በክቡር ጠቅላይ ሚ/ር የተሠጡ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተደረገ
ሱሉሉታ፡ ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም /አአልአ/ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በ2015 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዋና ዋና አፈፃፀም እና በስድስት ወራት የግምገማ መድረክ በክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ዐብይ አህመድ የተሠጡ አቅጣጫዎች ላይ በአካዳሚው ሱሉልታ አዳራሽ ውይይት አደረገ፡፡
ውይይቱ በማክሮ ኢኮኖሚ፣ ክፍላተ ኢኮኖሚ፣ መሰረተ ልማት፣ የሰው ሀብት ልማትና ማህበራዊ ጉዳይ እንዲሁም አስተዳደር፣ ፍትህና ውጭ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው፡፡
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ /ዶ/ር/ በ2015 በጀት የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የመንግስት ገቢና ወጪ፣ የጋራ ገቢ፣ የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የወጪ ንግድ፣ ተኪ ምርቶች፣ የዲጂታል ፋይናስ፣ የአገልግሎት ወጪ ንግድ፣ ሬሚታንስ፣ ፋይናስ ዘርፍና የዋጋ ግሽበት ላይ ሰፋ ያለ ገለፃ አድርገዋል፡፡
ዶ/ር ወንድዬ የስድስት ወራት አፈፃፀም ግምገማ ላይ ለገንዘብ ሚኒስቴር፣ ለገቢዎች ሚኒስቴር፣ ለፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ ለንግድ ዘርፍ፣ የተሰጡ አቅጣጫዎች ላይም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተካፈሉ የመስሪያ ቤቱ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በቀረበው ገለፃ ላይ ጥያቄና አስተያየት ያቀረቡ ሲሆን በአወያዩ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አከዳሚ አመራርና ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡
ሱሉልታ በሚገኘው የአካዳሚው የስልጠና ማዕከል 500 ሚሊዮን በአንድ ጀንበር የሚለው መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት ተከናውኗል፡፡
በችግኝ ተከላው ላይ የአካዳሚው አመራሮችን ጨምሮ በአካዳሚው ውስጥ በጸጥታ ስራ ላይ የተሰማሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

የአፍሪካ መሪዎችን በማሰልጠን የወደፊት ምጡቅ አፍሪካዊ መሪዎችን ለማፍራት ራእይ ይዞ እየሰራ እንደሚገኝ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አስታወቀ
************
የአካዳሚው ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር ሚዲያ አንዳሉት፥ ባለፉት 2 ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ በተለያዩ ደረጃ ለሚገኙ አስር ሺህ አመራሮች ስልጠና ሰጥቷል።
ስልጠናው በዋናነት ለፌደራል ተቋማት አመራርና ባለሙያዎች፣ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ለድፕሎማቶች፣ ለፌደራልና ለክልል ካቢኔዎች፣ ለየሴክተር አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች እየተሰጠ ነው።
አካዳሚው በፓንአፍሪካኒዝም፤ በኢትዮጵያ ስኬታማ በሆኑ እንደ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባሉ ተቋማት እና ከአመራር ጋር በተያያዙ በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ጥናት እየሰራ ይገኛል ተብሏል።
ኢትዮጵያ የምትገኝበት ጂኦግራፊዊ አቀማመጥ፣ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ መሆኗ፣ ነፃነቷን አስጠብቃ የቆየች ሀገር መሆኗ፣ ጥንታዊ ታሪክ ያላት ሀገር መሆኗ፣ በሀገረ መንግሥት ምስረታ ረጅም ታሪክ ያላት ሀገር መሆኗ በአፍሪካ ጉዳይ ልዩ ኃላፊነት እንድትሸከም አድርጓታል ነው ያሉት።