African Leadership Excellence Academy
2.34K subscribers
2.55K photos
96 videos
6 files
119 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን-ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ያለው በበኩላቸው ስለ አፍሌክስ በተደረገላቸው ማብራሪያ አመስግነው በሌሎች ሀገራት የሚገኝ የአመራር ማሰልጠኛ ማዕከል እና መሰረተ ልማት አይነት በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለመስራት መታቀዱ የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው አፍሌክስ የጀመረው ሪፎርም፤ ማስፋት እና ሽግግር ኢትዮጵያን እና አፍሪካን የሚያጎላ በመሆኑ በወጣቶች ስራ ፈጠራ እና ልማት፤ በሴቶች አቅም ግንባታ፤ በሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት ዙሪያ ከፋውንዴሽኑን ተልዕኮ እና ዓላማ ጋር በተናበበ መልኩ ከአፍሌክስ ጋር ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
የአፍሪካ አመራር ለህቀት አካዳሚ እና ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን-ኢትዮጵያ በጋራ ሊሰሩ በሚችሉባቸው መስኮች ዙሪያ ተወያዩ።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ለማስተር ካርድ ፋውንዴሽን-ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ያለው የአፍሌክስን የአመራር ልማት ፕሮግራሞች እና የሶስት ዓመት ስትራቴጂ ሰፊ ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎችም አብራርተዋል።
ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን-ኢትዮጵያ በወጣቶች ልማት እና ስራ ፈጠራ ዙሪያ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ዛዲግ በአፍሌክስ ጠቅላላ እና ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ላይ ተተኪ እና ሴት አመራሮችን አቅም ለመገንባት በተያዘው ዕቅድ ውስጥ ፋውንዴሽኑ በፕሮግራም ቀረጻ እና በቴክኒክ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እንደ ስሙ አፍሪካዊ ቅርጽ እና ይዘት እንዲኖረው በተሰራው ሪፎርም ውስጥም አፍሪካውያን ወጣቶች የሚገናኙበት እና ስለ አህጉሪቱ ልማት በሰፊው ተወያይተው የስራ ፈጠራ ችሎታቸውን የሚያዳብሩበት ተቋም እንዲሆን ፋውንዴሽኑ የመሰረተ ልማት፤ የማስተርስ ትምህርት እና የአመራር ልማት ፕሮግራም ዲዛይን ላይ ከአፍሌክስ ጋር ሊሰራ የሚችልበት መንገድ እንዳለ የጠቆሙት አቶ ዛዲግ የፋውንዴሽኑ ጉባኤዎችም በአፍሌክስ ማዕከል ውስጥ በሚደረጉበት ሁኔታ ላይ ሀሳብ አቅርበዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራር እና ሰራተኞች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተዘጋጀውን የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ኤግዚቢሽን ጎበኙ።
በኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) የተመራው ቡድን በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ኤግዚቢሽን ጎብኝቷል።
ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) በጉብኝቱ ላይ እንደተናገሩት ኤግዚቢሽኑ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እና ለዓለም ሰላም ያበረከተቸውን አስተዋጽኦ በግልጽ የሚያሳይ እንደሆነ ጠቁመው፤ የአሁኑ ትውልድም ቀደምት አባቶቹ በዓለም ዲፕሎማሲ መስክ ያስመዘገቡትን ድል እያስቀጠለ እንደሚገኝ ተመልክተናል ብለዋል።
ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) አያይዘውም የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራርና ሰራተኞች ለሀገር ልማት እና ብልጽግና የሚያበረክቱትን ድርሻ በጉልህ እንዲወጡ ጉብኝቱ የራሱን በጎ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል።
በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉ አመራሮች እና ሰራተኞች በበኩላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሀገራችንን የዲፕሎማሲ ታሪክ ሌሎች እንዲያውቁ ማድረጉ ትላንት የት እንደነበር እና ወደፊት የምንደርስበትን መንገድ ያመላከተ በመሆኑ ለአካዳሚው ተልዕኮ ስኬታማነት የስራ መነሳሳትን እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከ Global Center for Gender Equality ከመጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊ ጋር ተወያዩ:: Alex Munive በማዕከሉ Feminist Leadership ዳይሬክተር ሲሆኑ ስለ አፍሌክስ ሪፎርም: ሽግግር እና ማስፋት ፕሮግራም ገለፃ ተደርጎላቸዋል:: የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በጠቅላላ የአመራር ልማት ፕሮግራሙ ከቀረፃቸው አራት ፕሮግራሞች ውስጥ የሴቶች የአመራር ልማት ፕሮግራም አንዱ በመሆኑ ከማዕከሉ ጋር በትብብር መስራት እንደሚፈልጉ አቶ ዛዲግ ተናግረዋል::
Alex Munive በበኩላቸው ማዕከላቸው የአፍሌክስን የሴቶች የአመራር ልማት ፕሮግራም ለመደገፍ እና አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ጠቅሰው በፊንላንድ ሄልሲንኪ ከሚገኘው ተቋማቸው ጋር ውይይት በማድረግ ሁለቱ ተቋማት በትብብር የሚሰሩባቸውን መስኮች በመለየት ወደ ስራ እንደሚገቡ ገልጸዋል::
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከUNDP Regional Service Center for Africa ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ::
ርዕሰ አካዳሚው ለማትያስ ዘ. ናብ (ዶ/ር) Matthias Z. Naab (PhD) አፍሌክስ በሶስት ዓመት ውስጥ ስለሚተገብራቸው የአመራር ልማት ፕሮግራሞች እና ስለ ሪፎርም: ሽግግር እና ማስፋት ገለፃ አድርገውላቸዋል::
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በጠቅላላ (General) አራት እና በልዩ (Specialized )ሰላሳ ሰባት የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ቀርፆ ወደ ስራ እንደገባ የጠቀሱት አቶ ዛዲግ ለሁሉም ፕሮግራሞች ማስፈፀሚያ የሚሆን ከ2,500 በላይ ገፆች ያሉት ዝርዝር ስትራቴጂ እንደተዘጋጀ ለዳይሬክተሩ አብራርተዋል::
አቶ ዛዲግ አያይዘውም አፍሌክስ አስራ ሶስት የአመራር ልማት ፕሮግራም ማዕቀፍ ለይቶ እንዳዘጋጀ እና ለስምንቱ ቅድሚያ ሰጥቶ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት ባለ ድርሻ አካላት ጋር እየሰራ እንደሆነ እና ከ ዩ ኤን ዲ ፒ ጋርም በትብብር በመስራት አፍሌክስን ለሀገራችን እና ለአፍሪካዊያን መሪዎች የልህቀት ተቋም ለማድረግ እንደሚፈልጉ አቶ ዛዲግ ተናግረዋል::
ማትያስ ዘ. ናብ (ዶ/ር) Matthias Z. Naab (PhD) በበኩላቸው አፍሌክስ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያቀደው የሪፎርም: የማስፋት እና የሽግግር ስትራቴጂ የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው: የአመራር ልማት ፕሮግራሙ እንዲሳካ ዩ ኤን ዲ ፒ አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል::
ከአፍሌክስ ጋር ስትራቴጂያዊ አጋር በመሆን በትብብር ለመስራት እንዲቻልም ቀጣይ ውይይቶች እንደሚኖሩም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል::
አቶ ዛዲግ አብርሃ ከኮይካ ኢትዮጵያ KOICA- Ethiopia ካንትሪ ዳይሬክተር ቾ ሀን ዴኦግ Cho Han Deog ጋር ተወያዩ።
ካንትሪ ዳይሬክተሩ ስለ አፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ሪፎርም፤ ማስፋትና ሽግግር በርዕሰ አካዳሚው ሰፊ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
አቶ ዛዲግ በገለጻቸው ላይ እንዳብራሩት አካዳሚው አስራ ሶስት ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ወደ ስራ እየገባ እንደሆነ እና በሀገራችን የነበረውን የስልጠና ስርአት ወደ አመራር ልማት ፕሮግራም ለማሳደግ ሰፊ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመው፤ ለዚህም የሚሆን አራት ጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።
አካዳሚው አፍሪካዊ መልክና ይዘት እንዲኖረውም አራት መሰረታዊ ክፍተቶችን ለመሙላት እየተሰራ እንደሆነ ያስታወሱት አቶ ዛዲግ፤ አሁን ያለውን ህንጻ የውስጥ ዲዛይኑ የአፍሪካ ውክልና እንዲኖረው ለማድረግ በቀድሞ የአፍሪካውያን መሪዎች እና ታዋቂ ሰዎች በመሰየም እና የአፍሪካን ታሪካዊ ምስሎችን እና ቅርጻ ቅርጾችን በማስቀመጥ ለመስራት መታቀዱን ገልጸዋል።
በምክትል ፕሬዚደንት ደረጃ ዘርፍ በማቋቋም በአፍሪካውያን የሚመራ ሁለተኛውን ክፍተት ለመሙላት እየተሰራ እንደሆነ እና በሶስተኛ ደረጃም አፍሪካውያን ተማሪዎችን ተቀብሎ በሁለተኛ ዲግሪ የሚያስተምር የትምህርት ፕሮግራም ለመክፈት እየተሰራ ነው ያሉት አቶ ዛዲግ አፍሪካውያንን የሚወክል ራሱን የቻለ ቦርድ በማቋቋም ላይ እንገኛለን ብለዋል።
አፍሌክስን የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግም ሱሉሉታን እንደ ዳቮስ የሚል ፕሮጀክት መቀረጹን ያስታወሱት ርዕሰ አካዳሚው፤ ሸገር ሲቲን ከዳቮስ ከተማ ጋር በእህትማማች ከተማ ለማገናኘት ስራ መጀመሩንም ተናግረዋል።
ኮይካ ኢትዮጵያ KOICA- Ethiopiaም በአፍሪካ ፕሮግራሞች ላይ በዲዛይን እና ፕሮግራም ቀረጻ ፤ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችን ወደ አፍሌክስ እንዲያመጣ እና በሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ግንባታ ከአፍሌክስ ጋር በትብብር እንዲሰራ አቶ ዛዲግ ግብዣ አቅርበዋል።
የኮይካ ኢትዮጵያ KOICA- Ethiopia ካንትሪ ዳይሬክተር ቾ ሀን ዴኦግ Cho Han Deog በበኩላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ የልማት ስራ እየሰሩ እንደሆነ ገልጸው፤ የአፍሌክስን የአመራር ልማት ፕሮግራምን በቴክኒክ ለመደገፍ በኮሪያ ከሚገኙ የስልጠና እና የትምህርት ተቋማት ጋር በመነጋገር ምሁራን እና ኤክስፐርቶችን በፕሮግራም ቀረጻ እና ትግበራ ላይ አብረው እንዲሰሩ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። የሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ግንባታ ላይ ለመሳተፍም ቀጣይ ውይይት ማድረግ የሚቻልበት ዕድል እንዳለ ሀሳብ አቅርበዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና የፌደራል ስነ-ምግባርና ጸረ- ሙስና ኮሚሽን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ
****************
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና የፌደራል ስነ-ምግባርና ጸረ- ሙስና ኮሚሽን አመራሮች ጠንካራ የስነምግባር ስብዕና እንዲኖራቸውና ሃላፊነታቸውን መወጣት እንዲችሉ የሚረዳ የስነምግባር ማሰልጠኛ ማዕከል በጋራ ለመገንባት ስምምነት አድርገዋል።
የአካዳሚው ርእሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብረሃ እንደተናገሩት ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት ውጤታማና ግልጽ አሰራር እንዲኖራቸው የሚያግዝ ነው።
ተቋማት ስነምግባርና ሀቀኝነት ላይ ማዕከል አድርው መስራት እንደሚገባቸው አቶ ዛዲግ ተናግረዋል።
የፌደራል ስነ -ምግባርና ጸረ- ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ በበኩላቸው ስምምነቱ በመንግስት፣ በልማት ድርጅቶችና በህዝባዊ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ አመራሮችና ሰራተኞች ስነ-ምግባር የተላበሱና ሙስናን የሚታገሉ እንዲሆኑ ሚያስቸል ነው።
በአካዳሚው ውስጥ የሚገነባው ማዕከል ኮሚሽኑ የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ለመስጠት ያስችለዋል ብለዋል።
የማዕከሉ ግንባታ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።
የአካዳሚውን ፋሲሊቲ እና መሰረተ ልማቱን የጎበኙ ሲሆን ከአፍሌክስ ጋር ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ለማድረግም ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል።