ቄድሮን • qedron
449 subscribers
264 photos
32 videos
3 files
495 links
ተሽከርካሪ፡በስልክ፡መከታተያ፡እና፡መቆጣጠሪያ።
Tracking and security for your vehicles.
Download Telegram
📷

ዛሬ መነሻውን ከአዲስ አበባ አድርጎ ይጓዝ የነበረ  ተሳቢ መኪና ጌዴኦ ዞን፣ ወናጎ ወረዳ ውስጥ ተንሸራቶ ሲወድቅ ከመብራት ሽቦ ጋር ተገናኝቶ እሳት በመነቱ መኪናውን በእሳት ተቀጣጥሎ ወድሟል።

መኪናው ውስጥ የነበሩ ሰዎች ላይ ምንም ጉዳት ሳይደርስ ተርፈዋል።

ሌላኛው የሰሌዳ ቁጥር '  ኦ.ሮ 27555 ' የህዝብ ማመላለሻ መንገድ ስቶ ተገልብጦ በደረሰ አደጋ ሶስት ሰዎች ተጎድተው ዲላ ሆስፒታል ገብተው ህክምና ላይ ናቸው።

ፖሊስ አደጋ የደረሰው በነበረው ዝናብ ምክንያት በመንሸራተት እንደሆነ ጠቁሞ የክረምት ወቅቱ በመግባቱ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

#ጌዴኦዞንኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66951d557c0ca4bafb80cd88

የሙቀት መከላከያ ኮሮላ መኪና /double face/++
የሙቀት መከላከያ ኮሮላ መኪና /double face/++
- Published by Ethiopia Pharmaceutical Supplies Service

💵 ፕሮፎርማ Mon Jul 15th, 2024 - Mon Jul 15th, 2024

ምንጭ
ትኩረት- ለወባ- በሽታ!!!

#Ethiopia | የወባ ወረርሽኝ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል !

የወባ ወረርሽኝን ለመከላከል መወሰድ ያለባቸው ተግባራት እንደሚከተለው ቀርቧል

👉አጎበርን በአግባቡ መወጠርና ሁሌም
በአግባቡ መጠቀም

👉በፀረ-ወባ ኬሚካል በተነከረ አጎበር
ውስጥ መተኛት

👉የአጎበር አጠቃቀም ላይ ለነፍሰጡር.
እናቶችና ለህጻናት ቅድሚያ መስጠት

👉አጎበርን ለታለመለት አላማ በማዋልና
መጠቀም

👉የቤት ውስጥ የፀረ ወባ ትንኝ ኬሚካል
ቤትዎን ማስረጨት
👉በጸረ-ወባ ኬሚካል የተረጨ ግድግዳ ላይ
እስከ 6 ወር ቀለም አለመቀባት፣ እበት
ባለመለቅለቅ፣ በወረቀት አለመሸፈን

👉በግቢዎና በአካባቢዎ ያሉ ዉሃ የሚያቆሩ
ቦታዎችንና ቁሳቁሶችን እንደ መኪና ጎማ፣
የሸክላ ስባሪዎች፣ የወዳደቁ ጣሳዎች
ማስወገድ፣ ማፋሰስ፣ መደልደል

👉ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ማላብ፣ ራስ
ምታት፣ የሰውነት መጓጎል፣ ማቅለሽለሽና
ማስመለስ የወባ በሽታ ምልክቶች ሊሆኑ
ስለሚችሉ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና
ተቋም በመሄድ ምርመራ ያድርጉ።

👉በምርመራ የወባ በሽታ መሆኑ ከተረጋግጠ
በጤና ባላሙያ በታዘዘሎት መሰረት
መድኃኒቱን ጨርሶ መውሰድ

👉በወባማ አካባቢዎች ከአንድ ወር በላይ
ቆይተው ሲመለሱ የወባ በሽታ ምርመራ
በማድረግ ራስዎን ቤተሰቦን እና
ማህበረሰቡን ከወባ በሽታ ይከላከሉ:


Via ጌጡ ተመስገን

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66962883fe3d907205e10d16

procurement of labour works 11
- Published by Amanuel Mental Specialized Hospital

💵 ፕሮፎርማ Tue Jul 16th, 2024 - Tue Jul 16th, 2024

ምንጭ
በአዲስ አበባ ከተማ ኮድ 2 በፈረቃ ሊሆን ነው

#Ethiopia | በአዲስ አበባ በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት፤ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ሊደረግ ነው፡፡

በከተማዋ ጠዋትና ማታ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲቀሳቀሱ ሊደረግ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ለሸገር ተናግሯል፡፡

ጎዶሎ ቁጥር እና ሙሉ ቁጥር የኮድ 2 ተሽከርካሪዎችን በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርግ የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቷል ያሉት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የትራፊክ ቁጥጥርና ሁነት አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አያሌው እቴሳ ናቸው፡፡

እቅዱ በ2 እና በ3 ወር ጊዜ ውስጥ፤ በከተማው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኮድ 2 ተሽከርካራች በፈረቃ አንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል ተብሏል፡፡

የኦሮሚያንና የፌዴራልን ታርጋ ሳይጨምር የአዲስ አበባ ታርጋ ብቻ ያላቸው ተሽከርካሪዎች ከ755 ሺ በላይ ናቸው ያሉት አቶ አያሌው ከእነዚህ ውስጥ የበዙት ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በመሆናቸው ነው ጠዋትና ማታ በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚደረገው ሲሉም ለሸገር ተናግረዋል፡፡

Via ሸገር ኤፍኤም

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66977a04bb8fe18e813a783a

Purchase of Generator Maintenance service
for University Service
- Published by Bule Hora University

💵 ፕሮፎርማ Wed Jul 17th, 2024 - Wed Jul 17th, 2024

ምንጭ
አይ ቴክኖሎጂ😱😱

የሚስቱን ውስልትና በድሮን ታግዞ ያወቀው ባል

#Ethiopia | ሚስቴ የተለየ ባህሪ አሳይታለች በሚል መከታተል የጀመረው ባል በመጨረሻም ከአለቃዋ ጋር እንደምትወሰልት ደርሶበታል

አል-ዐይን

ባልየው በድሮን ታግዞ ባደረገው ክትትል በቅርቡ የደመወዝ ጭማሪ ካደረገላት ሌላ ባለትዳር ጋር ስትወሰልት የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል ለቋል

የሚስቱን ውስልትና በድሮን ታግዞ ያወቀው ባል

ጂንግ በመባል የሚጠራው ቻይናዊ ሰው ስሟ ካልተጠቀሰችው ባለቤቱ ጋር በትዳር ተሳስረው እየኖሩ ነበር፡፡

በአንድ ህንጻ ላይ ነገር ግን በተለያዩ ተቋማት ተቀጥረው ሲሰሩ የተዋወቁት እነዚህ ጥንዶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ፍቅራቸው ንፋስ ገብቶበታል፡፡

ባልተለመደ መልኩ ቤተሰቦቼን ልጠይቅ እየሄድኩ ነው በሚል ተደጋጋሚ ጥያቄ ለባሏ የምታቀርበው ይህች ሚስት ለመዝናት በባሏ ስትጠየቅም ይቅርታ እየጠየቀች እንደማይመቻት ስትናገር ነበርም ተብሏል፡፡

የሚስቱን ባህሪ መቀያየር ያስተዋለው ባልም በተለያዩ መንገዶች መከታተል ይጀምራል፡፡ ለዚህ ውጥኑም በድብቅ በድሮን የታገዘ ክትትል ሲያደርግየቆየው ባል በመጨረሻም ከአንድ ሰው ጋር ወደ ተሽከርካሪ ስትገባ ያያል፡፡

እስከ መጨረሻው ባደረገው ክትትልም ሚስቱ ከሌላ ሰው ጋር እየወሰለተች መሆኑን ያወቀ ሲሆን በሰውየው ላይ ባደረገው ክትትልም

ሚስትየው ከአለቃዋ ጋር ሆና ወደ ተለያዩ መዝናኛ ቦታዎች ሲገቡ እና ሲወጡ የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ መለቀቃቸውን ተከትሎ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡

via ጌጡ ተመስገን

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 6698cb84bb8fe18e813a7855

Brother toner cartridge TN-3417
- Published by BONGA UNIVERSITY

💵 ፕሮፎርማ Thu Jul 18th, 2024 - Thu Jul 18th, 2024

ምንጭ
ወላጆች ልጆቻችሁን ጠብቁ !!

በክረምት የእረፍት ጊዜ ወላጆች ለልጆቻቸው በቂ ጥበቃ እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና ሥራ አመራር ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል አሳሰበ።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ፣ ዛሬ (ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም) ከቀኑ 8 ሰዓት ገደማ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ወረገኑ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ውሃ ባቆረ ጉድጓድ የገባ ታዳጊ ህይወቱ ማለፉን ገልጸዋል።

" ውሃ ባቆረ ጉድጓድ ዋና ለመዋኘት የገባ የ13 ዓመት ታዳጊ ህይወቱ አልፏል" ያሉት አቶ ንጋቱ፣ "የኮሚሽኑ ጠላቂ ዋናተኞች የታዳጊውን አስከሬን አውጥተው ለፖሊስ አስረክበዋል " ብለዋል።

" በአዲስ አበባ ታዳጊዎችና ወጣቶች በቂ የዋና ችሎታ ሳይኖራቸው ለዋና በሚል ውሃ ባቆሩ ጉድጓዶች እየገቡ ህይወታቸውን ያጣሉ " ነው ያሉት።

አሁን ትምህርት ቤቶች ዝግ ስለሆኑ ታዳጊዎችና ወጣቶች ለጨዋታ በሚል ድርጊቱን ስለሚፈጽሙ ወላጆች በቂ ጥበቃ እንዲያደርጉላቸው አሳስበዋል።

ኮሚሽኑ አደጋውን ለመከላከል የሚያሰችሉ በሚል በተደጋጋሚ የሚያስተላልፋቸውን የጥንቃቄ መልዕክቶች ህብረተሰቡ፣ በተለይ ወላጆች፣ ታዳጊዎችና ወጣቶች  እንዲተገብሩ ጠይቋል።

ችግሩ እየተደጋገመ መሆኑ የተመላከተ ሲሆን፣ በዚህ አደጋ ምን ያህል ታዳጊዎች ህይወታቸውን እንዳጡ በቀጣይ የሚዳሰስ ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia


ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 669a5545bb8fe18e813a786f

Procurement of Ultrasound Probe
- Published by St. Peter Specialized Hospital

💵 50,000 ETB Fri Jul 26th, 2024 - Mon Jul 15th, 2024

ምንጭ
አደጋ ሳያደርሱ ለ50 ዓመታት ያሽከረከሩት

በድሬዳዋ ከተማ ለ 50 አመታት የትራፊክ አደጋ ሳያደርሱ ያሽከረክሩ የ 72 አመት ሹፌር ሽልማት ተበረከተላቸው

ከ 1966 ጀምሮ ለ50 አመታት በጠንቃቃ አሽከርካሪነት ከ አደጋ በፀዳ መልኩ ያሽከረክሩት የ 72 አመት ግለሰብ ከድሬዳዋ ከተማ የክብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በኢትዮጵያ ፖሊስ ሰራዊት በ 1962 ዓ/ም በሀረርጌ አውራጃ ተቀጥረው በተለያዩ ክፍለ ሀገራት ተዟዙረው አገልግለዋል የተባሉት ም/ኢ መሀመድ እንድሪስ ከከተማው ከንቲባ እጅ የክብር ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።

በፖሊስ ተቋም ሙያዊ ስነ-ምግባርን በመላበስ በሹፍርና ሙያ ከ 40 አመታት በላይ ያገለገሉ አባት ናቸው ም/ኢ መሀመድ እንድሪስ (ጋሽ ማሜ) ህዳር 27 ቀን 2004 ዓ.ም በጡረታ ከተለዩ በኋላም የድሬዳዋ የከተማ አዉቶብስ እያሽከረከሩ መሆኑን የድሬዳዋ ፖሊስ መምሪያ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን የላከዉ መረጃ ያመላክታል።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርም ለእኚሁ አሽከርካሪ የክብር ሽልማት ሰጥተዋል።

ም/ኢ መሀመድ እንድሪስ ኡሁንም በ 72 አመታቸው በድሬዳዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ የከተማ አውቶብስ በማሽከርከር ሀገር እና ህዝባቸውን እያገለገሉ ይገኛሉም ተብሏል።(ድሬዳዋ ፖሊስ)

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 669ba6c2bb8fe18e813a787a

Microtom Blade Low Profile
- Published by St. Paul's Hospital Millennium Medical College

💵 ፕሮፎርማ Mon Jul 22nd, 2024 - Sat Jul 20th, 2024

ምንጭ