የደቡብ ሱዳን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ልዑክ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን ጎበኘ፡፡
ልዑኩ ሱሉልታ በሚገኘው የተቋሙ የስልጠና ማዕከል ሲደርስ የአካዳሚው የፕሮግራም ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ ሕይወት አለማየሁ እና የስራ አመራር ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) አቀባበል ያደረጉለት ሲሆን ስለ አካዳሚው ተግባርና ኃላፊነት ሰፊ ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡
አካዳሚው እንደ አዲስ ከተቋቋመ ጀምሮ የአፍሪካን አመራር አቅም በሁለንተናዊ መልኩ ለመገንባት እየሰራ እንደሆነ የገለፁት ወ/ሮ ሕይወት የደቡብ ሱዳን የመረጃና ደህንነት ተቋምም አመራሮቹን የማሰልጠን ፍላጎት ካለው በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ም/ርዕሰ አካዳሚዋ አያይዘውም የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከፓን አፍሪካ ጋር የተያያዙ አዳዲስ የስልጠና ፕሮግራሞችን በመቅረፅ ወደ ስራ እየገባና የአፍሪካውያንን የስልጠና ፍላጎት በተደራጀ የስልጠና ማዕከል ውስጥ ለማሟላት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የደቡብ ሱዳን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና አስተዳደር አብርሀም ኬት ቢቾክ በበኩላቸው ለተደረገላቸው አቀባበልና ለተደረገላቸው ገለፃ አመስግነው በአካዳሚው ውስጥ ለመሰልጠን ፍላጎት እንዳላቸውና በአጭር ጊዜ ውስጥ የስልጠና ፍላጎታቸውን እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል፡፡ የአካዳሚውን የስልጠና ማዕከል በመጎብኘታቸውም ደስተኛ እንደሆኑና በማዕከሉ ባዩት መሰረተ ልማት መደነቃቸውን ተናግረዋል፡፡

ለንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መካከለኛ የስራ ኃላፊዎች ሲሰጥ የነበረው የክህሎት ስልጠና ተጠናቋል፡፡ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ውስጥ ለአራት ቀናት የተሰጠው ስልጠና ጥቅምት 13 ቀን 2015 ዓ.ም የተጠናቀቀ ሲሆን ሰልጣኞች በቆይታቸው የመሪነት ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ የሚያስችል በቂ ግንዛቤ እንዳገኙ በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ተነግሯል፡፡
የስልጠናው ዋና ዓላማም ሰልጣኞች ተመድበው ስለሚሰሩበት ኃላፊነት ያላቸውን እውቀት ክህሎት፣ችሎታና ልምድ እንዲፈትሹ ለማድረግ የታቀደ ሲሆን ይህንኑ ዓላማ ለማሳካትም በሰነድ የታገዘ ውይይት ተካሔዷል፡፡
ለአራት ቀን ስልጠናውን የሰጡት በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ሙሁራን ሲሆኑ ዶ/ር ጋሻው ኃይሌ፣ ዶ/ር ጌታቸው ድንቁ፣ ዶ/ር አብርኃም እንዳለው፣ ዶ/ር ቀነኒ ዳባና ወ/ሮ ሕይወት አለማየሁ ተጠቃሾች ናቸው፡፡
በዚህ ስልጠና ላይ 68/ስልሳ ስምንት/ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የመካከለኛ ደረጃ የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈውበታል፡፡

አዲስ አበባ ጥቅምት 16 ቀን 2015 ዓ.ም (አአልአ)፡- የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ (AFLEX) እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) በጋራ ለመስራት የውል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ሁለቱ ተቋማት በጋራ ስለሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ስምምነት በተፈራረሙበት ወቅት እንደተገለፀው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የካውንተር ኢንተለጀንስ አገልግሎት (Counter Intelligence Service) የሚሰጥ ሲሆን፤ አካዳሚውም ለሚያገኘው አገልግሎት ለአስተዳደሩ ክፍያ የሚፈጽም ይሆናል፡፡ የውል ስምምነቱ ለሁለት አመት የሚቆይ ሲሆን በዚህም የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እና አጠቃላይ የአካዳሚውን የሥራ ቦታ ከየትኛውም አይነት የኤሌክትሮኒክስ ጥቃት ሊያጋልጡ የሚችሉ ክፍተቶችንና ተጋላጭነቶችን ለመከላከል የሚያስችል የካውንተር ኢንተለጀንስ ቴክኒካል አገልግሎት (Proactive and event based counter espionage service) በኢመደአ በኩል የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ስምምነቱን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ ሕይወት አለማየሁ እና የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ ፈርመዋል፡፡
በስምምነቱ ላይ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ ሕይወት አለማየሁ እንደተናገሩት አካዳሚው ከኢትዮጵያ አልፎ ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት መሪዎችን የሚያሰለጥን ተቋም በመሆኑ የሚሰጣቸው አገልግሎቶችም ይሁኑ አጠቃላይ የአካዳሚው ቅጥረ ግቢ ከየትኛውም አይነት የኤሌክትሮኒክስ ጥቃት ስጋት ነጻ መሆኑን ቀጣይነት ባለው መልኩ ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት የአስተዳደሩ ዋና ተልዕኮ የተቋማትን የኢንፎርሜሽን ደህንነት ማረጋገጥ ሲሆን ይህንንም መነሻ በማድረግ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን ከኢንፎርሜሽን ጥቃት ለመከላከልና ደህንነቱን ለማስጠበቅ የሚያስችል የካውንተር ኢንተለጀንስ ቴክኒካል አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የቴክኖሎጂ አቅምም ይሁን ብቃት ያለው የሰው ሃይል ኢመደአ እንዳለው ተናግረዋል፡፡