አቶ ዛዲግ አብርሃ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ፕሬዚደንት አቶ አቤ ሳኖ ጋር ተወያዩ።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ በውይይቱ ላይ የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎችን አብራርተዋል።
ርዕሰ አካዳሚው ባቀረቡት ገለጻ ላይ እንደጠቀሱት አካዳሚው በልዩ የቢዝነስ አመራር ልማት ፕሮግራሙ የዘርፉን አመራርና ባለሙያዎች ለማብቃት ማቀዱን ገልጸው በፕሮግራም ቀረጻ እና ትግበራ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።
አቶ ዛዲግ አያይዘውም በአፍሌክስ ውስጥ ከሚገነቡ የሀሳብ ማመንጫ ማዕከላት ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የአመራር ማዕከል እንዲገነባ እና የባንኩ አመራሮችና ባለሙያዎች በማእከሉ በመጠቀም በጥናትና ምርምር ስራ ውስጥ የተሻለ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ፕሬዚደንት አቶ አቤ ሳኖ በበኩላቸው አፍሌክስ ለትውልድ የሚሸጋገር እና ከፍተኛ አመራሩን በተሟላ የአመራር ልማት ፕሮግራም ማዕቀፍ ውስጥ ለማብቃት ማቀዱን አድንቀው ከተቋማቸው ጋር በምን መልኩ መስራት እንደሚቻል ሰፋ ያለ የባለሙያዎች ውይይት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ከዲጂታል የአመራር ማዕከል ግንባታ ጋር በተያያዘም ከባንኩ የቦርድ አመራሮች እና ይህንኑ ከሚያጠና የባለሙያ ቡድን ጋር በመነጋገር በሚቀርበው ምክረ ሀሳብ መሰረት ከአፍሌክስ ጋር አብሮ ለመስራት ሀሳብ አቅርበዋል።

አቶ ዛዲግ አብርሃ ከግሎባል ኢነርጂ አሊያንስ ፎር ፒፕል ኤንድ ፕላኔት (The Global Energy Alliance for People and Planet) (GEAPP) ካንትሪ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከካንትሪ ዳይሬክተሯ ኤናስ ጋር በአፍሌክስ ሪፎርም፤ ሽግግር እና ማስፋት ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን የአካዳሚው የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች ለካንትሪ ዳይሬክተሯ ገለጻ አብራርተዋል።
ርዕሰ አካዳሚው አቶ ዛዲግ በገለጻቸው ላይ እንዳብራሩት አካዳሚው ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካውያን የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ እንደሆነ እና ይህንን ዓላማውን ለማሳካትም አራት የጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ቀርጾ በሶሰት ዓመት ውስጥ ለመፈጸም እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
አፍሌክስን የዓለም አቀፍ የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግም ሱሉሉታን እንደ ዳቮስ የሚል ስትራቴጂ ተቀርጾ እየተሰራ እንደሆነ እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ይህንኑ ዓላማ ለማሳካት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችን በአፍሌክስ ውስጥ እንዲደረጉ ለዳይሬክተሯ ጥሪ አቅርበዋል።
ለግሪን ኢኮኖሚ የሚሰሩ ተቋማትም በአፍሌክስ የሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ውስጥ የመሰረተ ልማት ግንባታ በማካሔድ አብረው እንዲሰሩ እና የአፍሌክስ ስትራቴጂያዊ አጋር እንዲሆኑ አቶ ዛዲግ ሀሳብ አቅርበዋል።

ኤናስ አብደላ በበኩላቸው ስለ አፍሌክስ በተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው ከአፍሌክስ ጋር አብረው ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ሰጥተዋል። በኢትዮጵያ ያለው የኢነርጂ ሀይል እና አጠቃቀም ከአረንጓዴ ኢኮኖሚ ጋር እንዲጣጣም ለማድረግ ሰፊ ስራ እንደሚጠይቅ እና የዓለም አቀፉን ግብ ለማሳካትም ጥናት እና ምርምሮችን ማድረግ ተገቢ መሆኑን ጠቅሰው በዚህ ዘርፍ አፍሌክስ የሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ለመገንባት ያቀደው ዕቅድ ተግባራዊ እንዲሆን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ካንትሪ ዳይሬክተሯ ኤናስ በፕሮግራም ቀረጻ፤ በመሰረተ ልማት እና በቴክኒካል ድጋፍ መስኮች ከአፍሌክስ ጋር አብረው ለመስራት ተጨማሪ ውይይት እንዲኖር የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል። የአካዳሚውን ፋሲሊቲም ጎብኝተዋል።

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በአፍሌክስ የአመራር ልማት ቅጥር ውስጥ የሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ለመገንባት ተስማማ።
ኮሚሽኑ ይህን የገለጸው ከአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ነው።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከክቡር ኮሚሽነሩ ጋር በነበራቸው ውይይት በአፍሌክስ ሪፎርም፤ ሽግግር እና ማስፋት ዙሪያ ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን የአካዳሚው የሪፎርም የማስፋት እና የሽግግር ስራዎች ላይ ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር አብረው ለመስራት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
ክቡር ኮሚሽነሩ አቶ ደበሌ ቃበታ እንደተናገሩት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሶስት ዓመታት ውስጥ ሊፈጽም ያቀዳቸው የአመራር ልማት ፕሮግራሞች የሀገራችንን አመራር ወደ ታላቅ ከፍታ የሚያሸጋግሩ እና ትውልድን የሚቀርጹ በመሆናቸው አካዳሚው ውስጥ ከሚገነቡ አስራ ሶስት የሀሳብ ማመንጫ ማእከላት ውስጥ አንዱን በመገንባት በጉምሩክ ዘርፍ ጥናትና ምርምር እንዲደረግበት እንደወሰኑ ገልጸዋል።
ክቡር ኮሚሽነሩ አያይዘውም ኮሚሽናቸው ለአገር ልማትና ዕድገት እንደሚሰራ ገልጸው የአፍሌክስ የአመራር ልማት ፕሮግራም ማዕቀፍም ከሀገር አልፎ በአፍሪካ ላይ ተጽእኖ በመፍጠር ከአፍሪካውያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጋር የሚያገናኝ ድልድይ በመሆኑ የኮሚሽኑ ድጋፍ ባስፈለገበት ሁሉ አብረው ለመስራት ቃል ገብተዋል።
አቶ ዛዲግ በበኩላቸው በጠቅላላ እና በልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ላይ በጋራ ለመስራት እና ክቡር ኮሚሽነሩ ካላቸው ዓለም አቀፍ የሽልማት ልምድ በመነሳት በአፍሌክስ የአመራር ሽልማት ማዕቀፍ ላይ ልምዳቸውን እና ተሞክሮአቸውን እንዲያካፍሉ ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ ዛዲግ አብርሃ ከ UNDP, UNIDO, UNESCO, እና UN ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ተወያዩ።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ስለ አፍሌክስ ሪፎርም፤ ማስፋት እና ሽግግር ውይይት ያደረጉት ከዶክተር ራሚዝ አላክባሮቭ (Dr. Ramiz Alakbarov, UN Assistant Secretary General and UN Resident and Humanitarian Coordinator) ከአኡሬሊአ ፓትሪዚአ (Aurelia Patrizia Calabro, UNIDO Representative and Director of the Regional Office) ከሳሙኤል ግባይዴ ዶኤ (Samuel Gbaydee Doe, UNDP, Resident Representative) እና ከዶ/ር ሪታ ቢሶናኡዝ (Dr. Rita Bissoonauth, UNESCO Director of Addis Ababa Liaison Office to AU & UNECA and Representative to Ethiopia) ጋር ነው። የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከUN ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በአፍሌክስ ሪፎርም፤ ሽግግር እና ማስፋት ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች ለሀላፊዎቹ አብራርተዋል።
ርዕሰ አካዳሚው አቶ ዛዲግ በገለጻቸው ላይ እንዳብራሩት አካዳሚው ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካውያን የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ እንደሆነ እና ይህንን ዓላማውን ለማሳካትም አራት የጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ቀርጾ በሶሰት ዓመት ውስጥ ለመፈጸም እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።