African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የአካዳሚው ተቋማዊ ለውጥ ሀገራዊ ለውጡን የሚሸከም፣ ዓለም አቀፍ ስታንዳርዶችን የሚያሟላ፣ ትኩረቱ የፖለቲካ አመራር መገንባትን ሆኖ ለሁሉም የሀገሪቱ ተቋማት ያለማቋረጥ የአመራር ትምህርትና ሥልጠና፣ ምርምርና ማማከር አገልግሎት በመስጠት ፕሮፌሽናል መሪዎች በስፋትና ያለማቋረጥ የሚያፈራ ጠንካራ ስትራተጅክ ተቋም መገንባት የሚል ግልጽ ዓላማ አስቀምጧል፡፡ አቶ ጥላሁን አረጋ
EMBASSY sends letter to Invitation to Sino pharm Covid-19 vaccine Inoculation
Embassy of the People’s Republic of china sends letter to invitation to Sino pharm covid-19 vaccine inoculation to FDRE Melees Zenawi Leadership Academy.
According to the letter sent by the counselor’s office, the invitation is, to support Ethiopia’s anti-pandemic efforts and as an appreciation for the esteemed Academy’s contribution to friendly relations and win-win cooperation between China and Ethiopia, The counselor’s office would like to offer Academy 40 doses (for 20 people) of Sino pharm Covid-19 vaccine which has been authorized for emergency use by the WHO. The Silk Road Hospital in Addis Ababa will provide Inoculation service.
አካዳሚው ‹‹ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለዘላቂ አገራዊ ብልፅግና›› በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት በአዳማ ከተማ እያካሔደ ነው፡፡
በፓናሉ ላይ ‹‹ነፃ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ባህርያትና ምንነት በኢትዮጵያ›› እና ‹‹ዴሞክራሲያዊ ምርጫና የባለድርሻ አካላት ሚና›› የሚሉ ፅሁፎች የቀረቡ ሲሆን የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የፓናል ውይይቱ አሁን እየተካሔደ ነው፡፡
ፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የአካዳሚው ጥናትና ምርምር ዘርፍ ምክትል ፕሬዚደንት አቶ ደምሴ ሽቶ እንደተናገሩት ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ በሳይንሳዊ ትንታኔ የታገዘ እንዲሆንና በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መረጃን ለህዝቡ ተደራሽ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ምክትል ፕሬዚደንቱ አያይዘውም በአገራችን የተጀመረውን የለውጥ ሒደት የሚደግፉ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ለመደገፍና ለማበረታታት የፓናል መድረኩ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡
በፓናል ውይይቱ ላይ የፌዴራልና የክልል የስራ ኃላፊዎች፤ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፤ የሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች፤ ሙሁራን፤ የሲቪክ ማህበራት ኃላፊዎችና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡
አካዳሚውን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶች አግባብነትና ጥራታቸውን በማያቋርጥ ሁኔታ ማሻሻል እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
አካዳሚው እያከናወነ ባለው ተቋማዊ ሪፎርም መሠረት በአፍሪካም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን የሚሰጡ አገልግሎቶች አግባብነትና ጥራታቸውን ለማስጠበቅ በየጊዜው እያሻሻሉና ግንዛቤ እየፈጠሩ መሄድ እንደሚገባ የገለፁት የአካዳሚው የአግባብነትና ጥራት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ዘሪሁን ናቸው፡፡
በአካዳሚው በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮች እና ከየስራ ክፍሎቹ ለተወከሉ የአግባብነትና ጥራት አደረጃጀት ኮሚቴ አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ለማድረግ መታቀዱን አቶ ሲሳይ ገልፀዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አያይዘውም በአካዳሚው የሚሠጡ የተለያዩ አገልግሎቶችና የሚከናወኑ ተግባራት አግባብነትና ጥራታቸውን በዕውቀት ላይ ተመስርቶ ለማሻሻል የሚያስችሉ ስራዎችን ለማከናወን፤ ተከታታይና ተገቢነት ያላቸው የድጋፍ ሂደቶችን የበለጠ ለማጠናከር እንዲሁም በሂደቱ የሚታዩ ጉድለቶችን ለማረም እና አካዳሚው ያስቀመጣቸውን ግቦች ለማሳካት የሚያስችሉ ስራዎችን ማከናወን የስልጠናው ዋና ዓላማዎች መሆናቸውን እና በሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ዙሪያ ከሰኔ 17 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ስልጠናው እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡
አካዳሚው ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችሉት ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረገ፡፡
ተቋሙ ከአገር ውስጥና ከውጭ አገራት ጋር በጋራ ለመስራት በያዘው ዕቅድ መሰረት ተመሳሳይ ተልዕኮና ዓላማ ካላቸው የሃገር ውስጥ ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አንዱ በመሆኑ በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይጥ አድርገዋል፡፡
አካዳሚው በስልጠና፣ በትምህርትና በጥናትና ምርምር ዘርፎች ሊሰራ ያሰባቸውን ጉዳዮች በተወካዮቹ አማካኝነት ያቀረበ ሲሆን ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንም የሚመለከታቸው የስራ ክፍል ኃላፊዎች ተገኝተው ፍሬያማ ውይይት ተደርጓል፡፡
በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የሰው ሃብት ብቃት ማረጋገጫ ፅ/ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ አጥኔ እንደተናገሩት የሃገርን ሃብት በውጤታማ መንገድ ለመጠቀምና በጋራ ለማደግ ተቋማት በቅንጅት ቢሠሩ የተሸለ ዕድል እንደሚገኝ ገልፀው ከአካዳሚው ጋር በመስራታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ሰኔ 15 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ
98ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 98ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለማቋቋም በተዘጋጀው ረቂቅ ደንብ ላይ ሲሆን የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም፣ ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አስተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት ማካሄድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በንድፈ ሀሳብ የተደገፈ ተግባር ተኮር የአመራር ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት በመስጠት ብሎም ችግር ፈቺ ምርምር በማካሄድ ሳይንሳዊ የለውጥ ሀሳቦችን በማመንጨት በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ሁለንተናዊ ብልጽግና እና መልካም አስተዳደር እንዲረጋገጥ የሚተጋ የአመራር ልህቀት ማእከል ማቋቋም የሚያስችል ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ መብትና ግዴታዎች ለማእከሉ የሚተላለፉ ይሆናል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
Channel name was changed to «African Leadership Excellence Academy»