Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
#ቴዲ_አፍሮ #ሰው_በልኬ
ምነው ብትሰማኝ አምላኬ
ፈልገህ ብትሰጠኝ ሰው በልኬ
እኔ አጣሁ ፈልጌ
ምነው ብትሰማኝ ፈጣሪ
መርቀህ ብትሰጠኝ አንድ አፍቃሪ
ከኔጋ ነዋሪ
ብዙ ዘመን ስባክን ከርሜ ሰው ፍለጋ
ዞሬ መጣሁ ዘዴ ካለህ ብዬ ወደ አንተጋ
የሞከርኩት አልሆንልህ አለኝ እውነተኛ
ያሰብክልኝ ሰው እንዳለ ለኔ በል ስጠኛ
ላይ ሳይ አይኔን አንስቼ ላይ ሳይ ወዳለህበት
ላይ ሳይ ጭንቄን ብትሰማ ላይ ሳይ ተው ምናለበት
ላይ ሳይ የፈጠርካትን ላይ ሳይ ያዳም መከታ
ላይ ሳይ የናቴን ምትክ ላይ ሳይ ተው ስጠኝ ጌታ
አምላኬ በል ስጠኝ ሰው በልኬ
ምን ይሳንሃል በል ስጠኝ ሁሉ በጅህ
ስማኝ ስጠራህ በል ስጠኝ እኔ ልጅህ
በል ስጠኝ አምላኬ በል ስጠኝ ሰው በልኬ
አ አ አ ምላኬ በል ስጠኝ ሰው በልኬ
ምነው ብትሰማኝ አምላኬ
ፈልገህ ብትሰጠኝ ሰው በልኬ
እኔ አጣሁ ፈልጌ
ምነው ብትሰማኝ ፈጣሪ
መርቀህ ብትሰጠኝ አንድ አፍቃሪ
ከኔጋ ነዋሪ
በዚች አለም ምነው ለኔ ብቻ ጠፋ አፍቃሪ
ሰው እያለ ባይተዋር አታርገኝ ተው ፈጣሪ
ካፈሩ ላይ የሰራሀት ነብሴ ናት ብቸኛ
ያሰብክልኝ ሰው እንዳለች ለኔ በል ስጠኛ
ላይ ሳይ አይኔን አንስቼ ላይ ሳይ ወዳለህበት
ላይ ሳይ ጭንቄን ብትሰማ ላይ ሳይ ተው ምናለበት ላይ ሳይ
የፈጠርካትን ላይ
ሳይ ያዳም መከታ
ላይ ሳይ የናቴን ምትክ ላይ ሳይ ተው ስጠኝ ጌታ
አምላኬ በል ስጠኝ ሰው በልኬ
ምን ይሳንሃል በል ስጠኝ ሁሉ በጅህ
ስማኝ ስጠራህ በል ስጠኝ እኔ ልጅህ
በል ስጠኝ አምላኬ በል ስጠኝ ሰው በልኬ
አ አ አ ምላኬ በል ስጠኝ ሰው በልኬ

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics