African Leadership Excellence Academy
2.37K subscribers
2.59K photos
97 videos
6 files
121 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
ኮይካ ኢትዮጵያ KOICA- Ethiopiaም በአፍሪካ ፕሮግራሞች ላይ በዲዛይን እና ፕሮግራም ቀረጻ ፤ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችን ወደ አፍሌክስ እንዲያመጣ እና በሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ግንባታ ከአፍሌክስ ጋር በትብብር እንዲሰራ አቶ ዛዲግ ግብዣ አቅርበዋል።
የኮይካ ኢትዮጵያ KOICA- Ethiopia ካንትሪ ዳይሬክተር ቾ ሀን ዴኦግ Cho Han Deog በበኩላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ የልማት ስራ እየሰሩ እንደሆነ ገልጸው፤ የአፍሌክስን የአመራር ልማት ፕሮግራምን በቴክኒክ ለመደገፍ በኮሪያ ከሚገኙ የስልጠና እና የትምህርት ተቋማት ጋር በመነጋገር ምሁራን እና ኤክስፐርቶችን በፕሮግራም ቀረጻ እና ትግበራ ላይ አብረው እንዲሰሩ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። የሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ግንባታ ላይ ለመሳተፍም ቀጣይ ውይይት ማድረግ የሚቻልበት ዕድል እንዳለ ሀሳብ አቅርበዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና የፌደራል ስነ-ምግባርና ጸረ- ሙስና ኮሚሽን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ
****************
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና የፌደራል ስነ-ምግባርና ጸረ- ሙስና ኮሚሽን አመራሮች ጠንካራ የስነምግባር ስብዕና እንዲኖራቸውና ሃላፊነታቸውን መወጣት እንዲችሉ የሚረዳ የስነምግባር ማሰልጠኛ ማዕከል በጋራ ለመገንባት ስምምነት አድርገዋል።
የአካዳሚው ርእሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብረሃ እንደተናገሩት ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት ውጤታማና ግልጽ አሰራር እንዲኖራቸው የሚያግዝ ነው።
ተቋማት ስነምግባርና ሀቀኝነት ላይ ማዕከል አድርው መስራት እንደሚገባቸው አቶ ዛዲግ ተናግረዋል።
የፌደራል ስነ -ምግባርና ጸረ- ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ በበኩላቸው ስምምነቱ በመንግስት፣ በልማት ድርጅቶችና በህዝባዊ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ አመራሮችና ሰራተኞች ስነ-ምግባር የተላበሱና ሙስናን የሚታገሉ እንዲሆኑ ሚያስቸል ነው።
በአካዳሚው ውስጥ የሚገነባው ማዕከል ኮሚሽኑ የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ለመስጠት ያስችለዋል ብለዋል።
የማዕከሉ ግንባታ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።
የአካዳሚውን ፋሲሊቲ እና መሰረተ ልማቱን የጎበኙ ሲሆን ከአፍሌክስ ጋር ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ለማድረግም ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በጋራ ሊሰሩ በሚችሉባቸው መስኮች ዙሪያ ተወያዩ።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከድርጅቶቹ ለመጡ የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች የአፍሌክስን የአመራር ልማት ፕሮግራሞች እና የሶስት ዓመት ስትራቴጂ ሰፊ ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎችም አብራርተዋል።
በሀገራችን በሁሉም ዘርፍ ያለውን አመራር አቅም ለመገንባት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለአፍሌክስ ስልጣን እንደሰጠው የገለጹት አቶ ዛዲግ፤ በሲቪል ማህበራት ውስጥ ያሉ አመራሮችን በአፍሌክስ ጠቅላላ እና ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ላይ በማካተት አብረው ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እንደ ስሙ አፍሪካዊ ቅርጽ እና ይዘት እንዲኖረውም የሲቪል ማህበረሰቡ ለአፍሪካውያን ተማሪዎች አዲስ በሚከፈቱ የማስተርስ ትምህርት ካሪኩለም ልማት እና በጠቅላላ እና በልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራም ዲዛይን ቀረጻ ላይ ሲቪል ማህበረሰቡ ከአፍሌክስ ጋር ሊሰራ የሚችልበት መንገድ እንዳለ የጠቆሙት አቶ ዛዲግ የራሱን ሀገራዊ አሻራ እንዲያሳርፍ እና በአፍሌክስ የመሰረተ ልማት ማስፋፋት ላይ አብረው እንዲሰሩ ጋብዘዋል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የሲቪል ማህበረሰቡ ተወካዮች በበኩላቸው አፍሌክስ የጀመረው ሪፎርም፤ ማስፋት እና ሽግግር ኢትዮጵያን ወደ ላቀ ከፍታ የሚያደርስ መንገድ ከመሆኑም በላይ ከአፍሪካውያን ጋር የሚያስተሳስረን በመሆኑ ያለንን ልምድና ዕውቀት ተጠቅመን የአፍሪካ አመራር ልህቀትን የስኬት መንገድ እናግዛለን ብለዋል።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ በአፍሪካ ህብረት የትምህርት፤ የሳይንስ፤ የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ሞሀመድ ቤልሆሲኔ Professor Mohammed Belhocine, Commissioner for Education, Science, Technology and Innovation (ESTI) ጋር ተወያዩ።
አቶ ዛዲግ በአካዳሚው የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች ዙሪያ ለኮሚሽነሩ ገለጻ አድርገውላቸዋል።
ገለጻውን ያዳመጡት ኮሚሽነሩ በሰጡት አስተያየት ከአፍሌክስ ጋር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር ከአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ በሁዋላ ቀጠሮ እንዲያዝላቸውና በዝርዝር ለመነጋገር ዝግጁ እንደሆኑ ተናግረዋል።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ በምስራቅ አፍሪካ አርብቶ አደሮች ኤክስፖ East Africa Pastoralist Expo ላይ በመገኘት የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች ለኤክሰፖው ተሳታፊዎች ገለጻ አድርገዋል።
በተለይም አካዳሚው በልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሙ ውስጥ የአርብቶ አደር ፕሮግራም ማካተቱን እና የዘርፉን አመራርና ባለሙያ አቅም ለመገንባት እየተሰራ እንደሆነ አቶ ዛዲግ አብራርተዋል።
ከአርብቶ አደር ጋር በተያያዘ ያለውን የጥናት እና ምርምር ስራዎች ለማስፋት እና የዘርፉ አመራር በሀሳብ ማመንጫ ማዕከላት ውስጥ ሆነው ጥናትና ምርምር ለማድረግ እንዲችሉም በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ውስጥ Center for Pastoralist Economic Transformation (CPET) እንዲገነባ ሀሳብ አቶ ዛዲግ ሀሳብ አቅርበዋል።
በዘርፉ የተሻለ የስራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎችም ሀገር አቀፍ ሽልማት እና ዕውቅና የሚሰጥበት የአፍሌክስ አዋርድ ፕሮግራም እንደሚኖርም አቶ ዛዲግ ገልጸዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ባቀረቧቸው ሶስቱም ፕሮጀክቶች ላይ የጋራ መግባባት የተፈጠረ ሲሆን በቀጣይ ሳምንታት ለሀሳብ ማመንጫ ማዕከሉ ስራ እንደሚጀመር ታውቋል።