Ethiopian music lyrics
274 subscribers
52 photos
1 video
1 file
8 links
የተለይዩ አዲስ እና የድሮ የሀገራችን ዘፈኖች ላይሪክስ እዚህ ላይ ያግኛሉ ።
Download Telegram
#ብስራት_ጋረደው #ሳላያት_ውዬ_አላድር
አያስቀረኝ ምሽት ፅልመት
እሄዳለሁ ላያት ካለችበት
ባይገታኝ አራዊቱ
ጀግና አርጎኛል ፍቅሯ ልበ ብርቱ
አልፈራሁም አላመነታ
ዓይኗን ካላየሁ የለኝም ፋታ
የሚመጣውን በውድቅት
በፍቅር አምላክ ከገዘትኩት
እሄዳለሁ አይነጋም ሌቱ
ፍቅሯ አክንፎኛል ያው ባለ መብቱ
ፋታ ነስቶኝ ፀንቶ መናፈቅ
አልጠብቅ ጀንበር እስክትፈነጥቅ
በነጎድጓድ ቢያወርደው ሰማይ ዶፉን
ማየት አይሳነውም ዐይኔም ውዱን
ተጋፍጬ አልፌ ሁሉንም ነገር
ያለ ጥርጥር ሳላያት ውዬ አላድር
ተላልፌ አራዊቱንም
ወስኛለሁ አልቀር አሁንም
አልፈራም የሌት አጋንንቱንም
ቢበረታ ቢያይል መውገድ
እሄዳለሁ ላያት ያችን የኔ ውድ
እኔን ፅልመት መቼ ይገርመኛል
አውቃለሁ ሁሉን ፍቅር ይክሰኛል
በነጎድጓድ ቢያወርደው ሰማይ ዶፉን
ማየት አይሳነው ዓይኔም ውድን
ተጋፍጬ አልፌ ሁሉንም ነገር
ያለ ጥርጥር ያለ ጥርጥር
ሳላያት ውዬ አላድር

Shear to your best friend for more lyrics@ethiopian_music_lyrics