Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ
47.6K subscribers
178 photos
2 videos
6 files
130 links
የዚህ ቻናል አላማ፣ ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን የህክምና አስተምሮት እና መልእክቶች ማስተላለፍ ነው።
📞 0974163424
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን 👉 @LEKETERO ወይም @Apointment1
ተጭነው ስም እና ስልክ አስቀምጡ።

ዶ/ር ሰይፈ (ጠቅላላ ሐኪም)
Download Telegram
👍2
በእርግዝና ግዜ፣ እናት ማህፀን ውስጥ እያለ በ አልኮል የተጠቃ ልጅ፣ በውልደት ግዜ ለየት ያለ የተፈጥሮ ገፅታ ይይዛል።

ከነዚህም ውስጥ
🖲 ከለይ እንደሚታየው፣ የአይን ቀዳዳ መጥበብ።

🖲 የራስ ቅል ማነስ

🖲 የላይኛው ከንፈር መሳሳት እንዲሁም በከንፈር እና በአፍንጫ መሀል የሚገኘው ስርጉድ ቆዳ መጥፋት እና መለስለስ

🖲 ጆሮ ላይ የሚከሰቱ የተለያዩ የአፈጣጠር ችግሮች ይገኙበታል።

ከዚህም በተጨማሪ ለአልኮል የተጋለጠ ፅንስ ከተወለደ በኋላ
👉የልብ
👉የአጥንት
👉የኩላሊት
👉የዐይን እና የጆሮ ችግር ያጋጥሟቸዋል

በተለያየ የእድሜ ክልል የሚታየው የ አእምሮ እና የስነ ልቦና ችግር እራሱን የቻለ የህክምና መገለጫ አለው።

ከዚህም ውስጥ።

🖲በህፃንነት ግዜ ነጭናጫና ሲበዛ አልቃሻ መሆን ፣ ዝግመታዊ እድገተ ለውጥ ማሳየት።

🖲በልጅነት ግዜ ትምህርት የመረዳት ችግር ፣ ከወትሮ ለየት ያለ ስሜታዊነት ማሳየት፣ የመርሳት ችግር

🖲በወጣትነት ግዜ ደሞ ከማህበረሰቡ ጋር የመግባባት ችግር፣ የችሎታ ወይም የክህሎት እጥረት፣ በተደጋጋሚ ለወንጀል የመጋለጥ ባህሪ ፣ ለወጥ ያለ የወሲብ ስሜት ባህሪ
እና የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው


።።።።ይቀጥላል ።።።
👍6
በእርግዝና ግዜ፣ እናት ማህፀን ውስጥ እያለ በ አልኮል የተጠቃ ልጅ፣ በውልደት ግዜ ለየት ያለ የተፈጥሮ ገፅታ ይይዛል።

ከነዚህም ውስጥ
🖲 ከለይ እንደሚታየው፣ የአይን ቀዳዳ መጥበብ።

🖲 የራስ ቅል ማነስ

🖲 የላይኛው ከንፈር መሳሳት እንዲሁም በከንፈር እና በአፍንጫ መሀል የሚገኘው ስርጉድ ቆዳ መጥፋት እና መለስለስ

🖲 ጆሮ ላይ የሚከሰቱ የተለያዩ የአፈጣጠር ችግሮች ይገኙበታል።

ከዚህም በተጨማሪ ለአልኮል የተጋለጠ ፅንስ ከተወለደ በኋላ
👉የልብ
👉የአጥንት
👉የኩላሊት
👉የዐይን እና የጆሮ ችግር ያጋጥሟቸዋል

በተለያየ የእድሜ ክልል የሚታየው የ አእምሮ እና የስነ ልቦና ችግር እራሱን የቻለ የህክምና መገለጫ አለው።

ከዚህም ውስጥ።

🖲በህፃንነት ግዜ ነጭናጫና ሲበዛ አልቃሻ መሆን ፣ ዝግመታዊ እድገተ ለውጥ ማሳየት።

🖲በልጅነት ግዜ ትምህርት የመረዳት ችግር ፣ ከወትሮ ለየት ያለ ስሜታዊነት ማሳየት፣ የመርሳት ችግር

🖲በወጣትነት ግዜ ደሞ ከማህበረሰቡ ጋር የመግባባት ችግር፣ የችሎታ ወይም የክህሎት እጥረት፣ በተደጋጋሚ ለወንጀል የመጋለጥ ባህሪ ፣ ለወጥ ያለ የወሲብ ስሜት ባህሪ
እና የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው


።።።።ይቀጥላል ።።።
👍3🙏1
Live stream started
Live stream finished (26 minutes)
Live stream started
Live stream finished (35 minutes)
ከፍተኛ የደም ስብ መጠን የጤና ጠንቅ መሆኑን የማያውቅ የለም።

🚩 ልብ ማለት ያስፈልጋል 🚩

ደረቅ ዘይት ወይም ከእንስሳት ምርት የሚወጣ ስብን አብዝቶ በመመገብ የምንሸምተው።

🖲 ውፍረት
🖲 የደም ግፊት
🖲 የ ስኳር በሽታ
🖲 የልብ ህመም
🖲 ስትሮክ

እና ሌሎችም የስነልቦና ችግሮች ተጠቃሾች ናቸው።

የደም ስብ ምርመራ የሚያካትተው

🖲 LDL
🖲 HDL
🖲 Total Cholesterol
🖲 Triglyceride

ይባላሉ።
እነዚህን ምርመራዎች ከየትኛውም ላቦራቶሪ ማግኘት ይቻላል
ለምርመራ በጠዋት ምግብ ከመበላቱ በፊት ሲሆን ትክክለኛ ውጤት ይሰጣል።

ውጤቱም ለጤነኛ ሰው።
🖲 Total cholesterol ከ 200 በታች
🖲 LDL ከ 100 በታች
🖲 HDL ከ 50 በላይ
🖲 Triglyceride ከ 150 በታች መሆን አለበት

።።።።።ይቀጥላል ።።።።
👍11
👉 ስፖርትን ሳያቋርጡ አዘውትሮ መስራት
👉 የ አታክልት ፣ ፍራፍሬ ፣ እና ከእፅዋት የተውጣጡ ምግቦችን መመገብ
👉 ከ ጥብሳጥብስ ምግቦች ይልቅ፣ የተቀቀሉ ምግቦችን መምረጥ
👉አልኮል የሚይዙ መጠጦችን በጣም መቀነስ

የደም ስብ መጠንን በደምብ አርገው የቀንሳሉ።

💥 ከዚህ ውጪ በሀኪም ትእዛዝ የሚሰጠው የ ደም ስብ መቀነሻ መዳኒት ግዜአዊ በሆነ መልኩ ብቻ የደም ስብን የመቀነስ እገዛ ያደርጋል።
👍62
💥የዐይን መንሸዋርን በህክምና ማስተካከል ይቻላል💥

👉 የመጀመሪያው የህክምና እርምጃ የዐይን መንሸዋረሩ በምን ምክንያት አንደመጣ መረዳት ነው።

ይሄን ማድረግ የሀኪም ስራ ይሆናል ማለት ነው።

ምክንያቱ ከታወቀ፣ እንዳስፈላጊነቱ የተለያዩ የህክምና አማራጮች ይኖሩታል።

🖲 በመነፅር
🖲 በአይን መሸፈኛ
🖲 በቀዶ ህክምና
🖲 የአይን ጡንቻ ላይ በሚወጋ መዳኒት እና
🖲 ለተጓዳኝ ህመሞች አስፈላጊውን ህክምና በማድረግ ይሆናል።

።።።።።ይቀጥላል ።።።።።
👍6
Forwarded from Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ (Dr. Seife)
💥የዐይን መንሸዋርን በህክምና ማስተካከል ይቻላል💥

👉 የመጀመሪያው የህክምና እርምጃ የዐይን መንሸዋረሩ በምን ምክንያት አንደመጣ መረዳት ነው።

ይሄን ማድረግ የሀኪም ስራ ይሆናል ማለት ነው።

ምክንያቱ ከታወቀ፣ እንዳስፈላጊነቱ የተለያዩ የህክምና አማራጮች ይኖሩታል።

🖲 በመነፅር
🖲 በአይን መሸፈኛ
🖲 በቀዶ ህክምና
🖲 የአይን ጡንቻ ላይ በሚወጋ መዳኒት እና
🖲 ለተጓዳኝ ህመሞች አስፈላጊውን ህክምና በማድረግ ይሆናል።

።።።።።ይቀጥላል ።።።።።
👍81
💥ዉርጃ 💥


👉 ዉርጃ ፅንስ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ከ 28 ሳምንት በፊት የሚያጋጥም የፅንስ መጨናገፍ ነዉ።

👉ይህም በራሱ ወይም ሆን ተብሎ ሊከናወን ይችላል።

👉 በኢትዮጵያ ህግ ነባራዊ ሁኔታ መሰረት ዉረጃየሚፈቀደዉ ፣

ከ 18 አመት በታች ለሆነች ሴት

*ፅንሱ በህይወት ለመቀጠል የማያሰቺል መሰረታዊ የአፈጣጠር ችግር ካለበት፣

*እናትዮዋ ከባድ የሆነ የልብ ፡ የሳንባ ወይም አዕምሮ ህመም ያለባት እንደሆነ፣

*እርግዝናዉ የተፈጠረዉ ተደፍራ ከሆነ ነዉ።

ዶ/ር ዮርዳኖስ
👍72
💥Vitiligo ለምፅ💥

ምንም እንኳን የቆዳ ቀለም ተፈጥሮ፣ የፀሃይ ጨረርን ከመከላከል ባሻገር ሌላ ተፈጥሮአዊ ጥቅም ባይኖረውም፣ የቆዳ ቀለም በ ግንዛቤ ላይ ያለው ተፅእኖ ከፍተኛ ነው።

ለምፅ የሚመጣበት አንድ ወጥ የሆነ ምክንያት የለውም። ነገር ግን ብዙ ምክንያቶች ለምፅን እንደሚያመጡ ይገመታል

ለምፅን ሊያስነሱ የሚችሉ ምክንያቶች
👉 የ ቫይረስ ኢንፌክሽን
👉 የ ሆርሞን መለዋወጥ
👉 ቆዳን የሚጎዱ ኬሚካሎች
👉 ጭንቀት እና
👉 ቆዳ ላይ የሚደርሱ አደጋዎች
ተጠቃሾች ናቸው።
ለምፅ በዋነኝነት ሊመጣ የሚችለው፣ የሰውነት የበሽታ ተከላለይ ህዋሶች፣ በቀለም አምራች ህዋሶች ላይ በሚያስከትሉት ጉዳት ነው።

ከዚህም ምክንያት ጋር ተያያዥነት ያላቸው፣ የተለያዩ የውስጥ ደዌ ህመሞች ፣ በለምፅ ታካሚዎች ላይ ሊያጋጥሙ ይችላሉ።

ለምሳሌ ያህል፣
👉 የ እንቅርት ህመም
👉 የስኳር በሽታ
👉 የደም ማነስ አይነት
👉 የ ላሽ በሽታና፣ እንዲሁም ሌሎች ከሰውነት ቁጣ ጋር የተያያዙ ተጓዳኝ በሽታዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ፣ የለምፅ ታካሚዎች አስፈላጊውን ምርመራና ክትትል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ።
👍6😢1
💥ይህ አይነቱ የቆዳ ለውጥ አብዛኛውን ግዜ እንደ ቀቁቻ እና ጭርት ተደርጎ ይታያል፣

⭐️ ነገር ግን ቋቁቻም ጭርትም አይደለም

በተለያዩ ምክንያቶች ቆዳ ለረጅም ግዜ ሲታከክ የሚፈጠር ነው።

⭐️ ከሰው ወደሰው በንክኪ አይተላለፍም

👉ህክምናው

ኮሌታ ያላቸውን ልብሶች አለማረግ

እከክ ሊያስነሱብን የሚችሉ ማናቸውንም ነገሮች ከመጠቀም መቆጠብ

በሀኪም ትእዛዝ የሚሰጡ የሚቀቡ የስቴሮይድ መዳኒቶችን በአግባቡ መጠቀም

ከጭንቀት ጋር ተንተርሶ ለሚመጣ ማሳከክ ተጨማሪ የስነልቦና ምክር እና ህክምና ያስፈልገዋል ።
👍2