በጸሎት ሰዓት ሐሳባችን ለምን ይበተናል?
ለምን በተምስጦ መጸለይ አቃተን?
/በጸሎት ሰዓት የዝሙት እና የክፉ…ሐሳቦች/
ክፍል አስራ አንድ
በቀሲስ መ/ር ሄኖክ ወ/ማርያም
ተወዳጀች ሆይ በክፍል አስር የአየር አጋንንት በጸሎት ሰዓት በእንቅልፍ፣በድካም፣በፈስ እና በሌሎችም እንዴት እንደሚፈትነን አይተናል፡፡ ሳልጠቅሰው የማላልፈው ስለምትሰጡኝ ገንቢ አስተያየት ሳላመሰግናችሁ አላልፍም፡፡ ግን በውስጥ መስመር ከችግራችሁ አንጻር በመፍትሄው ዙርያ ብዙዎች ትጠይቁኛላችሁ እኔም ካለኝ ግዚ አንጻር ሁላችሁንም ባይሆንም ባስ ያለውን እያየሁ በመፍትሄ ዙርያ መልስ ብሰጣችሁም መልስ ያልሰጠኃችሁ ቅር እንዳትሰኙብኝ አደራ!!! ምክንያቱም በተከታታይ ትምህርቱ ላይ ጠቅለል ያለ መልስ ስለምታገኙ፡፡
3ኛ/ የአየር አጋንንት በጸሎታችን ጊዜ በክፉ ሐሳቦችና በዝሙት ከሳች ምስሎች እንዴት እንደሚፈትነን እናያለን፡፡ አምላከ አበው ይርዳን፡፡
ሀ/ በጸሎት ሰዓት የዝሙት ሐሳብ ፦ በጸሎታችን ሰዓት አንዳንዴ የዝሙት ሐሳብ ውልብ ይልብናል፡፡ ሲብስም ጸሎቱን አስረስቶን ሰውነታችን እስኪሞቅ፣አፍረታችን እስኪነሳሳ ድረስ ይፈትነናል፡፡ ይህ ሁለት አንድምታ አለው፡፡
አንደኛው ፦ አጋንንት ሲሆን በስራ ድርሻው በዝሙት የሰለጠነው ልምድ ያለው የዝሙት አጋንንት ነው የሚፈትነን፡፡ ይህ የዝሙት አጋንንት በተለያየ መንገድ ሊጣባን ይችላል፡፡ በተለይ የወሲብ ፊልሞችን፣ወሲብ ቀስቃሽ ልብ ወለዶችን እና ወሲብ ነክ ጽሑፎችን የምናይና የምናነብ ከሆነ መንፈሱ በቀላሉ ውስታችን በመግባት ለዝሙት በመገፋፋት ሲበረታም በዝሙት በመጣል ይፈትነናል፡፡
ታድያ የወሲብ ፊልምን መመልከት፣ወሲብ ቀስቃሽ ጽሑፎችን ማንበብ ህርም ብለን ንስሐ ገብተን ከፍ ሲልም ቆርበን ጥሩ መንፈሳዊ እንሆናለን፡፡ ግን ያኔ ውስጣችን ገብቶ አድብቶ የነበረው የዝሙት አጋንንት በጸሎት ሰዓት መንቀሳቀስ ይጀምራል፡፡ በተለይ የወደቅንባቸውን ሰዎች እየከሰተ እንዴት ባለ መልኩ ዝሙት ፈጽመን ስጋዊ ደስታ እንዳገኘን በማሳየት ይፈትነናል፡፡
እኛም ያንን ቀድሞ የፈጸምነውን ዝምት ለመርሳት ምስሉን ከህሊናችን ለማራቅ ስንሞክር ጸሎታችንን ትተን ወደ መረበሽ ውስጥ እንገባለንን፡፡ አንዳንዴም ግራ ሲገባን እያማተብን ከእኛ ለማራቅ እጥራለን፡፡ ግን ከመራቅ ፈንታ የሐሳቡ ድግምግሞሽ ያስቸግረናል፡፡ እኛም በጸሎታችን መሃል በሚፈትነን ክፉ ሐሳብ በመሳቀቅ እግዚአብሔር ጸሎታንን የሚቀበለን እስከማይመስለን እንደርሳለን፡፡
ስለ ዝሙት አጋንንት ካነሳን ዘንዳ የዝሙት ሐሳብን በህሊና በልቦና ማስተናገድ ለከፋ ችግር ይዳርገናል፡፡ እስኪ ደፈር ብዬ ስለ ግለ ወሲብ ልንገራችሁ፡፡ በዝሙት መንፈስ ግፊት የዝሙት ሐሳብን በልቦናችን ስናስተናግድ ያንን ሐሳብ ልምድ እናደርገዋለን፡፡ ከዚያም ምናልባት ዝሙትን በተግባር መፈጸም ካልሆነልን በተግባር ዝሙት መጣል ያቃተው በግለ ወሲብ ይጥለናል፡፡
ዝሙትን በሁለተኛ አካል/ከሌላ ተቃራኒ ጾታ/ ጋር መፈጸም አልሆን ሲለን ከራሳችን ጋር እንድንፈጽም ያደርገናል፡፡ የዚህን ግለ ወሲብ አፈጻጸም አጋንንት ከፊልምና ከንባብ በማየት እንድንተገብረው ያደርገናል፡፡ ግለ ወሲብ በወንዶችም በሴቶችን ይጸናል፡፡ ደስታን ከሌላ ሰው ጋር ሳይሆን በራሳችን አካል እንድናገኝ ያደርገናል፡፡
የሚገርመው ለብዙዎች ግለ ወሲብን ከመተው የሐሺሽ ሱስን መተው ይቀላቸዋል፡፡ ከተጠናወታቸው ከዛ ተግባር ለመላቀቅ እጅጉን ይቸገራሉ፡፡ በግለ ወሲብ ዙርያ በስፋት ስለምመጣበት ለአሁኑ እዚህ ላይ ላብቃ፡፡ ግን እባካችሁ ከዚህ ተግባር ተቆጠቡ ሳይሆን ለመተው አስቡ፡፡ የዝሙት አጋንንት መጫወቻ አትሁኑ!!!
ሁለተኛው ፦ የአየር አጋንንት ቀድሞ በውስጣችን ከገባው የዝሙት መንፈስ ጋር አጋንንታዊ ግንኑነት/ኮኔክሽን/ በመፍጠር የአየር አጋንንቱ የዝሙት የሐሳብ ምስል በማምጣት ያሳየናል፡፡ ይህ ደግሞ ለእኛ እጅጉን የሚከብደን ፈተና ይሆንብናል፡፡ ምክንያቱም የዝሙት አጋንንቱ ከውስጥ የአየር አጋንንቱ ከውጭ በብርቱ ስለሚፈትነን ዳግም በዝሙት የመውደቅ አጋጣሚያችን በጣም ሰፊ ይሆናል፡፡
የሚገርማችሁ ብዙዎች ዝሙትን ህርም ብለው ንስሐ ገብተው ቆርበው ዳግም በዝሙት ኃጢአት የሚወድቁት፣ቁርባናቸውን የሚያፈርሱ በውስጣቸው ባለው የዝሙት አጋንንት እና በውጭ ባለው በአየር አጋንንት ጫና ነው፡፡
የአየር አጋንንት በጸሎታችን በሐል ድንገት የዝሙት ሐሳብ አምጥቶ ድቅን ሲያደርግብን ተመስጦአችንን በማጣት ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ እንገባለን፡፡ ይህም ለአጋንንቱ እኛን ለመረበሽ፣እግዚአብሔር ፊት እንድንሳቀቅ የሚጠቀምበት ስልቱ ነው፡፡ ልብ ካላችሁ ጸሎታችሁን ልትጀምሩ ስትሉ ሐሳቡ የለም ግን ድንገት የሚከሰት ስለሆነ እጅጉን ትጨነቃላችሁ፡፡ ግርም የሚላችሁ የዝሙት አጋንንት እፍረት ስለሌለው ቅዳሴ እያስቀደሳችሁ ሊፈትናችሁ ይችላል፡፡
ወገኖቼ አጋንንት ማለት የጭቃ ውስጥ እሾህ ማለት ነው፡፡ የጭቃ ውስጥ እሾህ ተጠንቅቃችሁም ይወጋቹኃል፡፡ አጋንንትም በመንፈሳዊ ህይወታችሁ ከተግባር ኃጢአት ብትጠነቀቁም በሐሳብ ኃጢአት በስውር እየወጋ ያሰቃያችሃል፡፡
በጸሎት ሰዓት የቱንም ያህል በዝሙት ሐሳብ ቢፈትናችሁም ሐሳቡን ከእናንተ ለማራቅ እየታገላችሁ በቅዱሳን ስም እየገዘታችሁ ለመጸለይ ሞክሩ እንጂ በፍጹም ‹‹በእግዚአብሔር ፊት ዝሙት እያሰብኩ ስለሆነ ጸሎቴን እግዚአብሔር አይሰማኝም›› ከሚለው የአጋንንት ወጥመድ ተላቃችሁ ጸልዩ፡፡ ወትሮም አጋንንቱ የሚፈልገው በተግባር ኃጢአት ቢያጣን በሐሳብ ኃጢአት ለማሰቃየት ስለሆነ ጸሎታችሁን እንዳትተዉ፡፡
ለ/ በጸሎት ሰዓት ክፉ ሐሳቦች ፦ የአየር አጋንንት በተለይ የማናውቃቸው የማናስባቸውን ክፉ ሐሳቦች በጸሎታችን ሰዓት እያመጣ በመደቀን በማሳሰብ እጅግ የተዋጣለት ነው፡፡ በመሰረቱ ብዙ ቅዱሳኖች ገድላቸው እንሚነግረን በሐልዮ ኃጢአት/በሐሳብ/ ሲቸገሩ እናያለን፡፡
ምንም ቢበቁ የቅድስና ማዕረግ ላይ ቢደርሱ ከሐልዮ ኃጢአት ስለማይርቁ እራሳቸውን እንደ ኃጢአተኛ ይቆጥራሉ፡፡ ይህ ማለት ሁሉም ቅዱሳን በኃልዮ ኃጢአት ይፈተናሉ ሳይሆን የተወሰኑት በተለይም ከቅድስናቸው የተነሳ በውዳሴ ከንቱ እንዳይወድቁበት ከእግዚአብሔር ፈተናው ይሰጣቸዋል፡፡ እነሱም ያላቸውን ቅድስና ተጋድሎ አስበው ከመመካት ይልቅ በህሊናቸው በሚፈተኑት የሐሳብ ኃጢአት እራሳቸውን እንደ ኃጢአተኛ እንዲቆጥሩ ያደርጋቸዋል፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስሙ በመጠርያው ሳይሆን በተግባሩ የተገለጠው የአየር አጋንንት ሳኦልን ክፉኛ ያሰቃየው እንደነበር ‹‹የእግዚአብሔር መንፈስ ከሳኦል ራቀ፣ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ አሰቃየው›› ተብሎ ተጽፏል፡፡ ብላቴናው ዳዊት በመዝሙር በገናን ሲደረድር የአየር አጋንንቱ ይርቅ ነበር፡፡ ይህም ‹‹ክፉ መንፈስም ከእርሱ ይርቅ ነበር›› ተብሏል፡፡ /1ኛ ሳሙ 16 ÷ 14-23/
ልብ ልትሉት የሚገባው የአየር አጋንንቱ ብላቴናው ዳዊት በበገና ሲጸልይ ይሄዳል፡፡ ዳዊት ሲሄድ የአየር አጋንንቱ እየመጣ ሳኦልን በክፉ ሐሳብ እያስጨነቀ ያሰቃየው ነበር፡፡ የማይያዝ የማይጨበጥ ግን እየሄደ እየመጣ ሳኦልን ያሰቃየው የነበረው የክፉ መንፈስ የአየር አጋንንት ካልሆነ ምን ሊሆን ነው?
በጸሎት ሰዓት ክፉ ሐሳብ የምንለው የአየር አጋንንቱ እያመጣ እንደ ሳኦል የሚበትንብም የተለያዩ ሐሳቦች ናቸው፡፡ ለምሳሌ ስለ እመቤታችን ድንግልና በስጋ እንድታስቡ ያደርጋቹኃል፡፡ አምላክን በድንግልና ወልዳለች የሚለውን ዶግማዊ ትምህርት ‹‹እንዴት ሊሆን ቻለ፣እንዴት አድርጋ ወለደች›› በማለት ክፉ ሐሳብ ውስጥ ይከታቹና ያስደነግጣቹኃል፡፡

የአየር አጋንንት በውስጣችሁ የስድብ መንፈስ በማስገባት በልባችሁ ቅዱሳንን የሚሳደብ ሐሳብ እንድታመነጩ ያደርጋችኃል፡፡ ያኔ እራሳችሁ ስለሚመስላችሁ ድንገተኛና ከፍተኛ ድጋጤ ውስት ትገባላችሁ፡፡ ይህ ክፉ ሐሳብ በጸሎታችሁ፣በቅዳሴ እና ብቻችሁን በሆናችሁ ሰዓት እየመጣ ያስቸግራችኃል፡፡
ከጸሎት ሰዓት ውጪ ባለው ጊዜያችሁ ለሰከንድ የማታስቡትን ነገር በጸሎታችሁ ሰዓት በፍጹም ልታደርጉት ቀርቶ ልታስቡት የማትችሉትን ሐሳብ እያመጣ ያስጨንቃችኃል፡፡ በነገራችን ላይ የማትፈልጉት ሐሳብ እየመጣ ሲረብሻችሁ እራሳችሁን መቆጣተር ስለማትችሉ ይህን ልምድ አጋንንቱ እንድታዳብሩ በማድርግ ለአእምሮ ጭንቀት፣ለማታውቁት ፍርሃት በመጨረሻም ለእብደት ሊዳርጋችሁ ይችላል፡፡ በዚህ መሰል ችግር ስንቱ የአየር አጋንንት ሰለባ ሆኖ ለማይመለስ የአእምሮ ህመም ተዳርጓል፡፡
በጸሎት ሰዓት አስደንጋጭ ክፉ ሐሳብ ሲረብሻችሁ እራሳችሁን እንዳታስጨንቁ ለመረጋጋት ሞክሩ፡፡ በልባችሁም ‹‹ፈጣሪዬ ሆይ እኔ ኃጢአተኛው ባርያህ በፊት ለጸሎት እንደቆምኩ አንተ ታውቃለህ፡፡ ግን በክፉ ሐሳብ የሚረብሽኝን አንተ በኪነ ጥበብህ እሰርልኝ አርቅልኝ›› በሉ፡፡ ደግሞም እግዚአብሔር የማንፈልገው ከልባችን የመነጨ የሚመስለውን፤የአየር አጋንንት ጾር እንደሆነ ስለሚያውቅ መለኮታዊ ጥበቃ ያደርግልናል እንጂ ለአጋንንቱ ፈተና እስከመጨረሻው አሳልፎ አይሰጠንም፡፡
ወዳጆቼ አንድ እውነት እወቁ! ብርቱ በሆነ በአጋንንት ውግያ ተሰላችታችሁ፣ተስፋ ቆርጣችሁ ጸሎታችሁን ከተዋችሁ የአየር አጋንንቱ የፈተና መልኩን እየቀየረ መፈጠራችሁን እስክትጠሉ ያስመርራችኃል፡፡ ልብ በሉ መሳርያ የታጠቀ ግን በድንገት እና በድክመቱ በጠላት መሳርያ የተመታ ብርቱ ወታደር እስኪሞት ይዋጋል እንጂ ገና ለገና ተመትቻለሁና እጅ ልስጥ አይልም፡፡
እናንተም መንፈሳዊ ወታደር ስለሆናችሁ በጥንተ ጠላታችሁ በአጋንንት ፍላጻ ብትመቱም፣በዝሙት እና በክፉ ሐሳብ ብትንገላቱም ጸሎትን እንደ መሳርያ በመጠቀም መዋጋት ነው የሚያዋጣችሁ፡፡
‹‹በጸሎቴ ሰዓት የዝሙት፣የክፋት እና የማልፈልጋቸው ሐሳቦች ስለሚያስቸግሩኝ ከምጸልይ ይቅርብኝ›› ካላችሁ በእውነት ነው የምላችሁ አጋንንቱ ሳይማርካችሁ እናንተ በፈቃዳችሁ ተማረካችሁለት፣እጅም ሰጣችሁት ማለት ነው፡፡ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‹‹በእግዚአብሔር ላይ ያለህን ተስፋ የቆረጥክ ቀን ለአጋንንት እጅ እንደሰጠህ ቁጠር›› ይላል፡፡ ስለዚህ በፈተናው ታግላችሁ ጸልዩ እንጂ ማንን ደስ ይበለው ብላችሁ ነው ጸሎታችሁን የምታቆሙት፡፡
እግዚአብሔር በእናንተ ተስፋ ሳይቆርጥ አውሎ እያስገባችሁ፣አምሽቶ እያነጋልችሁ፣ገመናችሁን ሰውሮ ከቤቱ ሳይርቃችሁ፣በጤና ጠብቋችሁ፣በህመም ከጤነኛው እኩል እያኖራችሁ… ኸረ ስንቱ ይዘረዘራል.. ይህንንና ሌሎች ድንቆችንም እያደረገላችሁ እንዴት በአጋንንት ፈተና ጸሎታችሁን ትተዋላችሁ?
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በአርጋኖን ምስጋናው ላይ በተደጋጋሚ አጋንንት ጸሎት ስንተው እጅጉን እንደሚደሰት ተናግሯል፡፡ ደስታውም የሚልቀው የእኛ ጸሎት መተው ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ ያለን ተስፋ ተሟጦ፣ቅድስናችን በኃጢአት ተግባር ተለውጦ ሲያይ ነው፡፡
እባካችሁ…እባካችሁ በጸሎት ሰዓት ምንም አስቡ ምንም ጸሎታችሁን ግን አትተዉ፡፡ ወዳጆቼ ጸሎት እኮ ማመስገኛ ብቻ ሳይሆን ከአጋንንት ጋር ጥርስ ለጥርስ የምትነካከሱበት፣ፊት ለፊት የምትፋጠጡበት፣መንፈሳዊ ትግል የምትገጥሙበት ስውር ጦርነት ነው፡፡
ጸሎት ስጋችሁን እና የሚፈትናችሁን አጋንንት የምታሸንፉበት ታላቅ መንፈሳዊሊተርፍ መሳርያችሁ ነው፡፡ ሰው እንዴት የጸሎት መሳርያውን ጥሎ፣ፈተናውን በራሱ ላይ ቆልሎ ቁጭ ይላል?
የአየር አጋንንቱ ‹‹እስከዛሬ ጸለይክ ምን አመጣክ? ጸሎትህ እንኳን ለሰው ላንተም አልሆነም ችግርህን አላቃለለም›› እያለ ሲሞግታችሁ ጸሎታችሁን እንዳትተዉ፡፡ ይቺ እናንተን ጸሎት የማስጣያ ዘዴው ስለሆነች ንቁበትበሌሎችም እወቁበት፡፡
4ኛ/ የአየር አጋንንት በጸሎት ሰዓት በሽንት፣በሰገራ፣በወገብ ህመም፣በማሳከክና ክስተቶች እንዴት እንደሚፈትነን እናያለን ……
ይቀጥላል…..
አንብበው ሲጨርሱ በችግሩ ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ያዳርሱ!!!
ሐምሌ 17/11/2010 ዓ.ም
አዲስ አባበ

‹‹ነብይነት በስልጠና›› ትምህርትና ስራ አልሆን ያለህ ናና ናና
/የነብይ ማሰልጠኛ ወይስ ማሰይጠኛ?/
ወዳጆቼ አሁንስ እኔ የነዚህ ሰዎች ነገር ትክት ነው ያለኝ፡፡ አሳፋሪ ጉዳቸው በአናት በአናታችን ተደራረበ ኸረ እንደው ምን ይሻለናል?
ቆይ ሁሉም ነገር አልሆን ብሎት ግራ የገባው ሁሉ በአንድ ወር ከሳምንት ነብይ የሚሆንበት ትምህርት ቤት ይከፈት፡፡
የዘመናችን ነብይ ነን ባዮች ከትንቢታቸው፣ወፈፌ ውሸታቸው አገር የፈታው ለካ ነብይነት በእግዚአብሔር ሹመት ሳይሆን በስልጠና ስለሆነ ነው፡፡ አይ አገሬ!
የሚያደርጉት ሲጠፈቸው ቢስዝነስ የሚሰሩበት ግራ ሲገባቸው ‹‹የነብይነት ትምህርት ቤት›› ብለው በጠራራ ጸሐይ ተጃጅልው ሰውን ያጃጅሉ! እኔ ይሄ ነብይ ማሰልጠኛ ብለው የከፈቱት ማሰይጠኛ ነው፡፡
ነብይነትን በትምህር አጋኛለሁ ብሎ የሚማር ካለ እርሱ ነብይ ሳይሆን ቃላባይ ነው፡፡
በመሰረቱ ነብይ ማለት ምን ማለት ነው? ነብይ ማለት የወደፊቱን የሚናገር ወይም የሚያመለክት ማለት ነው፡፡ በግሪክ ፕሮፊቴስ የሚለው ቃል ከሁለት ጥምር ቃል የተፈጠረ ሲሆን ‹‹ፕሮ›› የወደፊት ማለት ሲሆን ‹‹ፊሜ›› ደግሞ እናገራለሁ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ነብይ ማለት አንድ ነገር ከመሆኑ አስቀድሞ ሊሆን ያለውን በእግዚአብሔር ጸጋ የሚያመለክት ነው፡፡
ነብይ ሁለት ታላላቅ ስራዎችን ይሰራል፡፡ አንድኛው ማብሰር ሲሆን ሁለተኛው ስለ ወደ ፊት ማመልከት ነው፡፡
በመጸሐፍ ቅዱስ ታላላቅ ነብያት ስማቸው ከነግባራቸው ተጠቅሷል፣ትንቢታቸውም ተጽፏል፡፡ ግን የእነዚህ ነብያት ሹመት ከሰው ሳይሆን ከእግዚአብሔር ነው፡፡ ነብይነትን በስልጠና ሳይሆን በእግዚአብሔር ልግስና ነው ያገኙት፡፡
የዘንድሮ ነብይነት ሽቀጣ ነው፡፡ እስኪ በጥቂቱ የዘንድሮ ነብይ ነኝ ባዮች ቅጥፈት የታከለበት ትንቢቶችን እንይ፡፡ አንድ ያረገዘችን ሴት ያረገዘችው ወንድ አልያም ሴት መሆኑ ስለማይቀር የሆድዋን መግፋት አይተው በግምት ‹‹ጌታ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ ብሎሻል›› ብሎ ነብይ ባዩ ይናገራል፡፡ ትንቢት የተነገራት እናት ሴት ወልዳ ቁጭ፡፡ ነብዩም ከአልትራ ሳውንድ የማይሻል ይሆናል፡፡
ነብይ ነኝ ባዩ ‹‹ጌታ ነግሮኛል ከዛሬ ጀምሮ በሽታችሁ ተፈውሳል እስኪ አሜን በሉና ድህነታችሁን ተቀበሉ›› ተብለው ጅምላ ውሸት ሲታደላቸው ያልታደሉት ደግሞ ‹አሜን› ብለው ይጨፍራሉ በሐሰተኛ ነብያት ይታለላሉ፡፡
እንደ ኤልሳዕ ያለ እውነተኛ ነብይ ግን እንኳን ሰውን ምድርን የሚያጨነግፈውን ውሃ ይፈውሷል፡፡ /2ኛ ነገ 2÷21-22/
ስለ እነዚህ ነብያት ጌታችን ‹‹እጄም ከንቱ ራዕይን በሚያዩ፣ውሸትም በሚያምዋርቱ ነብያት ላይ ትሆናለች፡፡ እነርሱም በሕዝቤ ማህበር ውስጥ አይገኙም፣በእስራኤል ቤት መጽሐፍ አይጻፉም፣ወደ እስራኤል ምድር አይገቡም እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ›› ብሎ ነብዩ ሕዝቅኤል ተናግሯል፡፡ ት.ሕዝ 13÷9
ትንሽ ነካ የሚያደርጋቸው ነብይ ነኝ ባዮች ደግሞ ‹‹ይህቺን ከተማ በወንጌል የሚገለባብጡ ነብያት ይነሳሉ ብሎኛል እስኪ በወንጌል ከተማዋን ገለባብጣለሁ የምትል አሜን በል›› ይላል፡፡ እንኳን ከተማ ሊገለባብጥ የራሱ ይህወት ተገለባብጦ ይኖራል፡፡ ለመሆኑ ከተማዋን በወንጌል ትምህር መለወጥ እንጂ መገለባበጥ ይቻላል? እንዲህ ደፍሮ ለመናገር ቢያንስ አእምሮውን መታመም አለበት፡፡
ትንቢት ከእግዚአብሔር ሳይሆን ከኪሳቸው እያወጡ በሐሰት የሚሸቅጡ ነብይ ሳይሆኑ ቃላባይ የሆኑትን ነብዩ ኤርሚያስ በግሩም መልኩ ‹‹እነሆ ከምላሳቸው ትንቢት አውጥተው እርሱ ይላል በሚሉ ነብያት ላይ ነኝ ይላል እግዚአብሔር›› በማለት ተናግሯል፡፡ /ት.ኤር 23÷31/
ብዘዎች እነዚህ ሐሰተኛ ነብያት ህዝቡን ሳያስቱት፣ህይወቱን ሲያበላሹት አልፍ ተርፎ ገንዘባቸውን ሲበሉ እግዚአብሔር ለምን ዝም አላቸው የሚሉ አሉ፡፡ ነገሩ ወዲህ ነው፡፡ ጌታ ስለ ሐሰተኛ ነብያት ‹‹ተዉአቸው እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤በመከር ጊዜም አጫጆችን እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በነዶው እሰሩ ስዴውን ግን በጎተራ ክተቱ እላለለሁ›› ብሏል፡፡ /ማቴ 13÷30/
መቼም ከዚህ ‹‹የመንግስቱ ምስክር ትንቢታዊ ማዕከል የነብያት ማሰልጠኛ›› ከተባለው ነብይ ሳይሆን ቃላባይ የሆኑ ሐሰተኛ ሰዎች እንደሚፈለፈሉበት ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ነብይነትን በስልጠና ለዛውም በአንድ ወር ከሳምንት ማፍራት ከተቻለ ሰዉን በሙሉ በክረምት ስላልጠና መናጢ ቀሳጢ ነብይ ማድረግ አይከብድም፡፡
እንደው ነብይነትን ከዲፕሎማ ታሳንሱት? እሱስ ይቅር በሌቭል ከሚሰጥ ኮርስ ታሳንሱት? ታድያ ሰዉ በየዩኒቨርሲቱ ለዓመታት ከሚማረው ትምህርት ነብይነት ቀሎ ነው? ኸረ አፍራችሁ አታሳፍሩን! ለነገሩ ቀላችሁ ስላቀለላችሁት ነው በአንድ ወር ከሳምንት ነብይ እናረጋለን የምትሉት፡፡
በሉ እንግዲ ክርስቶስ በጸጋው ያልሾማቸውን እናንተ በስልጠና ነብይ ሹሙና አገራችን ከአለም አገራት እንደ ሩጫው፣እንደ ቡናው በነብያት አንደኛ የሆነች አገር አድርጉልን፡፡
ወይ ፈጣሪዬ ዘንድሮ መስከረም ሳይጠባ፣ስንት የሚያስነባ ነበር ታሰማኝ!
ለማንኛውም ክርስቶስ ባልሰጣችሁ ጸጋ፣ወደ ነብያት ልጠጋ ብላችሁ ወደ ማሰልጠኛው ሳይሆን ወደ ማሰይጠኛው ከሄዳችሁ ጥሩ ነብይ ሳይሆን ከኪሱ ትንብትን መዥረጥ አድርጎ የሚናገር ቃላባይ ትሆናላችሁ፡፡ ስለዚህ ከሐሰተኛ የነብይ ማሰይጠኛ ይጠንቀቁ፡

ለምን በተመስጦ መጸለይ አቃተን
/በጸሎት ሰዓት በሽንት፣በወገብ፣በልብ ህመመ…/
ከፍል አስራ ሁለት
በቀሲስ መ/ር ሄኖክ ወ/ማርያም
ተወዳጆች ሆይ በክፍል አስራ አንድ የአየር አጋንንት እና የዝሙት አጋንንት በጸሎት ሰዓት በፍትወት ሐሳብና በክፉ ሐሳብ እንዴት እንደሚፈትነን አይተናል፡፡
አሁን ደግሞ የአየር አጋንንት በጸሎት ሰዓት በሽንት፣በሰገራ፣በወገብ ህመም እና በሌሎችም እመለከታለን፡፡ የዳንኤል አምላክ ምስጢሩን ይግለጽልን!!!
4ተኛ/ የአየር አጋንንት በጸሎት ሰዓት በሽንት፦ በመሰረቱ ሽንትን ስናነሳ ብዙዎች በተኙበት አልጋ ላይ ይሸናሉ፣በድንጋጤ ሽንት ያመልጣቸዋል፣ጸሎት ላይ ቅዳሴ ላይ፣ጉባኤ ላይ፣ጸበል ሊጠመቁ ሲሉ ሽንት ይወጥራቸዋል፡፡ ይህ እራሱን የቻለ የዓይነ ጥላ መንፈስ ምልክት ነው፡፡
ከደቂቃዎች በፊት ሽንታችንን ሸንተን ጸሎት ስናደርግ በተለይ ጸሎታችን በሚነበብ መጽሐፍ ከሆነ አይነ ጥላው ከእኛ በተሻለ የጸሎቱን ኃይል ስለሚያውቅ በመጨነቅ በሽንት እንድወጠር ያደርገናል፡፡ የሚገርመው ጸሎታችንን አቋርጠን ሽንታችንን ለመሽናት ስንሄድ ሽንት ላይኖረን ይችላል፡፡
በዚህ ጊዜ የአየር አጋንንቱ ከአይነ ጥላ ጋር በማበር ትንሽዋን ሽንት ብዙ በማስመሰል ያሳስበናል፡፡ እኛም በዛን ሰዓት ሐሳባችን ከጸሎታችን ጋር ሳይሆን ከሽንታችን ጋር ይሆናል፡፡
እድሜ ለሐኪሞቻችን ዛሬ ሽንት በቁመናችን በእቅልፋችን የሚያሸናን አይነ ጥላ የሳይንስ ከለላ ስላገኘ እርሱ የሚያሸናንን ሽንት ከኩላሊት ህመም ጋር ስለሚያያዙ ጥሩ ሽፋን አግኝቷል፡፡ ሽንት መቋጠር የማይችሉና ሽንት የሚያመልጣቸው ሰዎች ችግራቸው አይነ ጥላ ሳይሆን የኩላሊት ችግር ይመስላቸዋል፡፡
አይነ ጥላ እኛን ሽንት በማሸናቱ ብዙ ነገር ይጠቀማል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሴት በመኝታዋ ሽንቷን የምትሸና ከሆነ የነገ የትዳር ህይወቷን ጥያቄ ውስጥ ትከተዋለች፡፡ ‹‹አግብቼ ባሌ ስር እየሸናው ከምዋረድ፣ይህቺ ሽንታም ከምባል ትዳሩ ቢቀር ይሻላል›› አስብሏት የትዳር እድልዋን ይዘጋል፡፡
እኔም እማኝ ሆኜ የምነግራችሁ ዕለት ዕለት በአላጋዋ ላይ እየሸናች ለ37 ዓመት የኖረች ልጅ ትዳር ያልያዘችበት ምክንያት በሽንት ነው፡፡ ይህቺ ልጅ ከመንፈሳዊ ወንዶች በተደጋጋሚ የትዳር ጥያቄ ሲቀርብላት ሌሊት ለዘመናት በመሽናትዋ ትዳር ለመያዝ ፈርታ በብቸኝነት ህይወት ትኖራለች፡፡
የሚያሳዝናችሁ ሌሊት በአልጋዋ ላይ የምትሸናው ሽንት ሽታው የሚሰነፍጥ፣የሚያፍን ሽታ አለው፡፡ በአይነ ጥላ መንፈስ ጥቃት፣ሌሊት በአልጋ ላይ የሚሸና ሽንት ሽታው የተለየ ነው፡፡
አይነ ጥላው ሽንቷን እሱ እንደሚያሸናት እሷም ቤተሰብም እንዳይነቃበት ሽንት ማሸናትን ከህጻንነት ስለሚያስጀምር ‹‹እሷ እኮ ከልጅነቷ ጀምሮ ነው የምትሸናው፣እሱ በልጅነቱ ነው የጀመረው›› እንዲባል ቤተሰብን እኛንም እያለማመደን እናድጋለን፡፡
በማርቆስ ወንጌል የተጠቀሰው ልጁ የታመመበት ሰው የሚደነቅ ሰው ነበር፡፡ ምክንያቱም ልጁን ወደ ጌታችን ሲያመጣው እላዩ ላይ አደሮ ያሰቃየው የነበረ ርኩስ መንፈስ ጌታን ባየ ጊዜ ጣለው አንፈራገጠው፡፡ ጌታም ‹‹ከያዘው ስንት ዘመን ነው›› ብሎ ሲጠይቀው የልጁን ችግር ያወቀውና የተረዳው አባት ‹‹ከህጻንነቱ ጀምሮ ነው›› አለው፡፡ ልብ በሉ አጋንንት ምን ያህ ከህጻንነታችን ጀምሮ በእኛ በማደር፣ለከፋ ችግር እንደሚዳርገን ልናውቅ ይገባል፡፡ /ማር 9÷20-22/ አጋንንቱም የሰውዬውን ልጅ ማሰቃየት ብቻ ሳይሆን ሊያቃጥለው ወደ እሳት፣ሊገለው ወደ ውሃ ሙላት፣ይከተው እንደነበር ተጽፏል፡፡ /ማር 9÷22/
ወላጆቻችን ይህን ችግር ከህጻንነታችን ጊዜ ጀምሮ ቢያውቁ ኖሮ ዛሬ አጋንንቱ በወጣትነት በአዋቂነት ዘመናችን ባልተጫወተብን ነበር፡፡ የሚገርመው የዚህ ልጅ በሽታ እኛ በተለምዶ የሚጥል በሽታ የምንለው ግን በመንፈሳዊው ደግሞ ደፋቂው የአየር አጋንንት ነበር፡፡
የሚገርመው ሽንት በተኙበት ሲሸኑ በህልማቸው ሳይሆን በእውናቸው የሚሸኑ ነው የሚመስላቸው፡፡ ከሸኑ በኃላ ከተኙበት ሲነቁ አልጋቸው ረጥቦ ከፍተኛ መሸማቀቅ ውስጥ ገብተው ይገኛሉ፡፡ ቤተሰብም ልጃቸው ላይ አይነ ጥላው እንደሚያሸናት ስለማያውቁ ደበኛው አይነ ጥላ በእናት አባትዋ አፍ ላይ ሆኖ ‹‹አንቺ ሽንታም! ሽንትሽ ሰለቸኝ፣ፍራሹን አበላሸሽው›› እያለ ያሰድባቸዋል ይሰድባቸዋል፡፡
አይነ ጥላው የበለጠ ሊያሸማቅቃችሁ ለቅሶ ቤት፣ሠርግ ቤት፣ከጓደኛ ጋር በምትተኙበት ጊዜ አሸንቷችሁ ያሳፍራቹኃል፡፡ ይህ ለአይነ ጥላው ትልቅ ጥቅም አለን፡፡ ምክያቱም ስንተኛ በራሳችን ተማምነን እንዳንተኛ የስነ ልቦና ጦርነት ለመክፈት ይጠቀምበታል፡፡
ታድያ አይነ ጥላው ሽንት በማሸናት ወቅት የአየር አጋንንቱ ድርሻ ምንድነው? ካልን የአየር አጋንንቱ በምትሃት በእውን የመሰለ ሽንት ቤት፤ትምህርት ቤት፣ቤት ውስጥ፣መንገድ እና ሌላም ምስል በህልም በማሳየት ይተባበራል አይነ ጥላ ደግሞ ያሸናል፡፡
ምናልባት አይነ ጥላ ባይኖርብን ደግሞ የአየር አጋንንቱ አይነ ጥላውን በመወከል በጸሎት ሰአት ያልተለመደ ሽንት እንዲወጥረን፣ለጸሎት እንዳንነሳ ቀድሞ በማሸናት ይፈትነናል፡፡
† የአየር አጋንንት በጸሎት ሰዓት በሰገራ፦ በክፍል አስር የአየር አጋንንት በሆድ
መንፋት፣በግሳት እና በፈስ እንዴት እደሚፈትን አይተናል፡፡ ግን አጋንንቱ በጸሎት ሰዓት ሆዳችንን እየነፋ፣እየቆረጠ ሲያስቸግረን እኛም ምንም ይምጣ ጸሎቱን አንተውም ስንል ሰገራ የመጣን እንዲመስለን ያደርጋል፡፡ በዚህ ሁኔታ ሆዳችን ሲጨነቅ ሐሳባችንም መጨነቅ ስለሚጀምር ለጸሎታችን ትኩረት በመንፈግ ሽንት ቤት ስለመሄድ እናስባለን፡፡ ባስ ካለም ሽንት ቤት ገብተን ስንቀመጥ የተቃጠለ አየር አልያም ልፋጭ መሰል ነገር ይወጣል እንጂ በሰገራ እንዳልተቸገርን እናውቃለን፡፡
አንዳንዴም በጸሎት ሰዓት ሆዳችንን ቅስፍ አድርጎ በውጋት ይይዘናል፡፡ እኛም የሆድ ህመሙን፣ውጋት ቁርጠቱን መቋቋም ሲያቅተን ጸሎቱን ለመተው እንገደዳለን፡፡ ስለዚህ የፈለገው ነገር በጸሎታን ጊዜ ቢከሰትም ተቋቋሙን ችለን መጸለይ ይገባናል፡፡ /በአይነ ጥላ ዙርያ ከዚህ ትምህርት ፍጻሜ በኃላ ስለ ውስጥ አይነ ጥላና ስለ ውጭ ገርጋሪው አይነ ጥላ በተለይም ስለሚያደርስብንና ስላደረሰብን ብዙ የህይወት ኪሳራ በሰፊው እንማማራለን/
† የአየር አጋንንት በጸሎት ሰዓት በወገብ ህመም ፦ የአየር አጋንንት፣አይነ
ጥላ፣ዛር እና ዛር ውላጅ፣መተት የመሳሰሉት በጸሎት ሰዓት ወገባችንን በመክፈል፣ለመቆም እስኪያቅተን ድረስ ከፍተኛ የህመም ስሜት እንዲሰማን፣ወገባችን ረትቶ እንዳይቆም በማንቀጥቀጥ፣የቁርጥማጥ ስሜት እንዲሰማን በማድረግ የተካኑ ናቸው፡፡ በመሰረቱ ለጸሎት ስትቆሙ ወገባችሁን የሚያማችሁ እራሳችሁ ሳትሆኑ እናንተን የሚፈትነው አጋንንት በጸሎት ሰዓት መቆም ስለማይችል የእሱን ስቃይ ነው በእናንተ የምታዩት፡፡
ሌላው ለሌላ ተግባር ለረጅም ሰዓት ስትቆሙ ወገባችሁን አያማችሁም ግን በጸሎት ሰዓት ወገባችሁን አሟችሁ መቆም ካቃታችሁ እግዚአብሔር የምትጸልዩት የጸሎት ኃይል በግልጽ እያሳያችሁ ነው፡፡ ጸሎት ምን ያህል አጋንንትን እንደሚያንቀጠቅጥ በራሳችሁ አያችሁ ማለት ነው፡፡
ቆማችሁ የምታደርሱት ጸሎት የእናንተን ሳይሆን የጋንንትን ወገብ እየፈለጠ፣እያንቀጠቀጠ ስለመሆኑ እርግጠኛ ሁኑ እንጂ እናንተ እንደ ታመማችሁ አትቁጠሩ፡፡
ዛሬ የዲስክ መንሸራተት፣የወገብ መቀጨት እየተባለ ሰው የሚሰቃይበትን ቆም ብሎ ማሰብ አለበት፡፡
አጋንንት በጸሎት ሰዓት በወገብ ህመም እኛን በመፈተኑ ምን ጥቅም ያገኛል? ብንል ብዙ ጥቅም ያገኛል

፡፡ አንደኛ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን ቆመን እንዳንጸልይ ያደርገናል፡፡ እኛም ቆመን መጸለይ ሲያቅተን ቁጭ ብሎ መጸይን እንመርጣለን፡፡ እኛ ቁጭ ብለን ስንጸልይ አጋንንቱ በቀላሉ በእንቅልፍ ስለሚፈትነን ጸሎታችንን አስትቶ ያስተኛናል፡፡ ወገኖቼ ስንቴ ይሆን ጸሎታችንን ጀምረን እንቅልፍ እየጣለን ጸሎቱን ትተን በዛው የተኛነው?
ሁለተኛው ቆሞ ከመጸለይ ብዛት የሚመጣን የድካማችንን በረከት ለማሳጣት ይመቸዋል፡፡ ስምኦን ዘአምድ የተባለው ጻድቅ ለረጅም ዓመታት በአንድ ድንጋይ ላይ ቆሞ በመጸለዩ የመቆሙ ድካም ‹‹አምድ›› የሚለውን ልዩ ቅጥያ ስም ለማግኘት በቅቷል፣በዚህም ታውቋል፡፡
ወዳጆቼ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለረጅም ዓመታት ሲጸልዩ ከመቆም ብዛት አንድ እግራቸው እንደ ሸንኮራ አገዳ ተሰብሮ ነበር፡፡ በአንድ እግራቸው ለሰባት ዓመት በመጸለያቸው ይህ ታሪካቸው በምድር ለእኛ ሲነገር፤በሰማያዊት እየሩሳሌም ደግሞ በክብር ለመታሰብያ ተጽፏል፡፡ ስለዚህ ተጋድሎን እንዳቅም ከመለማመድና አጋንንትንም ከመዋጋት አንጻር ቆሞ መጸለይ ትልቅ በረከት አለው፡፡ ስለዚህ የፈለገ ወገባችሁን ቢያማችሁም ቆማችሁ ለመጸለይ ሞክሩ ልመዱ፡፡
ዋናው ደግሞ ቆመን ስንጸልይ አጋንንቱ ወገባችንን የሚያሳምመን የወገብ ህመሙ ከወገብ ተነስቶ ከእግራችን እስከ እጃችንና ሌላም አካላችን ስለሚደርስ ከፍተኛ የጸሎት ትኩረት ማሳጣትና የሐሳብ መረበሽ ውስጥ ስለምንገባ ልባችን ይሰረቃል፡፡ በዚህም ጸሎቱ አለቀ አላለቀ እያልን ገጽ በመቁጠር አጭሩ ጸሎት ረዝሞ እንዲታየን ያደርገናል፡፡ በዚህም ተመስጦ ውስጥ መግባት እንዳንችል ያደርገናል፡፡
† የአየር አጋንንት እና አይነ ጥላ በጸሎት ሰዓት በፍርሃት ይፈትነናል ፦ በጸሎት
ሰዓት ፍርሃት በሴቶች ላይ ጎልቶ ይታያል፡፡ የሚገርመው ብዙዎች ሌሊት ወይም ጠዋት በቤታቸው ውስጥ ጸሎት እያደረጉ ፍርሃት ውስጥ ይገባሉ፡፡ አንድ ነገር ኮሽ ካለ በዛ ጸጥታ ድንግጥ ይላሉ፡፡ ሰው እግዚአብሔር ፊት ለጸሎት ቆሞ ይፈራል? ይህ አየር አጋንንት የፈተና ስልት ነው፡፡
ለጸሎት ቆመን ትከሻችንን ጀርባችንን ሊከብደን እና የሆነ ነገር ከኃላችን ያለ እስኪመስለን ይሰማናል፡፡ እንደ ጥላ ያለም ነገር የሚታየን ይመስለናል፡፡ በዚህም እንፈራለን፡፡ ፍርሃቱ የልብ ምታችንን ይጨምርና ትንፋሻችን ሮጦ እንደ ደከመው ሰው ቁርጥ ቁርጥ ይላል፡፡
ልክ እንደ አየር አጋንንቱም አይነ ጥላውም ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ ይከተናል፡፡ በፍርሃታችንም ሰውነታችን ሊንቀጠቀጥ እጅና እግራችን ሊዝል ይችላል፡፡ የአየር አጋንንቱና አይነ ጥላው በጸሎታችን እንዳንመሰጥ፣ሐሳባችንን ሰብስበን እዳንጸልይ በፍርሃት ይጠቀምብናል፡፡
ሌሊት ተነስታችሁ ጸሎት ስታደርጉ በመነሳታችሁ የተበሳጨው አጋንንት የሚያደርገውን ቢያጣ ስለ ሌባ ያሳስባቹኃል፡፡ ‹‹አሁን ሌባ ቢመጣስ፣የሆነ ነገር ብሆንስ›› እያለ በሩ የሚሰበር እስኪመስለን የፍርሃት ጫና ውስጥ ይከታቹኃል፡፡
ጸሎት ስታደርጉ ምንም ነገር በሌለበት ሰውነታችሁ ላይ የሆነ ነገር የሚሄድ እስኪመስላችሁ ድርስ ያስፈራቹኃል፡፡
በነገራችን ላይ ፍርሃትን በጸሎት ሰዓት አነሳን እንጂ አጋንንት በቀን ጥላችንን፣ሰዎችን እንድንፈራ ያደርገናል፡፡ በተለይ አይነ ጥላው ሰው ፊት ስናወራ እንድንፈራ፣ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ወይም ዝግጅት ላይ ስንጠራ በሰው መሃል መሄድ እስኪያቅተን እግራችን እስኪማታ ድረስ ፍርሃት ይለቅብናል፡፡
ምናልባት በስንት ጭንቅ ሰው መሃል ብንቀላቀልም ልናወራ/ልንናገር ስንል አንደበታችን ይያያዛል ምላሳችን ይንተባተባል፡፡ ከማውራት ይልቅ ፍርሃት ይታይብናል፡፡
አጋንንት የጨለማ ሠራዊት ስለሆነ የቤታችንን ጨለማ እንድንፈራ ያደርገናል፡፡ ማብራት ከጠፋማ የጊቢው ጨለማ ሲኦል መስሎ ስለሚታየን እንፈራለን፡፡ ደፈር ብለን ብንወጣ እንኳ ጨለማው ይከብደንና ድንገተኛ ፍርሃት ውስጥ እገባለን፡፡
ብዙ እህት ወንድሞች በተለይ በትምህር ቤት ተማሪ ፊት ለመናገር ይፈራሉ፡፡ ከፍርሃት የተነሳ ሽንታቸው ሊያመልጣቸው የሚደርሱ አሉ፡፡ ይህ ሁሉ የአየር አጋንንቱና የአይነ ጥላው ውጤት ነው፡፡
† በጸሎት ሰዓት ልብ ድክም ማለት ፦ ይህ በተለይ ሌሊት ለጸሎት በምንነሳበት
ወቅት ጎልቶ ይታያል፡፡ ከእንቅልፋችን ተነስተን ለጸሎት ስንቆም እረፍት ያደረገ ሰውነት ሳይሆን የደከመ ሰውነት ይዘን የምንጸልይ ይመስለናል፡፡
‹‹በጸሎት ሰዓት አጋንንት ለምን ልባችንን ያዝላል ያደክማል?›› ካልን ልባችን ሲዝል ወይም ሲደክም ህሊናችን፣ሐሳባችን፣የመጸለይ ፍላገታችን፣እጅ እግራችን ብሎም ሙሉ ሰውነታችን ስለሚዝል፣ስለሚደክም ጥሩ የጸሎት እንቅፋት ይሆንለታል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ትንፈሽ ስለሚያጥረን የጸሎት ሞራላችን ሙትት ይላል፡፡
ስንቆም ልባችን ይመታል አልያም ድክም ይለናል፡፡ የሁሉንም መፍትሄ መጨረሻ በማጠቃለያ ትምህር ላይ ብዘረዝርም በጸሎት ሰዓት ልባችን እንዳይደክም ከመጸለያችን በፊት 41 ጊዜ መስገድ ከበረታን ደግሞ 64 ጊዜ መስገድ ከጠነከርን ደግሞ 105 ጊዜ ብንሰግድ ልባችን ላይ ተቀምጦ የሚፈትነን አጋንንት ይጠፋል፡፡
ሁሉም አጋንንቶች በሰው አካላት ለማደር ልብን ይመርጣሉ፡፡ ልብ የሰውነት ማዕከላዊ መዝገብ ስለሆነ አጋንንት ልብ ላይ ቁጭ ካለ በቀላሉ የፈለገውን ተንኮል መስራት ይችላል፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ በመልዕክቱ ‹‹ልቡን እያሳተ›› ብሎ የተናገረው አጋንንት ልብ ላይ ቁጭ ብሎ እኛን እየመሰለ እንደሚያስተን ያሳየናል፡፡ /ያዕ 1÷26/
ነብዩ ሙሴ የፈርኦንን ታሪክ በጻፈልን በዘጸአት ላይ አጋንንት ምን ያህል ፈርኦንን ልቡ ላይ ቁጭ ብሎ ልቡን እያደነደነ፣ለቅስፈት ሞት እያጀገነ እንደተጫወተበት ‹‹ልቡን አደነደነ፣እግዚአብሔርም እንደተናገረ አልሰማቸውም›› በማለት ጽፎልናል፡፡ /ዘጸ 8÷15/ በዚሁ ምዕራፍ ላይ ፈርኦን ‹‹ልቡን አጸና›› ተብሏል፡፡
በጌርጌሴኖን አከባቢ ለረጅም ዓመታት ልብስ ሳይለብስ በመቃብር ቤት በሌጊዎን አጋንንት ይሰቃይ የነበረው ሰው ልቡ ስለተሰወረ የሚያደርገውን ስለማያውቅ በአከባቢው እጅግ ይፈራ ነበር፡፡ ጌታ ከፈወሰው በኃላም ከጌታችን እግር ስር ቁጭ ብሎም ‹‹ፈሩ›› የተባለው ልብን ስቶ የሚያደርገውን ስለማያውቅ ነው፡፡ /ሉቃ 8÷35/
አጋንንት ልባችን ላይ ተቀምጦ የማንፈለወገውን እንድንሰራ፣ያልፈለግነውን እንድናስብ ያደርገናል፡፡ ስለዚህ አጋንንት ልባችን ላይ ከተቀመጠ ሰፊውንና ማዕከላዊውን ይዞታ ስለያዘ እኛ ማንፈልገውን ግን እርሱ የሚፈልገወን ያደርጋል፡፡
አንዳንዴ ጥድፍ ብለን አንድ ነገር ከወሰንን በኃላ ለጊዜው ጥሩ ይመስለናል ግን ካለፈ በኃላ ጉዳቱ ግልጥ ይልልናል፤ያኔ ትርፉ አጉል ጸጸት ብቻ ነው፡፡ ብዙዎች በትዳር፣በእጮኝነት ጊዜ አጋንንቱ ለመለያት ካሰበ የአንዱን ልብ ማደንደን እንቢኝ ያስብልና መለያቱ ከመጣ በኃላ በውሳኔያችን እንድንጸጸት ያደርገናል፡፡
አጋንንት ልባችን ውስጥ ከገባ የፈለገውን የማድርግ ኃይል አለው፡፡ አንድ መረሳት የሌለበት ነገር ዛሬ ዛሬ የልብ ህመምተኛው በዝቷል፡፡ እግዚአብሔር በሌለበት ልብ ውስጥ አጋንንት እየገባበት መልኩን በመቀየር የልብ ህመም በመምሰል ያሰቃያል ለሞትም ይዳርጋል፡፡
5ኛ/ የአየር አጋንንት በጸሎት ሰዓት ንስሐ የገባንበትን፣የረሳነውን ኃጢአት በማስታወስ መውቀስ፣በጥርጥ እና በጭንቀት መፈተን ………
ይቀጥላል …….
የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃነት፣የህጻኑ ቂርቆስ የቅድስት ኢየሉጣ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡
አንብበው ሲጨርሱ በችግሩ ለሚሰቃዩት ሁሉ ሼር ማድረጉን እንዳይረሱ!
ሐምሌ 19/11/2010 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የተወደዳችሁ የተዋህዶ ልጆ በጠየቃችሁን መሰረት ሰለ "መቁጠሪያ ሞስጢረ" እነሆ ብለናል #ሼር በማረግ እንደተለመደው ለሌሎች እናካፍል ።
♦መቁጠሪያ♦
♦በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያናችን ከሚገኙና ሰይጣን ዲያብሎስን ከምንዋጋበት መሣሪያዎቻችን መካከል አንዱ መቁጠሪያ ነው : :
" በአንተ ጠላቶቻችን እንወጋቸዋለን በስምህም በላያችን የቆሙትን
እናዋርዳቸዋለን " መዝ.43 (44) : 5
መቁጠሪያ ለሰው ልጅ በጣም ከሚያስፈልጉት በፀሎት ጊዚያት ውስጥ አንዱ ነው ምክንያቱም ከዛሬ መቶ ሃያ አመት በፊት የነበሩ አባቶች በመቁጥሪያ ፀሎት በመፀለይ ሀይል አጋንንትን በመቀጥቀጥ ድል ያድርጉ ሥጋቸውንም ለነብሳቸው ያስገዙት ነበር ፡፡ አሁን ግን ተረስቶ መቁጠሪያ ለቆራቢ ነው መቁጠሪያ ለሞለክሴ ለበቁ ሰዎች እየተባለ ይገኞል ይህ ስተት ነው ፡፡
♦በመፅሐፍ ቅዱስ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9 : 27
" ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን
እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ። " እየጎሰምሁ ሲል እየቀጠቀጥኩ ማለቱ ግልፅ
ነው ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ሰይጣን ነበረበትና እንዲህም በማለት ተናግሮ ነበር
" ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው።"
ስለዚህ ነገር ከእኔ እንዲለይ ሦስት ጊዜ ጌታን ለመንሁ።"
(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12 7:8)
(1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 2:18) " ጳውሎስም አንድና ሁለት ጊዜ፥ ሰይጣን ግን አዘገየን።"
ቅዱስ ጳውሎስ በውስጡ ያደረውን ሰይጣን በመቀጥቀጥም
ጭምር እንደሚዋጋው ተናግሯል ፡፡
በቤተክርስቲያናችን ካህናትና በንሰሐ አባቶቻቸንና በተባረከ መቁጠሪያ
በእግዚአብሔር አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ በእመቤታችን ድንግል
ማርያም በቅዱሳን መላእክት ስም እየጠራን በውስጤ ያደርክ ክፉ መንፈስ
ተቃጠል እያልን ሁሉቱ ትከሻዎቻችን : መሀል ጀርባችንን እንዲሁም ሕመም የሚሰማን ቦታ ስንቀጠቅጥ
- የማቃጠል ወይም የመለብለብ የመውረር ወይም የመንዘር
- የመብላት ወይም የማሳከክ በሰውነት ክፍላችን ውስጥ የመዘዋወር
ስሜት ና እንደ ድንጋይ በድን መሆን እንዲሁም
- ጭንቀላታችንን ሁለት ከፍሎ የራስ ምታት ዓይነት ሰሜት ከተሰማን
ሰይጣን በውስጣችን አድፍጦል ማለት ነው : : ስለሆነም የእግዚአብሔርን
መንገድ ይዘን
✞ እየፆምን
✞ እየጸለይን እየተንበረከክን
✞ እየሰገድን
✞ ሥጋና ደሙን እየወስደን ከላይ እንደተገለጸው በመቁጠሪያችን
እየቀጠቀጥን ክፉ መንፈሶችን ማንበርከክ በመጣል የእግዚአብሔር ልጆች መሆን እንችላለን ከእግዚአብሔር የተሰጠን የተሥፋው ሀይል እንዲህ ይላል ::
"እንሆ እባቡንና ጊንጡን ተረግጡ ዘንድ በጠላትም ሀይል ሁሉ ላይ
ሥልጣን ሰጥቻችዋለሁ የሚጐዳችሁም ምንም የለም :: " ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ሰለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።" ሉቃስ 10 : 19 -20
ሁሌ ቤተ ክርስቲያን መመላለስ ሳይሆን ስንሄድ እና ቤታችን ምን ማድረግ እንዳለብን ማወቅ
ሁሌ በርትተን በደስታ እንስገግ የአምልኮ ስግደት ለቅድስትሥላሴ ብቻ ሁሌ የሚሰገድ::
1.አምልኮ ስግደት
ለአብ እሰግዳለሁ:
ለወልድ እሰግዳለሁ:
ለመንፈ ስቅዱስ እሰግዳለሁ:
ምስጋና ይሁን ለአብ:
ምስጋና ይሁን ለወልድ:
ምስጋና ይሁን ለመንፈስ ቅዱስ:
በረከቱን ለሰጠን:
ሀይሉን ላበዛልን:
በዚህ ሰአት ላቆመን:
በቸርነቱ መንገድ ለመራን:
በዚህ ሰእት በጸጋ ለጠበቀን:
በብርሀኑ ሐይል ለመራኸን:
ላንተ ክብርምስጋና ይግባው:
ሐሌሉያ ለአብ:
ሐሌሉያ ለወልድ:
ሐሌሉያ ለመንፈስ ቅዱስ:
ቅዱስ እግዚአብሔር:
ቅዱስ ሐያል:
ቅዱስ ሕያው:
ቅዱስ ኤልሻዳይ:
ቅዱስ አዶናይ:
ቅዱስ ያህዌ:
ቅዱስ ፀባኦት:
ቅዱስ ኢየሱስ:
ቅዱስ ክርስቶስ:
ቅዱስ አማኑኤል:
የድንግል ማርያም ልጅ:
ክብር ምስጋና ይግባው::እያልን እንሰግዳለን::
2. የፀጋ ስግደት
ቅዱስ ገብርኤል ፀጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ እንዳላት እኛም እንዲሁ እያልን ለእመቤታችን የፀጋ ስግደት እንሰግዳለን::
ለድንግል ማርያም ክብር ምስጋና ግገባሻል እያልን እንሰግዳለን::
3. የንስሐ ስግደት
ኪሪያላይሶን ኢየሱስ:
ኪሪያላይሶን ክርስቶስ:
ኪሪያላይሶን አማኑኤል:
እቤቱ ክርስቶስ ሆይ ማረን:
አቤቱ አምላክ ሆይ ማረን:
አቤቱ መድሀኒአለም ሆይ ማረን:
አቤቱ የድንግል ማርያምልጅ ሆይ ማረን:: እያልንእንሰግዳለን::
4. የክብር ስግደት
ለቅዱሳን መላእክት ለቅዱሳን ጻድቃን ለሰማእታተ የሚሰገድ
ኦ: ቅዱስሚካኤል: ለቅዱስሚካኤል እሰግዳለው በቅዱስሚካኤል እሰግዳለው
ኦ: ቅዱስገብርኤል.... እያልን የአክብሮት ስግደት እንሰግዳለን::
---------------------------------------
ክብረ በአል ከሆነ
ስብአት ለአብ:
ስብአት ለወልድ:
ስብአት ለመንፈስ ቅዱስ:
ቅዱስ እግዚአብሔር:
ቅዱስ ሀያል:
ቅዱስ ህያው:
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ::እያልን እንሰግዳለን::
------------------------------------------------------------------
እርኩስ መንፈስ እየተቃወመ ካስቸገረ በመቁጠርያ እየቀጠቀጡ
እግዚኦ መአር ነክርስቶስ
በእንተ ማርያም መአርነ ክርስቶስ
ኪሪያላይሶን እየሱስ
ኪሪያላይሶን ክርስቶስ
በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
የዲያቢሎስን ሰራዊት በሰበረው በሀያሉ በቅዱስሚካኤል ስም
ለቅድስት ድንግል ማርያም ብስራትን ባበሰረው በቅዱስ ገብርኤል ስም
ውስጤ የተደበቅክ ጠላቴ ነርቭ የሆንከው በሽታ የሆንከው
ቅዠት የሆንከው ተስፋመቁረጥ የሆንከው መንፈስ ገስፅሃለው
በገንዘቤ ላይ በባህሪዬ ላይ አዛዥ አትሆንም
ይህ መንገድህ ተሽሯል ተሰርዟል
በመቁጠርያ እየቀጠቀጡ በድንግልማርያም ስም ወደግባርውጣና ታሰር ይባላል::
ምንጭ "በማለዳ መያ`ዝ መጽሐፍ''በመልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ
ለአባታችችን ለመልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ እድሜና ጤና ይለግስልን አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ይቆየን