶች ከንፈር እና ደረት እንዲሁም በብልት አካባቢ የተጋነነ ፀጉር የሚያበቅሉ ከሆነ በህክምናው Hirsutism ይባላል።
🖲ምክኒያቱም በነዚህ የሰውነት ክፍል ላይ ያሉ ፀጉሮች በ ወንዴ ሆርሞን ስለሚታዘዙ ነው።
🖲ነገር ግን ከሆርሞን ጋር ባልተገናኘ መልኩ ወንዶችም ሴቶችም ከልክ ያለፈ ወይም በሰውነታቸው ላይ የተጋነነ የፀጉር አበቃቀል ሲኖር ደሞ በህክምናው Hypertrichosis በመባል ይጠራል።
🖲የስሙ ልዩነት ያስፈለገው፣ አመጣጡ እና የህክምና ምርመራ አማራጮችን ለመለየት ነው።
🖲ስለነዚህ 2 ችግሮች በምስል የተደገፈ መረጃ እና የህክምና አማራጮቻቸውን በ YouTube ላይ አስቀምጫለሁ።ትምህርት እንደምታገኙበት ተስፋ አደርጋለሁ። አመሰግናለሁ
ለመመልከት ይሄን ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/lXW2ZVdxrHA

👍237❤89🥰13👏4😱2
➕➕ ሬንጅ መድሀኒት ይሆናል?➕➕
🖲ሬንጅ መዳኒት ሊሆን ይችላል፣ አዎ አብዛኞቻችን የምናቀው አስፋልት ሲሰራበት ነው። Coal Tar ወይም ሬንጅ።
🖲በህክምናው ዘርፍ፣ በዋነኝነት ለፎረፎር እና ሶርያስስ ለተባለ ስር ሰደድ የቆዳ በሽታ ህክምና፣ በሻምፖ፣ በሳሙና እና በክሬም መልክ ተቀላቅሎ ህክምና ላይ ይውላል።
🖲አንዳንዴ ጥራታቸውን ያልጠበቁ የመዋቢያ ግብአቶች ውስጥ፣ ለማቅለሚያነት ተብሎ በድብቅ ሊጨመር ይችላል።
🖲ለምሳሌ አንዳንድ የጥቁር ሂና አይነቶች በውስጣቸው ይሄንን ሬንጅ ይይዛሉ ፣ነገር ግን በላያቸው ላይ ሬንጅ ወይም Coal Tar እንደሚይዙ አይፃፍባቸውም።
🖲ይህ Coal Tar ታዲያ አደገኛነቱ፣ አንዳንድ ሰዎች ላይ የፀሀይ ንክኪ ሲኖረው ቆዳን በከፍተኛ ሁኔታ ሊያስቆጣ ይችላል።
🖲ይህም የሆነበት ምክኒያት፣ አንዳንድ ንጥረ ነገሮች የፀሀይ ንክኪ ሲኖራቸው፣ ይዘታቸው ይቀየር እና ቆዳን እንዲቆጣ ያደርጉታል።
🖲ስለዚህም ከዚህ በፊት ተጠቅማችሁ የማታቋቸውን የመዋቢያ ግብአቶች ከመጠቀማችሁ በፊት፣ ቅድሚያ በትንሽ ቆዳ ላይ አስቀድሞ መሞከር ያስፈልጋል።
🖲ከዚህ ባለፈ መልኩ ደሞ ፀሀይ በብዙ መልኩ ቆዳን ሊጎዳ እንደሚችል ግልፅ ነው።
🖲ከፀሀይ ንክኪ ጋር በተያያዘ መልኩ የሚመጡ የቆዳ ጉዳቶችን፣ እንዲሁም የፀሀይ መከላከያ አጠቃቀም ላት የሚታዩ ጉድለቶችን በተመለከተ ሰፋ ያለ መረጃ YouTube ላይ አስቀምጫለሁ።
👇👇
https://youtu.be/KkV-tlknCEo
መልካም ግዜ።

👍239❤69🥰18🤩3
➕➕ ቫይታሚን ዲ ➕➕
🖲ለረጅም ግዜ የቆየ ካልሆነ በቀር ወዲያውኑ የሚታይ የህመም ምልክት የለውም።
🖲ከፍተኛ የቫይታሚን ዲ እጥረት ያለባቸው ሰዎች የደረት እና የቋንጃ አጥንትታቸው ላይ ጫን ተብሎ ሲነካ ህመም ይሰማቸዋል
🖲አንዳንዴ ደሞ የትከሻ እና ክንድ መዛል ይኖራቸዋል። እንዲሁም አልፎ አልፎ የመሚመጣ የእግር ህመምም ሊያጋጥማቸው ይችላል።
🖲የእጅ እና የትከሻ መዛል ካለ፣ ከቫይታሚን ዲ እጥረት ባሻገር በተለያዩ፣ የጡንቻ ፣የነርቭ እና የደምስር ችግሮች ምክኒያትም ሊፈጠር ይችላል።
🖲ከሌላ ተጌዳኝ ችግር የመጣ ካልሆነ በቀር፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ቫይታሚን ዲ ከካልሲየም ጋር በመዳኒት መልኩ ሲሰጥ፣ ወዲያውኑ በተወሰነ ግዜ ውስጥ ፈውስ ይኖረዋል።
🖲የፀጉር መነቃቀል ያለባቸው ሰዎች እንዲሁም አንዳንድ የውስጥ ቁጣን ተከትለው የሚመጡ በሽታዎች ያሉባቸው ሰዎች ላይ፣ አንዳንዴ የቫይታሚን ዲ እጥረት ይታያል።
🖲የቫይታሚን ዲ ይዘት የሚለካው IU በሚባል ልኬት ነው፣
(1 mg) ቫይታሚን ዲ ከ (40,000 IU) ጋር እኩል ነው።
👉ከአንድ አመት በታች ያሉ ህፃናቶች በቀን 400 IU ወይም(0.001 mg ) ቫይታሚን ዲ በቂያቸው ነው።
👉ከ 1 አመት እስከ 70 አመት ላሉ ሰዎች በቀን 600 IU ወይም (0.0015 mg) ቫይታሚን ዲ በቂያቸው ነው።
👉ከ 70 አመት በላይ ያሉ አዛውንቶች በቀን 800IU ወይም (0.002 mg) ቫይታሚን ዲ ያስፈልጋቸዋል።
🖲ልብስን አውልቆ 30 ደቂቃ ያህል የጠዋት ፀሀይ ላይ የተቀመጠ ሰው ፣ ቀይ ከሆነ ከ 20 እስከ 30ሺ IU የሚሆን ቪታሚን ዲ፣ እንዲሁም ጠይም የሆነ ሰው ላይ ደሞ ከ 8 እስከ 10ሺ IU የሚሆን ቪታሚን ዲ በ 24 ሰአት ውስጥ ሰውነት ማዘጋጀት ይችላል።
🚩እድሜ ጠገብ አዛውንቶች ሰውነታቸው በፀሀይ ጨረር ቫይታሚን ዲን የማምረት አቅሙ ይቀንሳል
🚩ህፃናቶች ከተወለዱ ከ 2 ሳምንት በኋላ በቀን ከ15 እስከ 20 ደቂቃ የጠዋት ፀሀይ ያስፈልጋቸዋል።
🚩ታዲያ ፣ለህፃንም ሆነ ላዋቂ ፣ፀሀይ በሚሞቅበት ግዜ ማናቸውንም ቅባቶች መቀባት ፈፅሞ አስፈላጊ አይደለም
🖲ከዚህ ውጪ ቫይታሚን ዲን ከምግብ ማግኘትም ይቻላል።
🖲ቫይታሚን ዲ እንደሌላው በብዙ የምግብ ዘርፎች ውስጥ አይገኝም፣
🖲የአሳ ዘይት፣ የአሳ ስጋ፣ ቱና ፣ ጉበት እና እንቁላል የመሳሰሉት ምግቦች በደረጃ የተቀመጠ የ ቫይታሚን ዲ ይዘት አላቸው።
👉አንድ የሻይ ማንኪያ የአሳ ዘይት አንድ ሰው በቀን ውስጥ የሚያስፈልገውን 2 እጥፍ ቫይታሚን ዲ ይይዛል።
👉100 ግራም የአሳ ስጋ ወይም ቱና ደሞ ከ 70 እስከ 90 በመቶ የሚሆነውን በቀን ውስጥ የሚያስፈልገውን የቫይታሚን ዲ መጠን ይይዛል።
👉ጉበት፣እና እንቁላል ደሞ አነስተኛ መጠን ያለው ቫይታሚን ዲ በውስጣቸው ይይዛሉ።
🖲የታሸጉ ምግቦች ላይ በተለይ ለህፃናት እንዲሁም ላዋቂ የሚዘጋጁ የዱቄት ወተቶችን ጨምሮ፣ አንድ ሰው በቀን ውስጥ ሊያስፈልገው የሚችለውን የቫይታሚን ዲ መጠን በውስጣቸው ይጨመርባቸዋል።
🖲ከዛ ባለፈ ደሞ፣ ቫይታሚን ዲ በእንክብል እና በሽሮፕ መልክ በተለያየ መጠን ይገኛል
🖲ከፍተኛ የቫይታሚን ዲ እጥረት የተገኘበት ሰው በ 50ሺ IU የተዘጋጀውነን ቫይታሚን ዲ 1 ፍሬ በሳምንት አንድ ግዜ እንደ እጥረቱ ደረጃ ከ 3 ሳምንት እስከ 3 ወር ሊሰጠው ይችላል
🖲ከቫይታሚን ዲው ጋር አብሮ እንዲሰራ ካልሲየምም አብሮ ይታዘዛል
🖲የአጥንት መሳሳት ላለባቸው አዛውንቶች ደሞ በቀን 1000 IU ቫይታሚን ዲ ከካልሲየም ጋር እስከ 3 ወር ድረስ ሊሰጥ ይችላል።
🚩በ 50ሺ IU የተዘጋጀው ቫይታሚን ዲ በቀን በቀን አይወሰድም።
🖲ምክኒያቱም ይህ ከፍተኛ መጠን ያለው ቫይታሚን ዲ በቀን በቀን የሚወሰድ ከሆነ፣ ከልክ ላለፈ የቫይታሚን ዲ ችግር ሊያጋልጥ ይችላል
🖲ከልክ ያለፈ መጠን ያለው ቫይታሚን ዲ የተወሰደ ከሆነ በደም የሚገኘው የካልሲየም መጠን ከልክ ያለፈ ሰለሚሆን፣ ከዚህ ጋር ተያትዘው የሚመጡ የተለያዩ የህመም ስሜቶች ለምሳሌ
🖲ድካም ድካም ማለት፣ በውሀጥም መቸገር እና ሽንት በተደጋጋሚ ግዜ መሽናት፣ የሆድ ድርቀት፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ የመሳሰሉ የህመም ምልክቶች ይኖራሉ።
🖲እንዲህ አይነቶቹ የህመም ምልክቶች ሲያጋጥሙ ታዲያ፣ የካልሲየም ይዘት ያላቸውን ምግቦች ባለመመገብ እንዲሁም በህክምና እና በመዳኒት እገዛ፣ በእንድ ወር ግዜ ውስጥ እነዚህን ችግሮች መመለስ ይቻላል።
የበለጠ መረጃ YouTube ላይ አስቀምጫለሁ
👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/SlD6HeKj_jI

እጅና ትከሻ መዛል | የአጥንት ህመም | የቫይታሚን ዲ እጥረት (Vitamin D) Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ #drseife #medical #habesha
👍420❤81🥰22😢8🙏8😱6🤩6
➕➕ የሽንት እርግዝና ምርመራ ➕➕
🖲በሽንት የሚደረግ የእርግዝና ምርመራ Urin HCG Test ይባላል።
🖲ይህ የምርመራ መንገድ፣ እርግዝና መፈጠሩን ማሳየት የሚችለው፣ የወር አበባ ከቆመ ከ2 ሳምንት በኋላ ምርመራ የተደረገ ከሆነ ነው።
🖲አብዛኛውን ግዜ የሽንት እርግዝና ምርመራ ሲደረግ፣ የጠዋት ሽንት ላይ ቢሆን ይመረጣል።
🖲ምርመራው እርግዝና ከሌለ 1 መስመር ያሳያል እርግዝና የተፈጠረ ከሆነ ደሞ 2 መሰረመር ያሳያል።
🖲በቅርቡ ወደሀገራችን የገባ፣ የሽንት እርግዝና ምርመራ መሳሪያ አለ፣ ዋጋው ርካሽ ከመሆኑም ባሻገር አጠቃቀሙም በአማርኛ የተፃፈ ነው። ቲና ይባላል። በየተኛውም ፋርማሲ ይገኛል
🖲ጤና ተቋም ሳትሄዱ በቤታችሁ መጠቀም ትችላላችሁ
🖲የዋና አከፋፋዮች አድራሻ
👉Company : Labora International Trading Plc
👉Tele:0911104930

👍335❤85🥰38🤔23👏20🙏16
➕➕ማይግሬን ➕➕
🖲ራስ ምታት የብዙ በሽታትዎች መገለጫ የሆነ የህመም ስሜት ምልክት ነው።
🖲ከድካም ፣ ከስራ ጫና እና ከእንቅልፍ እጦት የመሳሰሉ አነስተኛ ችግሮች አንስቶ፣ ከቀላል እስከ ከባድ ደረጃ የሚደርሱ ተለያዩ ኢንፌክሽኖች ሲኖሩ እና፣ እንዲሁም እንደ የእምሮ እጢ ያሉ ጠንከር ያለ የህክምና እርዳታ የሚያስፈልጋቸው የጤና ችግሮች ድረስ፣ ከተጓዳኝ የህመም ስሜቶች ባሻገር፣ የራስምታት፣ አንደኛው የህመም ስሜት መገለጫ ነው።
🖲 በህክምናው ረገድ ከ200 በላይ የሚሆኑ የራስምታት አይነቶች አሉ።
🖲አንዳንዶቹ የራስ ምታት እነቶች ቀላል እና የማያሰጉ ሲሆኑ፣ አንዳንዶቹ ደሞ ለህይወት አስጊ የሆኑ የራስ ምታት አይነቶች ናቸው።
🖲የራስ ምታት ህመም፣ በደፈናው፣ በሁለት ዋና ዋና መንገዶች ይከፈላል
🖲 የራስምታቱ የመጣው ከተጓዳኝ የጤና እክል ከሆነ በህክምናው (Secondary Headache ) ተብሎ ይጠራል።
🖲ነገር ግን ራስምታቱ የጀመረው በራሱ ከሆነ ፣ወይም ደሞ የራስ ምታት አምጪ የሆነ ተጓዳኝ የጤና እክል ሳይኖር የሚመጣ የራስ ምታት ከሆነ፣ በህክምናው የመጀመሪያ ደረጃ የራስ ምታት ወይም ( Primary Headache) ተብሎ ይጠራል።
🖲 የመጀመሪያ ደረጃ ራስ ምታት ህመምሞች ተብለው የተከፈሉት ወደ 20 የሚሆኑ የራስ ምታት አይነቶች ናቸው።
🖲አብዛኞቹ ተመሳሳይ የሆነ የህመም ባህሪን ያሳያሉ፣ ነገር ግን በተወሰነ መልኩ አንዳቸውን ካንዳቸው መለየት የሚያስችል የራሳቸው የሆነ የህመም ባህሪዎች አሏቸው።
🖲ከነዚህ ውስጥ ታዲያ ዋነኛው እና በብዛት የሚታወቀው የራስ ምታት አይነት፣" ማይግሬን "ተብሎ የሚጠራው የራስ ምታት አይነት ነው።
🖲ማይግሬን ፣ማይግሬን ተብሎ ከመጠራቱ በፊት፣ "Hemikrania "በመባል ይታወቅ ነበር፣ የግሪኮች ቃል ነው፣ ትርጉሙም ግማሽ የጭንቅላት ክፍል እንደማለት ነው።
🖲በቆይታም ይህ ቃል ወደላቲን ቋንቋ ሲቀየር "Hemigranea" ተባለና፣ በግዜ ሂደት ወደ ፈረንሳይኛ ቋንቋ ተቀይሮ አሁን ላይ በሚጠራበትን ማይግሬን የሚባለውን ስያሜ ይዞ ይገኛል።
🖲የማይግሬን ራስምታት ከመለስተኛ እስከ ከባድ የሚሆኑ የራስምታት ደረጃዎች በውስጡ ይይዛል። እነዚህም በ6 የማይግሬን የራስ ምታት አይነት የተገለፁ ናቸው።
🖲 ስለማይግሬን ራስምታት ባህሪዎች እና ህክምናውን በተመለከተ ሰፋ ያለ መረጃ በ Youtube ቻናሌላይ አስቀምጫለሁ። በቪዲዮው ላይ ያልተመለሰ ጥያቄ ካላችሁ በኮሜንት ላይ አስቀምጡልኝ። አመሰግናለሁ።
👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/WZT0f5uRjIc

እራስ ምታት| የማይግሬን ህክምና | Migraine | Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ #drseife #medical #habesha
ይህ ቪዲዮ የሚያብራራው አንድ ሰው በራስምታት ህመም ሲጠቃ የሚደረገውን የህክምና ሂደት እና የማይግሬን ራስምታት ህመምን በተመለከተ፣ ዋና ዋና የህመም ምልክቶች እንዲሁም፣ ህክምናውን በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ይሰጣል።
👍271❤85🙏37🥰15🎉1
➕➕ የሸንተረር ህክምናው ➕➕
🖲 ከአንድ ሰው የሰውነት ክፍል ላይ ሸንተረር በብዙ ቦታዎች ጎልቶ ሊወጣ ይችላል።
🖲መቀመጫ፣ ሆድ፣ ዳሌ፣ ብብት፣ ጭን እና እግር የመሳሰሉት የሰውነት ቦታዎች፣ አብዛኛውን ግዜ ሸንተረር የሚወጣባቸው የሰውነት ክፍሎች ናቸው።
🖲አነዚህ የቆዳ ሸንተረሮች በህክምናው Striae ተብለው ይጠራሉ። የያዙትን ቀለም እና የወጡበትን ምክኒያት በማገናዘብም የተለያየ ስያሜ ይሰጣቸዋል።
🖲በእርግዝና ምክኒያት የወጣ የቆዳ ሸንተረር ከሆነ በህክምናው Striae Gravidarum ተብሎ ይጠራል ።
🖲ከውፍረት ጋር በተያያዘ መልኩ የሚወጣ ሸንተረር ሲሆን ደሞ Striae Distensae ይባላል
🖲ከዚህ ውጪ ደሞ ፣ ከቆዳ መሳሳት ጋር በተያያዘ መልኩ የሚወጣ ሲሆን በህክምናው Striae Atrophicans በመባል ይታወቃል።
🖲እነዚህ የህክምና ስያሜዎች ሸንተረሩ የወጣበትን ምክኒያት አመላካች የሆኑ ስያሜዎች ናቸው።
🖲ከዚህ በተለየ መልኩ ደሞ የሸንተረሩን ቀለም በማገናዘብ ሸንተረሩ እንደሚይዘው ቀለም የህክምና ስያሜም ይሰጠዋል።
🖲አንድ ሸንተረር በቆዳ ላይ ሲወጣ እንደጊዜ ቆይታው 4 አይነት ቀለሞችን ሊይዝ ይችላል።
🖲ቀይ ሊሆን ይችላል፣ ጥቁር ሰማያዊ ውይም ጥቁር ሆኖ ሊወጣ ይችላል፣ እንዲሁም ነጭ የቀለም ይዘት ሊኖረው ይችላል።
🖲አዲስ ወይም በቅርቡ የወጣ የቆዳ ሸንተረር ቀይ ሆኖ ይታያል፣ ቦታውን በእጃቹ በምትዳብሱበት ግዜ አበጥ ያለና ጠንከር ያለ ይዘት ይኖረዋል። ይሄ በህክምናው strae rubra ተብሎ ይጠራል፣ ቀይ ሸንተረር እንደማለት ነው ትርጉሙ።
🖲ሸንተረርን ለማጥፋት የተዘጋጁ ብዙ አይነት የህክምና አማራጮች አሉ፣ ነገር ግን ሸንተረርን የማጥፋት አቅማቸው ሁሉም ሰው ላይ ተመሳሳይ አይደለም።
🖲ወይም አንድ ወጥ በሆነ መልኩ ሸንተረርን ከሁሉም ሰው ላይ ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋ የሚችል ነው ተብሎ የተቀመጠ የህክምና መንገድ የለም። እንደ ህክምና አማራጭ ሆነው የቀረቡት፣
👉በሚቀባ መልክ የተዘጋጁ ቅባቶች፣
👉የጨረር ህክምና፣
👉ቆዳን የመፋቅ እና የመብጣት ህክምናዎች፣ micridermaabresion እና microneedling ይባላሉ በህክምናው
👉እና የ PRP ህክምና ናቸው
🖲 ስለነዚህ የህክምና መንገዶች በሰፊው YouTube ላይ አስቀምጫለሁ። ለመመልከት ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።
👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/FNN-IicACW4

👍366❤75🙏47🥰44🤩16👏15🎉13