Bridge The Gap Ethiopia
ጥቅምት 12 እና 13 ላይ በ አዳማ ራስ ሆቴል ግቢ
ነጻ የ ጡት ካንሰር ምርመራ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም አዘጋጅተናል።
ለበለጠ መረጃ በነዚህ ስልክ ቁጥሮች ይደውሉ
0968062153
0924502991

👍233❤74🥰26🤩12
➕➕ ሽበት ለሚያስቸግረው ➕➕
🖲 የአንድ ሰውን እድሜ ተንተርሰው ከሚመጡ የተፈጥሮ ለውጦች መሀል አንደኛው የሽበት መውጣት ሆኖ ሳለ ነገር ግን ሽበት ሁልግዜ የእድሜ መግፋትን ብቻ አመላካች አይደለም።
🖲 የአንድ ሰው ፀጉር ያለግዜው ሲሸብት ታዲያ፣ በማህበረሰብ ዘንድ የእድሜ መግፋትን የሚያመላክት ሆኖ ስለሚታይ፣ ከስነውበት አኳያ የስነልቦና ጫና ማሳደሩ የማይቀር ነው።
🖲 ካለግዜው የሚመጣ ሽበት ሲኖር አንዳንድ ሰው ላይ የስነልቦና ጫና ከመፍጠሩ ባሻገር ሊያደርስ የሚችለው ተጨባጭ የጤና እክል አይኖርም።
🖲 አንድ ሰው ላይ በተፈጥሮ ሽበት የሚጀምርበት እድሜ ፣በዘር የተለያየ ነው፣ ያም ማለት ከአፍሪካውያኖች ፀጉር ይልቅ፣ የምእራባውያን እና የእሲያውያን ፀጉር ቀድሞ ይሸብታል።
🖲በአፍሪካውያኖች ወይም በጥቁር ማህበረሰቦች ላይ፣ ሽበት ከ 34 እስከ 54 አመት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ ይጀምራል ፣ ለዚህም አማካዩ እድሜ 43 አመት ነው።
🖲 ከ6 እስከ 23 በመቶ የሚሆኑ አፍሪካውያን ወይም የጥቁር ማህበረሰቦች፣ እድሜያቸው 50 አመት ሲደርስ፣ ግማሽ የሚሆነው የራስ ቅላቸው ላይ ያለው ፀጉር ይሸብታል።
🖲 በዚህ መሰረት ታዲያ፣ በጥቁር ማህበረሰቦች ዘንድ፣ ያለግዜው የሚመጣ ሽበት የሚባለው፣ ሽበቱ የጀመረው ከ 30 አመት እድሜ በታች የሆነ ሰው ላይ ከሆነ ነው።
🖲 ካለግዜው የሚመጣ ሽበትን ከሚያስከትሉ ምክኒያቶች ውስጥ አብላጫውን ድርሻ የሚይዘው ተፈጥሮ ነው፣ በቤተሰብ የሚኖር ቀድሞ የሚመጣ ተፈጥሮአዊ ሽበት፣ በልጆች ላይም ሊከሰት ይችላል።
🖲 በዚህ ቪዲዮ ላይ የፀጉር ቀለም አይነቶችን በተመለከተ፣ እና ሽበት ያለግዜው የሚጀምርበትን ምክኒያት፣ እንዲሁም በህክምናው ዘርፍ የሚደረገውን ሁኔታ አብራርቻለሁ።
🖲 ሙሉ ቪዲዮውን ለማየት የሚቀጥለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/-WVnwP0pMiQ

YouTube
ሽበት ያለግዜው ሲመጣ | premature gray hair | Dr.Seife | ዶ/ር ሰይፈ
👍172❤85🏆39🥰13🎉11🤩11🙏4
➕➕ የስኳር በሽታ ➕➕
🖲 ሽንትን በመቅመስ ነበር በድሮ ግዜ የስኳር በሽተኛ የሚታወቀው፣ ሽንት ሲቀመስ ጣፋጭነት ካለው እና እንዲሁም ሽንት በተሸናበት ቦታ ቁጫጭ ወይም ጉንዳኖች የሚሰበሰቡ ከሆነ ያ ሰው የስኳር በሽተኛ መሆኑን ያመላክት ነበር።
🖲የስኳር በሽታ በህክምናው" diabetes melitus "በመባል ይታወቃል፣ ይህ ቃል የተወረሰው ከጥንታዊ የግሪኮች ቃል ሲሆን ቀጥተኛ ትርጉሙም "የሚጣፍጥ ሽንት" እንደማለት ነው።
🖲የስኳር በሽታ ወነኛ መገለጫው የደም የስኳር መጠን መብዛት ወይም ከቁጥጥር ውጪ መሆን ነው። ለዚህም ታዲያ የስኳር በሽታ የሚነሳበትን ተፈጥሮአዊ ሂደት በማገናዘብ፣ በህክምናው የስኳር በሽታ በ 2 ጠቅለል ባለ ምድብ ይከፋፈላል።
🖲አይነት 1 እና አይነት 2 የስኳር በሽታ፣ በህክምናው ቋንቋ T1DM እና T2DM በመባል የሚታወቁ ናቸው
🖲ነገር ግን የስኳር በሽታ ፣በህክምናው ዘርፍ፣ ከዚህም ውጪ የተለያዩ የህክምና መንገድ ያላቸው፣ የስኳር በሽታ ምድቦች ሊኖሩት ይችላል
🖲አንድ ጤናማ ሰው ላይ፣ ተፈጥሮአዊ የስኳር ቁጥጥር ሂደት በሚኖርበት ግዜ፣ አንድ ሰው ቁርስ ሳይበላ የሚኖረው የደም ስኳር መጠን ፣ 1 ሊትር የሚሆን ደም ውስጥ ከ 7 እስከ 10 mg መሆን አለበት።
🖲ወይም ደሞ በህክምናው አቆጣጠር፣ ጤናማ የደም ስኳር መጠን ቁርስ ሳይበላ በፊት፣ ወይም ለ 8 ሰአት የፆመ ሰው ላይ ከ 70 እስከ 100 mg/dl መሆን አለበት፣ ወይም ደሞ አንድ ሰው ምግብ ከተመገበ ከ 2 ሰአት በኋላ ያለው የደም ስኳር መጠን ከ 140 mg/dl ያነሰ መሆን አለበት ማለት ነው።
🚩 ታዲያ ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳይኖራቸው የስኳር በሽታ ምርመራ ማድረግ ያለባቸው ሰዎች እነማናቸው?
🚩 በምርመራ ስኳር የተገኘበት ሰው ሁሉ እድሜ ልክ መዳኒት መውሰድ አለበት?
🚩የስኳር በሽታ ከመጣ በኋላ መመለስ ይቻላል?
🖲በዚህ ቪዲዮ ላይ የስኳር በሽታ አይነቶችን በተመለከተ፣ ለስኳር በሽታ አጋላጭ የሆኑ ፣ ዘልማዳዊ ተግባሮችን እና የህመም ምልክት ሳይኖር፣ ግዴታ ለስኳር በሽታ ምርመራ ማድረግ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች በተመለከተ አጠር አድርጌ አብራራለሁ። ለመመልከት የሚቀጥለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።
አመሰግናለሁ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/2o9DO3wdJcw

የሚጣፍጥ ሽንት | ስር ሰደድ በሽታ | Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ #dr
👍240❤42🙏31🤩24🥰10💯4
➕➕ ከልክ ያለፈ ላብ ➕➕
🖲 በተፈጥሮ የመጣ፣ ምንም አይነት ተጓዳኝ በሽታ ወይንም በምርመራ የተገኘ ምክኒያት የሌለው ከልክ ያለፈ ላብ በህክምናው primary hyperhidrisis ይባላል
🖲 በእጅ እና በእግር ላይ የሚጀምር ክልክ ያለፈ ላብ በልጅነት እድሜ የሚጀምር ሲሆን፣ በብብት ላይ የሚኖር ከልክ ያለፈ ላብ የሚጀምረው ደሞ በኮረዳነት እንዲሁም በጉርምስና እድሜ ክልል ያለ ሰው ላይ ነው።
🖲 በህክምናው ፣በተፈጥሮ የመጣ ወይም ምክኒያቱ የማይታወቅ ከልክ ያለፈ ላብ ብሎ ለመፈረጅ፣
👉 ችግሩ 6 ወር እና ከዛ በላይ የቆየ መሆን አለበት።
👉ይህ አይነቱ ችግር ፣ እድሜያቸው ከ25 አመት በላይ የሆኑ ሰዎች ላይ የሚጀምር ከሆነ፣ ምናልባትም ተጓዳኝ የጤና ችግር መኖሩን ሊያመላክት ይችላል።
👉ይህ አይነቱ ከልክ ያለፈ ላብ የሚፈጠረው አንድ ሰው በሚንቀሳቀስበት ሰአት ወይም በቀኑ ክፍለግዜ ሲሆን፣ አንድ ሰው በሚተኛበት ሰአት ከልክ ያለፈ ላብ የሚያልበው ከሆነ ፣ ተጓዳኝ የጤና ችግሮች መኖራቸውን አመላካች ነው።
👉በተፈጥሮ የሚመጣ ከልክ ያለፈ ላብ ፣ከቤተሰብ በዘር ሊወረስ ስለሚችል፣ በቅርብ ዘመድ ላይ ተመሳሳይ ችግር ያለ ከሆነ ይህ አይነቱ ችግር በተፈጥሮ ለመምጣቱ አንደኛው ጠቋሚ ምልክት ይሆናል።
🖲 አንድ ሰው ላይ ከቅርብ ግዜ ወዲህ የመጣ ፣ተደጋጋሚነት ያለው ፣በከፊልም ሆነ በመላ ሰውነት ላይ የሚታይ፣ ከዚህ በፊት ያልተለመደ፣ ከልክ ያለፈ ላብ የሚያጋጥም ከሆነ ሀኪም ጋር ቀርቦ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል።
🖲 እድሜያቸው ከ 25 በታች የሆኑ ሰዎች ፣በእጅ ፣በእግር እና በብብት አካባቢ የሚታይ ከልክ ያለፈ ላብ ያላቸው ከሆነ ከተጓዳኝ የጤና ችግር የመጣ አለመሆኑ በምርመራ ከተረጋገጠ በኋላ፣ ላብን ሊቀንሱ እና ሊያጠፉ የሚችሉ፣ በሚቀባ ፣ በሚዋጥ፣ በሚወጋ፣ በጨረር እና በቀዶ ህክምና መልኩ የተዘጋጁ የተለያዩ የህክምና መንገዶች እንደ አማራጭ ይቀርባሉ።
🖲ከነዚህም ውስጥ እንደ መጀመሪያ ደረጃ ህክምና የሚሰጠው : በተለያየ መጠን በሚቀባ መልክ የተዘጋጀው Aluminium Chloride ነው።
🖲ይህ መዳኒት ከ 6.25 እስከ በ20% የይዘት መጠን በሚቀባ መልክ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የላብ መውጫ ቀዳዳዎችን በመድፈን ከልክ ያለፈ ላብን የሚቀንስ ነው።
🖲ይህ መዳኒት በተለያዩ የምርት ስሞች ሊገኝ የሚችል ነው። በፋርማሲ ደረጃም በሀኪም ትእዛዝ ተቀምሞ ሊሰጥም ይችላል።
🖲በፋብሪካ ደረጃ ተዘጋጅተው ገበያ ላይ ከቀረቡት ምርቶች ውስጥ እንደ Drysol, Certain dry, Hydrosal, Odaban የመሳሰሉ ምርቶች ይገኙበታል
🖲እነዚህን መዳኒቶች ስትጠቀሙ ለመጀመሪያው 1 ሳምንት ማታ ማታ ብቻ በደረቀ ብብት ላይ ተቀብቶ ጠዋት ላይ መታጠብ፣ በመቀጠልም በሳምንት አንዴ ወይም 2 ግዜ ብቻ መጠቀም።
🖲እርጥበት ባለው ቆዳ ላይ የሚቀባ ከሆነ እንዲሁም በተቀባበት ቦታላይ እንቅ አድርጎ የሚይዝ ፒጃማ ተለብሶ የሚተኛ ከሆነ የቆዳ መቆጥቆጥን እና ማቃጠልን ያስከትላል።
🖲ይህ መዳኒት ከፍተኛ የ አልሙኒየም ይዘት ያለው ስለሆነ ከሀኪም ትእዛዝ ውጪ ለረጅም ግዜ መጠቀም እና፣ እንዲሁም አዛውንቶች እና የኩላሊት ድክመት ያለባቸው ሰዎች ፈፅሞ እንዲጠቀሙት አይመከርም።
🖲ከዚህ ዉጪ ያሉ ረዘም ላለ ግዜ ላብን የሚያቆሙ የህክምና መንገዶችም አሉ፣ ሙሉ መረጃውን በ YouTube ቻናሌ ላይ አሰወቀምጫለሁ። ለመመልከት የሚቀጥለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ። አመሰግናለሁ።
👇👇👇👇
https://youtu.be/eqUp9BejiyY

ከልክ ያለፈ የብብት ላብ | Hyperhidrosis | Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ #drseife #medical #habesha
👍155🥰23❤21💯17🏆9🙏6
➕➕ መጥፎ የላብ ጠረን ➕➕
🖲 ምን አይነት ዶዶራንት ነው የምትጠቀሙት ወይም የትኛው አንቲፐሪስፖይራት ነው ለናንተ የሚስማማው?
🖲 ዶዶራንት እና አንቲፐሪስፖይራንት ሁለት የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸው፣ ምርቶች ናቸው።
🖲 አንድ ሰው ብብት ላይ ፣ከልክ ያለፈ ላብ ስላለ ብቻ መጥፎ የላብ ጠረን ይፈጠራል ማለት አይደለም።
🖲 አንድ ሰው ቆዳ ላይ ሁለት አይነት የላብ አምራች እጢዎች ይገኛሉ፣ እነዚህ የላብ አምራች እጢዎች አቀማመጣቸው እና የሚያመርቱት የላብ ይዘት የተለያየ ነው።
🖲 ታዲያ፣ ማናቸውም አይነት የላብ እጢዎች የሚያመነጩት የላብ አይነት፣ በአንዳንድ የጤና ችግሮች ምክኒያት ካልሆነ በስተቀር፣ አብዛኛውን ግዜ የተፈጥሮ ሽታ ወይም ጠረንን የያዘ አይደለም።
🖲 ነገር ግን በቆዳ ላይ የሚገኙ ጥቃቅን ህዋሳት፣ ከላብ የሚወጣውን የስብ እና የፕሮቲን ይዘት፣ እንደ ምግብ በመጠቀም ያብላሉት እና፣ መጥፎ ጠረን ወዳለው ንጥረ ነገር ይቀይሩታል።
🖲 በሌላ መልኩ ደሞ አንድ ሰው፣ መጥፎ የላብ ጠረን እንዲኖረው አስተዋፆ የሚያደርጉ የተለያዩ ምክኒያቶች አሉ፣
👉 በቆዳላይ ፣በተለይ በሰውነት እጥፋቶች መሀል የሚወጣ የቆዳ ኢንፌክሽን ካለ፣
👉 አብሽ ቀይ ሽንኩርት እና ነጭሽንኩርት የበዛበት ምግብ በብዛት የሚመገቡ ሰዎች፣
👉ከፍተኛ የኩላሊት ድክመት ያለባቸው ታካሚዎች፣
👉 የአልኮል መጠጥ እና የ ፔኒሲሊን ይዘት ያላቸው መዳኒቶች ለረጅም ግዜ የሚወሰዱ ከሆነ ፣ የሰውነት ጠረንን የመቀየር አቅም አላቸው።
🖲ከዚህ በተለየ መልኩ ደሞ አንዳንድ ሰዎች ላይ የሚታይ የስነ አእምሮ ችግር አለ፣ በህክምናው Delusional bromosis ወይም Olfactory reference syndrome በባል ይታወቃል። የዚህ ችግር ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ምንም አይነት የሰውነት ጠረን ሳይኖራቸው ፣ነገር ግን ሰውነታቸው መጥፎ ጠረን ያለው እንደሆነ ያህል ይሰማቸዋል።
🖲 አንድ ሰው ላይ ፣መጥፎ የሆነ የብብት ወይም የሰውነት ላብ ጠረን ሲያጋጥም፣ ምን መደረግ አለበት?
👉በብብት ቆዳ ላይ የሚታይ የቆዳ ገፅታ መቀየር ካለ
👉መጥፎ ጠረን በተፈጠረበት ቦታ ላይ ፣ የቆዳ ማሳከክ ፣መቅላት እና ማንኛውም አይነት የህመም ስሜት የሚታይ ከሆነ፣
🚩 ችግሩ ከተጓዳኝ የቆዳ በሽታ እንዲሁም በሌላ የጤና ችግር ምክኒያት የመጣ ሊሆን ስለሚችል ሀኪምጋ መቅረብ ያስፈልጋል።
🖲 አንድ ሰው ላይ፣ ተጓዳኝ የቆዳም ሆነ የውስጥ ደዌ እና የስነአእምሮ ችግር ሳይኖር ፣መጥፎ የላብ ጠረን የሚያጋጥም ከሆነ፣ በመጀመሪያ ደረጃ መደረግ ያለበት ተግባር ወትሮአዊ በሆነ መልኩ ንፅህናን መጠበቅ ነው።
👉 ለዚህም ተመራጭ የሚሆኑት በውስጣቸው እንደ Clindamycin እና Benzoyle Peroxide የመሳሰሉ የፀረ ተህዋስያን መዳኒት የተጨመረባቸው ሳሙናዎች ናቸው። እነዚህን ሳሙናዎች በመጠቀም መጥፎ የላብ ጠረን ባለበት ቦታ በቀን 2 ግዜ መታጠብ ያስፈልጋል።
👉 በብብት እና በብልት አካባቢ የሚበቅል ፀጉር ፣ላብን እና መጥፎ ጠረንን የሚፈጥሩ ጥቃቅን ህዋሳት አጣብቆ ስለሚይዝ ፣በቦታው ላይ ያለ ፀጉርን ማሳጠር።
👉ብብት ላይ ጥብቅ የሚል ልብስን አለመልበስ ፣
መጥፎ የሰውነት ጠረን እንዲባባስ የሚያደርጉ ፣እንደ አብሽ፣ የአልኮል ይዘት ያላቸው መጠጦች፣ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት እና ቅመማ ቅመሞች የበዙበት ምግብን አለማዘውተር ያስፈልጋል።
🖲 አብዛኛውን ግዜ ደሞ፣ የላብ መጠንን የሚቀንሱ እና መጥፎ ጠረንን የሚሸፍኑ፣ አንቲቶሪስፖይራንቶች እና ዶዶራንቶች፣ ለዚህ ችግር ተጨማሪ መፍትሄዎች ናቸው።
🖲 አንድ ምርት ላይ ዲኦዶራንት (Deodorant )የሚለው ፅሁፍ ብቻ ካለው፣ የሚያመላክተው መጥፎ ጠረንን በጥሩ መአዛ የሚተካ መሆኑን ብቻ እንጂ የላብ መጠንን የሚቀንስ አይደለም።
🖲አንድ ዶዶራንት ላይ አንቲፐሪስፖይራንት (Antiperispirant) የሚል ፅሁፍ ካለው፣ በውስጡ የላብ መውጫ ቀዳዳዎችን በመድፈን ፣የላብ መጠንን መቀነስ የሚችል ይዘት እንዳለው ያመላክታል።
🖲ገበያ ላይ ፣የብብት ላብ እና ጠረንን ለመቀነስ የተዘጋጁ ዶዶራንቶች እና አንቲፐሪስፖይራንቶች ፣በተለያየ ይዘት የተዘጋጁ ናቸው፣
🖲 ከነዚህ ውስጥ አብዛኛውን ግዜ፣ ቁጡ ለሆነ ቆዳ ተስማሚ የሚሆኑት ምርቶች ፣በሚዳሰስ መልክ የተዘጋጁት የዶቭ ምርቶች ናቸው። እነዚህ በውስጣቸው ሽታን እና የላብ መጠንን የሚቀንስ የአልሙኒየም ይዘት ያላቸው ምርቶች ናቸው።
🖲 ከዛ በተጨማሪ ደሞ፣ የአልኮል ይዘት እና ሽታ የሌላቸው ምርቶች፣ አብዛኛውን ግዜ ተስማሚ እና የቆዳ ቁጣን የማይፈጥሩ ምርቶች ናቸው።
🖲 ሽታ የሌላቸውን የላብ መቀነሻ ምርቶች የምትጠቀሙ ከሆነ፣ እነዚህ ምርቶች ላብን የመቀነስ አቅማቸው የሚጨምረው፣ ላብ በሚያልብ ግዜ በመጠቀም ሳይሆን፣ ታጥቦ በደረቀ ብብት ላይ ፣ማታማታ ብትቀቧቸው እና ጠዋት ላይ ፣የፀረተህዋስያን ይዘት ባላቸው ሳሙናዎች ብትታጠቡ ፣የሰውነት መጥፎ ጠረንን ለማጥፋት የበለጠ አቅም ይኖራቸዋል።
🖲 እነዚህን ምርቶች በምስል ለማየት እና የበለጠ መረጃ ካስፈለገ፣ YouTube ቻናሌ ላይ ሰፋ ያለ መረጃ አስቀምጫለው። ለመመልከት የሚቀጥለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ። አመሰግናለሁ።
👇👇👇👇👇
https://youtu.be/18QQBY5Mlz0

የብብት ጠረን ህክምና | Bromhidrosis and deodorants | Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ #drseife #medical
👍247❤41🥰32👏26👌26🙏9🤩1
➕➕የእንግዴ ልጅን መመገብ ለሰው አይመከርም ➕➕
🖲ሰሞኑን አንድ በአሜሪካ የምትኖር እህታችን በወሊድ ግዜ ስላጋጠማት አስደንጋጭ ሁኔታ በዩቱዩብ ቻናሏ ላይ ለቃ አይቼ ነበር። ምናልባት አይታችሁት ሊሆን ይችላል። (Meski Tube)
🖲 በቪዲዮው ላይ ሁለተኛ ልጇን በምትወልድበት ግዜ፣ የእንግዴ ልጁን የምትመገብ ከሆነ ባለሞያዎቹ ሊሰጧት ፈቃደኛ እንደሆኑ እየነገሯት እንደነበር እና፣ እሷም ይህንን መረጃ ለመጀመሪያ ግዜ በመስማቷ ተደናግጣ እንደነበር ታስረዳለች።
🖲በአሜሪካ ፣ በዩሮፕ እና በእሲያ የሚኖሩ አንዳንድ ማህበረሰቦች፣ በቂ እና አሳማኝ የሆነ መረጃ ሳይኖራቸው ይህን ፀያፍ ድርጊት ሲተገብሩት ይታያል።
🖲 ለድርጊታቸው እንደ ምክኒያት የሚያቀርቡት የጤና ጥቅም፣ አሉባልታ እና ግምታዊ ግንዛቤ ላይ ተንተርሰው እንጂ፣ በምንም አይነት አሳማኝ የጥናት ምርምር የተደገፈ አይደለም።
🖲ይህንን አስመልክቶ ሰፋ ያለ መረጃ በዩቲዩብ ቻናሌ ላይ አስቀምጫለው ይህንን ምልክት ተጭናችሁ ብትገቡ ታገኙታላችሁ። 👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/WsItmZciDNo
🖲ለማንኛውም አንድ እናት ከወለደች በኋላ የፈሰሳት ደም እንዲተካ፣ መሀፀኗ እንዲያገግም እና በቂ የጡት ወተት ማምረት እንድትችል ፣
👉 የበሰለ ወይም በንፅህና የተጋጀ የተመጣጠነ ምግብን መመገብ
👉በቀን ከ2.3 እስከ 2.6 ሊትር የሚሆን ፣ከማንኛውም አይነት የአልኮል መጠጥ የፀዳ ፈሳሽን መውሰድ እና እንዲሁም።
👉ከወሊድ በኋላ የሚኖር ማንኛውም አይነት አሳሳቢ የህመም ስሜት ሲኖር፣ ሀኪምን በማማከር እንጂ
🖲የዚህ አይነቱን ተግባር መፈፀም፣ እስከ አሁነ ድረስ፣ በህክምና ያተደገፈ እና ሊያስገኝ የሚችለው የጤና ጥቅም ፈፅሞ እንደሌለ በጥናት ምርምሮች የተረጋገጠ ነው።
መልካም ግዜ

👍283👏21👌15❤5🎉4🙏4🤩1
Forwarded from Ruth Hailu
እንደድሮ ፋርማሲ ከፋርማሲ መድኅኒት ፍለጋ መዞር ቀረ…
በሀገራችን ያለውን መድኅኒት በቀላሉ ያለማግኘት ችግርን ለማቃለል በባለራዕይ ሴት ሐኪሞች ለህብረተሰባችን የቀረበ
ፋርማኔት የሞባይል መተግበሪያን ወደ ስልክዎት በመጫን ካሉበት ቦታ ሆነው የሚፈልጉት መድኅኒት የሚገኝበትን ቦታ በነፃ ይወቁ::
ቤተሰባችንን ይቀላቀሉ::
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bluemedconsultancy.pharmanet_eth
Telegram link: https://t.me/Bluemedconsultancy
Facebook link:
https://www.facebook.com/Bluemedethiopia/
ለበለጠ መረጃ: +251903004645

👍154❤39👏33👌1
🛑❌እነዚህን አጭበርባሪ ሌቦች ለፖሊስ በማጋለጥ ተባበሩኝ።🔴❌❌❗️❗️
ከዚህ በታች ያለው ምስል የምታዩት በኔ ስም የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንት ነው።
🔴ህገወጥ መዳኒቶችን ለህብረተሰቡ እየሸጡ እና እያታለሉ ይገኛሉ፣ በምስሉ ላይ ያስቀመጥኩት፣ ብዙ ሰዎችን የሚያጭበረብሩበት የባንክ አካውንት እና ስም ነው።
🟢የኔ ትክክለኛው የፌስቡክ አካውንት ይሄ ነው
https://fb.me/seifemedfb
🔴እኔ አሁንም ወደፊትም ምንም አይነት መዳኒት አልሸጥም፣ በኔ ስም እና ፎቶ መዳኒት ሲሸጥ ካያችሁ እባካችሁ በቶሎ ለፖሊስ አመልክቱ።
ዶ/ር ሰይፈ
🔴🔴🔴እባካችሁ ሼር ሼር ሼር ሼር
ከዚህ በታች ያለው ምስል የምታዩት በኔ ስም የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንት ነው።
🔴ህገወጥ መዳኒቶችን ለህብረተሰቡ እየሸጡ እና እያታለሉ ይገኛሉ፣ በምስሉ ላይ ያስቀመጥኩት፣ ብዙ ሰዎችን የሚያጭበረብሩበት የባንክ አካውንት እና ስም ነው።
🔴እኔ አሁንም ወደፊትም ምንም አይነት መዳኒት አልሸጥም፣ በኔ ስም እና ፎቶ መዳኒት ሲሸጥ ካያችሁ እባካችሁ በቶሎ ለፖሊስ አመልክቱ።
ዶ/ር ሰይፈ
🔴🔴🔴እባካችሁ ሼር ሼር ሼር ሼር
Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
👍122❤9🙏8👌5🥰4👏4🤩4
🛑❌እነዚህን አጭበርባሪ ሌቦች ለፖሊስ በማጋለጥ ተባበሩኝ።🔴❌❌❗️❗️
ከዚህ በላይ ያለው ምስል የምታዩት በኔ ስም የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንት ነው።
🔴ህገወጥ መዳኒቶችን ለህብረተሰቡ እየሸጡ እና እያታለሉ ይገኛሉ፣ በምስሉ ላይ ያስቀመጥኩት፣ ብዙ ሰዎችን የሚያጭበረብሩበት የባንክ አካውንት እና ስም ነው።
🟢የኔ ትክክለኛው የፌስቡክ አካውንት ይሄ ነው https://fb.me/seifemedfb

👍132🥰18❤14👏5👌4