Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
#ሄለን_በርሄ # የኔ_ፍቅር

ባትኖርም ካጠገቤ ከጎኔ ብትለየኝም
እኔስ አይሃለሁ አንተ ባታየኝም
ሳይህ ሳይህ ባድር ብዉል አይወጣልኝም
ፍቅር ያንተስ ፍቅር ፍቅር ያንተስ ፍቅር
ካጠገብህ ሁኜ ባላጫዉትህም
ገላህን አቅፌ ምንም ባልስምህም
በመንፈስ ካንተዉ ነኝ መቸም አልለይም
በሃሳብ መነጸር ሁሌ ነዉ የማይህ
ዉቅያኖስ ባህሩ አድማስ ብጋርደኝ
ወሳንተ መምጣቴን ማንም አያግደኝ መምጫ መንገድ ሁሉ ቢዘጋ
ቢታገድ
ፍቅር ያደርሰኛል ባሳብ አየር መንገድ
የኔ ፍቅር ፍቅር አገናኝተህ ከምትለየኝ
የኔ ፍቅር ፍቅር ምነዉ በፊት ባታሳየኝ
የኔ ፍቅር ፍቅር ወይ ዉሰደኝ ወይ አምጣልኝ
የኔ ፍቅር ፍቅር ያለዚያማ ጉዴ ነዉ እንጃልኝ ቀኑን በትካዜ ብቻየን
ሳወራ
ደግሞ ሊተካልኝ ሌሊቱም በተራ
ገና ገደም እንዳልኩ ካልጋዉ ስንገናኝ
የሃሳብ ሰመመን ጉዞ ነዉ የሚቀናኝ
ድንገት ከተፍ ስል ካለህበት ቦታ
እየተላቀስን በናፍቆት በደስታ ታዲያ ምን ያደርጋለ ነበር ቢሆን
በዉኔ
ለካስ በህልሜ ነዉ የማገኝህ እኔ
የኔ ፍቅር ፍቅር እዉን አርገዉ ፍታዉ ህልሜን
የኔ ፍቅር ፍቅር እንድወጣዉ ርሃብ ጥሜን
የኔ ፍቅር ፍቅር ወይ ዉሰደኝ ወይ አምጣልኝ
የኔ ፍቅር ፍቅር ያለዚያማ ጉዴ ነዉ እንጃልኝ
Shear to your friends for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ሄለን_በርሄ #ልቤ_ላንተ_እንጂ
ልቤ ላንተ እንጂ ለሌላው የለው ቦታ
ያልከፈለህ ገና አለ ውለታ
እኔ አንድዬን ምለምነው
ላንተ ሰላም ጤና ነው ምማፀነው
ገና በማለዳው ፈክታ
አ ሀ ሀ
ሳለች ጀምበር
ኦ ሆነ ሆነ
ጨላልሞበት አይኔ ለማየት ሲቸገር
ከልብህ አብርቶ የፍቅር ፀሐዩ
ሳልታይ አየኸኝ ልቤ ፍቅሬ ሆይ
ኖሮኝ ባላደርግልህ ዛሬም ባላኮራህ
ለኔ በቂዬ ነው መኖርህ በጤናህ
እኔ ምፈልገው ይሄን ነው /፬
ከፍቶህ አይኔ እንዳያይ ብዬ ነው /፬
ልቤ ላንተ እንጂ ለሌላው የለው ቦታ
ያልከፈለህ ገና አለ ውለታ
እኔ አንድዬን ሰለምነው
ላንተ ሰላም ጤና ነው ምማፀነው
ያንተን መልካምነት በቃላት ዘርዝሬ
መመለስ አልችልም ባፌ ተናግሬ
ውለታህን ቆጥሮ የሰማይ ንጉሱ
እኔ አቅም የለኝም ይክፈልልኝ እሱ
ኖሮኝ ባላደርግልህ ዛሬም ባላኮራህ
ለኔ በቂዬ ነው መኖርህ በጤናህ
እኔ ምፈልገው ይሄን ነው /፬
ከፍቶህ አይኔ እንዳያይ ብዬ ነው /፬

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics