የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጽሑፎች በPDF እና በድምጽ
2.16K subscribers
51 photos
2 videos
26 files
54 links
እዚህ ቻናል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት የሚያንጸባርቁ ጽሑፎች ይለቀቃሉ
Download Telegram
ጊንጥ አና ጊንጠኞች!!
//ዳንኤል ክብረት//

ብዙ ጊዜ ጊንጥ የሚለውን ቃል ስሰማ ብዙም ትኩረት አልሰጠውም ነበር ዛሬ ግን ጊንጥ አሪፍ ነገር አስተማረኝ፡፡ ይህንን እንድል ያስገደደኝ የዛሬው ፅሁፌ መነሻ የሆነኝ አጭር ታሪክ ነው ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡
አንድ ሽማግሌ ውሃ ውስጥ ሊሰምጥ ያለ ጊንጥ ያዩና ሊያድኑት ይፈልጋሉ፡፡ ከዚያም ጊንጡን ከውሃው ለማውጣት እጃቸውን ዘርግተው አነሱት በዚህ ጊዜ ጊንጡ ነደፋቸው እሳቸውም ደንግጠው ለቀቁት ጊንጡም ተመልሶ ወደውሃው ገባ፡፡ ሽማግሌው አሁንም የጊንጡን ውሃ ውስጥ መስመጥ ተመልክተው ድጋሚ እጃቸውን ለእርዳታ ዘረጉለት አሁንም በድጋሚ ጊንጡ ነደፋቸው ሲለቁት አሁንም ውሃ ውስጥ ገባ፡፡ ይህንን የሽማግሌውን ትእይንት የሚመለከት አንድ ሰው ወደ ሽማግሌው ጠጋ ይልና ‹‹ይህ እኮ ክፉ ፍጥረት ነው ጊንጥ እሱን ለማዳን ሲሉ እርሶ እየተጎዱ እኮ ነው›› አላቸው።
ሽማግሌውም እንዲህ ሲሉ መለሱ ‹‹የጊንጡ ተፈጥሮ መናደፍ ነው፡ የኔ ተፈጥሮ ደግሞ መርዳትና ማገዝ ነው፡ ስለዚህ ተፈጥሮዬ ክፉ አደለምና ጊንጡን ከመርዳት አላቋርጥም አረዳዴን ግን አስተካክላለሁ›› አሉና ጥቂት አሰብ አድርገው ተነስተው ከዛፉ ላይ አንድ ቅጠል ቀንጥሰው በቅጠሉ ጊንጡን ይዘው አወጡትና ህይወቱን አተረፉለት፡፡
እኛም እንዲህ ነን ሰውን ለመርዳት ስንሄድ ብዙ ጊንጦች ይነድፉናል፡ ደግ ልናደርግ ስንጓዝ ብዙ እንቅፋቶች ይመቱናል፡፡ ነገር ግን ጊንጡ እንዳይነድፈን እናደርጋለን እንጂ እንቅፋቱ እንዳይመታን እንጠነቀቃለን እንጂ እንዴት ደግ ማድረግ እናቆማለን ???
አንተም አንቺም ሁላችንም እዚህ ምድር ላይ ያለን ሰዎች በሙሉ ስንፈጠር ደግና መልካም ነን፡፡ ግን ሰውን ክፉ የሚያደርገው ተፈጥሮው ሳይሆን መጥፎ አጋጣሚ ነው፡፡ ለዛ እኮ ነው በነዚህ ጊንጦች ስለተነደፍን መልካም ለማድረግ ቅስቀሳ በጎ ለመስራት ማጣራት መጠራጠር በሌላ አይን መመልከት ጀመርን፡፡
እስኪ የዛሬዋን አዲስ ቀናችንን እንዲህ ብንውላትስ ሰው ስንረዳ እንደጊንጥ በሚሆኑ ሰዎች ተሸንፈን መልካም ከማድረግ ከምንቆጠብ የምንረዳበትን መንገድ ለይተን ብናውቅስ፡፡ በነገራችን ላይ ለሰው በጎ ማድረግ ሲባል በገንዘብ ብቻ ይመስለናል አይደለም በየቤቱ ገንዘብ ኖሮት ሰው የናፈቀው ህሊና አለ ስለዚህ አንዳንዶች ፈገግታችንን አንዳንዶች እኛነታችንን አንዳንዶች መሰማትን ይፈልጋሉና በየደረስንበት ለመልካም ነገር ጊንጥ ፈርተን እምቢ እንዳንል፡፡
መልካም የምታደርጉ ሁሉ ግን ጊንጡንም ቢሆን ከማዳን አትቦዝኑ። https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
ጴጥሮስን ለታላቅ ንስሓ የቀሰቀሰው የዶሮ ጩኸት ነበር ... ‹የዶሮ ጩኸት ጴጥሮስን ለንስሓ አበቃው› የሚለው ታሪክ ከዶሮ ጩኸት አልፎ እልፍ ሰባኪያን ‹ንስሓ ግቡ› እያሉ ሲጮኹ እየሰማን ምንም ለማይመስለን ለእኛ ለልበ ደንዳኖቹ መልእክቱ ምን ይሆን? የዶሮዎቹን ጩኸት ሰምቶ በመመለስ ፈንታ የዶሮዎቹን የአጯጯህ ስልት እያወዳደርን ሰባኪያን ለምናማርጥ ለእኛ መልእክቱ በእርግጥ ምን ይሆን?

በእርግጥ የዶሮውም እድል የሚያስቀና ነው፡፡ አንድ ጊዜ ጮኾ የወደቀውን ጴጥሮስ እንዲነሣ መቀስቀስ መቻሉ የታደለ ሰባኪ ያደርገዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ስንጮኽ ውለን አንድ ሰው ለንስሓ ማብቃት ላልቻልን ሰባኪያን ይህ ዶሮ ምንኛ የሚያስቀና ነው? ለነገሩ በልማዱ ዶሮ ጮኾ ሌሎቹን ከማስነሣቱ በፊት እሱ ተነሥቶ ክንፉን እያርገበገበ ከፍ ከፍ ይላል፡፡ እኛ ግን ራሳችን በኃጢአት ተኝተን ሌላውን ለንስሓ ለመቀስቀስ የምንሞክር እንቅልፋም ዶሮዎች ስለሆንን በጩኸታችን የረበሽነው እንጂ የቀሰቀስነው ሰው የለም፡፡

"ሕማማት" ከተሰኘው ባለ 528 ገጽ መጽሐፍ 2ኛ ምዕራፍ የተወሰደ https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
በሰሙነ ሕማማት የሚፈጸሙ ሥርዓቶች

1.ስግደት:-በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል::
2. ጸሎት:- በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው::
በነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ::
3.ጾም:-በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት /አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች/ አይበሉም:: በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል::
4.አለመሳሳም:-አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም:: መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ. 3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29
5.አክፍሎት:-እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው::
6.ጉልባን:-ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው::
7.ጥብጠባ:-ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው:: ይህም የጌታ ምሳሌ ነው::
8.ቄጠማ:-ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን::

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም
ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም:: https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
ንዜኑ ሞተከ ወትንሳኤከ ቅድስተ እግዞኦ።አቤቱ ሞትህን እና ቅድስት ትንሳኤህን እንናገራለን። ክርስቶስ ተንሰዐ አሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሠሮ ለሰጣን አግአዞ ለአዳም ሠላም እምይእዜሰ ኮነ ፈሰሐ ወሠላም:: ይህ በዓል የሰላም የደስታ የፍቅር የንስሐ በዓል ይሁንልን:: ይህ በዓል ስናከብር አቅመ ደካሞችን ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናትን በማሰብ ይሁን :: መልካም የትንሳኤ በዐል ። https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

✞ ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

✞ ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

✞ ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

✞ ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

✞ አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

✞ ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

✞ እሁድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
Wudasie Mariam.apk
1.4 MB
ኦርቶዶክሳዊ አፕሊኬሽኖች ለአንድሮይድ ተጠቃሚዎች
https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
“ማግባት ለሚሹ”

የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር

ከምንም በፊት የጋብቻ ዓላማን ማወቅ አለባችሁ፡፡ በሕይወታችን ለምን ጋብቻ እንደሚያስፈልገን መረዳት አለባችሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ ነገርን አትጠይቁ፡፡ እናስ የጋብቻ ዓላማው ምንድነው? ለምንድነው እግዚአብሔር ጋብቻን የሰጠን? ብጹዕ ጳውሎስን እናድምጠው፤ እንዲህ ያለውን፦ "ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑሮው፤ ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራሷ ባል ይኑራት" (1ኛ ቆሮ.7፥2)። "ከድህነት ይወጣ (ትወጣ) ዘንድ" ነው የሚለውን? ወይስ "ሀብት ለማግኘት ሲባል" ነው የሚለውን? አይደለም፡፡ ታዲያ ምንድነው የሚለው? ከዝሙት እንጠበቅ ዘንድ፤ ራሳችንን መቆጣጠር እንችል ዘንድ፤ ንጽህናን ገንዘብ እናደርግ ዘንድ፤ በትዳር አጋራችን ደስ ተሰኝተን እግዚአብሔርን እናመሰግን ዘንድ፡፡ አያችሁ ይኼ ነው የጋብቻ ስጦታው ይኼ ነው የጋብቻ ፍሬው፤ ይኼ ነው የጋብቻ ጥቅሙ፡፡

ስለዚህ ልጆቼ! እማልዳችኋለሁ፦ትልቁን ጥቅም ዘንግታችሁት ዓይናችሁን በትንሹ ላይ አታሳርፉ፡፡የትዳር አጋርን ስትመርጡ የሀብት ጉዳይ የእናንተ ትልቅ አጀንዳ ሊኾን አይገባም፡፡ ስለ ሀብት ብሎ የትዳር አጋርን መምረጥ ድንቁርና ነው፤ ሀብት ነገ ሊጠፋ ይችላልና፡፡ ስለዚህ ለትዳር የምትመርጡት ሰው ከምንም በላይ መንፈሳዊ ሀብቱን ተመልከቱ፡፡ በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ይበልጥ የሚጠቅማችሁ ይኼ ነውና፡፡

አባቶች ሆይ! አብርሃምን ምሰሉት፡፡ አብርሃም ለልጁ ለይስሐቅ ሚስትን ሲፈልግለት፦ ሀብትን አላየም፤ የንጉሣውያን ቤተሰብን አልተመለከተም፤ አፍአዊ ውበትን መመዘኛ አላደረገም፤ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ መስፈርትን አልደረደረም፡፡ የነፍስ ንጽህናን እንጂ፡፡

እናቶች ሆይ! ሴት ልጆቻችሁን እንደ ርብቃ አሳድግዋቸው፡፡

እናንተ ማግባትን የምትሹ ወጣቶች ሆይ! ይስሐቅን ምሰሉት፦ ዘፈንን፣ ዳንኪራን፣ ሳቅና ስላቅን፣ የከበሮንና የዋሽንት ጫጫታን፣ ሌላውንም የዲያብሎስ ትርኢት በሰርጋችሁ ቀን አታስቡ፡፡ ከዚህ ይልቅ በምታደርጉት ኹሉም ላይ እግዚአብሔር እንዲቀድማችሁ ለምኑት፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ትዳራችሁ ፍቺ፣ ዝሙት፣ ቅናት፣ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ የሌለበት ኾኖ ይፀናላችኋል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ፥ ሌላው በረከትም ተትረፍርፎ ይመጣላችኋል፡፡ የአውሎ ነፋስ ዓይነት በዙሪያችሁ ቢነፍስም፥ አትነዋወፁም፡፡

እናንተ ልጃገረዶች ሆይ! ርብቃን ምሰሏት፡፡ የትዳር አጋራችሁን ፍጹም ለማፍቀር የተዘጋጃችሁ ኹኑ፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ቤታችሁ ፍጹም ሰላማዊ ባሎቻችሁ የምትልዋቸውን የሚያደርጉና በፍቅራችሁ የሚንበረከኩ ይኾናሉ፡፡ ትዳር እንዲህ ኾኖ ሲጀመር፥ እግዚአብሔርንና ወላጆቹን ደስ የሚያሰኝ ልጅ ይገኝበታል፡፡

የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ የገዛነው ዕቃ ችግር ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም፤ እስከ ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡ ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ፥ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ፤ ከኹሉም በፊት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ፡፡ https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
ቤተክርስቲያን አትታደስም!
@EOTCbook

ዘላለማዊነት አንዱ የቤተክርስቲያን መገለጫ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ዘላለማዊት ናት፡፡ መሠረቷ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ ነውና እርሷም ዘላለማዊት ናት፡፡ በአካለ ሥጋ ያሉ ክርስቲያኖችና በአካለ ነፍስ ያሉ ቅዱሳን ከክርስቶስ ጋር ያላቸው አንድነት ዘላለማዊ ነውና ቤተክርስቲያንም ዘላለማዊት ናት፡፡ ዘላለማዊ ናት ስንል ዘላለማዊነቷ በመጠበቅ (ጠብቆ ይነበብ) እንጂ በመታደስ (እየታደሰች) አይደለም፡፡ ክርስቶስ የምታረጅ፣ የምትለወጥ ወይም የምትጠፋ ቤተክርስቲያን አልመሠረተም፡፡ የማያረጅ ነገር ደግሞ አይታደስም፡፡ ሁል ገዜ አዲስ ነውና፡፡ ከዚህ ውጭ ቤተክርስቲያን ትታደስ ማለት ግን የሚከተሉትን መሠረታዊ ስህተቶች/ክህደቶች ያስከትላል፡፡
1. ቤተክርስቲያን ትታደስ ማለት፡- ሐዋርያዊ መሠረት አያስፈልጋትም በየጊዜው ሌላ መሠረት ያስፈልጋታል ማለት ነው፡፡
2. ቤተክርስቲያን ትታደስ ማለት፡- መሥራቿ አጉድሎ ነው የመሠረታት ናትና እኛ እናሟላት እንደማለት ነው፡፡
3. ቤተክርስቲያን ትታደስ ማለት፡- በእርሷ የነበሩ በእርሷ የኖሩ አልፀደቁም እንደማለትም ነው፡፡
4. ቤተክርስቲያን ትታደስ ማለት፡- የምትፈጽማቸው ምሥጢራት ለድኅነት አያበቁምና ይሻሻሉ ማለት ነው፡፡
5. ቤተክርስቲያን ትታደስ ማለት፡- እኛ ከቀደሙት የተሻልን ነንና የተሻለች ቤተክርስቲያን እንመሥርት እንደማለት ነው፡፡
ስለዚህ ቤተክርስቲያን ትታደስ የሚለው አስተሳሰብ መሠረታዊ ስህተት ነው፡፡ አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት የሚቀየሩ ወይም የሚሻሻሉ አይደሉም፡፡ ጸንተው የሚኖሩ እንጂ፡፡ ነገር ግን ሁለት በቤተክርስቲያን ዘንድ እድሳት የሚያስልጋቸው ነገሮች አሉ፡፡ እነርሱም የቤተክርስቲያን አስተዳደርና የክርስቲያኖች ሕይወት ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለቱ ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ አንጻር በየጊዜው እየታዩ ሊሻሻሉ ይችላሉ፡፡ አስተዳደሩን ማዘመን ያስፈልጋል፡፡ የምዕመናን ሕይወት ደግሞ በንስሐ እየታደሰ ይኖራል፡፡ ከዚህ ውጭ ግን ሰውን የምታድሰው ቤተክርስቲያን እራሷ አትታደስም፡፡

አስተምህሮ ዘተዋህዶ! https://t.me/ethiopianorthodoxbooks
"ወደ_ምስራቅ_ተመልከቱ_ማለት_ምን_ማለት_ነው"??
በኦርቶዶክስ። ተዋህዶ ሀይማኖታችን ቤተ ክርስቲያን
የምታንፀው ምስራቁን አቅጣጫ ጠብቃ ነው እንድሁም ከቤተ
ክርስቲያኑ ጋር አብሮ የሚሰራው ቤተለሄም። በስተ ምስራቅ
በኩል ይደረጋል በፆለት ሰአትም ወደ ምስራቅ ዙረን ነው
የምንፀልየው በስረአተ ቀብር ላይም የሞተ ሰው ሲቀበርእራሱ
ውደ ምዕራብ እግሩ ወደ ምስራቅ። ሆኖ ይቀበራል።ሌላው
ዳቆኑ በስረአተ ቅዳሴው ላይ ወደ ምስራቅ ተመልከቱ ይላል
ለምን??
፩ የአዳም አባታችን ጥንተ ርስተ ገነት በምስራቅ ናት ዘፍ 2*8
፪÷፰ ይች እርስታችን በአዳም በደል ምክንያት በክሩቤል
ሰይፍ ተዘግታ ስትኖር ሞትን ድል አድርጎ በደልን ክሶ ጌታችን
መዲሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በሞቱ ከፈተልን ሉቃ
23*43። ፳፫*፵፫ ወደ ምስራቅ በዞርን ቁጥርወደ ገነት
ለመግባት የተሰጠን ተስፍፋ ትዝ ይለናል የተከፈተችውም
ቤታችን ገነት በእምነት ውለል ብላ ትታየናለች በክርስቶስ
ያገኘነውን ፀጋ እናስባለን ምድራዊያን አለመሆናችንንም
እናስባለን
፪ ጌታ የተውለደው በምስራቅ ነው
ሰበአሰገል ኮኩቡን ያዩት በምስራቅ ሲሄን ያኮከብ የምህረት
እግዝያብሄር ምሳሌ ነው እርሱን ወደ እግዝያብሄር
እንዳደረሳቸው ሁሉ እኛንም ወደ ለመለመው መስክ
ይመራናል ማቴ ፳፪*፲፬ 22*14 ወደ ምስራቅ በዞርን
ቁጥር። የጌታን መውለድነ ያደረገልንን ውለታ ይታውሰናል
የምህረት ኮከብ እየመራን መሆኑን ትዝ ይለናል
፫ ምስራቅ የእመቤታችን ምሳሌ ነው
ከምስራቅ ጨለማውን የሚገፈው።ፀሀይ እንደሚውጣ ሁሉ
ከእመቤታችን ከድንግል ማርያምም የአለም የሀጥያት ጨለማ
የሚገፍ ፀሀይ ፅድቅ እየሱስ ክርስቴስ ውጥቷል። ተገኝቷል
ለእናንተ ስሜ የምትፈሩ የፅድቅ ፀሀይ ትወጣላችሁአለች።
ሚል ፬*፩ 4*1 ህዝ ፵፬*፩÷፬ 44*1-4 ነብዩ ህዝቀየልም
እመቤታችንን ያያት በምስራቅ ነው ስለዚህ ውደ ምስራቅ
በዞርን ቁጥር እመቤታችንን እናስታውሳለን የፅድቅ ፀሀይ
ክርስቶስ ስለተውለደልን በጨለማ አለመሆናችን ትዝ እያለን
ከሀጥያት እንርቃለን
፬ የአለም ድህነት የተገኘው በምስራቅ ነው
ጌታ የተስቀለውና አለምን ያዳነው በምስራቅ ነው እየሩስ
አሌም ምስራቃዊት ከተማ ናት በመሆኑ ውደ ምስራቅ በዞርን
ቁጥር የተሰቀለውን ክርስቴስንና የተከፈለልንን ዋጋ እናስባለን
፭ ክርስትናና ቤተ ክርስቲያን የተመሰረቱት በምስራቅ ነው
የመጅመሪያው ቤተ ክርስቲያን የተመስረተውበ በእየሩስ
አሌም ሲሆን ውንጌል የተሰበከው ከዚህ በመነሳቱ ነው
ስለዚህ ውደ ምስራቅ ስንዞር የቤተ ክርስቲያን ጉዞ የውንጌል
መስፋፋትን የህዝብ ና የአለም መዳን ትዝ ይለናል
፮ ምስራቅ የእግዝያብሄር ክብር መገለጫ ነው
ኢሳ ፳፰*፲፫ 28*13። እግዝያብሄር በምስራቅ
የእስራኤልንም አምላክ የእግዝያብሄርንም ስም በባህር
ደሴቶች አከበሩ ህዝ ፵፫*፪ 43*2 የእስራኤልንም አምላክ
ክብር ከምስራቅ መንገድ ውጣ ።
፯ የጌታ ዳግም ምፅአትም ከምስራቅ ነው
ዘካ ፲፬*፲፬ 14*14
ውስብሀት ለእግዝያብሄር አሜን:: https://t.me/ethiopianorthodoxbooks