Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ
47.6K subscribers
178 photos
2 videos
6 files
130 links
የዚህ ቻናል አላማ፣ ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን የህክምና አስተምሮት እና መልእክቶች ማስተላለፍ ነው።
📞 0974163424
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን 👉 @LEKETERO ወይም @Apointment1
ተጭነው ስም እና ስልክ አስቀምጡ።

ዶ/ር ሰይፈ (ጠቅላላ ሐኪም)
Download Telegram
***የአባላዘር በሺታ********

*የአባላዘር በሺታ የመራቢያ አካላትን የሚያጠቃ በሺታ ነዉ።።።።

*አብዛኛዉን ጊዜ የሚተላለፈዉ በግብረ ስጋ ግንኙነት አማካኝነት ነዉ።።።።።።

*ሴቶች ከወንዶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸዉ ።።።።

*ሺንት ሺሸኑ ማቃጠል ወይም መቆጥቆጥ፣ከሴትም ወይም ወንድ ብልት የሚወጣ ነጭ ወይም ቢጫ ፈሳሺ፣የብልት ማሳከክ፣ብልት አካባቢ የሚፈጠርቁስለት ዋና ዋና ምልክቶች ናቸዉ።።

*ልቅ የሆነ የግብረ ስጋ ግንኙነት፣ከ1በላይ የፆታ ጓደኛ መያዝ ና ሌሎችም ለአባላዘር በሺታ የሚያጋልጡ ነገሮች ናቸዉ።።።

*ህክምና ያለዉ በመሆኑ ምልክቶች ሲታዩ ቶሎ ህክምና ማግኘት ያስፈልጋል።።።

*የአባላዘር በሺታ አንድ ሰዉ በሚታከምበት ጊዜ የትዳር ጓደኛዉ ምልክት ባይኖረዉም መታከም ይኖርበታል።
👍4
👍3
*🌴🌴🌴🌴🌴🌴**
ይህ ሶኳር ህመም ከሚያስከትላቸዉ
የጤና ችግሮች አንዱ ነዉ።

ስኳር ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ ትናንሽ የደም ስሮች ላይ በሚያሰከትለዉ ተፅዕኖ ከፍተኛ ነዉ።

በወቅቱ ህክምና ካላገኘ ጋንግሪን ወደ ተባለ ችግር ብሎም እግር እሰኸመቆረጥ ሊያደርስ ይችላል።።።

ሰፋ ያሉ እና ጥብቅ የማያደርጉ ጫማዎችን መጠቀም ይመከራል
👍5
💥የአንድ ጨቅላ ህፃን አይን ቢጫ መሆን የጤነኝነትም እነዲሁም የበሽታም ምልክት ሊሆን ይችላል።

💥 ዋናው ነገር ምልክቶችን አስተውሎ መመልከት ነው።

👉 የህፃኑ አይን ቢጫ የሆነው ያለምንም በሽታ መሆኑ በሀኪም ከተረጋገጠ፣ ህፃኑን ፀሀይ በማሞቅ በቶሎ መመለስ ይቻላል።

💥 አይን ቢጫ የሆነው ከበሽታ የሆነ እንደሆነ ከፍተኛ የ ቢሊሩቢን መጠን ከሚያደርሰው ጉዳት ለመታደግ አፋጣኝ ህክምናዎች አስፈላጊ ናቸው።

💥💥💥💥እነዚህም💥💥💥💥

የ ሰማያዊ ብርሀን ህክምና
የደም መቀየር ህክምና እና
በደም ስር በሚሰጥ መዳኒት ህክምና ናቸው

⭐️ እነዚህ ህክምናዎች በደረጃቸው የሚሰጡት በ ጨቅላ ህፃናት የፀኑ ህሙማን ክፍል ሲሆን፣ በደም ውስጥ እንዳለው የ ቢሊሩቢን መጠን እና የበሽታ ደረጃ፣ በተናጥል ወይም አንድላይ ሊሰጡ ይችላሉ

።።።።።ይቀጥላል ።።።።።
👍6
ቀርባችሁ ህክምና ማድረግ የምትፈልጉ፣ በዚህ አድራሻ ቀጠሮ ለማስያዝ ስም እና ስልክ ቁጥር አስቀምጡ። ይደውሉላችሁዋል

ለቀጠሮ ብቻ!!

👇👇👇
@SMCAHP

እኔን አስቀድማችሁ ለመጠየቅ ደሞ በዚህ መደወል ይቻላል
👇👇👇
+251974163424 ዶ/ር ሰይፈ
👍2
የመሀፀን እጢ እያለ ልጅ መውለድ ይቻላል

⭐️ነገር ግን እጢው ያደገበት ቦታ እንዲሁም መጠን እና ብዛት በፅንሱ እንዲሁም በእናትየዋም ላይ ተፅእኖ ሊያሳድር ይችላል።

⭐️እርግዝና ከተፈጠረ እጢው ሊያደረግ ወይም ሊከስም ይችላል።

⭐️በሚከስምበት ግዜ ከፍተኛ ህመም ያስከትላል

⭐️እጢው የወጣበት ቦታ በፅንሱ ላይ አስተዋፆ ሊያደርግ ይችላል።

⭐️ማለትም እጢው በማህፀን በር አካባቢ ከሆነ በምጥ ግዜ እንዲሁም በወሊድ ግዜ መስተጓጐልን የመፍጠር አቅም አለው።

⭐️የመሀፀን እጢ በወሊድ ግዜ የደም ፍሰትን ሊያስከትል ስለሚችል፣ ቀጠሮን አክብሮ ክትትል ማረግ ስፈላጊ ነው።

⭐️ለዚህም ጥብቅ ክትትል ያስፈልገዋል።

⭐️እጢው በመሀፀን ግድግዳ ስር ከሆነ እና መጠኑ እንዲሁም ብዛቱ ከፍተኛ ከሆነ ውርጃን ሊያመጣ ይችላል።

👉👉የመሀፀን እጢ ህክምና በ 3 አይነት ዘርፍ ይሰጣል

በቀዶ ጥገና
በመድሀኒት
ደምስርን በማክሰም

💥💥እነዚህ የህክምና አማራጮች የሚሰጡት በሀኪም ውሳኔ ነው።
👍61👏1
🖲 እንድትገነዘቡ የምፈልገው 🖲

🚩 ፊንጢጣ ላይ የሚወጣ እብጠት ሁሉ ኪንታሮት አይደለም 🚩

🧠 ማንኛውም በፊንጢጣ አካባቢ የሚወጣ እብጠት በሀኪም መታየት አለበት 🧠

ኪንታሮት እንዴት እንደሚመጣ ባይታወቅም ነገር ግን ብዙ አጋላጭ ምክንታቶች አሉት ቪዲዮ ላይ እንደሰማችሁት።

ኪንታሮት በሁለት ይከፈላል
🚩 የውስጥ እና የ ውጭ

🖲 የውስጥ ኪንታሮት 4 የ እድገት ደረጃ አለው
👉 ደረጃ 1 እና 2 በ መድሀኒት ይታከማል
👉 በመዳኒት ያልዳነ ደረጃ 2 እና ከዛ በላይ የሆኑት ደሞ የመቋጠር እና የቀዶ ህክምና አማራጮች አሉዋቸው።

🖲 የውጪ ኪንታሮት ካልታከመ በውስጡ ደም ይረጋና ለከፍተኛ እና ድንገተኛ የፊንጢጣ ህመም ያጋልጣል።

🖲 የውስጥ ኪንታሮት ደሞ፣ ከህመም ይልቅ የመድማት በህሪ ያሳያል፣ እያደገ ሲመጣ ደሞ፣ የመታነቅ፣ የመቁሰል እና የመምገል ባህሪ ስላለው፣ በፊንጢጣ አካባቢ ቁጣን እና ህመምን ይፈጥራል።
👍18
**የወር አበባ መዛባት****

መደበኛ የወር አበባ ዑደት...
* ከ 1 እስከ 8 ቀን በአማካኝ 5 ቀን የሚቆይ

*ከ21 እስከ 35 ቀን ባለዉ ጊዜ በአማካኝ በየ28ቀን የሚመጣ

*ከ10እስከ 80ሚሊ ሊትር ደም በአማካኝ እስከ 50ሚሊ ሊትር ደም

*ጠቆር ያለ እና የማይረጋ አይነት ነዉ።
ይህ መደበኛ የወር አበባ ዑደት ነዉ።

ከዚህ ሁኔታ በመጠን ፣በቆይታ ወይም በአይነቱ የተለየ የወር አበባ ዑደት የወር አበባ መዛባት ይባላል።

*ምክንያቶቹ እንደ እድሜ ደረጃቸዉ የተለያዩ ናቸዉ።

*ምልክቶቹ የወር አበባ ከጊዜዉ ቀድሞ መምጣት፣አሳልፎ መምጣት፣የደም መጠኑ መብዛት ወይም በጣም ማነስ ሊሆን ይችላል።

*ህክምናዉም ምርመራ ማድረግና ምክንያቱን መለየትን ና ማወቅ ሲሆን

*የህክምና አማራጮች እንደምክንያቱ የሚወሰን ሆኖ :

*የህመም ማስታገሻ፣የወር አበባ ማስተካከያ ክኒኖች እና የኦፕሬሺን አማራጮች አሉት።።።።።።።።።።።።
👍61
ሽበት የሚጀምርበት አማካይ እድሜ በጥቁሮች ላይ 43.9 ነው

👉 ካለ እድሜ የመጣ ሽበት የሚባለው በጥቁሮች ወይም በአፍሪካውያን ላይ እድሜያቸው ከ 30 አመት በታች የሆኑ ሰዎች ላይ ሲወጣ ነው

👉 ያለ እድሜ የሚመጣ ሽበት ምክኒያታዊ ሊሆን ይችላል።

👉 ሽበቱ የመጣበት ምክንያት ህክምናውን ይወስናል።

👉 ከታይሮይድ ህመም እንዲሁም በ መድሀኒት የጉንዮሽ ጉዳት እንዲሁም ከምግብ እጥረት የመጣን ሽበት መመለስ ይቻላል

👉 ይህም ማለት ለተጓደኝ ህመሞች ህክምና በማድረግ እንዲሁም የቫይታሚን ቢ 12 እጥረትን በማከም ሽበት ወደቀድሞ ይዘቱ የመመለስ እድል ይኖረዋል።

👉 በተጨማሪም vitamin E እና vitamin C የሚይዙ የፀጉር ቅባቶችን እንዲሁም መታጠቢያዎችን መጠቀም። እንቅስቃሴ እና በቂ እንቅልፍ በማድረግ ጭንቀትን ማስወገድ ያለእድሜ የሚመጣ ሽበትን የመከላከል አቅም አላቸው።
👍13🙏1
🖲 ያለመፀነስ ችግር ወይም Infertility የሚባለው በአንድ አመት የትዳር ቆይታ ያለመከላከያ ወትሮአዊ ግንኙነት እየተደረገ ፅንስ ካልተፈጠረ ነው።

🖲 ምክንያቱ ከታወቀ መፍተሔ ሊኖረው ስለሚችል ሁለቱም ፆታዎች ምርመራ ማድረግ አለባቸው።

🖲 የሚያስፈልጉት ምርመራዎች በጥቂቱ

👉 የ ሀብለ ዘር ምርመራ ( semen analysis )
👉 የ ታይሮይድ ምርመራ ( TFT)
👉 የመራቢያ አካል እይታ ( U/S, HSG,MRI)
👉 የስነ ደዌ ምርመራ ( pathology )
👉 የ ደም ሆርሞን ጥናት እና እንዲሁም
👉 ጠቅላላ የደም ምርመራ ታካሚዋ/ታካሚው እንደሚያሳየው ወይም እንደሚናገረው ምልክት ብቻ በሀኪም የሚታዘዙ ምርመራዎች ናቸው።

🖲 ህክምናው እንደ ምክንያቱ ይወሰናል።

👉 የመራቢያ አካል ተፈጥሮአዊ ወይም ከግዜ በኋላ የመጣ ችግር ከሆነ
➧በቀዶ ህክምና
👉 የሆርሞን ችግር ካለ
➧በመድሀኒት
👉 ምክንያት የሚሆን ተጓዳኝ በሽታ ካለ
➧ለተጓዳኝ በሽታው ህክምና
በማድረግ
👉 እንቁላል እና ሀብለዘር እንዲመረት በማረግ
➧ovulation induction
👉 በሰው አገዝ መንገድ
➧IVF
እና የመሳሰሉት ይገኙበታል።
👍5
ያለ መፀነስ ችግር https://vm.tiktok.com/ZMdPGY6sd/
ክትትል የማይደረግለት የ አስም በሽታ አየባሰ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ የሳምባ ጉዳትም እያስከተለ ይሄዳል።

በአግባቡ የህክምና ክትትል በማድረግ እና አስምን ከሚቀሰቅሱ ተግባራትም ሆነ ሁኔታዎች እራስን ማራቅ ግድ ይላል።

አስም በድንገተኛ መልኩ አየር ሲያሳጥር በቶሎ ወደአቅራቢያ ወደሚገኝ የጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል።

መደንገጥ መርበትበት እና መሮጥ አያስፈልግም

አስምን ለመቆጣጠር እንደ ደረጃው ከ 1 እስከ 4 አይነት መድሀኒቶች ሊያስፈልጉ ይችላሉ።

ቀላል አስም በ 1 መዳኒት ብቻ መቆጣጠር ይቻላል።

እየባሰ ሲሄድ ግን ተጨማሪ መዳኒቶች አስፈላጊ ይሆናሉ።

የሚሰጡት መደበኛ የመዳኒት አይነቶች፣

➢የሚነፋ ፈጣን መልስ ያለው
➢የሚነፋ ረዘም ያለ መልስ ያለው
➢የሚነፋ ስቴሮይድ
➢የሚዋጥ ስቴሮይድ

ከዚህም ውጪ በሀኪም ትእዛዝ እንደ አስም ደረጃው ለረጅም ግዜ የሚሰጡ መዳኒቶችም አሉ።


https://vm.tiktok.com/ZMdHaq1Qx/


።።ይቀጥላል።።።
👍92
🖲 በአንድ ሰው ቆዳ ላይ ከ 1.5 _1.8 ሚሊየን የሚደርሱ 3 አይነት ዝርያ ያላቸው የላብ አምራች እጢዎች ይገኛሉ

🖲 ብዛታቸው እንዲሁም የሚያመርቱት የላብ አይነት እና መጠን በሰውነት ክፍል ይወሰናል።

🖲 በተጓዳኝ በሽታ ምክንያት የመጣን ከልክ ያለፈ ላብ ማለብን ለተጓዳኝ በሽታው ህክምና በማድረግ ማስተካከል ይቻላል

🖲 ከተጓዳኝ በሽታ ውጪ የመጣ ከልክ ያለፈ ላብ፣ ለህክምና አስቸጋሪ ቢሆንም፣ ነገር ግን ራሱን የቻለ የህክምና አማራጮች አሉት

እነዚህም

🌿 በሚቀባ እና በሚዋጥ መዳኒት
🌿 በነርቭ እና በቆዳ ላይ በሚደረግ ቀዶ ህክምና እና
🌿 እንዲሁም የቦቶክስ እና የማይክሮ ዌቭ ህክምና ይገኙበታል።

👉 በሚቀባ እና በሚዋጥ መልኩ የሚሰጡ የላብ ማጥፊያ መዳኒቶች ግዜያዊ ናቸው።
👉 በሚወሰዱበትም ግዜ ጥንቃቄ ያስፈልጋቸዋል።

👉 ለእግር ለእጅ እና ለብብት የምንጠቀማቸው ለላብ የሚሰጡ መዳኒቶች የተለያዩ ናቸው።

👉 ለእግር ላብ ፎረማልድሀይድ፣ ለብብት እና ለእጅ ደሞ አልሙኒየም ክሎራይድ ወይም ግላኮፓይሮኒየምን የሚይዙ ቅባቶች ወይም መጥረጊያዎች ናቸው።

👉👉👉 እነዚህ መዳኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት ስላላቸው የሀኪም ትእዛዝ እና ክትትልን ይፈልጋሉ።

https://vm.tiktok.com/ZMdXVPLRq/


https://t.me/seifemed
👍181🥰1
🖲 መጥፎ የሰውነት ጠረን አብዛኛውን ግዜ ለባለቤቱ ባዳ ነው።
👉ማለትም አንድ ሰው መጥፎ የሰውነት ጠረን እንዳለው የሚነግረው ሌላ ሰው ነው፣ አፍንጫችን የራስ ጠረንን ስለሚለምድ።

🖲ላብ በተፈጥሮ ሽታ ኖሮት ከሰውነት አይወጣም፣ ነገርግን በቆዳላይ የሚገኙ ባክቴሬያዎች፣ በላብ የሚወጣውን ፋቲ አሲድ ወደ ሽታ ወዳለው ተረፈምርት ሲቀይሩት መጥፎ ተሰውነት ጠረንን ይፈጥራል።



🖲አብዛኛውን ግዜ የወንድ መጥፎ ጠረን ከሴት መጥፎ ጠረን ይለያል ።

🖲ይህም የሆነበት ምክንያት፣
      👉በ ወንድ ላይ የሚገኘው ኮርኒባክቴሪየም
      👉በ ሴትላይ ደሞ ስታፊሎኮከስ የተባለ ተህዋስ ስለሚገኝ ነው

🖲መጥፎ ጠረንን ለማጥፋት ብዙ መንገዶች አሉ
      👉ነጽህናን አዘውትሮ መጠበቅ
      👉ብብት አካባቢ የሚገኝ ፀጉርን መቀነስ
      👉እንዲሁም አንቲሴፕቲክ የሚይዙ ሳሙናዎችን እና ዶዶራንቶችን መጠቀም እና
      👉 ከዚህ ባለፈ መልኩ ደሞ በህክምና ማጥፋት ይቻላል።

🖲 ዶዶራንት እና አንቲፐሪስፓይራንት የተለያየ ይዘት አላቸው

🖲 ጥራታቸውን የጠበቁ ዶዶራንቶች አብዛኛውን ግዜ አንቲሴፕቲክ ይይዛሉ

🖲 አንቲፐሪስፓይራንቶች ደሞ የላብ ማጥፊያ ጨው ይይዛሉ

🖲 አንዳንዴ ደሞ ሁለቱንም ቀላቅለው የሚይዙ ምርቶች በገበያ ላይ ይገኛሉ።

🖲 እነዚህን ንጥረ ነገሮች ለረጅም ግዜ ሰውነት ላይ መጠቀም ራሱን የቻለ የጎንዮሽ ጉዳት አለው።

🖲 በማንኛውም ግዜ መጥፎ የሰውነት ጠረን ሲያጋጥም ንፅህናን በመጠበቅ የማይስተካከል ከሆነ ሀኪምን ማማከር ተገቢ ነው።

ቲክቶክ 👉 https://vm.tiktok.com/ZMd4NbpVH/

ዩቲዩብ 👇
https://youtube.com/shorts/eRV3CAfsAew?feature=share

ቴሌግራም 👇
https://t.me/seifemed
👍14👏1
👍31