ቄድሮን • qedron
448 subscribers
264 photos
32 videos
3 files
497 links
ተሽከርካሪ፡በስልክ፡መከታተያ፡እና፡መቆጣጠሪያ።
Tracking and security for your vehicles.
Download Telegram
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66c6fe1b1ab8285b9d2f124a

procurement of spare part 01/2017
- Published by Ministry of Industry

💵 ፕሮፎርማ Thu Aug 22nd, 2024 - Thu Aug 22nd, 2024

ምንጭ
👍1
በ 5 እጥፍ ጭማሪ የተደረገበት አዲሱ የሶስተኛ ወገን አርቦን ክፍያ ተፈፃሚ መሆን ጀመረ

አዲሱ የሦስተኛ ወገን የተሸከርካሪ መድን ፖሊሲ ከዛሬ ጀምሮ ተፈፃሚ መሆን መጀመሩ ተሰምቷል ። በዚህ 50 እጥፍ ጭማሪ የተደረገበት የአርቦን ክፍያ በአንድ ሰው ላይ ለሚደርስ የሞት አደጋ 5 ሺህ ብር የነበረዉ አሁን ወደ 250 ሺህ ብር ከፍ እንዲል ሆኗል።

በአዲሱ ደንብ መሰረት በአንድ ሰው ላይ ለሚደርስ ለአካል ጉዳት እስከ ብር 40 ሺህ ያልበለጠ የገንዘብ ካሳ ይከፈል የነበረ ቢሆን አሁን ግን 250 ሺህ ብር እንዲሆን ተደርጓል። እንዲሁም በንብረት ላይ ለሚደርስ ጉዳት ወይም ኪሳራ ከብር 100 ሺ ያልበለጠ የገንዘብ ካሳ የሚከፈል የነበረ ሲሆን አሁን ወደ 200 ሺህ ብር ከፍ ማለቱ ካፒታል ሰምቷል።

በስራ ላይ የነበረዉና የሚኒስትሮች ምክርቤት በአዋጅ ቁጥር 799/2002 የተሸከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድን ዋስትና የአርቦን መጠንና የመድን ፈንድ ታሪፍን በተመለከተ ያስተላለፈው ዉሳኔ በአዲሱ ደንብ መሻሩ ታዉቋል።

(Capital)

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66c84f981ab8285b9d2f1656

procurement of furniture

- Published by Ministry of Trade and Regional Integration

💵 ፕሮፎርማ Fri Aug 23rd, 2024 - Fri Aug 23rd, 2024

ምንጭ
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66c993061ab8285b9d2f1ae5

Procurement of Glucometers with strips
- Published by St. Peter Specialized Hospital

💵 ፕሮፎርማ Sat Aug 24th, 2024 - Sat Aug 24th, 2024

ምንጭ
የሞት አደጋ
5 ሺህ ብር የነበረዉ አሁን ወደ 250 ሺህ ብር ከፍ ብሏል

#Ethiopia | በሰው ላይ ለሚደርስ የሞትና የአካል ጉዳት የሚከፈለው ካሳ መጠን ወደ 250 ሺህ ብር ከፍ ብሏል።

አዲሱ የሦስተኛ ወገን የተሸከርካሪ መድን ፖሊሲ ከዛሬ ጀምሮ ተፈፃሚ መሆን መጀመሩን ተገለፀ።

5 እጥፍ ጭማሪ የተደረገበት የአርቦን ክፍያ በአንድ ሰው ላይ ለሚደርስ የሞት አደጋ 5 ሺህ ብር የነበረዉ አሁን ወደ 250 ሺህ ብር ከፍ እንዲል ሆኗል።

በአዲሱ ደንብ መሰረት በአንድ ሰው ላይ ለሚደርስ ለአካል ጉዳት እስከ ብር 40 ሺህ ያልበለጠ የገንዘብ ካሳ ይከፈል የነበረ ቢሆን አሁን ግን 250 ሺህ ብር እንዲሆን ተደርጓል።

እንዲሁም በንብረት ላይ ለሚደርስ ጉዳት ወይም ኪሳራ ከብር 100 ሺ ያልበለጠ የገንዘብ ካሳ የሚከፈል የነበረ ሲሆን አሁን ወደ 200 ሺህ ብር ከፍ ማለቱን ዘገባው ጠቅሷል።

በስራ ላይ የነበረዉና የሚኒስትሮች ምክርቤት በአዋጅ ቁጥር 799/2002 የተሸከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድን ዋስትና የአርቦን መጠንና የመድን ፈንድ ታሪፍን በተመለከተ ያስተላለፈው ዉሳኔ በአዲሱ ደንብ መሻሩ ታዉቋል።

ስናሽከረክር ጠንቀቅ ማለቱ ይበጃል!

via getu temsgen

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ የተከሰከሰው የቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ከአደጋው በፊት የኤሌክትሪክ ችግሮች እንዳሉበት የሚያሳየውን መረጃ መደበቁን የቀድሞ የቦይንግ ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ።

ፋውንዴሽን ፎር አቪየሽን ሴፍቲ የተባለ ቡድን የሚመሩት የቦይንግ የቀድሞ ሥራ አስኪያጅ ለ157 ሰዎች እልቂት የሆነው እና ከስድስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የተከሰከሰው 737 ማክስ 9 አውሮፕላን የኤሌክትሪክ ችግሮች እንዳሉበት በኩባንያው ይታወቅ ነበር ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በዝቅተኛ ከፍታ ላይ ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን እንደሚችል እና በርካታ እክሎች እንደነበሩበት ይፋ አድርገዋል።

ፋውንዴሽኑ በአሁኑ ወቅት እየበረሩ ያሉ ከ1000 በላይ የቦይንግ አውሮፕላኖች በሚመረቱበት ወቅት በነበሩ ችግሮች ምክንያት የኤሌክትሪክ ብልሽት ስጋት እንደተጋረጠባቸው ገልጿል።

ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ጉዞውን በጀመረ በስድስት ደቂቃዎች ውስጥ የተከሰከሰው አውሮፕላን የኤሌክትሪክ ብልሽቶች ነበሩበት ብለዋል።

አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት ወቅት አዲስ ሞዴል 737 ማክስ 9 ነበር።

ከዚያ ቀደም ብሎ ተመሳሳይ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን በኢንዶኔዥያው አየር መንገድ አደጋ ተከስክሶ የ189 ሰዎች ሕይወት ተቀጥፏል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66cc441a1ab8285b9d2f209d

PROCURMENT FOR ICT MATERIAL

- Published by Ministry of Agriculture

💵 500,000 ETB Thu Oct 10th, 2024 - Mon Aug 26th, 2024

ምንጭ
የዘመን መለወጫን የበዓል ገቢያ ለማረጋጋት 50 ሚሊየን ሊትር የምግብ ዘይቱ ወደ ኢትዮጵያ መግባት ጀመረ

#Ethiopia | የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል እና ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ታስቦ በመንግስት ግዢ የተፈጸመው 50 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከጅቡቲ ወደ የተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የማጓጓዝ ስራ ዛሬ ጀምሯል።

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዛሬ እንዳስታወቀው፤ ከዚህ ቀደም መንግስት የኑሮ ወድነትን ለማሻሻል እና ገበያን ለማረጋጋት ተከታታይነት ያለው እርምጃ እንደሚወስድ ቃል በገባው መሠረት 50 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከጅቡቲ ወደ የተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የማጓጓዝ ስራ ዛሬ ጀምሯል።

የምግብ ዘይቱ በኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር እና በመኪና ተጭኖ ወደ አገራችን መግባት የጀመረ ሲሆን፣ ይህ የፍጆታ ዕቃ በዋናኝነት የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል እና ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ታስቦ በመንግስት ግዢ የተደረገ ነው ተብሏል።

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፓርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ከኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ጋር በመቀናጀት በሚቀጥሉት ጊዜያት በተቀላጠፈ መልኩ 50 ሚሊየን ሊትር የምግብ ዘይት ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ የሚሰራጭ እንደሚሆን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በድረ ገጹ ላይ ጠቁሟል።

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
👍1
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66cd87871ab8285b9d2f2742

Purchase of Forested Sticker (2)
- Published by Documents Authentication and Registration service

💵 ፕሮፎርማ Tue Aug 27th, 2024 - Tue Aug 27th, 2024

ምንጭ
በማገዶ ጭስና ተቀጣጣይ ነገሮች የሚመጣ
- የሳንባ ካንሰር መስፋፋቱ ተጠቆመ

በማገዶ እንጨትና ተቀጣጣይ ነገሮች አማካይነት የሚመጣ የሳንባ ካንሰር መጨመሩን የኢትዮጵያ ቶራሲክ ሶሳይቲ ባወጣው ጥናት አመልክቷል፡፡ “የሳንባ ካንሰር የተጋላጭነት መጠን በሴቶችና በወንዶች መካከል ተመጣጣኝ ነው" ብሏል - ጥናቱ፡፡

ብዙዎቹ የሳንባ ካንሰር ታማሚዎች ወደ ሕክምና ተቋማት የሚመጡት ዘግይተው መሆኑ ያመለከተው ጥናቱ፤ የሳንባ ካንሰር አራት ደረጃዎች እንዳሉትም ይጠቁማል፡፡ በመጀመሪያው የሳንባ ካንሰር ደረጃ ላይ የሚገኝ ታማሚ ወደ ሕክምና ተቋም ከመጣ፣ የመዳን ዕድሉ ሰፊ መሆኑን የሚጠቅሰው ጥናቱ፤ በሦስተኛና አራተኛ ደረጃ ላይ ሆኖ ከመጣ ግን የመፈወስ ዕድሉ ጠባብ ነው ይላል።

በአገራችን ከ90 በመቶ በላይ የሳንባ ካንሰር ታማሚዎች ወደ ሕክምና ቦታ የሚመጡት የመጨረሻዎቹ ሁለት ደረጃዎች ላይ ከደረሱ በኋላ መሆኑን የገለጸ ጥናቱ፤ በኢትዮጵያ የሳንባ ካንሰር ሕሙማን አማካይ ዕድሜ፣ ከሌሎች አገራት አማካይ የሳንባ ካንሰር ታማሚዎች አንጻር ወጣት መሆናቸው ተጠቁሟል። በዚህም 55 ወይም 56 ዓመት ዕድሜያቸው ላይ ታማሚ እንደሚሆኑ ነው ጥናቱ ያረጋገጠው፡፡

ጥናቱ በማገዶ እንጨቶች፣ በከሰል፣ በኩበት ጭስና ሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮች የሚመጣው የሳንባ

“የሳንባ ካንሰር በሲጋራ ጭስ አማካኝነት የሚመጣ ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ሲጋራ የሚያጨሱ ሴቶች ቁጥር ከ1 በመቶ በታች ሆኖ ለሳንባ ካንሰር ያላቸው ተጋላጭነት ግን ከወንዶች እኩል ነው" ሲል የኢትዮጵያ ቶራሲክ ማሕበር በጥናቱ አመልክቷል።

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66cee7641ab8285b9d2f2d45

Purchase Requisition Transit service
- Published by Armauer Hansen Research Institute

💵 ፕሮፎርማ Thu Aug 29th, 2024 - Wed Aug 28th, 2024

ምንጭ
👍1
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66d062cf1ab8285b9d2f34c9

Lot 1 Laboratory Apparatus & Equipment

- Published by Ethiopian Environmental Protection Authority

💵 50,000 ETB Wed Sep 4th, 2024 - Tue Aug 20th, 2024

ምንጭ
በውሃ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል እና በትራንስፖርት አቅርቦት ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተደረገ

#Ethiopia | በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ መሰረት በውሃ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል እና በትራንስፖርት አቅርቦት ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ መደረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የተጨማሪ እሴት ታክሱ የሚመለከተው ከአንድ ቤተሰብ ወርሃዊ አማካይ ፍጆታ በላይ ኤሌክትሪክ እና ውሃን በብዛት የሚጠቀመው የመክፈል አቅም ያለው የህብረተሰብ ክፍል ነው ተብሏል፡፡

መንግስት አነስተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል በመኖሪያ ቤቱ የሚጠቀመውን አማካይ ወርሃዊ የውሃና ኤሌክትሪክ ፍጆታ ከታክሱ ነፃ የሚያደርግ ሲሆን ከታክሱ ነፃ ከተደረገው በላይ የውሃና ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተፈፃሚ እንዲሆን ያደርጋል ተብሏል፡፡

በተመሳሳይ የትራንስፖርት አገልግሎትም ተጨማሪ እሴት

ሚኒስቴሩም የትራንስፖርት አገልግሎትም ላለፉት 22 ዓመታት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ እንዲሆን የተደረገው አነስተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል ለትራንስፖርት የሚያወጣው ወጪ እንዳይንር እንዲሁም በጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚከፈለው ታክስ የዕቃዎችን ዋጋ መናር እንዳያስከትል በማሰብ ነበር ብሏል፡፡

በመሆኑም ከህዝብ እና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ውጪ ለሌሎች የትራንስፖርት አገልግሎቶች የዚህ አይነቱን ድጋፍ ማድረግ ተገቢ ባለመሆኑ፣ መንግስት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የመሆን መብት ባለሶስት እግር ተሽከርካሪን ሳይጨምር ከስምንት መቀመጫ በላይ ያላቸው ተሸከርካሪዎች መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

Via getu temsgen

ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
🤔1
ፈገግታ ሲያስቀጣ 🙄

ሰሜን ኮርያ አትሌቶቿን ልትቀጣ መሆኑ ተነገረ

በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በድብልቅ ጠረጴዛ ቴኒስ ውድድር ለሀገራቸው ሰሜን ኮርያ የብር ሜዳልያ ያስገኙት አትሌቶች በሀገሪቱ መንግሥት ሊቀጡ መሆኑ ተገልጿል።

የሰሜን ኮርያ መንግሥት አትሌቶቹን ለመቅጣት እየመረመረ የሚገኘው ከደቡብ ኮርያ አትሌቶች ጋር በፈገግታ ተሞልተው ፎቶ መነሳታቸውን ተከትሎ መሆኑ ተነግሯል።

በኪም ጆንግ ኡን የሚመራው የሰሜን ኮሪያ መንግሥት የሀገሪቱ አትሌቶች ወደ ፓሪስ ሲያመሩ የደቡብ ኮሪያን ጨምሮ ከየትኛውም ሀገር አትሌቶች ጋር እንዳይነጋገሩ አስጠቅቆ እንደነበር ተገልጿል።

በሀገሪቱ ከዚህ በፊት በውድድሩ ደካማ አቋም ያሳዩ አትሌቶች ትችት እና ቅጣት እንደተጣለባቸው ሲገለፅ ግዴታቸውን ባለተወጡት ላይ ደግሞ በነፃ የጉልበት ስራ እንዲሰሩ መደረጉ ተጠቁሟል።

tikvaheth sport
ቴዘርን GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth
#ጨረታ@SeledaGramBot
tender 66d17c0b1ab8285b9d2f3a5e

ኮንስራክሽን 23
paint
- Published by National Intelligence and Security Service

💵 xx,xxx.xx ETB Fri Aug 30th, 2024 - Fri Aug 30th, 2024

ምንጭ