‹‹እኛ እና ምን አገባኝ ባህሪያችን››
+++++++++++++++
ልክ ትራፊክ መብራት ይዞን ስንቆም፣ ከሰፈር ጀምሮ ስከተለው የነበረውን ዘናጭ ሃውንዳይ መኪናውን ያለ ፍሬቻ አንዴ ወዲህ፣ አንዴ ወዲያ እየነዳ ሲበጠብጠኝና ሲያበሳጨኝ የነበረው ሰውዬ ጭራሽ የገረመኝን ነገር አደረገ፡፡
አሁንም ምንም ምልክት ሳያሳየኝ በድንገት ከመስመር ወጣና ባዶ ወደነበረው ለአውቶቢስ ብቻ የተፈቀደ መቆሚያ ላይ ሲጢጥ አድርጎ ቆመ፡፡
ይሄ ሰውዬ በዚህ በጠዋት ጠጥቶ ነው ወይስ አንግቶበት…ሆ!
‹‹ይሄ ቦታ ለሌላ መኪና ክልክል እንደሆን አያውቅም ወይስ ማን አለብኝነት ነው? …››አልኩና መሪዬን እንደያዝኩ ዞር ብዬ አየሁት፡፡
በግራ እጁ ስልክ ይዞ በቀኝ እጁ መሪውን እየደበደበና እየተወራጨ ያወራል…
‹‹ወይ ጉድ…ከቤቱ ሲወጣ ማን ጃስ ብሎት ነው እንዲህ መንገዱን ሲያተራምስ የቆየው…ጭራሽ አሁን አውቶቢስ መቆሚያ ላይ ቆሞ በስልክ ፡፡
---
በነጋታው ያ ሰውዬ በድንገተኛ የልብ ህመም እዚያው ቆሞ ያየሁት ቦታ ላይ መኪናው ውስጥ ሞቶ እንደተገኘ በየሶሻል ሚዲያው ላይ ሲወራ አየሁ፡፡
ወሬው እንደሚለው፣ ገና ከቤቱ እንደወጣ ከባድ ህመም ደረቱን ሰቅፎ ይዞት የቻለበት ቦታ መኪናውን አቁሞ መታመሙን ለመንገር ለሚስቱ ለመደወል ቢችልም ፣ እንደኔ ያለው አላፊ አግዳሚ በሞገደኛ አሽከርካሪነቱ እየረገመው ከመሄድ ውጪ ምን ሆኖ ብሎ ስላላስተዋለው የሚደርስለት አጥቶ እዛው ሞተ፡፡
የሟሟቱን አሳዛኝነት፣ የእኔን ምንም አለማድረግና የሚስትና ትናንሽ ልጆቹን ፎቶ ማየቴ ተደምረው በፀፀት አለንጋ ተገረፍኩ፡፡
#ሂወት

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth