የመምህር ግርማ ወንድሙ የወንጌል ተማሪዎች
425 subscribers
22 photos
2 videos
1 file
2 links
የመምህርን ትምህርቶች እንማማራለን ከጠላት እንዴት እንደምናመልጥ እንወያይለን የፀሎት ስርአት ቦታ ሁሉ ይካተታሉ...ተቀላቀሉ
Download Telegram
የተወደዳችሁ የተዋህዶ ልጆ በጠየቃችሁን መሰረት ሰለ "መቁጠሪያ ሞስጢረ" እነሆ ብለናል #ሼር በማረግ እንደተለመደው ለሌሎች እናካፍል ።

መቁጠሪያ

በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያናችን ከሚገኙና ሰይጣን ዲያብሎስን ከምንዋጋበት መሣሪያዎቻችን መካከል አንዱ መቁጠሪያ ነው : :

" በአንተ ጠላቶቻችን እንወጋቸዋለን በስምህም በላያችን የቆሙትን
እናዋርዳቸዋለን " መዝ.43 (44) : 5

መቁጠሪያ ለሰው ልጅ በጣም ከሚያስፈልጉት በፀሎት ጊዚያት ውስጥ አንዱ ነው ምክንያቱም ከዛሬ መቶ ሃያ አመት በፊት የነበሩ አባቶች በመቁጥሪያ ፀሎት በመፀለይ ሀይል አጋንንትን በመቀጥቀጥ ድል ያድርጉ ሥጋቸውንም ለነብሳቸው ያስገዙት ነበር ፡፡ አሁን ግን ተረስቶ መቁጠሪያ ለቆራቢ ነው መቁጠሪያ ለሞለክሴ ለበቁ ሰዎች እየተባለ ይገኞል ይህ ስተት ነው ፡፡

በመፅሐፍ ቅዱስ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9 : 27

" ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን
እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ። " እየጎሰምሁ ሲል እየቀጠቀጥኩ ማለቱ ግልፅ
ነው ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ሰይጣን ነበረበትና እንዲህም በማለት ተናግሮ ነበር

" ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው።"
ስለዚህ ነገር ከእኔ እንዲለይ ሦስት ጊዜ ጌታን ለመንሁ።"
(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12 7:8)

(1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 2:18) " ጳውሎስም አንድና ሁለት ጊዜ፥ ሰይጣን ግን አዘገየን።"

ቅዱስ ጳውሎስ በውስጡ ያደረውን ሰይጣን በመቀጥቀጥም
ጭምር እንደሚዋጋው ተናግሯል ፡፡

በቤተክርስቲያናችን ካህናትና በንሰሐ አባቶቻቸንና በተባረከ መቁጠሪያ
በእግዚአብሔር አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ በእመቤታችን ድንግል
ማርያም በቅዱሳን መላእክት ስም እየጠራን በውስጤ ያደርክ ክፉ መንፈስ
ተቃጠል እያልን ሁሉቱ ትከሻዎቻችን : መሀል ጀርባችንን እንዲሁም ሕመም የሚሰማን ቦታ ስንቀጠቅጥ
- የማቃጠል ወይም የመለብለብ የመውረር ወይም የመንዘር
- የመብላት ወይም የማሳከክ በሰውነት ክፍላችን ውስጥ የመዘዋወር
ስሜት ና እንደ ድንጋይ በድን መሆን እንዲሁም
- ጭንቀላታችንን ሁለት ከፍሎ የራስ ምታት ዓይነት ሰሜት ከተሰማን
ሰይጣን በውስጣችን አድፍጦል ማለት ነው : : ስለሆነም የእግዚአብሔርን
መንገድ ይዘን
✞ እየፆምን
✞ እየጸለይን እየተንበረከክን
✞ እየሰገድን
✞ ሥጋና ደሙን እየወስደን ከላይ እንደተገለጸው በመቁጠሪያችን
እየቀጠቀጥን ክፉ መንፈሶችን ማንበርከክ በመጣል የእግዚአብሔር ልጆች መሆን እንችላለን ከእግዚአብሔር የተሰጠን የተሥፋው ሀይል እንዲህ ይላል ::

"እንሆ እባቡንና ጊንጡን ተረግጡ ዘንድ በጠላትም ሀይል ሁሉ ላይ
ሥልጣን ሰጥቻችዋለሁ የሚጐዳችሁም ምንም የለም :: " ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ሰለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።" ሉቃስ 10 : 19 -20
ሁሌ ቤተ ክርስቲያን መመላለስ ሳይሆን ስንሄድ እና ቤታችን ምን ማድረግ እንዳለብን ማወቅ
ሁሌ በርትተን በደስታ እንስገግ የአምልኮ ስግደት ለቅድስትሥላሴ ብቻ ሁሌ የሚሰገድ::
1.አምልኮ ስግደት
ለአብ እሰግዳለሁ:
ለወልድ እሰግዳለሁ:
ለመንፈ ስቅዱስ እሰግዳለሁ:
ምስጋና ይሁን ለአብ:
ምስጋና ይሁን ለወልድ:
ምስጋና ይሁን ለመንፈስ ቅዱስ:
በረከቱን ለሰጠን:
ሀይሉን ላበዛልን:
በዚህ ሰአት ላቆመን:
በቸርነቱ መንገድ ለመራን:
በዚህ ሰእት በጸጋ ለጠበቀን:
በብርሀኑ ሐይል ለመራኸን:
ላንተ ክብርምስጋና ይግባው:
ሐሌሉያ ለአብ:
ሐሌሉያ ለወልድ:
ሐሌሉያ ለመንፈስ ቅዱስ:
ቅዱስ እግዚአብሔር:
ቅዱስ ሐያል:
ቅዱስ ሕያው:
ቅዱስ ኤልሻዳይ:
ቅዱስ አዶናይ:
ቅዱስ ያህዌ:
ቅዱስ ፀባኦት:
ቅዱስ ኢየሱስ:
ቅዱስ ክርስቶስ:
ቅዱስ አማኑኤል:
የድንግል ማርያም ልጅ:
ክብር ምስጋና ይግባው::እያልን እንሰግዳለን::
2. የፀጋ ስግደት
ቅዱስ ገብርኤል ፀጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ እንዳላት እኛም እንዲሁ እያልን ለእመቤታችን የፀጋ ስግደት እንሰግዳለን::
ለድንግል ማርያም ክብር ምስጋና ግገባሻል እያልን እንሰግዳለን::
3. የንስሐ ስግደት
ኪሪያላይሶን ኢየሱስ:
ኪሪያላይሶን ክርስቶስ:
ኪሪያላይሶን አማኑኤል:
እቤቱ ክርስቶስ ሆይ ማረን:
አቤቱ አምላክ ሆይ ማረን:
አቤቱ መድሀኒአለም ሆይ ማረን:
አቤቱ የድንግል ማርያምልጅ ሆይ ማረን:: እያልንእንሰግዳለን::
4. የክብር ስግደት
ለቅዱሳን መላእክት ለቅዱሳን ጻድቃን ለሰማእታተ የሚሰገድ
ኦ: ቅዱስሚካኤል: ለቅዱስሚካኤል እሰግዳለው በቅዱስሚካኤል እሰግዳለው
ኦ: ቅዱስገብርኤል.... እያልን የአክብሮት ስግደት እንሰግዳለን::
---------------------------------------
ክብረ በአል ከሆነ
ስብአት ለአብ:
ስብአት ለወልድ:
ስብአት ለመንፈስ ቅዱስ:
ቅዱስ እግዚአብሔር:
ቅዱስ ሀያል:
ቅዱስ ህያው:
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ::እያልን እንሰግዳለን::
------------------------------------------------------------------
እርኩስ መንፈስ እየተቃወመ ካስቸገረ በመቁጠርያ እየቀጠቀጡ
እግዚኦ መአር ነክርስቶስ
በእንተ ማርያም መአርነ ክርስቶስ
ኪሪያላይሶን እየሱስ
ኪሪያላይሶን ክርስቶስ
በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
የዲያቢሎስን ሰራዊት በሰበረው በሀያሉ በቅዱስሚካኤል ስም
ለቅድስት ድንግል ማርያም ብስራትን ባበሰረው በቅዱስ ገብርኤል ስም
ውስጤ የተደበቅክ ጠላቴ ነርቭ የሆንከው በሽታ የሆንከው
ቅዠት የሆንከው ተስፋመቁረጥ የሆንከው መንፈስ ገስፅሃለው
በገንዘቤ ላይ በባህሪዬ ላይ አዛዥ አትሆንም
ይህ መንገድህ ተሽሯል ተሰርዟል
በመቁጠርያ እየቀጠቀጡ በድንግልማርያም ስም ወደግባርውጣና ታሰር ይባላል::
ምንጭ "በማለዳ መያ`ዝ መጽሐፍ''በመልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ
ለአባታችችን ለመልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ እድሜና ጤና ይለግስልን አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ይቆየን