ቄድሮን • qedron
449 subscribers
264 photos
32 videos
3 files
494 links
ተሽከርካሪ፡በስልክ፡መከታተያ፡እና፡መቆጣጠሪያ።
Tracking and security for your vehicles.
Download Telegram
#ኢትዮቴሌኮም : ዛሬ የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ ሆኗል።

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በተካሄደ ሥነ-ስርዓት የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ ተደርጓል።

የአክሲዮን ሽያጭ ጊዜው ከዛሬ ጥቅምት 6 ጀምሮ እስከ ታኅሣስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል፡፡

ዝርዝር መረጃ ፦

- በ2016 በወጣው የሂሳብ ሪፖርት የድርጅቱ ካፒታል ➡️ 100 ቢሊዮን ብር ነው።

- በዓለም አቀፍ የ3ተኛ ወገን የገበያ ተመን መሰረት ድርጅቱ የሚያወጣው ዋጋ ➡️ 300 ቢሊዮን ብር ነው።

- በመጀመሪያው ዙር መደበኛ የአክሲዮን ሽያጭ የቀረበው ➡️ 100 ሚሊዮን ሼር ነው።

- የአንድ ሼር ዋጋ ➡️ 300 ብር ነው።

- 100 ሚሊዮን ሼር በ300 ብር ሲሸጥ ኢትዮ ቴሌኮም ከሼር ሽያጭ ➡️ 30 ቢሊዮን ብር ያገኛል።

- ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን ➡️ 33 ሼር ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 9,900 ብር ይሆናል።

- ከፍተኛው መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 3,333 ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ ➡️999,900 ብር ይሆናል።

- መግዛት የሚቻለው ከዛሬ ጥቅምት 6 እስከ ታህሳስ 25 ድረስ ይሆናል።

- የሼር አባላቱ የሚታወቁት ➡️ ጥር 23/2017

- ሽያጩ በቴሌብር ብቻ የሚደረግ ይሆናል።

- ክፍያውን በ48 ሰዓት ውስጥ መክፈል ይቻላል።

- አንድ አክሲዮን ግዢ ሲፈጸም ከአክስዮኑ ዋጋ በተጨማሪ 1.5% የአገልግሎት ክፍያ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፍል ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth