for-coder
432 subscribers
102 photos
54 videos
23 files
138 links
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
በAI ዘርፍ ተስፋ እና ስጋትን ይበልጥ ያጫረው Veo 3 . . . ለዚህ ዝግጁ ነን ?

ግዙፉ የአለማችን የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጎግል Veo 3 የተሰኘ ቪዲዮ የሚሰራ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ከሰሞኑ ከለቀቀ በኋላ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል።

የቴክኖሎጂ ኩባንያው አዲስ ያስተዋወቀው Veo-3 በራሱ ቪዲዮ ሰርቶ ድምፅን ከቪዲዮው ጋር የሚያዋህድ ሲሆን ከዚህ በፊት ከነበሩት በጥራት ከፍ ያለ ነው።

መተግበሪያው ከOPEN AI ምርት ከሆነው sora ለየት የሚያደርገው በሰዎች መካከል የሚደረጉትን ንግግሮች እውነት እስኪመስል ድረስ ድምፅና ምስልን በማቀናበር ማቅረቡ ነው።

በዚህ የጎግል አዲሱ ቴክኖሎጂ የተሰሩ ቪዲዮዎች (ከላይ እንዳለው አይነት) ከእውነተኛ ቪዲዮች ለመለየት በሚያዳግት ደረጃ የቀረቡ ሲሆን የቋንቋ አማራጩም ከዚህ ቀደም ከነበሩት እጅጉን የሚሻል ነው ተብሏል።

አሁን ላይ መተግበሪያውን ለመጠቀም የ249.9 ዶላር ወርሃዊ ክፍያ ያስፈልጋል ተብሏል።

በርካታ በVeo 3 የተሰሩ ቪዲዮዎች ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲለቀቁ አብዛኛው ሰው ከእውነተኛ ቪዲዮዎች ለመለየት ሲቸገር ተስተውሏል።

ቴክኖሎጂው ይፋ በሆነ በጥቂት ቀናት በአማርኛ ቋንቋ ተሰርተው የተለቀቁ ቪዲዮዎችን እንኳን ብንመለከት በቀላሉ ለመለየት አስቸጋሪ ሆኗል። ከዚህ ቀደም ድምጽ ላይ የነበሩ ክፍተቶች በአጭር ጊዜ ተሻሽለው እንደቀረቡ ተነግሯል።

ጎግል በተጨማሪ FLOW የተሰኘ የተለያዩ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መተግበሪያዎችን ያካተተ እና ፊልም ሰሪዎች በፈለጉት መንገድ ፊልማቸውን እንዲሰሩ የሚያግዝ የፊልም መስሪያ መተግበሪያንም ይፋ አድርጓል።

ይህም በዘርፉ ስጋትንም ተስፋንም ይዞ መምጣቱ ተነግሯል።

ተጠቃሚዎች በVeo 3 መስራት የሚፈልጉትን ነገር በፅሁፍ እንደሚያስገቡ የተነገረ ሲሆን መተግበሪያው ከተሰጠው ፅሁፍ በመነሳት እውነተኛ የሚመስል ቪዲዮን ከሰራ በኋላ ትክክለኛ የሚመስሉ ድምፆችን በመጨመር ለተጠቃሚዎች ያቀርባል።

ተጠቃሚዎች የቀረበላቸውን ቪዲዮ ካዩ በኋላ FLOW የተሰኘውን ሌላ የጎግል መተግበሪያ በመጠቀም የካሜራ አንግልና የገፀ ባህሪያትን እንቅስቃሴ መቀየር ይችላሉ ተብሏል።

ወጪን ከመቀነስ አንፃር በ500 ሺህ ዶላር ሊሰራ የሚችልን የመድሃኒት ማስታወቂያ በVeo 3 ከ500 ዶላር ባነሰ ገንዘብ በአንድ ቀን ውስጥ መስራት እንደተቻለ ተሰምቷል።

አንዳንድ ሰዎች ስለ አዲሱ ቴክኖሎጂ " ፈጠራን ይቀንሳል " በሚል ሃሳባቸውን እያንፀባረቁ ሲሆን ተመልካቾች ደግሞ እውነተኛ ቪዲዮ አለመሆናቸውን ለመለየት መቸገራቸው ሌላ ፈተና ነው ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውም ከCNBC እና AXIOS ነው ያሰባሰበው።

Video Credit : Ehud Ai Studio

#AI #Google #Gemini

Via @TikvahethMagazine