Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
#ጂጂ_ሺባባው #ፍቅር_ይበልጣል
አዲስ አዲሱን አይተው ቢመኙ
ለማን ይበጃል ከሺ ቢተኙ
አለም ሁሉ ላንተ አይሆንም
አትመኝ ይቺንም ያቺንም
ፍቅሬ ላስጠንቅቅህ ብትሰማኝ ቢገባህ
ሁሉን ለኔ ስትል አንዱን ታጣዋለህ
ቃል የለኝም አንተን የማናግርበት
ልብስ ምን ያደርጋል ውስጡን ካልተረዱት
ይቆርጣል ይፈልጣል ውጋት ነው ወይ ፍቅሬ
በሰው ልሳን አትዋል እርም ነው በሀገሬ
በምን ልሸፍነው ይሄን ዐይንህን
እንዴትስ ልወቀው ልብህን.....
እኔንም እሷንም ወደድኩ...
ወደድኩሽ
እንዲህ እንደባዘንክ ግዜው እንዳይመሽ
ሰቀቀን ሀዘን ነው ከሺ ገላ ትርፉ
ከልብ የማይወጣ ምን ቢንሰፈሰፉ
ዛሬ ስማኝ ዛሬ ምናገረውን
ለጥፋት ለከንቱ አትባዝን
የወረት ቁራኛ ለምን ትሆናለህ
ፍቅሬ ባንተ ፅኑ መሆኑን ታውቃለህ
ልቡ ልቡን ቢሰጠኝ ልቡን .....
አልመኝም አልማዝ ወርቅ እንቁ ስጦታውን
ከሺ አልማዝ ከብዙ እንቁ ከሺ ሀብት
ፍቅር ይበልጣል ከልብ አክብረው ከያዙት
እርከን አብጅለት ለገላህ መሄጃ
ተበትኖ እንዳያልቅ ሳይኖረው ማገጃ
አንተ አንተን ብቻ ወደድኩህ ማለቴ
ምን ይመስልህ ይሆን ላንተ ምክኒያቴ
መውደዴን ከልቤ ገልጠህ ብታየው
ታዝንልኝ ነበር ትጠነቀቅልኝ
ዐይን ወረተኛ አዲስ አዲሱን
መቼም አይከደን ሳይገል ያየውን
ጨዋ ሰው ባልጠፋ በሞላው ሀገር
ኧረ ምን ይሉታል ባንተ መቸገር
አይቺሉት መከራ ስቃይ ጉዞ ........
ልቻለው ፍቅር ነው ፍቅር ነው መንገዴ

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics