Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
#አስቴር አወቀ#እርቄ ሂጃለው


ጊዜው ይርዘም እንጂ
መች እረሳሃለው
በሆነ ባልሆነው
እናፍቅሃለው
አይግረምክና
ዛሬም ወድሃለው
አንጀቴን አስሬ
ይኸው እኖራለው
እርቄ ሄጃለሁ
ሁሉን ትቼ
ትዝታን በልቤ
አስቀርቼ
ምነው የምቀጣ
የምቸገር
ከቶ ምን ይሆን
የአንተ ፍቅር
ተማምነው ተዋደው
አብረው የኖሩት
ሲለዩት ይፋጃል
እንደ እግር እሳት
በልቤ ወድጄ
በአፌ የማቀብጥህ
ትቼ የማልተውህ
እኔው ነኝ ወዳጅህ
አይቻልምና
የአንዳንድ ስው ናፍቆት
መውደድን በወጉ
ፍቅር ያስተማሩት
እርቄ ሄጃለሁ
ሁሉን ትቼ
ትዝታን በልቤ
አስቀርቼ
ምነው የምቀጣ
የምቸገር
ከቶ ምን ይሆን
የአንተ ሚስጥር
የልቤ ምሰሶ
ዘንጉ ተሠበረ
የማይመነጠር
ምሽግ የነበረ
በፅኑ ትዝታ
እራቀው መንገዴ
እስቲ ላሠላስልህ
ደግሞ እንደ ልማዴ
ኢየው ልቤ ጥሎኝ
ተነስቶ ሲሄድ
ባንተ መወስወሱን
አድርጎ ልማድ
Ethiopian music lyrics:
#አስቴር አወቀ#እርቄ ሂጃለው


ጊዜው ይርዘም እንጂ
መች እረሳሃለው
በሆነ ባልሆነው
እናፍቅሃለው
አይግረምክና
ዛሬም ወድሃለው
አንጀቴን አስሬ
ይኸው እኖራለው
እርቄ ሄጃለሁ
ሁሉን ትቼ
ትዝታን በልቤ
አስቀርቼ
ምነው የምቀጣ
የምቸገር
ከቶ ምን ይሆን
የአንተ ፍቅር
ተማምነው ተዋደው
አብረው የኖሩት
ሲለዩት ይፋጃል
እንደ እግር እሳት
በልቤ ወድጄ
በአፌ የማቀብጥህ
ትቼ የማልተውህ
እኔው ነኝ ወዳጅህ
አይቻልምና
የአንዳንድ ስው ናፍቆት
መውደድን በወጉ
ፍቅር ያስተማሩት
እርቄ ሄጃለሁ
ሁሉን ትቼ
ትዝታን በልቤ
አስቀርቼ
ምነው የምቀጣ
የምቸገር
ከቶ ምን ይሆን
የአንተ ሚስጥር
የልቤ ምሰሶ
ዘንጉ ተሠበረ
የማይመነጠር
ምሽግ የነበረ
በፅኑ ትዝታ
እራቀው መንገዴ
እስቲ ላሠላስልህ
ደግሞ እንደ ልማዴ
ኢየው ልቤ ጥሎኝ
ተነስቶ ሲሄድ
ባንተ መወስወሱን
አድርጎ ልማድ

shear to your frinds
@ethiopian_music_lyrics
#አስቴር_አወቀ # ስኳር


አለሜ መቼም እንደ ስኳር
አለሜ ይጣፍጣል ስምህ
አለሜ ደግሞም ምን ሊባል ነው
አለሜ ወደድኩኝ ደግሜ
አለሜ ጠይመይ ቀይ ዳማው
አለሜ ልዩ ነው ቀለሙ
አለሜ እንደው እንደ ስኳር
አለሜ ይጣፍታል ስሙ
እንደው እንደው ስሙ(3)
እንደው እንደው ስኳር ስኳር ስኳር ኣለኝ
ብቀምሰው ከንፈሩንተመኘሁኝ
አቤት አቤት አቤት እንዴት እሆናለው ባይ
ሰዉነቱን
አቤት አቤት አቤት(2) ያንተንስ ፈራሁኝ
እህል ኳንዳለኝ ያንተንስ ፈራሁኝ ለሩቅ
ትቀመሳለህ____ ትጣፍጣለህ እንደው እንደ ማር
እንደ ስኳር እንደ ስኳር
ስምክን ቢጠራ በየደቂቃው ኣትጠገብምበሚጣፍጠዉ እንደው
ትላለ ስኳር ስኳር
አለሜ ሳመኝ በከንፈርህ
አለሜ
አለሜ ኣዲስ ነገር የለም
አለሜ ጉዴ ኣንዲት ሰሞን ነው
አለሜ እኔም ስኳር ነኝ
አለሜ ፍቅር ነኝ ፍቅር
አለሜ ለወደደኝ ደስታ
አለሜ ላፈቀረኝ ማር
እንደው እንደው ስሙ(3)
እንደው እንደው ስኳር ስኳር ስኳር ኣለኝ
ብቀምሰው ከንፈሩን
አቤት አቤት አቤት እንዴት እሆናለው ባይ
ሰውነቱን
አቤት አቤት አቤት(2) ያንተንስ ፈራሁኝ
እህል ኳንዳለኝ ያንተንስ ፈራሁኝ ለሩቅ ተመኘሁን
ትቀመሳለህ____ ትጣፍጣለህ እንደው እንደ ማር
እንደ ስኳር እንደ ስኳር
ስምክን ቢጠራ በየደቂቃው ኣትጠገብም እንደው
ትላለ ስኳር ስኳር
አለሜ መቼም እንደ ስኳር
አለሜ ይጣፍጣል ስምህ
አለሜ ደሞም ምን ሊባል ነው
አለሜ ወደድኩኝ ደግሜ
አለሜ ጠይመይ ቀይ ዳማው
አለሜ ልዩ ነው ቀለሙ
አለሜ እንደው እንደ ስኳር
አለሜ ይጣፍታል ስሙ
እንደው እንደው ስሙ(3)
እንደው እንደው ስኳር ስኳር ስኳር ኣለኝ
ብቀምሰው ከንፈሩን
አቤት አቤት አቤት እንዴት እሆናለው ባይ
ሰዉነቱን (2)
አቤት አቤት አቤት(2) ባይ ሰውነቱንሰዉነቱን
እንዴት እሆናለው ባይ ሰዉነቱን
ስኳር ስኳር ኣለኝ ብቀምሰው ከንፈሩን
እንዴት እሆናለው
አይ
አይ ሰዉነቱን
አይ ሰዉነቱን
ባይ ሰዉነቱን
ባይ ሰዉነቱንንንንንንንንንንንንንንንንንን

Shear to your best friends for more lyrics @ethiopian_music_lyrics
#አስቴር_አወቀ # አይዞኝ

ደርሶ ድንገት ቢቸግረኝ
ውሃ ውሃ ቢጠማኝ
ሰውነቴ ቢደክምብኝ
የፈጠረኝ ጥሎ አይጥለኝም
አይዞኝ አይዞኝ አይዞኝ አይዞኝ (2x)
አይዞኝ
አይዞኝ አይዞኝ አይዞኝ አይዞኝ(2x)
አረ አይዞኝ
ስራ ጠፍቶ ቢቸግርህ
ጤና ጠፍቶ ብተኛ ታመህ
ቀን ጨልሞ ቢታይህ
የሚደርስልህ ዘመድ አለህ
አይዞህ አይዞህ አይዞህ አይዞህ (2x)
አይዞህ
አይዞህ አይዞህ አይዞህ አይዞህ(2x)
አረ አይዞህ
ዙርያው ገደል ሆኖ እህህ..
ቢጨልምብህ እህህ...
ሃገርና ወገን እህህ..
ዘመድም አለህ ህህ..
በጣምም ቢጨንቅ እህህ..
ብታጣም መድረሻም አሃሃ..
ሃገር ወገን አለህ..
የሚሆን መሸሻ አአ..
ይመጣል ይሄዳል ፍቅርና ሰው
ወስዶ ማይመልስያ ሞት ብቻ ነው
ሆዴ ረጋ ረጋ በል እረጋ ረጋ
አትወርድ ቆላ አትውጣ ደጋ
አረ ወዴት ወዴት ወዴት ወዴት ነው
አንድም መኖር ነው
አንድም መሞት ነው (2x)
አው...
በሰው ሃገር ቢከፋሽ
የሰው ክፉ ቢያሳዝንሽ
ሃገር ወገንሽ ቢናፍቅሽ
እስኪያልፍ ያለፋል እቴ አይክፋሽ
አይዞሽ አይዞሽ አይዞሽ አይዞሽ(2x)
አይዞሽ
አይዞሽ አይዞሽ አይዞሽ አይዞሽ(2x)
አረ አይዞሽ
ሃገር ነፃ ሲሆን እኛም ነፃነን
ሰላም እንደር ሰላም ያውለም
መልካም እንዲሆን ለሁላችን
እንፀልያለን በህሊናችን
አይዞን አይዞን አይዞን አይዞን(2x)
አይዞን አይዞን
አይዞን አይዞን አይዞን (2x)
አረ አይዞን
Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#አስቴር_አወቀ #
እኔም_ሀገር_አለኝ
ሁሉም ሀገር ሀገር ሀገር ይላል
ይህ ሀገረ ብርቁ /2x
የሀገር ፍቅር ስሜት ልቤን አቃጠለው
መጥቼ የማያት ሀገሬን መቼ ነው
ሰላም ላንቺ ይሁን ለውዲቷ እናቴ
ካለሁበት ቦታ ከልብ ከናፍቆቴ
ካለሁበት ቦታ ከልብ ከናፍቆቴ
አመት በዓል ደረሠ ይገዛ አዲስ ልብስ
በጉ ዶሮ ይቅረብ ዳቦም ይቆረስ
ጨዋታው ሲደራ ዘመድ ሲደሰት
ትዝ ይለኝ ጀመረ እርቄ ስሄድ
ሀገሬ ኢትዮጵያ ለምለሟ አበባዬ
ሳስብሽ ይፈሳል እምባዬ በላዬ
ብደሰት ብጫወት ሳይነካ ክብሬ
ባምር ብንቆጠቆጥ እኔስ በሀገሬ
የወንዜ ፏፏቴ አቀማመጥሽ
ለምለሟ ሀገሬ እምዬ ድምቀትሽ
ሁሉም ሀገር ሀገር ሀገር ይላል
ይህ ሀገረ ብርቁ
እኔም ሀገር ሀገር ሀገር አለኝ
የሚታይ በሩቁ
ሁሉም ሀገር ሀገር ሀገር ይላል
ይህ ሀገረ ብርቁ /2x
Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#አስቴር_አወቀ #ወይኔ_ጉዴ_ፈላ
ልቤን እንደበላ ልብህን ሳልበላ
ስታንሰፈስፈኝ አንጀቴን ስትበላ
ዘንድሮስ ተሸነፍኩ ወይኔ ጉዴ ፈላ (2x)
እኔስ ጉዴ ፈላ ወይኔ ጉዴ ፈላ (4x)
ስትልብኝማ ዝንጥንጥ ቅብጥብጥ
ሆዴን እክክ አድርገክ ምራቄን ስታስውጥ
አመለጠኝ ብዬ ስፈራ ስፈራ
ጭንቀቴ አይወራ ውሉ አይወራ
ውይ ውዩ ውዩ ውሉ አይወራ(4x)
አካልክ በሙሉ ፍቅርን ያነገቡ
አድፍጠው ከቃሉ በሰዎች ሲገቡ
ስነሳ ተነሳው ስተኛ እተኛለሁ
በሱስክ ተጠምደው አንተን ያዛጋሉ
ዎዬ ኦ ዎዬ ኦ
በፍቅርክ ሞቅታ አካሌን ስትረታ
መንፈሴን ሰብስበክ ስታለብስ እርካታ
ከስንቶቹ ወንዶች ከብዙ ጋጋታ
በፍቅር ጨዋታ ነህ እኮ አንድ ጌታ
አንድ ጌታ(4X)
ልቤን እንደበላ ልብህን ሳልበላ
ስታንሰፈስፈኝ አንጀቴን ስትበላ
ዘንድሮስ ተሸነፍኩ ወይኔ ጉዴ ፈላ (2x)
እኔስ ጉዴ ፈላ ወይኔ ጉዴ ፈላ(4X)
አንተ የወንድ አውራ የፍቅር ሳተና
ሲፈጥርክ የተቻርክ መለሎ ቁመና
የአካሉ ንጉስ የጀግኖቹ ጀግና ተው አታንገላታኝ ቶሎ ና ቶሎ ና
ዎዬ ኦ ዎዬ ኦ
ስትልብኝማ ዝንጥንጥ ቅብጥብጥ
ሆዴን እክክ አድርገክ ምራቄን ስታስውጥ
አመለጠኝ ብዬ ስፈራ ስፈራ
ጭንቀቴ አይወራ ውሉ አይወራ
ውይ ውዩ ውዩ ውሉ አይወራ(4x)
ልቤን እንደበላ ልብህን ሳልበላ
ስታንሰፈስፈኝ አንጀቴን ስትበላ
ዘንድሮስ ተሸነፍኩ ወይኔ ጉዴ ፈላ (2x)
እኔስ ጉዴ ፈላ ወይኔ ጉዴ ፈላ (4x)

Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics
#አስቴር_አወቀ #ጠንበለል
ጥርት እንደ ሰማይ ልቅም እንደ ስንዴ
አጀብ የደም ግባት እንዲህም አለ እንዴ
አልሻም ብር አምባር ጉትቻ ቀለበት
የኔ ጌጥ እሱ ነው የውበቴ ውበት
ዛላው ዘለግ ያለ የባህር ማሽላ
ልቤን እንክት አርጎ በፍቅር የበላ
እሱንም ስወደው ልቡን በጣም ሰምነው
በክፉ እሚያነሣው እንዴት ያለ ሰው ነው
መላ ሆዴ ቀጭን ኩታ ለብሶ
መጣ እየጋለበ ኮርኩሮ ፈረሱን
ያውና ከማዶ መጣሲንጎማለል
አካል ሸሞንሟና ዘንካታ ጠንበለል
አሀ ጠንበለል አ…. ጠንበለል
አሀ ጠንበለል አሀሀሀ ጠንበለል
አይናማ ነው ሎጋ አየሁት ተናዞ
ልቤን ከልቡ ጋር አነባብሮ ይዞ
ቀለብ አይሆነውም አልሰጥም አንጀቴን
ያውለት እንጀራ የወዳጅነቴን
የትውልድ አገሩ እሱን የበቀለ
ሌላ አላፈራም ወይ እየቀላቀለ
ልበ ኩሩ ነበርኩ አንጀተ ደንዳና
እንስፍስፍ አልኩ እንጂ እሱን ወደድኩና
Shear to your best friend for more lyrics
@ethiopian_music_lyrics