Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
#ኩኩ_ሰብስቤ# እና #ቴዲ_አፍሮ# እዮሃ_አበባዬ#


የበረሃው ሀገር ስደተኛ
ሀገሬ ካልገባሁ እኔ አልተኛ
ሀገሬ ሳልገባ እኔ አልተኛ
እፎይ ባለ ልቤ የኔ ነፍስ
ሀገሬ ስገባ ስመለስ /2x/
ያሳደገኝ መሶብ የቤቴ ገበታ
እህል ማቋረሱ የቸገረው ለታ
ይህንን ለማየት ባይፈቅድልኝ ክብሬ
ስደትን መርጬ ወጣሁኝ ካገሬ
ደፋ ቀና ብዬ ሀሳቤን ላልሞላው
የበረሃው ውሎ ሰውነቴን በላው
ክረምቱ ወቶ በጋው ሲገባ
ይናፍቀኛል አዲስ አበባ
አደይ ሲፈካ እንደዘመን አጥቢያ በእንቁጣጣሹ ባገርሽ ኢትዮጵያ
እዮሃ አበባዬ መስከረም ጠባ
ጓዜን ጠቅልዬ መች ሀገሬ ልግባ
አበባዬ እዮሃ አበባዬ በመስከረም -----
ጃኖ አሰርቼ እንደ አደይ ፈክቼ
ታየኝ ማታ የእንቁጣጣሽ ለታ
አየሁ በህልቤ አገሬ ላይ ሁኜ
ከህልሜ ስነቃ ከህልሜ ስነቃ
እዛው ነኝ ለካ እዛው ነኝ ለካ
እዛው ነኝ ለካ እዛው ነኝ ለካ
የበረሃው ሀሀር ስደተኛ
ሀገሬ ካልገባሁ እኔ አልተኛ
ሀገሬ ሳልገባ እኔ አልተኛ
እፎይ ባለ ልቤ የኔ ነፍስ
ሀገሬ ስገባ ስመለስ /2/
በደሃው መንደሬ ተኩዬ ሳልዳር
በሰው በረሃ ላይ ሆኗል የኔስ አዳር
ወንድም እህቶቼን ላስተምር ልረዳ ቤተሰቤን ላግዝ ስደክም ለባዳ
አምላኬን ለመንኩት ----
እድሌ እንዲባረክ በኢትዮጵያ ሀገሬ
ባየሽ ሀገሬ አንቺ እናት አለም
ያለ ሀገር ኑሮ ህይወት አይደለም
የሚቆምልኝ የለኝ ጠበቃ
የሰው መሆኔ ምነው ቢያበቃ
እዮሃ አበባዬ መስከረም ጠባ
ጓዜን ጠቅልዬ መች ሀገሬ ልግባ
አበባዬ እዮሃ አበባዬ በመስከረም -----
ጃኖ አሰርቼ እንደ አደይ ፈክቼ
ታየኝ ማታ የእንቁጣጣሽ ለታ
አየሁ በህልቤ አገሬ ላይ ቆሜ
ከህልሜ ስነቃ ከህልሜ ስነቃ
እዛው ነኝ ለካ እዛው ነኝ ለካ
እዛው ነኝ ለካ እዛው ነኝ ለካ
እዛው ነኝ እዛው ነኝ እዛው ነኝ
እዛው ነኝ እዛው ነኝ እዛው ነኝ
መልካም በዓል

Shear to your friends
@ethiopian_music_lyrics
#ቴዲ_አፍሮ #ኡኡታዬ
ዘመን ያገነነው ጅብ ቆሟል ከበሬ
አፌ እዳታስበላኝ ባለመናገሬ
እያየ ስትወጣ ልትጫወት በሳት
ምን ያረጋል አፌ ካለፈ ብትወቅሳት
አልፎ በዝምታ በስተመጨረሻ
ቢጮህ ምን ያረጋል ጅብ ከሄደ ውሻ
ተናገራት አፌ ሳይመጣ ደመና
ጅቡ ከበራፌ ላይ ነውና
ኡኡ በል እንጂ አፌ ውጣ ከተራራ
ድምፅ ሳይገጫጭ አንዱ ከአንዱ ጋራ
ኡኡ ሳትል አፌ ዛሬ በሰዓቱ
ጅብ ከሄደ ውሻ ይሆናል ጩኸቱ
ኡኡታዬ ላይሰማ ያኔ
እሪ ብል አሁን እስክነቃ ልሳኔ
እሪታዬ ቃል ላይሰማ
ኡሳልል ኡባልል ኡሳልል ያኔ
አፌ አፌ ሰሚ ለሌለው ያኔማ
ዘመን ያገነነው ጅብ ቆሟል ከበሬ
አፌ እዳታስበላኝ ባለመናገሬ
እያየ ስትወጣ ልትጫወት በሳት
ምን ያረጋ አፌ ካለፈ ብትወቅሳት
አልፎ በዝምታ በስተመጨረሻ
ቢጮህ ምን ያረጋል ጅብ ከሄደ ውሻ
ተናገራት አፌ ሳይመጣ ደመና
ጅቡ ከበራፌ ላይ ነውና
ኡኡታዬ ላይሰማ ያኔ
እሪ ብል አሁን እስክነቃ ልሳኔ
እሪታዬ ቃል ላይሰማ
ኡሳልል ኡባልል ኡሳልል ያኔ
አፌ አፌ ሰሚ ለሌለው ያኔማ
ቀለበትሽ ከ'ኔ ልብሽ ከሌላ ሰው
ይሄ አለመታመን ቤትን ከፈረሰው
ለሶስቱ ጉልቻ ገባው ስል ከቤቴ
ነፍሴ እዳትጠራ በቀለበት ጣቴ
አፌ በዝምታ ብታልፋት በንቀት
ከነባለቤት ነው የጥሪ ወረቀት
ተናገራት አፌ ሳይመጣ ደመና
ጅቡ ከበራፌ ላይ ነውና
ኡኡታዬ ላይሰማ ያኔ
እሪ ብል አሁን እስክነቃ ልሳኔ
እሪታዬ ቃል ላይሰማ
ኡሳልል ኡባልል ኡሳልል
ያኔ አፌ አፌ ሰሚ ለሌለው ያኔማ
ኡኡታ ተይ መኝታ ከ'ኔ ሌላ....

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ቴዲ_አፍሮ #ሰው_በልኬ
ምነው ብትሰማኝ አምላኬ
ፈልገህ ብትሰጠኝ ሰው በልኬ
እኔ አጣሁ ፈልጌ
ምነው ብትሰማኝ ፈጣሪ
መርቀህ ብትሰጠኝ አንድ አፍቃሪ
ከኔጋ ነዋሪ
ብዙ ዘመን ስባክን ከርሜ ሰው ፍለጋ
ዞሬ መጣሁ ዘዴ ካለህ ብዬ ወደ አንተጋ
የሞከርኩት አልሆንልህ አለኝ እውነተኛ
ያሰብክልኝ ሰው እንዳለ ለኔ በል ስጠኛ
ላይ ሳይ አይኔን አንስቼ ላይ ሳይ ወዳለህበት
ላይ ሳይ ጭንቄን ብትሰማ ላይ ሳይ ተው ምናለበት
ላይ ሳይ የፈጠርካትን ላይ ሳይ ያዳም መከታ
ላይ ሳይ የናቴን ምትክ ላይ ሳይ ተው ስጠኝ ጌታ
አምላኬ በል ስጠኝ ሰው በልኬ 3×
ምን ይሳንሃል በል ስጠኝ ሁሉ በጅህ
ስማኝ ስጠራህ በል ስጠኝ እኔ ልጅህ
በል ስጠኝ አምላኬ በል ስጠኝ ሰው በልኬ 2×
አ አ አ ምላኬ በል ስጠኝ ሰው በልኬ
ምነው ብትሰማኝ አምላኬ
ፈልገህ ብትሰጠኝ ሰው በልኬ
እኔ አጣሁ ፈልጌ
ምነው ብትሰማኝ ፈጣሪ
መርቀህ ብትሰጠኝ አንድ አፍቃሪ
ከኔጋ ነዋሪ
በዚች አለም ምነው ለኔ ብቻ ጠፋ አፍቃሪ
ሰው እያለ ባይተዋር አታርገኝ ተው ፈጣሪ
ካፈሩ ላይ የሰራሀት ነብሴ ናት ብቸኛ
ያሰብክልኝ ሰው እንዳለች ለኔ በል ስጠኛ
ላይ ሳይ አይኔን አንስቼ ላይ ሳይ ወዳለህበት
ላይ ሳይ ጭንቄን ብትሰማ ላይ ሳይ ተው ምናለበት ላይ ሳይ
የፈጠርካትን ላይ
ሳይ ያዳም መከታ
ላይ ሳይ የናቴን ምትክ ላይ ሳይ ተው ስጠኝ ጌታ
አምላኬ በል ስጠኝ ሰው በልኬ 3×
ምን ይሳንሃል በል ስጠኝ ሁሉ በጅህ
ስማኝ ስጠራህ በል ስጠኝ እኔ ልጅህ
በል ስጠኝ አምላኬ በል ስጠኝ ሰው በልኬ 2×
አ አ አ ምላኬ በል ስጠኝ ሰው በልኬ

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#ቴዲ_አፍሮ #አይን_አፋር_ነኝ❤️

ጉድ ያረገኝ አይኔ ነው
አይቶሽ በክፉ ቀን
እንድግባባሽ ፈልጌ
ሰው ቢያስተዋውቀን
አሳፈርሽኝ መውደዴን
ልነግርሽ ብሞክር
ምን ጨካኝ ነሽ የማትራሪ የማይገባሽ ፍቅር
❤️
እንኳን ተናግረሽኝ በሰው ፊት
አይን አፋር ነኝ እኔ ከበፊት
ደፍሬ ባወራሽ አንቺን ብቻ
አደረግሽኝ የሰው መዛበቻ
❤️
ስንት ቆንጆ አለፈኝ እስከዛሬ
ቀርቦ ለማናገር በማፈሬ
ዛሬ አንቺን ብጠይቅ ቃል ቢወጣኝ
ልክ እንደ ህፃን ልጅ አይንሽ ቀጣኝ
❤️
ስፈራ ስችር አናግሬሽ
ምነው መለሽኝ አሳፍረሽ
ፍቅሬን መግለፄ ምን ክፋት አለው
ተይ ፊት አትንሽኝ ባክሽ አፍራለው
ተይ ፊት አትንሽኝ አፍራለሁ
❤️
አረ ተይ
እንኳንስ ፊት ነስተሽኝ
ድሮም አይን አፋር ነኝ
ጉድ ያረገኝ አይኔ ነው
አይቶሽ በክፉ ቀን
እንድግባባሽ ፈልጌ ሰው
ቢያስተዋውቀን
አሳፈርሽኝ መውደዴን ልነግርሽ ብሞክር
ምን ጨካኝ ነሽ የማትራሪ የማይገባሽ ፍቅር
❤️
ሰው ቢያደፋፍረኝ እንድነግርሽ
ብዬ አሸንፎኛል በቃ ፍቅርሽ
ገና ሳይሽ ጠፋኝ ምገባበት
ፊት ነሳሽኝ እና ሰው ባለበት
ስንት ቆንጆ አለፈኝ እስከዛሬ
ቀርቦ ለማናገር በማፈሬ
ዛሬ አንቺን ብጠይቅ ቃል ቢወጣኝ
ልክ እንደ ህፃን ልጅ አይንሽ ቀጣኝ
❤️
ስፈራ ስችር አናግሬሽ
ምነው መለሽኝ አሳፍረሽ
ፍቅሬን መግለፄ ምን ክፋት አለው
ተይ ፊት አትንሽኝ ባክሽ አፍራለው
ተይይ ፊት አትንሽኝ አፍራለው አረ ተይ
ተይ እዳዬ
እንኳንስ ፊት ነስተሽኝ
ድሮም አይን አፋር ነኝ
ድሮም አይናፋር ነኝ
❤️
❤️
❤️shear to your friends for more lyrics @ethiopian_music_lyrics