Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
#አብዱ_ኪያር #እድሜ_ዳኛው
ክፉና ደጉን ሳናውቅ በልጅነት ህይወት
ኩልትፍትፍ ባለ አንደበት መፈንደቅ መጫወት
ግጥማችን ቤት አይመታ ስርዐቱንም አናውቀው
በጭብጨባ ነበረ ሰፈሩን ምናደምቀው
ተረሳሽ ወይ እስቲ ላስታውስሽ
እቅፍ ኣድርጌ የማጫውትሽ
እኔና አንቺን ያጣመረን
ዘፈን ነበር ያፋቀረን
አደግንና ተቀየረ
መፍራት ማፈር ተጀመረ
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
ፍቅርሽ በልጅነት ያኔ ተጀምሮ
እያሰቃየኝ ነው አድጎና ጨምሮ
የልቤን ገልጬ መናገር ጨንቆኛል
እድሜ ግልጽነቴን ከላዬ ነጥቆኛል
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
ከ ሀ ግዕዝ ለ ግዕዝ በፊት ኣሊፍ ባ ታ ሳንል
ዘፈን ነበር የምናውቀው ሳናጠና ፊደል
መቼም ከልቤ አይጠፋም ያ ምንወደው ጭፈራ
ጮክ ብለን የምንዘፍነው በነጻነት ሳንፈራ
ተረሳሽ ወይ እስቲ ላስታውስሽ
እቅፍ ኣድርጌ የማጫውትሽ
እኔና አንቺን ያጣመረን
ዘፈን ነበር ያፋቀረን
አደግንና ተቀየረ
መፍራት ማፈር ተጀመረ
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
አቅፌ ልስምሽ ልቤ ይከጅልና
እንዴት ብዬ ላርገው ሆነብኝ ፈተና
ገና አይንሽን ሳየው እጨናነቃለሁ
እድሜ ነጻነቴን ወስዶት እፈራለሁ
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
የተሰማንን ዘፍነን በየዋህነት የኖርነው
ድሮ ልብ ሳንገዛ በልጅነት እድሜ ነው
ግልጽነት እና እውነት ስሜታችን ላይ ነበር
ልብ ስንገዛ ጠፋ አቤት የግዢ ነገር
የላይኛው ፍቅር ሰጠን
ነጻነትን አለበሰን
የምድሩ የታችኛው
ፈረደብን እድሜ ዳኛው
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
አንቺንም እንደኔ ያደርግሻል ወይ
የልብን መናገር ያስፈራሻል ወይ
ስሜቴ በሙሉ አፍቅራት ይለኛል
ውድድ ውድድ አርጋት አትተዋት ይለኛል
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
እድሜ ዳኛው እድሜ ዳኛው
እድሜ ዳኛው




Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics