የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጽሑፎች በPDF እና በድምጽ
2.15K subscribers
51 photos
2 videos
26 files
54 links
እዚህ ቻናል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት የሚያንጸባርቁ ጽሑፎች ይለቀቃሉ
Download Telegram
ዐብይ ጾም

ዐብይ ጾም ማለት ምን ማለት ነው?

ዐብይ ጾም ለምን ዐቢይ ተባለ?
ጾም ማለት ፡- ለዘላዓለም ሁሉንም ሕዋሳት ከኃጢአት መከልከል፣ለተሰነ
ጊዜ እህል ከመብላት ዉሃ ከመጠጣት መታቀብ ወይም ለተወሰኑ ወራት
ከጥሉላት ከስጋ ፣ከወተት፣ከቅቤ፣ከእንቁላል፣በአጠቃላይ ከእንሰሳት
ዉጤት መከልከል ነው።
+
#የጾም_ጥቅም ፦ የሥጋ ምኞትን የምታጠፋ የነፍስን ቁስል የምታደርቅ
ለጎልማሶችም ጸጥታንና እርጋታን የምታስተምር ከእንሰሳዊ ግብር ጠባይ
የምትከለክልና ሰው መላእክትን መስሎ የሚኖርባት ደገኛ ሥርዓት ነች፡፡

በብሉይ ኪዳን ብዙ ሰዎች በጾም ተጠቅመዋል እግዚአብሔር የጾምን
ሥርዐት የደነገገው ገና ከጥዋቱ አዳምን በፈጠረበት ወቅት ነው ፡፡ እጸ
በለስን አትብላ ማለት ትዕዛዝ ቢሆንም ትዕዛዙ ግን የጾም ትዕዛዝ ነው
አዳምና ሔዋን ይህን የጾም ሥርዐት በመሻር እጸ በለስን በልተው
በመገኘታቸው ምን እንደደረሰባቸው በቅዱስ መጽሐፍ ላይ የምና ነበው
ነው፡፡
በጾም የተጠቀሙ ቅዱሳን አበው ጾምን የጸሎት እናት የእንባ ምንጭ
የጽድቅ መሠረት ደገኛ ሥርዐት በማለት ይገልጻሉ፡፡
ጾም በብሉይ ኪዳን ስንመለከት፦
በሕዝብ ላይ የተቃጣውን መከራ ለማቅለል ተጠቅመውበታል መጽ ኢያሱ
7÷6 -9፣ መጽ አስቴር 4÷16 ፣ትንቢተ ዮናስ 1 ፣ መ.ሳሙኤል ካል
12÷17 ዘዳ 9÷9 -18፣ትንቢተ ኢዩኤል 2÷14 ፣መዝ 34(35) ÷ 13
ትን.ዳን 10÷2 መዝ 108÷ 24
ጾም በሐዲስ ኪዳን
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሥራው ሁሉ መጀመሪያ ያደረገው ጾምን
ስለሆነ መሥራቹ ክርስቶስ ነው በሐዲስ ኪዳን ጾም የታዘዘ ስለመሆኑ
የሚከተሉትን ጥቅሶች እንመለከታለን
ማር 2 ÷20 ፣ማር 9÷29 ፣ማቴ 6÷16 ፣ ሉቃ 6÷21 ፣ሐዋ 13÷3
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለጾም ሥርዐትና ደንብ
አውጥታለች በዓመት ውስጥ ሰባት የዓዋጅ አጽዋማት እንዳሉና
ማንኛውም ክርስቲያን እንኝህን አጽዋማት እንዲጾም ታዛለች እነዚህም
አጽዋማት
 ዐቢይ ጾም
ጾመ ሐዋርያት
ጾመ ስብከት (ጾመ ነብያት)
 ጸመ ፍልሰታ
ጾመ ድኅነት
 ጾም ነነዌ
ጾመ ገሃድ
ከነዚህ አጽዋማት ውስጥ የምንመለከተው ዐቢይ ጾም ነው።
ዐቢይ ጾም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሥርዓት መሰረት የአዋጅ
ፆም የሚባሉ ሰባት አፅዋማት አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከልም በጊዜው ረዥም
ደግሞም በስያሜው የተለየውን አብይ ጾምን እንመ
1. ዐብይ ጾም ማለት ምን ማለት ነው
በመጀመሪያ ‹‹ዐቢይ›› የሚለው ቃል ‹‹አበየ›› ከሚለው የግዕዝ ግስ
የተገኘ ነው፡፡
ትርጓሜውም ‹‹ከፍ አለ›› ማለት ነው፡፡
2. ዐብይ ጾም ለምን ዐቢይ ተባለ
ዐብይ ጾም ዐብይ የተባለበት ሦስት አበይት ምክንያቶች እንመለከታለን
2.1. ጌታቸን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ የጾመው ሥለሆነ ማቴ
4፡2-3
2.2. በቀኑ ቁጥር ከሌሎች አጽዋማት ስለ ሚበልጥ የቀኑ ብዛትም 55
ቀን ነው፡፡
2.3. ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች እንዲሁም ደግሞ ሶስቱ ርዕሰ ኃጢአት
የሚባሉት ትዕቢት፣ስስት ፍቅረ ነዋይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ድል
የተመቱበት ስለሆነ ይህ ጾም አብይ (ታላቅ) ተብሏል፡፡ ማቴ 4፡3-11
የዐብይ ጾም የተለያየ ስያሜዎች
ዐብይ ጾም ከቀኑ ርዝማኔ በተጨማሪ ጾሙ የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡
+
°#ጾመ ሁዳዴ፡- #ሁዳድ ማለት ሠፊ (ትልቅ) የእርሻ ቦታ ማለት ነው፡፡ ይህም ጾም ደግሞ በቀኑ ብዛት ትልቅ (ሠፊ) በመሆኑ የሁዳዴ ጾም ይባላል፡፡
°#የካሳ_ጾም፡- እንዲህ የተባለበት ምክንያቱ ደግሞ አዳምና ሔዋን በዲያቢሎስ ግዞት እያሉ ክርስቶስ ደሙን በመክፈል (በመካስ) ነጻ ስላውጣቸው የካሳ ጾም ተብሎሏል
°#የድል_ጾም ፡-ይህም ደግሞ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ጾም ሰይጣንን ድል ያደረገበት በመሆኑ የድል ጾም ተብሏል፡፡
°#ጾም_አስተምህሮ፡- ይህ ጾም ‹‹ጾም አስተምህሮ›› የተባለበት ምክንያት ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማስተማር የጾመው በመሆኑ ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ የተለያዪ ስያሜዎች አሉት ‹‹የመሸጋገሪያ ጾም፣ ‹‹የስራ መጀመሪያ ጾም ››
+
#የዐብይ_ጾም_ሳምንታት
ዐብይ ጾም በያዘው በ55 ቀኑ ውስጥ 7 ቅዳሜና 8 እሁዶቸን ይዟል የእነዚህ የስምንቱ እሁዶች የተለያየ ስያሜ አላቸው፡፡ ስያሜአቸውንም የሰጣቸው የቤተክርስቲያናችን የዜማው ሊቅ የሆነው ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡
1፣ ዘወረደ
2፣ ቅድስት
3፣ ምኩራብ
5፣ ደብረዘይት
6፣ ገብረ ሔር
7፣ ኒቆዲሞስ
4፣ መጻጉዕ
8፣ ሆሳዕና
+++

ቀደምት ሊቃውንት ሁለት ዓይን የተሰጠን በአንዱ የራሳችን በሌላው
የሌላውን ለማየት ነው፡፡ ሁለት ጆሮ የተሰጠን በአንዱ የራሳችንን
በሌላው የሌላውን ለመስማት ነው፡፡ ሁለት እጅ የተሰጠን በአንዱ
ለመስጠት በሌላው ለመቀበል ነው፡፡ ሁለት እግር የተሰጠን በአንዱ
ወደራሳችን በሌላው ወደ ሌላው ለመሄድ ነው ይሉ ነበር፡፡
፳፩ ፳፩ ፳፩ ፳፩ ፳፩
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የሲኦል ደጆች አይችሏትም
ቤተክርስቲያን አትታደስም!
የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም
እንማልዳለን!
(መጽሐፈ ሚስጢር)
የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን
መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣
የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ
ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን!!!
†† † † ††
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!!

†† † † ††
ከዋክብት የሚያመሰግኑት
በስማቸውም የሚጠራቸው:
የፀጋው ብዛት የማይታወቅ
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለሐዋሪያት
እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን እንደገለጽክላቸው ለእኛም
ግለጽልን። አሜን አሜን አሜን!!!
†† † † ††
ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
ወ ለ ወ ላ ዲ ቱ ድ ን ግ ል
ወ ለ መ ስ ቀ ሉ ክ ቡ ር
https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
#​​ጾመ_ፍልሰታ (ክፍል ፩)

📌“ፍልሰታ” የሚለው ቃል የሚገልጸው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለቆ መሔድን መሰደድን መፍለስን ያመለክታል። ይህም የእመቤታችንን ሥጋ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መፍለሱን በኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረበት መነሣቱን ለማመልከት ይነገራል።

📌ጾመ ፍልሰታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፷፬ ዓመት በዚች ምድር ኖራ እንደ አንድ ልጇ መሞቷን መነሣቷንና ማረጓን ያዩ ዘንድ ሐዋርያት የጾሙት ጾም ነው። ጾሙ ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ነሐሴ ፲፮ ቀን ሲጾም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ከደነገገቻቸው ሰባቱ አጽዋማትም አንዱ ነው። ፍትሐ ነገስትአንቀጽ፲፭
ሃይማኖታዊ መሠረት
እመቤታችን ከአባቷ ከቅዱስ ኢያቄም እና ከእናቷ ከቅድስት ሐና ነሐሴ ፯ ቀን ተጸንሳ ግንቦት ፩ ቀን በአድባረ በሊባኖስ ተወልዳለች። “እምሊባኖስ ትወጽዕ መርዓት ፦ ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች “እንደተባለ ። እመቤታችን በእናት አባቷ ቤት ሦስት ዓመት፤ በቤተ መቅደስ ዐሥራ ሁለት ዓመት፤ ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ፡ ከዮሐንስ ወልደዘብዴዎስ ዘንድ ዐሥራ አራት ዓመት ከዘጠኝ ወር ቆይታ በ ፷፬ ዓመት ዕድሜዋ በ፵፱ ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። የእመቤታችንን ስም የሚገልጹ የውዳሴ ጽሑፎችም በእድሜዋ ልክ ተደርሰዋል። ለምሳሌ የውዳሴ ማርያም ቁጥር ፷፬ ነው፤ የመልክአ ማርያም ቁጥርም ፷፬ ነው።

#ቅዱሳን_ሐዋርያት_እና_አስከሬኗ ባረፈች ጊዜ ቅዱሳን ሐዋርያት ተሰባስበው አስከሬኗን ይዘው ወደ ጌቴሴማኒ መቃብር ለማሳረፍ ሲሄዱ አይሁድ ለተንኮል አያርፉምና ተተናኮሏቸው። ቀድሞ ልጇ ሞቶ ተነሣ፣ ዐረገ እያሉ ሲያስቸግሩን ና ሲያውኩን ይኖራሉ: አሁን ደግሞ እሷም ተነሣች፣ ዐረገች ሊሉ አይደል በማለት አይሁድ ተሰባስበው አስከሬኗን በእሳት እናቃጥላት ብለው ተነሱ፡፡ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ተራምዶ አጎበሩን ጨበጠው መልአክ ሁለት እጁን በሰይፍ ቀጣው ከአጎበሩ ተንጠልጥሎ ቀረ፡፡ የእመቤታችንንም አስከሬን ነጥቆ ከሐዋርያው ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አኑሯቸዋል ። ከዚያ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት ሥጋዋን አግኝተው ይቀብሩት ዘንድ በዐረፈች በስምንተኛው ወር ከነሐሴ ፩ ጀምሮ እስከ ነሐሴ ፲፬ ቀን ድረስ ሁለት ሱባዔ ይዘው በዐሥራ አራተኛው ቀን ሥጋዋን ከጌታ ተቀብለው በጸሎትና በምህላ በፍጹም ደስታ በጌቴሰማኔ ዐሳረፉት ። በ ሦስተኛውም ቀን ተነስታ ስታርግ ከሰዱቃውያን ወገን የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ አያት። እርሱም በቀብር ሥርዓቱ ጊዜም አልነበረም። ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ ሲመጣ ስታርግ አገኛት ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ ይላል፡፡ ሊያስተምር ወደ ሌላ ቦታ ሂዶ ነበርና። በዚያም ሲያስተምር ሰንብቶ በደመና ተጭኖ ሲመጣ ያገኛታል። ትንሣኤዋን ከርሱ ሰውራ ያደረገች መስሎት አዝኖ «ቀድሞ የልጅሽን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንቺን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁን ?» ብሎ ቢያዝንባት እመቤታችንም አይዞህ አትዘን እነዚያ ትንሣኤየን ዕርገቴንም አላዩም አንተ አይተሃል ተነሣች ዐረገች ብለህ ንገራቸው ብላ የያዘችውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው፡፡
ይቀጥላል......

🔸# ዲ/ን ብስራተማርያም
#​​ጾመ_ፍልሰታ (ክፍል ፪)

#ትንሣኤና_ዕርገቷ
ከርሱ በቀር ማንንም ትንሣኤዋን እንዳላየ ነግራ አጽናናችው። ለሌሎቹ ሐዋርያትም እንዲነግራቸው ለምልክትም (ለምስክርም እንዲሆነው ሰበኗን ) መግነዟን ሰጥታው ዐረገች። +ቶማስም ኢየሩሳሌም ደርሶ ሐዋርያትን «የእመቤታችን ነገርስ እንደምን ሆነ?» ሲል ቢጠይቅ «አግኝተን ቀበርናት ዕኮ» አሉት። እርሱ ምስጢሩን አዉቆ ደብቆ «ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተው ይህ ነገር አይመስለኝም » እንዴት ይሆናል ? አይደረግም ይላቸዋል። ጴጥሮስም አንተ እንጂ ልማድህ ነው አንተ ብቻ ተጠራጥረህ አትቀርም አንተ እየተጠራጠርክ ሰውን ሁሉ ስታጠራጥር ትኖራለህ አለው፡፡ እርሱም የያዘውን ያውቃልና ጸጥ ብሎ ይሰማቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስ ተቆጥቶ ሄዶ መቃበሩን ቢከፍተው አጣት ደንግጾ ቆመ «አታምኑኝም ብዬ እንጂ እመቤታችንስ ተነሣች ዐረገች አላቸው » ሁኔታውንም ተረከላቸውና ለምስክር ይሁንህ ብላ የሰጠችውን ሰበኗን አሳያቸው ሰጣቸውም። ከዚህ በኋላ ለበረከት ይሆናቸው ዘንድ ሰበኑን ተካፍለው ወደ የአህጉረ ስብከታቸው ሄዱ። ዛሬ በቅዳሴ ጊዜ ዲያቆኑ በሚይዘው የመጾር መስቀል ላይ በሁለት ቀዳዳዎች አልፎ ተጠምጥሞ የምናየው መቀነት መሰል ጨርቅ የዚያ ሰበን ምሳሌ ነው።
📌በዓመቱ ሐዋርያት ከያሉበት ተሰባስበው ቶማስ ዕርገትሽን አይቶ እኛስ እንዴት ይቀርብናል ብለው ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምርው ሱባዔ ቢይዙ ከሁለት ሱባዔ በኋላ እንደገና ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ለማየት በቅተዋል። ሐዋርያዊት፤ ጥንታዊት የሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናም ምእመኖቿ ከእመቤታችን በረከትን እንዲያገኙ ይጾሙ ዘንድ ይህን ሐዋርያት የጾሙትን ጾም እንዲጾሙ አዉጃለች። ምእመናንም በተለየ መልኩ በጾም በጸሎት በሱባዔ ጽሙድ ሆነው ይህን ወቅት ያሳልፋሉ።
የእመቤታችን ትንሣኤ ድንገት እንደእንግዳ ደራሽ እንደ ውኃፈሳሽ የተደረገ ሳይሆን በቅዱሳት መጻሕፍት በትንቢተ ነቢያት የተገለጸ ነው። ነቢዩ ዳዊት በመዝሙር ፻፴፩ ቁጥር ፲ ላይ « ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅደስከ፤ አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦትም» ይላል። በዚህም ምእመናንን ወደ ምታሳርፍበት ወደ መንግሥተ ሰማያት የመቅደስህ ታቦት ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ አለ። ታቦት የጽላት ማደርያ እንደሆነ ሁሉ እመቤታችንም ለክርስቶስ ማደርያ በመሆኗ አማናዊት ታቦት ትባላለች።

🔖ንጉስ ሰሎሞንም በመኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፲ ላይ «ውዴ እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፤ ወዳጄ ሆይ ተነሽ፡ ውበቴ ሆይ ነይ» ብሏል። እዚህ ላይ «ወዳጄ …ዉበቴ»” የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት ። ክቡር ዳዊት መዝሙር ፵፬ ቁጥር ፱ ላይ « ወትቀውም ንግስት በየማንከ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኍብርት ፤ በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች» እንደሚል ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛነቱን ከፈጸመ በኋላ ወደ ቀደመ ክብሩ እንደ ዐረገ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በቀኙ ትቀመጥ ዘንድ «ተነሽ ነይ» አላት ። እንግዲህ ይህንና የመሰለዉን ሁሉ ይዘን የእናታችንን ዕረፍቷን ትንሣኤዋን እንዘክራለን እንመሰክራለንም።
ጾሙን አጋንንትን ድል የምንነሳበትና የበረከት ያድርግልን !
ምንጭ ÷ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘእሑድ

🔸# ዲ/ን ብስራተማርያም