ቄድሮን • qedron
449 subscribers
264 photos
32 videos
3 files
496 links
ተሽከርካሪ፡በስልክ፡መከታተያ፡እና፡መቆጣጠሪያ።
Tracking and security for your vehicles.
Download Telegram
#ኢትዮጵያ

ጤፍን ጨምሮ በሌሎች የግብርና ግብዓት ምርቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ መሆናቸውን የሚወስነዉ መመሪያዉ ተግባራዊ መደረግ እንደጀመረ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።

የገንዘብ ሚኒስቴር በአገር ውስጥ የሚመረቱ እና ከውጭ አገር የሚገቡ እቃዎች እንዲሁም በአገር ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ መሆናቸውን አረጋግጧል።

ከሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ በተጀመረው በዚህ መመሪያ ዉስጥ የእህልና ጥሬጥሬ ፣ የግብርና ምርቶች እና የበሰሉ ወይም የተዘጋጁ ምግቦች / መጠጦች ይገኙበታል ።

በዚህ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሚሆኑ እቃዎችን ለመወሰን በወጣው መመሪያ ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል መሰረታዊ የሆኑ የምግብ አቅርቦቶችን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ሆኖ እንዲገዛ ማድረግ የወጪ ጫናውን በማርገብ ረገድ ጠቀሜታ አለው ተብሏል።

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ከተደረጉት መካከል ፦
➡️ ጤፍ፣
➡️ ስንዴ፣
➡️ ገብስ ፣
➡️ ማዳበሪያ ፣
➡️ የእንስሳት መድሃኒት እንዲሁም በካፒታል ሊዝ ስምምነት የሚቀርብ የካፒታል ዕቃዎች ይገኙበታል።

መረጃው የካፒታል ጋዜጣ ነው።

ቴዘርን የመኪና መቆጣጠሪያ GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth