ጥቅምት 28፣ 2015 ዓ.ም (አአልአ) አካዳሚው ለኢትዮጵያ ጉልህ ጠቀሜታ የሚሰጡ የተለያዩ ስልጠናዎችን እየሰጠ መሆኑ ተገለፀ። ይሕ የተገለፀው በአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ውስጥ ለመካከለኛና ለከፍተኛ ዲፕሎማቶች በተዘጋጀ ስልጠና መክፈቻ ላይ ነው፡፡
የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ በስልጠናው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት አካዳሚው ለሀገር ግንባታ ትልቅ ሚና የሚኖራቸውን ስልጠናዎች እየሰጠ እንደሆነና የዛሬውም ስልጠና የዚሁ አንድ አካል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ርዕሰ አካዳሚው እንደገለፁት በስልጠናው ዲፕሎማቶች ብቃት ያለው ስብዓና እንዲላበሱ እና የላቀ የዲፕሎማሲ ሰራ ለመፈፀም የሚያስችል ከፍተኛ ስልጠና በአካዳሚው እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል ። ዶ/ር ምህረት አያይዘውም ዲፕሎማቶች ኢትዮጵያ ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ በመገንዘብ ለብሔራዊ ጥቅሟ መከበር አበክረው ሊሰሩ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በበኩላቸው ሥልጠናው በዲፕሎማሲ ባህልና ታሪክ ፣ በዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ሥርዓት ውስጥ ያሉ ወቅታዊ የዲፕሎማሲ ተግባራት ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የተለያዩ የዲፕሎማሲ ጫናዎች ውስጥ መሆኗን ጠቅሰው ፥ ዲፕሎማቶች ወቅቱን ያገናዘበ የዲፕሎማሲ ሥራ ሊያከናውኑ ይገባል ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት የዲጅታል ዲፕሎማሲ ስራን ማጠናከር ፣ እውነትን እና ሀቅን በመያዝ የተለያዩ አካላት ተፅዕኖ በመቋቋም ተልዕኮውን በአግባቡ የሚወጣ ዲፕሎማት እንደሚያስፈልግ ነው የገለጹት፡፡
አምባሳደር ብርቱካን ፥ የዲፕሎማቶችን ብቃት ለማሳደግ የሰው ኃይል ልማት ሥራ፣ የውጭ አገልግሎት አዋጅ ማሻሻያና ብዝሃነትን ያገናዘበ ምርጫ በማድረግ አቅምና ብቃት በመጨመር የበለጠ የመፈፀም አቅማችን እያጠናከርን ነው ብለዋል ።

ሴቶችን ወደ ውሳኔ ሰጭነት ለማምጣትና አቅማቸውን ለመገንባት እየተሰራ እንደሆነ ተገለፀ፡፡ በሴቶች አመራር ልማትና ማብቃት ፕሮጀክት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደርጓል ፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ ሕይወት አለማየሁ በምክክር መድረኩ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት አካዳሚው ከቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን (Bill and Melinda Gates Foundation) ጋር በመተባበር ሴቶችን ለማሳደግ የሚረዳ የሴቶችን የውሳኔ ሰጭነት ሚና ለማሳደግ የሚረዳ የሴቶች የአመራር ልማት ፕሮጀክት (WLDP) ቀርፆ ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዋል፡፡
ወ/ሮ ሕይወት አያይዘውም ፕሮጀክቱ ሊያሳካ ያቀዳቸውን ውጥኖች የጠቆሙ ሲሆን መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመተባበር ሴት አመራሮችን ለማብቃትና በቁልፍ የመካከለኛ አመራር ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ሚና እንዲኖራቸው ይሰራል ብለዋል ፡፡
የምክክር መድረኩም በፕሮጀክቱ ላይ የሚሳተፉ ሴት አመራሮችን ለመምረጥና በቀጣይ በጋራ መሰራት በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ለመወያየት እንደሆነ ም/ርዕሰ አካዳሚዋ ተናግረዋል ፡፡
የፕሮጀክቱ ማናጀር አቶ መስፍን በሃይሉ ስለ ፕሮጀክቱ አጠቃላይ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት የሚመረጡ የሴት አመራሮችን መስፈርት አብራርተዋል፡፡ በቀረበው ገለፃ ላይም ጥሪ የተደረገላቸው የተቋማት አመራሮች ጥያቄና አሰስተያየት ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ በቂ ምላሽም ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ ከ10 በላይ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡