African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ተደረገ
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮችና ሰራተኞች በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
ውይይቱን የመሩት የአካዳሚው ስራ አመራር ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሠ (ዶ/ር) የአካዳሚው አመራርና ሰራተኛ በተሰማራበት የስራ መስክ ስራውን በኃላፊነት እንዲሰራ፣ የሚሰራጩ ሃሰተኛ መረጃዎችን እንዲከላከልና አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ አሳስበዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የአካዳሚው አመራርና ሰራተኞች በበኩላቸው በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት መደረጉ ተገቢና ወቅታዊ መሆኑን በማንሳት በተሰማሩበት ሙያ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንደሚወጡና እየተወጡ እንዳሉም አንስተዋል፡፡ በየአካባቢያቸውም የፀጥታ ሃይሉን በማገዝ አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥማቸው ለሚመለከተው አካል እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል፡፡
እንኳን አደረሳችሁ!! እንኳን ከዘመን ዘመን በሰላም አሸጋገራችሁ!!
አዲሱ ዓመት የሰላም፤ የጤና እና የስኬት ይሁንላችሁ!!
አካዳሚው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለመላው የአካዳሚው ማህበረሰብ የአዲስ ዓመት የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፏል፡፡
በመልካም ምኞት መልዕክቱ መጪው 2015 አዲስ ዓመት የሰላም፣ የደስታ፣ የብልጽግና ዓመት እንዲሆን በበመኘት መላው የአካዳሚው አመራርና ሰራተኛ እንደተቋም የስኬት ዘመን እንዲሆን እና ተባብረን የምናድግበትና የተሸለ ውጤት የምናስመዝግብበት ዓመት እንዲሆን መልካም ምኞቱን አስተላልፏል፡፡
እንኳን ለሰራተኞች ዓመታዊ በዓልና የጉብኝት ቀን አደረሳችሁ!!
ከመስከረም 09-10 2014 ዓ.ም
የአካዳሚው አመራሮችና ሠራተኞች ለመከላከያ ሠራዊት ደም ለገሱ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮችና ሠራተኞች ዛሬ ለመከላከያ ሠራዊት ደም ለገሡ።
የአካዳሚው ምክትል ርእሰ አካዳሚ ዶክተር ወንድዬ ለገሰ በደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ላይ እንደገለጹት፤ መከላከያ ሠራዊቱ በግንባር መተኪያ የሌለው ክቡር ሕይወቱን እየሰጠ ስለሆነ ባለን አቅም ሁሉ ማገዝ አለብን።
በአንድ በኩል በየተሠማራንበት የሙያ መስክ ጠንክረን በመሥራት በጦርነቱ ኢኮኖሚው እንዳይጎዳ መሥራት አለብን ያሉት ዶክተር ወንድዬ፤ ተገደን የገባንበትን ጦርነት በአጭር ጊዜ በድል ማጠናቀቅ እንድንችልም በግንባር እየተዋደቀ ለሚገኘው ሠራዊት ደም ከመለገስ ጀምሮ አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ አገራችንን ማዳን አለብን ብለዋል።
በተለያዬ ጊዜ ደም መለገሳቸውን አስታውሰው፤ አሁን ላይ አገርን ለመታደግ የማይተካ ሕይወቱን ሰጥቶ እየተዋደቀ ለሚገኘው መከላከያ ሠራዊት የሚለገሰው የሚተካ ደም ነው። በመሆኑም ለዚህ ጀግና ሠራዊት ደም በመለገሳቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።
ደም ከለገሱ የአካዳሚው ሠራተኞች መካከል አቶ አወል አሊ እንደገለጹት፤ አገርን ለማዳን ዋጋ እየከፈለ ካለው ሠራዊት ጎን መቆማቸውን ለመግለጽ ደም መለገሳቸውን ተናግረዋል።
መላው ኢትዮጵያውያንም ደም በመለገስም ሆነ በማንኛውም መልኩ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል
ወይዘሮ አልማዝ መኮንን በበኩላቸው፤ ከዚህ ቀደም ሠራዊቱን በተለያየ መልኩ ሲደግፉ መቆየታቸውን ገልጸዋል ።
"ዛሬም ደም በመለገሴ ግንባር ድረስ ተሰልፌ አገሬን የታደኩ ያህል ተሰምቶኛል" ያሉት ወይዘሮ አልማዝ፤ ጦርነቱ በድል ተጠናቆ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የየበኩሉን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
በፋንታነሽ ክንዴ
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራርና ሠራተኞች የተለያዩ ተቋማትን ጎበኙ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራርና ሠራተኞች የኢፌዲሪ አየር ኃይልን፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አሰተዳደር፣ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትንና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ በተቋማቱ ያለው ጠንካራ የሥራ ባህል የታየበትና አገሪቱ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ እያለፈች ቢሆንም እየተተገበሩ ያሉ አገራዊ ሪፎርሞች ውጤታማ መሆናቸውን የተገነዘቡበት ነው።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ምክትል ርእሰ አካዳሚ ወይዘሮ ሕይወት አለማየሁ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፤ በተቋማቱ የታየው ጠንካራ የሥራ ባህልና ስኬት ለአካዳሚው ሠራተኞች ትልቅ መነሳሳት የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመው፤ ጠንክሮ በመሥራት ችግር ፈቺ የሆኑ ተግባራትን ለአገር ማበርከት እንደሚቻል ልምድ ያገኘንበት ነው ብለዋል።
አካዳሚው በአፍሪካ ደረጃ የአመራር ልህቀት ማዕከል የመሆን ራዕይ አንግቦ እየተንቀሳቀሰ ነው ያሉት ምክትል ርእሰ አካዳሚዋ፤ አካዳሚው ከእነዚህ ተቋማት ጋር በትብብር በመሥራት የታለመውን አገራዊ የመልማት እቅድ እውን ለማድረግ የበኩሉን ሚና ለመወጣት ዝግጁ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
ጉብኝቱ ትልቅ መነሳሳትና ሞራል እንደፈጠረላቸው የጠቆሙት የአካዳሚው ሠራተኞች፤ በተቋማቱ ውስጥ በተመለከቱት ሥራ አገራዊ ኩራት እንደተሰማቸውም ጠቁመዋል።
የአካዳሚው አመራርና ሠራተኞች ጉብኝት ከትናንት ጀምሮ ዛሬም በመከናወን ላይ ያለ ሲሆን፣ ከተቋማቱ ጉብኝት በተጨማሪ በምሥራቅ ሸዋ ዞን በክላስተር የለማ የስንዴ ማሳንም ጎብኝተዋል።
በፋንታነሽ ክንዴ
እናመሰግናለን!!
አቶ አሸብር አህመድ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ውስጥ በልዩ ስልጠና ዳይሬክተርነት ሰርተዋል፡፡ በጡረታ እስከተሰናበቱበት ድረስም በቅንነትና በታማኝነት አገልግለዋል፡፡ አካዳሚውም የምስጋና በዓል አዘጋጅቶ በክብር ሸኝቷቸዋል፡፡ አቶ አሸብር በተቋሙ ውስጥ በሰጡት አመራር እናመሰግናለን፡፡