Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
#ቴዲ_አፍሮ #አይን_አፋር_ነኝ❤️

ጉድ ያረገኝ አይኔ ነው
አይቶሽ በክፉ ቀን
እንድግባባሽ ፈልጌ
ሰው ቢያስተዋውቀን
አሳፈርሽኝ መውደዴን
ልነግርሽ ብሞክር
ምን ጨካኝ ነሽ የማትራሪ የማይገባሽ ፍቅር
❤️
እንኳን ተናግረሽኝ በሰው ፊት
አይን አፋር ነኝ እኔ ከበፊት
ደፍሬ ባወራሽ አንቺን ብቻ
አደረግሽኝ የሰው መዛበቻ
❤️
ስንት ቆንጆ አለፈኝ እስከዛሬ
ቀርቦ ለማናገር በማፈሬ
ዛሬ አንቺን ብጠይቅ ቃል ቢወጣኝ
ልክ እንደ ህፃን ልጅ አይንሽ ቀጣኝ
❤️
ስፈራ ስችር አናግሬሽ
ምነው መለሽኝ አሳፍረሽ
ፍቅሬን መግለፄ ምን ክፋት አለው
ተይ ፊት አትንሽኝ ባክሽ አፍራለው
ተይ ፊት አትንሽኝ አፍራለሁ
❤️
አረ ተይ
እንኳንስ ፊት ነስተሽኝ
ድሮም አይን አፋር ነኝ
ጉድ ያረገኝ አይኔ ነው
አይቶሽ በክፉ ቀን
እንድግባባሽ ፈልጌ ሰው
ቢያስተዋውቀን
አሳፈርሽኝ መውደዴን ልነግርሽ ብሞክር
ምን ጨካኝ ነሽ የማትራሪ የማይገባሽ ፍቅር
❤️
ሰው ቢያደፋፍረኝ እንድነግርሽ
ብዬ አሸንፎኛል በቃ ፍቅርሽ
ገና ሳይሽ ጠፋኝ ምገባበት
ፊት ነሳሽኝ እና ሰው ባለበት
ስንት ቆንጆ አለፈኝ እስከዛሬ
ቀርቦ ለማናገር በማፈሬ
ዛሬ አንቺን ብጠይቅ ቃል ቢወጣኝ
ልክ እንደ ህፃን ልጅ አይንሽ ቀጣኝ
❤️
ስፈራ ስችር አናግሬሽ
ምነው መለሽኝ አሳፍረሽ
ፍቅሬን መግለፄ ምን ክፋት አለው
ተይ ፊት አትንሽኝ ባክሽ አፍራለው
ተይይ ፊት አትንሽኝ አፍራለው አረ ተይ
ተይ እዳዬ
እንኳንስ ፊት ነስተሽኝ
ድሮም አይን አፋር ነኝ
ድሮም አይናፋር ነኝ
❤️
❤️
❤️shear to your friends for more lyrics @ethiopian_music_lyrics