👉🏻በመጀመሪያ የትዳር አጋርን ለመምረጥ ብዙ ሊደከም ይገባል
፡ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል አንድን ዕቃ ስንገዛ ስለሚሸጡልን ሰዎች መረጃ እንደምንሰበስብ የሚያዋጣን መኾኑን እንደምናመዛዝን ከሉ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት የትዳር አጋሩን ሲመርጥ እጅግ ከፍ ያለ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም የገዛነው ዕቃ የተበላሸ እንደ ሆነ ልንመልስ እንችላለን አንዴ ወደ ትዳር ከገባን በኋላ ግን የትዳር አጋራችንን መለወጥ አንችልም፡፡ ታዲያ መምረጥ የምንችለው
ሀ/👉🏻 ፍቃደ እግዚአብሔርን በመጠየቅ:-
ከምንም በፊት እግዚአብሔርን ልንጠይቅ ይገባል፡፡ ሊቁ አንዲህ ይላል ማግባት ስትፈልግ አስቀድመህ ጸልይ አሳብህን ለእግዚአብሔር ንገረው፡፡ እግዚአብሔር መርጦ እንዲሰጥህ ለምነው፡፡ ጭንቀትህን ሁሉ በእርሱ ልይ ጣለው፡፡ አንተ እንደዚህ እርሱ እንዲመርጥልህ የምታደርግ ከኾነም አክብረኸዋልና እርሱም ለአንተ በጎ የትዳር አጋርን በመስጠት ያከብርሃል፡፡ ታዲያ አስቀድመን እንዲህ ብናደርግ ወደ ትዳር ስንገባ ፍቺ አይገጥመንም ሚስት ወይ ባል ሌላ አይመኝም በሌላ በማንም እንዳንቀና ያደርገናል ጠብ ክርክር አይኖርም ከጠብ ይልቅ ታላቅ የኾነ ሰላምና ፍቅር በመካከል ይኖራል፡፡ እነዚህን ደግሞ በጎ ምግባራትን ትሩፋትን ለመፈጸም አንቸገርም፡፡
አንድ ሰው አይቶ ስለ ወደደ፤ ሃይማኖት ስላለው፤ በጎ ምግባርን ገንዘብ ስላደረገ ብቻ ይህን ማግባት አለብኝ ብሎ ሊወስን አይገባውም፡፡ ወደውሳኔ ከመምጣት በፊት ያሰብኩት አሰብ የማነው የእግዚአብሔር አሳብ ሊሆን ይችላል ወይ የራሴ ወይ ደግሞ የዲያብሎስ አሳብም ሊኾን ይችላል ብለን ቆም ብለን ማሰብ ይገባል፡፡ አስቀድመን የንሰሐ አባታችንን ማማከር በጸሎት ሊረዱን ከሚችሉ መንፈሳውያን አባቶች ወይም እናቶች ጋር ተመካክሮ የዓቅማቸንን ያህል ሱባኤ መያዝ ተገቢ ነው፡፡ በተቻለን አቅም ደግሞ ስናማክር የትዳር ተቀዳሚ ዓላማ ያልገባቸው ሰዎችን ለእርዳታ እና ለምክር ባንጠይቅ የተሸለ ነው፡፡ በሰዎች ምስቅልቅል ሕይወት የሚነግዱም ስላሉ፡፡ ከዚህ ሁሉ ይልቅ የእግዚአብሔርን እርዳታ መጠየቅ በናንተ መሃል ሽማግሌ ለመሆን አያፍርም፡፡ መንፈሳዊ ሕይወታችሁ ጽኑዕ የትዳራችሁ ዋና ግብም ጽድቅ እንዲሆን እግዚአብሔርን ጠይቁ፡፡ ይሄን አድርገን እግዚአብሔር መፍቀዱን በምን እናውቃለን ብንል እግዚአብሔር በራዕይ ወይ በድምጽ እንዲነግረን አንጠብቅ ፍቃዱ ከሆነ ያች በአቅማችን የያዝናት ሱባኤ የመረጥነው ሰው የእግዚአብሔር ፍቃድ ከኾነ ያለን መውደድ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ አሳቡ የራሳችን ምኞት ወይ የዲያብሎስ ምክር አሳብ ከነበረ ግን ጸሎት የማያፈርሰው የጠላት አጥር የለምና ስለዛ ሰው የነበረን አሳብ ይጠፋል፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ካልሆነ ያ የጀመርነው ጓደኝነት በሆነ ምክንያት እግዚአብሔር ያስቀረዋል። ለዚህ ምሳሌ ሊሆን የሚችለው የአበ ብዙኀን የአብርሃም አገልጋይ ለይስሐቅ ሚስት ለማምጣት በተላከ ጊዜ ያደረገው ጸሎትና ርብቃን የለየበት መንገድ፡፡ ዘፍ 24፡12
ለ/ 👉🏻የትዳርን ዓላማን በደንብ መረዳት፡- የትዳር የመጀመሪያ ዓላም ጽድቅን መፈጸም ነው፡፡ ሌሎቹ ዓላማዎች በዚህ ስር ይጠቃለላሉ
ልጅን ለመውለድ ብቻ አስቦ ማግባት አይገባም የትዳር አንዱ ዓላማ ልጅ መውለድ ቢኾንም ቅሉ ላይወልድም ይችላልና ፡፡
ወጪውን ለመቀነስ ብሎም አያግባ ዓላማው ከዚህም ያልፋል
አንድ ለአንድ መወሰን ጥሩ በሚል ብቻም ማግባት የለበትም መልካም ቢሆንም በውስጡ ከዝሙት ተጠብቆ ጽድቅን ለመፈጸም ካልሆነ ምክንያቱም ከአሕዛብም የጽድቅ አሳብ ሳይኖራቸው የሚወሰኑ አሉና፡፡
መልኳም ወደድኹ ብሎም ማግባት ውበት ባይጠላም እርሱ ግን የትዳር ዓላማ አይደለም ይህንን አድንቆ ከገባ ከተወሰንኑ ቀናት በኋላ አይማርከውም ይለምደዋልና፡፡ ሌላም ቆንጆ ቢያይ ልሂድ ሊል ነው።
እነዚህ ዓላማ ሳያደርግ ግን ጽድቅን አስቦ የገባ ባይወልድ እንኳ አይፋታም፤ ሩካቤ ባያደርግ፤ ቢሰንፍ እንኳን እራሳቸውን ከዝሙት ተጠብቀውና ራሳቸውን ገዝተው የትዳር አጋራቸውንም እግዚአብሔርን በማመስገን ይኖራሉ እንጂ አይፈቱም፡፡ ጋብቻ ግቡ ይኼ ነውና፡፡ መገንዘብ ያለብን ጋብቻ ወደ ቅድስና የሚያደርስ እንጂ በራሱ ጽድቅ አለመኾኑን ነው፡፡ ጋብቻ በእምነት ያገኘነውን ልጅነት አጽንተን እንድንይዝ እግዚአብሔር ወደ መምሰል እንድናደርግ የሚያደርግ ከድንግልና ሕይወት ቀጥሎ ያለ አንድ የሕይወት መንገድ እንጂ በራሱ ቅድስናን የሚሰጥ አለመሆኑን ነው፡፡ ሰለዚህ የትዳር አጋራችን ስንመርጥ ወደምንፈልገው ግብ የሚያደርሰንና እርሱም አብሮን የሚደርስ ሊኾን ይገባዋል፡፡ ፍቃደ እግዚአብሔር አስቀድመን ስንጠይቅና እግዚአብሔርም ጸሎታችንን ሲሰማ የሚሰጠን የትዳር አጋር ለዚህ ተቀዳሚ ዓላማ የሚስማማንን ነው፡፡ ይሄ ባይሆን ግን የትዳር ዓላማ ሳይገባን የምንገባበት ከኾነ ግን የትዳር አጋራችን የቱንም ያህል መንፈሳዊ ቢኾንም እንኳን አስቸጋሪ ነው፡፡
አንድ ምሳሌ እንይ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ብቻ አይተው የሚያገቡ ሰዎች ስግብግብ ነጋዴዎችን ይመስላሉ ይላል ሊቁ ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ። ስግብግብ ነጋዴዎች መርከቦቻቸውን ከዓቅም በላይ ዕቃ ስለሚጭኑባቸው ማዕበሉን መቋቋም አይችሉም፡፡ ይሰጥማሉ የማይችሉትን ሸክም ለመሸከም የሚገቡ ሰዎችም እንደዚህ ናቸው፡፡ የማይችሉትን የትዳር አጋራቸውን ጠባይ ለመሸከም ይገደዳሉ፡፡ ይህን ለመሸከም ሲሉ ከዓቅማቸው በላይ ወደ ኾነ ተጋድሎ ይገባሉ፡፡ ተጋድሎው በራሱ መልካም ቢኾንም ከዓቅማቸው በላይ ስለሚኾን ይመረራሉ፡፡ አንዱ ብዙ እንጸልይ፤ ብዙ እንስገድ፤ እንጹም ሲል ሌላኛው ግን ከዓቅሙ በላይ ስለሚኾንበት በዚህ ይሰናከልበታል፡፡ ሲከፋም ወደ ውጭ ማየት ሊመጣ ይችላል፡፡ በዓቅማቸው የሚጋቡ ከሆነ ግን ሚስቶች የቱንም ያህል ክፉ ቢኾኑም እንኳን ባሎች፡- ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚቶቻችሁን ውደዱ የሚለውን ቃል እግዚአብሔር ለመፈጸም አይቸገሩም፡፡ ሚስቶቹም ባሎቻቸውን በጌታ ለመታዘዝ አይቸገሩም፡፡ እህቴ እኔም የምመክርሽ ፍቃደ እግዚአብሔርን ጠይቂ!!!

🌼አቃፊው -- አባት🌼
ሲሰድቡት ውለው_________ሲመርቅ ያድራል
ሊገድሉት ሲሹት............ከሞት ያድናል
እያስለቀሱት ..............እንባን ያብሳል
ሲገፈትሩት...............በፍቅር ያቅፋል
ለሚያሳድዱት.........እጅ ይዘረጋል
እውን እንዳንተ አባት ይገኛል?
ለጠወልግነው የሆንከን ታዛ
በፀጋህ ሀይል ገፃችን ወዛ
ምን ቢያስድዱህ ብትሆን ባይተዋር
ወደቁ ከእግርህ ዳኑ ከሞት ጣር
እንዲያ ሲሰድቡህ ሲያሳዱህ
ችለህ ማለፍህ ሳያንስብህ
በእጅህ ሊድኑ ከእግርህ ቢወድቁ
አቅፈህ ሳምካቸው ዳኑ ሊደምቁ
አባ ኑርልን ዘላለም አለም
ጠላትን አሳድ ከአለም አለም
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ውድ የመምህር ግርማ ፍሬዎች እንኳን ለ፪ሺ፲፪ አዲስ አመት አደረሳችሁ
🌺🌸🌼🌼አዲሱ አመት🌼🌼🌺🌸
ንስሀየምንገባበት፣የምንቆርብበት፣የተጣላን የምንታረቅበት፣በሀገራችንም በሀይማኖታችንም ያንዣበብው መከራ የሚያልፍበት፣ ከክፉ መሰሪ ጥንተ ጠላታችን የምንላቀቅበት፣ሰው የምንሆንበት፣ ከምንም በላይ ከእማዋይሽ፣ ከወለላይቱ፣ ከፍቅር እናት፣ስለኛ ከማትደከመዋ፣ከአንድዬ እናት፣ሁሉ ለእርሷ ሁሉ ስለእርሷ ለተፈጠረላት፣የሰይጣንን ምርኮ ካራገፈችው፣ብንጠላት ከማትጠላን፣ብንተዋት ከማትተወን፣ ቅዱሳን ምስጋናዋን አላልቅ ቢላቸው በእንባ ከጨረሱላት፣መላእክት አምላካቸውን ካዩባት፣ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የምንጣበቅበት፣በረከቷን፣አማላጅነቷን፣ በገፍ የምናፍስበት አመት ያድርግልን
🌼አሜን🌼

ከነፍስ ስደት ታድነን ዘንድ እመቤታችንን እንማፀናት፡ ከክፉው ከአውሬው እጅ እንድታላቅቀን ሰግደን እንለምናት
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
መልአከ መንክራት መምህር ግርማ በአሜሪካ በካንሳስ የተናገሩት ድንቅ መልእክት
የአባታችንን ደስታ አይታችሁ ይህንን የ ቪዲዮ መልእክት ሼር በማድረግ ጠላታችንን ዲያቢሎስ አሳፍሩት እስኪ share Share share
ስጋ ወደሙ ውሰዱ የሚል ጠንቋይ እንዲህ ከሆነ አረ ሁላችሁም ጠንቋይ ሁኑ! እግዚአብሔር ይርዳችሁ የእግዚአብሔርን ስራ ከሰራን እንጠላለል
የእግዚአብሔርን ስራ ከሰራን እንሰደዳለን
ዝም ብላችሁ ከተቀመጣችሁ ቴሌቭዥን ነን ማለት ነው አይሆንም የእግዚአብሔርን ስራ መስራት አለብን የእግዚአብሔርን የስራ ውጤቱ ደግሞ በብዙ መከራ ውስጥ አሳልፎ ዛሬ እኔና እናንተን በአሜሪካ በቅድስት ቤተክርስቲያን አገናኝቶናል ።
በመቀጠልም በኮሎራዶ ካንሳስ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አባታችን አቡነ ናትናኤል እንዲቀሩብን አንፈልግም ከእርሶ ተማሪ ጋር በመሆን በአሜሪካ ቤት ሰርቼ እጠብቆታለሁ በማለት ለ መልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ ቃል ገብተዋል ።
የበረከት ስራም ለቤተክርስቲያኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ዶላር ገቢ ሆንዋል ።
ይህን ያደረገ እግዚአብሔር ይመስገን!
<<እንዳትሰናከሉ ይህን ተናግሬአችኋለሁ።
2፤ ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል። >> የዮሐንስ ወንጌል 16 ፤ 1

Forwarded from በማለዳ ንቁ ! (Natnael S. 🕆)
መሠረታዊ የአምልኮት ትምህርት.docx
399.8 KB
✞ መሠረታዊ የአምልኮት ትምህርት ✞
እድለኛ የሆነ፤ በጥሞና አንብቦ ወደ ምግባር ሲያወርደው በሕይወቱ የሚታይ መንፈሳዊውም ሥጋዊም ለውጥ ያመጣል፡፡
ለራሳችሁ ስትሉ ንቁ!
ከንቱነት ይብቃችሁ!

ሕዝቅኤል 7
¯¯¯¯¯"¯¯¯¯¯
¹⁹ ብራቸውን በጎዳናዎቹ ላይ ይጥላሉ ወርቃቸውም እንደ ጕድፍ ይሆናል፤ በእግዚአብሔር መዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ያድናቸው ዘንድ አይችልም። እርሱ የኃጢአታቸው ዕንቅፋት ሆኖአልና ሰውነታቸውን አያጠግቡም ሆዳቸውንም አይሞሉም።
…
²⁷ ንጉሡም ያለቅሳል፥ አለቃም ውርደትን ይለብሳል፥ የምድርም ሕዝብ እጅ ትንቀጠቀጣለች፤ እንደ መንገዳቸውም መጠን አደርግባቸዋለሁ፥ በፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።

Forwarded from “ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “
የምሥራች
በ ቅርብ ቀን የሚለቀቅ የሚወደድ አዲስ ዝማሬ
በዲያቆን ኃይለመለኮት ግርማ ወንድሙ
( አትልፋ ጠላቴ )
ለቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞች በሙሉ ምንም እንኳን በዚህ ዓመት በአስቸጋሪ እና በጭንቅ ውስጥ ሆነን ቢሆንም ስብሐተ እግዚአብሔርን ማቋረጥ የባሰ ጭንቅ ስለሆነ ጠላት ቢሮጥ እግዚአብሔር ከያዝን ምንም እንደማያመጣ የሚያስረዳ ወቅታዊ የመዝሙር ቪዲዮ ሲሆን
በ እንሳሮ ፊልም ED ፕሮዳክሽን በልዩ ሁኔታ የተቀረፀ ድንቅ የሚወደድ ዝማሬ ነው የተለየ ያማረና ፍሬያማ ሥራ እንዲሆን ደክመንበታል፡፡ በጣም በጣም ደክመንበታል፡፡ ጥሩ ነገር ለማቅረብ ለማድረግ የሚቻለውን አቅም ተጠቅመናል፡፡ ጊዜ ገንዘብ እና ጉልበታችንን ከ ሶስት ሳምንት በላይ በደንብ የፈተነ ሥራ ቢሆንም እግዚአብሔር ይመስገን ጨርሰን ልናቀርብላችሁ ተዘጋጅተናል፡፡
እንግዲህ የነፍሳችሁን መንገድ ሰማያዊ ለማድረግ ነው ጥረቱ፡፡ በየ ሥራ ቦታችሁ በሁሉ ቦታ ጠላት አንደማይጠፋ የተረጋገጠ ቢሆንም እውነትን ከያዝን የእግዚአብሔር ኃይል እንደሚበልጥ የሚገልጥ መዝሙር ነው የልፋታችን ውጤቱ እናንተ ናችሁ፡፡ እንግዲህ እኛ እዚህ ድረስ ስንታትር እናንተ ፍሬያማ በመሆን በከንቱ እንዳልደከምን በምግባረ አምልኮ ሕይወት ለሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን በሙሉ ላልሰሙት በማሰማት በ Facebook በ YouTube በሁሉም ሚድያ በማስተላለፍ ይህን መዝሙር ለዓለም እናዳርስ ሁላችንም በየግል media ችን share በማድረግ ግዴታችንን እንወጣ!
በቅርብ ቀን ይጠብቁ!
ከዲያቆን ኃይለመለኮት ግርማ

ከመልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ አንደበት
🤭🤭🤭🤭🤭🤭🤭🤭🤭🤭🤭🤭🤭🤭
በእናት አባት ትከሻ ላይ ሆኖ የሚቆጣጠርህ ጠላት ካለ ሁሉም ነገር ስቃይ ይሆንብሀል😭
ተስፋ የሌለው ጠላት ተስፋ ካስቆረጠህ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮሀል ማለት ነው ወዳጄ ቤትህን በቅዱሳን ስዕላት እጠርና ተስፋዬ እግዚአብሔር ነው በል ውጤቱን ታየዋለህ😳
ቤትህ ካንተ ጋር ማምለክ ሲጀምር እጅግ ከፍተኛ ጦርነት ይገጥምሀል ያምሀል፣ይጨንቅሀል፣ይሰለችሀል፣ ግን ግድ የለም ክርስቶስ አንተን ሊያነግስ ያን ሁሉ መከራ አይቶ የለ እርሱ ህይወትህ ላይ እንዲነግስ ታገስ!!!!😍
መጀመሪያ ዲያብሎስ ሲይዝህ አይንህን ነው የሚይዘው በእርሱ አይን ነው የምታየው ከዛ ሁሉም የምታየው ነገር ስቃይ ነው አልገጠመህም? ታዲያ በርከክ ብላ የዳዊት ልጅ ሆይ ብለህ ተጣራ እንደ በርጠሚዎስ 😳
ገዳም ለገዳም አትሩጡ ጠላት አብሯችሁ እየዞረ ሳትድኑ ያስቀራችኋል እልፍኝህን ዝጋና በስውር ለሚያይ አባትህ ውስጥህን አሳየው😳
ውስጥህ አትችለውም ካለህ አንተ አይደለህም ሌላ አካል አለ በክርስቶስ ስም ተዋጋው🙋
ክፉ መናፍስት በማንኛውም ጊዜ ወደ እኛ ሊገቡ ይችላሉ አትደንግጡ!! ጠዋትና ማታ ተንበርክከህ በመቁጠሪያ ዠልጠው 🏃
ሲጨንቅህ፣ ሰውነትህ ሲከብድህ፣ እንባ እንባ ሲልህ ፣ መዝናኛ ቦታ ከምትሄድ ፀሎት ቤትህ ግባና ዠልጠው በመቁጠሪያ ስገድበት🏃🏃🏃 ለውጡን ታየዋለህ
ውስጥህ አንተ የማትፈልገው አንተ አለ? እርሱ እኮ ነው አይን ጥላ የተባለው አንተን ይመስላል ግን ክፉ ነገር ብቻ ነው የሚወደው መልካም ነገር ላይ ይጎትትሀል አሁን መውጣት ያቀትህ ችግር ካለ አይነጥላ አለብህ ማለት ነው መፍትሄው አንድ ብቻ ነው ወደ አምላክ እጅህን ዘርጋ
ይቀጥላል
"""" ለተጨነቀች ነፍስ ሁሉ ትዳረስ መፅናኛም ትሁናት"""

Watch "🔴 አዲስ ዝማሬ "እመቤቴ ማርያም" ዘማሪ ዲያቆን አማን ኡርጌሳ" on YouTube
https://youtu.be/n_7yB-vZuZ0
https://youtu.be/n_7yB-vZuZ0
YouTube
🔴 አዲስ ዝማሬ "እመቤቴ ማርያም" ዘማሪ ዲያቆን አማን ኡርጌሳ
በማኅቶት ቲዩብ የተለቀቁ ተወዳጅ መዝሙሮችን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፡፡
👇 👇 👇
https://bit.ly/3C2YHGp
"እመቤቴ ማርያም" ዘማሪ ዲያቆን አማን ኡርጌሳ
👇 👇 👇
https://bit.ly/3C2YHGp
"እመቤቴ ማርያም" ዘማሪ ዲያቆን አማን ኡርጌሳ
ለመርቆርዮስ በመርቆርዮስ ⛅️
ወዳጅ እንኳን ያልከው በስቃይህ ሲስቅ
የሚረዳህ ጠፍቶ በእንባህ ስትሳቀቅ
ቀንህ ሰላም ጠፍቶት ሌትህ አልነጋህ ብሎ
ተክዘህ ስትቆዝም ራስህ አዘንብሎ
ሞት ሞት ሲሸትህ ስትጠብህ ምድር
መፍትሄ ስታጣ ለመጣብህ ችግር
እንዲህ በረከክ ብለህ የምትነግረው አባት
እሱም ዝም ብሎ አንባህን ሲያነባት
አንገቱ ስር አቅፎህ ጌታ እኮ አለልህ
አትፍራ ልጄ ነህ አትጨነቅ ሲልህ
ያን ጥቁር ደመና በቃል ሲገፍልህ
አንተም ደስታህ አስክሮህ ሲጎርፍልህ እንባህ
እግሩን እጁን እየሳምክ አባ አባ እያልከው
እሱም በድርጊትህ ሳግ እየተናነቀው
እቅፍ ሲያደርግህ አንባሳዬ እያለ
ታዲያ ከዚህ በላይ ውድ ህይወት የታለ
የሺ ቀን በደልህ በአንድ ቀን ፈቶልህ
በድስታህ ደስ ብሎት ልጄ ልጄ የሚልህ
ታዲያ የኔ ወዳጅ 😢
ቀኑ ጭንቅ የሆነው
ህይወት የሚመረው
እንባህ የማይደርቀው
ይህን ቅዱስ አባት ያጣህበት ቀን ነው
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
አባ በረከትዎን ያሳድርብን ዘንድ ወደ አምላክዎት አሳስቡልን
ወዳጅ እንኳን ያልከው በስቃይህ ሲስቅ
የሚረዳህ ጠፍቶ በእንባህ ስትሳቀቅ
ቀንህ ሰላም ጠፍቶት ሌትህ አልነጋህ ብሎ
ተክዘህ ስትቆዝም ራስህ አዘንብሎ
ሞት ሞት ሲሸትህ ስትጠብህ ምድር
መፍትሄ ስታጣ ለመጣብህ ችግር
እንዲህ በረከክ ብለህ የምትነግረው አባት
እሱም ዝም ብሎ አንባህን ሲያነባት
አንገቱ ስር አቅፎህ ጌታ እኮ አለልህ
አትፍራ ልጄ ነህ አትጨነቅ ሲልህ
ያን ጥቁር ደመና በቃል ሲገፍልህ
አንተም ደስታህ አስክሮህ ሲጎርፍልህ እንባህ
እግሩን እጁን እየሳምክ አባ አባ እያልከው
እሱም በድርጊትህ ሳግ እየተናነቀው
እቅፍ ሲያደርግህ አንባሳዬ እያለ
ታዲያ ከዚህ በላይ ውድ ህይወት የታለ
የሺ ቀን በደልህ በአንድ ቀን ፈቶልህ
በድስታህ ደስ ብሎት ልጄ ልጄ የሚልህ
ታዲያ የኔ ወዳጅ 😢
ቀኑ ጭንቅ የሆነው
ህይወት የሚመረው
እንባህ የማይደርቀው
ይህን ቅዱስ አባት ያጣህበት ቀን ነው
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
አባ በረከትዎን ያሳድርብን ዘንድ ወደ አምላክዎት አሳስቡልን