Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ
47.6K subscribers
178 photos
2 videos
6 files
130 links
የዚህ ቻናል አላማ፣ ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን የህክምና አስተምሮት እና መልእክቶች ማስተላለፍ ነው።
📞 0974163424
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን 👉 @LEKETERO ወይም @Apointment1
ተጭነው ስም እና ስልክ አስቀምጡ።

ዶ/ር ሰይፈ (ጠቅላላ ሐኪም)
Download Telegram
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ
ስም እና ስልክ 👉 @LEKETERO ላይ አስቀምጡ

👉ዶ/ር ሰይፈ 📞 +251974163424
ብዙ መልእክቶች ስለምቀበል እና እያንዳንዱን ለማንበብ ጊዜ ስለማይበቃ እባክዎን ይህን ቁጥር ለመደወል ብቻ ይጠቀሙ።

አመሰግናለው!
🖲ብጉር ከመክሰሙ በፊት የቆዳ ቁጣ የሚያስከትል ከሆነ፣ ጠባሳ እና ጥቋቁር ነጠብጣብ የመፍጠር እድል አለው።

🖲 ብጉር ጠባሳ እንዳይፈጥር የሚደረጉ ጥንቃቄዎች።

👉ብጉርን አለመነካካት፣
👉አለማፈንዳት እና፣
👉የህክምና ክትትል በማረግ የሚሰጡ መዳኒቶችን በሀኪም ትእዛዝ ብቻ መጠቀም ያስፈልጋል

🚩በተደጋጋሚ የሚወጣ ብጉር፣ ተደጋጋሚ ክትትል ያስፈልገዋል

🖲 የብጉር ጠባሳ የሚያብጥ ወይም ደሞ የሚሰረጉድ ሊሆን ይችላል

🖲 ባጠቃላይ 4 አይነት የብጉር ጠባሳዎች አሉ
👉 3 የሚሰረጉድ እና
👉 1 የሚያብጥ

🖲 የብጉር ጠባሳ አይነት የሚወሰነው፣ በቆዳ ተፈጥሮ እንዲሁም በወጣው የብጉር አይነት እና ደረጃ ስለሆነ፣ አንድ ሰው ሁሉንም አይነት የብጉር ጠባሳዎች ሊይዝ ይችላል

🖲 የብጉር ጠባሳው ደረጃ አነስተኛ ከሆነ ማለትም ወደውስጥ ያልገባ ከሆነ እንዲሁም ከ 50 cm የአይን እይታ እና በታች ብቻ መለየት የሚቻል ከሆነ፣ በሚቀቡ የቆዳ መገሽለጫዎች የመጥፋት እድል አለው

🖲ለብጉር ጠባሳ የሚሰጡ የህክምና አይነቶች።

👉በ ኬሚካል እና በመሳሪያ ቆዳን መገሽለጥ
(Chemical peel and Microdermabresion)
👉የጨረር ህክምና  (laser therapy)
👉ስብ ህዋስ የመውጋት ህክምና (Fat transplant)
👉የራስን ደም አጥልሎ የመውጋት ህክምና (PRP)
👉በቀጫጭን መርፌ የመብጣት ህክምና (Needling)
👉ጠባሳውን ቆርጦ ማውጣት (Punch technique)

🖲እንዲሁም ለሚያብጥ ጠባሳ ደሞ

👉በቅዝቃዜ የማድረቅ ህክምና (Cryotherapy)
👉ጠባሳ ላይ በሚወጋ (IST)
👉ቆዳ ላይ በሚደረግ ቀዶህክምና አማራጮች አሉት

🖲አንድ ሰው እንዳለበት የጠባሳ አይነትና ደረጃ፣ ህክምናዎቺ በተናጠል እንዲሁም ተቀላቅለው ሉሰጡ ይችላሉ።

በቪዲዮ ለማየት
👇
https://youtu.be/Tg3QbHit_-Q
👍16🎉3
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ
ስም እና ስልክ 👉 @LEKETERO ላይ አስቀምጡ

👉ዶ/ር ሰይፈ 📞 +251974163424
ብዙ መልእክቶች ስለምቀበል እና እያንዳንዱን ለማንበብ ጊዜ ስለማይበቃ እባክዎን ይህን ቁጥር ለመደወል ብቻ ይጠቀሙ።

አመሰግናለው!
👍3
"አንዱ የአርሰናል ደጋፊ ደዉሎ 'ዶክ' የምር ግን የላም ወተት ጥሩ ነዉ? ብሎ ጠየቀኝ!!!"

ይህን ፅሁፍ ባየሁ ጊዜ የዉነት ነበር የሳቁት።ብቻየን ሰንተከተክ ያየኝ ሰዉ ምናልባት የአዕምሮ ጤናየ ሳያጠራጥረዉ አይቀርም።።።ፅሁፉን ያገኘዉት ሀኪም ፔጅ ከሚባል ገፅ ላይ ነበር።

የጥዬቄዉን መልስ ባየሁ ጊዜ አሁንም እየሳኩ ነበር።።

ኧረ ይሄን አልተማርነዉም bro ፍታኝ ይላል መልሱ።

ህክምና ላይ ላለ ና ከ እግር ኳስ ጋር ግንኙነት ላለዉ ሰዉ በዉነትም ዘና የሚያደርግ ነገር ነዉ።።።

እኔ ደሞ ይሄን ለኛ ቻናል ተከታታዮች በዚህ መልኩ አቀረብኩት።።።

"የምር ግን የላም ወተት ጥሩ ነዉ???"

🤴 የላም ወተት ካርቦ ሃይድሬት፣ኘሮቲን፣ቅባት ና ማዕድናትን አካቶ የያዘ በመሆኑ ጥሩ ነዉ።።

ነገርግን የላም ወተት ከአንድ ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት አይመከርም።

የላም ወተት ከእናት ጡት ወተት ጋር ሲነፃፀር የፕሮቲን መጠኑ በጣም ከፍተኛ ነዉ ነገር ግን ወደ ሰዉነታቸዉ ገብቶ ጥቅም የመስጠት አቅሙ(bio avaolability) በጣም ዝቅተኛ ነዉ።።

በተጨማሪም የህፃናቱ አንጀት በደንብ የዳበረ ባለመሆኑ የአንጀት መድማት ያስከትላል።።

ይህ የአንጀት መድማት ደግሞ ህፃናቱ ላይ የደም ማነስን ያመጣል።

በመሆኑም በተቻለ መጠን ከአንድ አመት በታች የሆኑ ህፃናት የላም ወተት ባይጠቀሙ ይመከራል።።

ከአንድ ዐመት በታች የሆኑ ህፃናት የናት ጡት የማያገኙ ከሆነ ከእናት ጡት ጋር ተቀራራቢ የሆነ ፎርሙላ ቢጠቀሙ ይመከራል።።።።።።

👌👌👌ዶ/ር ዮርዳኖስ👌👌
👍17🤩1
🖲የስረኛው የቆዳ ክፍል፣ መሰረታዊ መዋቅር የሆኑት፣ ንጥረነገሮች፣
➢collagen, elastin

🖲ከእድሜ እና ከቆዳ ጉዳት ጋር ተያይዞ መጠናቸው እንዲሁም ጥራታቸው እየቀነሰ ሲመጣ፣ የቆዳ መጨማደድ ይጀምራል።

🖲ይህንን ተፈጥሮአዊ ሂደት የሚደግፉ ማናቸውም ሁኔታዎች፣ እድሜን ሳይጠብቁ የቆዳ መጨማደድ እንዲኖር አስተዋፅኦ ያደርጋሉ።

👉ዘልማዳዊ የሆነ ተደጋጋሚ የፊት ገፅታ መኖር
👉በፊት መተኛት ማዘውተር
👉ሲጋራ ማጨስ እንዲሁም
👉ለፀሀይ ብርሀን ለረጅም ግዜ መጋለጥ

🖲የቆዳን ጥንካሬ እና የመሳሳብ ብቃትን በመቀነስ
በግዜ ሂደት የቆዳ መጨማደድን የመፍጠር አቅም አላቸው።

🖲የቆዳ መጨማደድ ስስ ሆኖ ሲጀምር  rhytide ይባላል
በሚቀቡ ቅባቶች የመመለስ አቅም አለው።

🖲እነዚህም ቅባቶች በውስጣቸው የሚይዙት ንጥረነገር የቆዳ መሰረታዊ የሆኑ ንጥረ ነገር አምራች ህዋሶች በቀላሉ እንዳይጎዱ ያደርጋል። እነዚህም

👉Alpha lypoic Acid 5%
👉የ ቪታሚን ኤ ተዋህፆ Retinol
👉በ ቪታሚን E, እና C የሚይዙ ቅባቶች
👉እንዲሁም Selinium እና zink የሚይዙ ቅባቶች ተጠቃሽ ናቸው።

🖲ከዚህ ውጪ ግዜአዊ የሆኑ በቆዳ ስር እና በፊት ጡንቻላይ የሚወጉ የህክምና አይነቶችም አሉ።

🖲በጠቅላላው ለፊት መጨማደድ የሚሰጡት ህክምናዎች

👉ከፀሀይ ብርሀን ራስን መከላከል
👉የቪታሚን እና አንቲ ኦክሲዳንት ቅባቶች መጠቀም።
👉የፊት ጡንቻን የማደንዘዝ ህክምና (Botox)
👉በቆዳስር በሚሞሉ (Fillers)
👉በጨረር ህክምና (Laser ,
👉ቆዳን የመወጠር ቀዶጥገና ናቸው

https://t.me/seifemed
https://t.me/seifemed
https://t.me/seifemed
👍212😱1
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ
ስም እና ስልክ 👉 @LEKETERO ላይ አስቀምጡ

👉ዶ/ር ሰይፈ 📞 +251974163424
ብዙ መልእክቶች ስለምቀበል እና እያንዳንዱን ለማንበብ ጊዜ ስለማይበቃ እባክዎን ይህን ቁጥር ለመደወል ብቻ ይጠቀሙ።

አመሰግናለው!
👍2
Myiasis የቆዳ ትል

🔴አንዳንድ የዝምብ ዝርያዎች ተገልብጦ የተሰጣ ልብስ ላይ እዲሁም አፈር ላይ የሚጥሉት እንቁላል እርጥበት እና የቆዳ ንክኪ ካገኘ ቆዳውስጥ በመግባት ማደግ ይጀምራል

🔴ይህ እጭ የሚያድግበት ቦታ እንደ ንክኪው ይወሰናል።

👉በቆዳ ላይ
👉አፍንጫ እና በአፍ ውስጥ
👉በጆሮ
👉በቁስል ላይ እና ከ እጩ ጋ ንክኪ በተደረገበት የሰውነት ክፍል ላይ የመውጣት አቅም አለው

🔴እጩ ቆዳውስጥ ዘልቆ በገባ ከ 10 -15 ቀናት ውስጥ ማደግ ሲጀምር ብጉንጅ የመሰለ ጫፉ የሚመረቅዝ ህመም ያለው እብጠት ይፈጠራል።

🔴አንዳንዴ ከዚህ በተለየ መልኩ ደሞ መስመር ይዞ እየሰፋ የሚሄድ እብጠትም ሊታይ ይችላል።

🔴ይህ እብጠት አንዳንድ ግዜ የማሳከክ ባህሪ ሊኖረው ይችላል።

🔴ህክምናው

💥ካደገበት ቦታ ቆዳን ሰንጥቆ እጩን በማውጣት ነው።

በቪዲዮ ለማየት
👇
https://youtu.be/wQuf9_9NX2c

https://t.me/seifemed
https://t.me/seifemed
https://t.me/seifemed
👍14
Forwarded from God Is Good
3🙏2👍1
👍4
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ
ስም እና ስልክ 👉 @LEKETERO ላይ አስቀምጡ

👉ዶ/ር ሰይፈ 📞 +251974163424
ብዙ መልእክቶች ስለምቀበል እና እያንዳንዱን ለማንበብ ጊዜ ስለማይበቃ እባክዎን ይህን ቁጥር ለመደወል ብቻ ይጠቀሙ።

አመሰግናለው!
👍7
👍9🥰61