African Leadership Excellence Academy
2.29K subscribers
2.47K photos
96 videos
6 files
114 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Insightful and engaging Panel discussion on policies and practices in Africa

Africa Day - Pannal One - Policy In Practice-

What's the significance of celebrating Africa Day

How to remove barriers to integration

Panelists

🎤Zadig Abreha, AFLEX president

🎤Abebaw Bihonegn, IGAD head of mission to Ethiopia

🎤David Valee, AFLEX board member

🎤Gashaw Ayferam, Researcher, Institute of Foreign Affairs

#AfricaDay2025 #AFLEX #PanelDiscussion

#PolicyandPractice #EmpoweringYouth
"አፍሌክስ ጸጥታ በተሞላበት በራሱ ስፍራ መስራቱ ለስራው ውጤታማነት ጉልህ አስተዋጽዖ ያበረክታል!" ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር)

የአፍሌክስ አመራር እና ሰራተኞች በዋናው መስሪያ ቤት የአድራሻ ለውጥ ላይ ውይይት አደረጉ


አዲስ አበባ - ሰኔ 10/2017 - (አፍሌክስ):- በአዲስ አበባ የሚገኘው የአካዳሚው ዋና መ/ቤት ሱሉልታ ወደሚገኘው የአመራር ልማት ማዕከል የአድራሻ ለውጥ ሊያደርግ በመሆኑ በዚህ ሂደት የተቋሙን የአሰራር ውጤታማነት እና የሰራተኛውን ተጠቃሚነት ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።

ውይይቱን የመሩት የአካዳሚው የቢዝነስና አስተዳደር ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) ዋና መ/ቤቱ ከአመራር ልማት ማዕከሉ ርቆ መገኘቱና በኪራይ ህንጻ ላይ መሆኑ ተቋሙን ለብዙ ወጪዎች ዳርጎ መቆየቱን አስታውሰው አሁን የሚደረገው ለውጥ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

"ሰራተኛ ወደ ስራው ቀርቦ መስራት አለበት!" ያሉት ዶ/ር ወንድዬ "አፍሌክስ ጸጥታ በተሞላበት በራሱ ስፍራ መስራቱ ለስራው ውጤታማነት ጉልህ አስተዋጽዖ ያበረክታል!" ብለዋል።

"የሰራተኛውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እና የቤት ፍላጎትን ለማሟላት ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ እየተሰራ ነው።" ሲሉም አክለዋል።

በውውይቱ የትራንስፖርት እና የመመገቢያ ካፌ አገልግሎት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውን ተሳታፊዎች በጥያቄ መልክ አንስተዋል።
ከሰራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎች የዝውውር ሂደቱን የሚመሩ ኮሚቴዎች ምላሽ ሲሰጡ የአድራሻ ለውጡ ዋነኛ አላማ የተቋሙን ራዕይ ማሳካትና የተቋሙን ማህበረሰብ መጥቀም መሆኑን በዝዝር አስረድተዋል።

በነፋሻማዋ ሱሉልታ ከተማ የሚገኘው የአመራር ልማት ማዕከሉ ከዚህ ቀደም ከ600 በላይ እንግዶችን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን አሁን ደግሞ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ምቹ ቢሮዎችን ያካተተ ህንጻ ተገንብቶ በመጠናቀቁ ዋና መ/ቤቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደዚያ ለማዘዋወር ዝግጅቶች መጠናቀቃቸው በውይይቱ ላይ ተገልጿል።
#ትክክለኛ_ጥያቄ_የመጠየቅ_ኃይል_እና_ትውልዳዊ_እምርታ_የማስመዝገብ_ጥበብ_እና_ሳይንስ፡ -ከግለሰብ እስከ ሀገር- በአፍሌክስ ፕሬዚደንት ዛዲግ አብርሃ

👉 ጥየቄ መጠየቅ ብቻውን በቂ አይደለም ጥያቄው ትክክለኛ ነው አይደለም ነው ዋናው

👉 የሰው ልጅ ሲፈጥረው ጥያቄ ይጠይቃል

👉 ትክክለኛ ጥያቄ የ liberation /የነፃነት መንገድ ነው

👉 የ leadership መንገድ ነው የ አመራር መንገድ ነው

👉 የመማሪያ መንገድ ነው የrecarination የእንደገና የመነሳት መንገድ ነው

👉 ሶክራቲክ /Socratic /መንገድ ሶክራቲክ ምንድን ነው

👉 በጥያቄ ነው አይደል asking the right question leads to truth/ትክክለኛ ጥያቄ መጠየቅ ወደ እውነት ያመራል

ዛሬ ምሽት

በአፍሌከስ የፌስቡክ እና የዩቲዩብ ገጾች👇

Facebook: https://web.facebook.com/aflexacademy.gov.et

YouTube: https://www.youtube.com/@AfricanLeadershipExcellenceAca
አሶሳ 11/10/2017 ዓ.ም (አፍሌክስ):- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት በአግባቡ በመጠቀም የህዝቦች ህይወት እንዲቀየር ተግቶ መስራት የአመራሮች ተቀዳሚ ሥራ ሊሆን ይገባል ሲሉ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ተናገሩ ።

ፕሬዚደንቱ "በእውቀትና በክህሎት የተገነባ አመራር ለላቀ ውጤት " በሚል መሪ ቃል ለክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጡ ነው።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ዋና ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ እንዳሉት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በበርካታ የተፈጥሮ በረከቶች የታደለ መሆኑን ጠቅሰዋል ።

እነኚህ የተፈጥሮ በረከቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ ከተቻለ ደግሞ የሀገርን ሁለንተናዊ ልዕልና ለማረጋገጥ መሠረት የሚሆን ነው ብለዋል ።

ከወርቅ እስከ ድንጋይ ከሰል፣ ከቀርቃሃ እስከ ማንጎ፣ ከወንዞች እስከ ለም የእርሻ መሬት በሚጠበቀው ልክ ለምተውና ጥቅም ላይ ውለው የህዝቡ ህይወት መቀየርን አመራሮች ተቀዳሚ አጀንዳ ማድረግ እንደሚገባቸውም ገልፀዋል።

በተለይ ክልሉ የኢትዮጵያዊያን የመጪው ዘመን የብርሃን አቢዮት አብሳሪው ታላቁ የህዳሴ ግድብ መገኛ መሆኑ ደግሞ የጂኦ ፖለቲካ የስበት ማዕከል እንዲሆን አድርጎታልም ብለዋል ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለው እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ድምር ውጤቱ የምዕራብ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማዕከል እንደሚያደርገው ጠቅሰዋል ።

እናም የክልሉ አመራሮች ክልሉ ያለውን እምቅ አቅም ተረድተው ያሉ ፀጋዎችን ወደ ሀብት መቀየር የሚያስችል ዝግጁነትን መላበስ እንደሚገባም አሳውቀዋል ።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ትኩረት ያደረጉ የስልጠና አርዕስቶች ላይ ስልጠና እየሰጡ ይገኛሉ ።
አመራሩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ወደ ተግባር በመቀየር የመምራት ክህሎቱን ማሳደግ ይገባል:- አቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት

አሶሳ 11/10/2017 ዓ.ም (አፍሌክስ):- አመራሩ በተከታታይ የሚሰጡ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ወደ ተግባር በመቀየር የመምራት ክህሎቱን ማሳደግ እንደሚገባ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ገለጹ።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ❝በእውቀትና በክህሎት የተገነባ አመራር ለላቀ ውጤት❞ በሚል መሪ ቃል ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

እንደ ሀገር እየተሰጡ የሚገኙ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ የሚያስችሉ መሆኑን አቶ ዛዲግ አብርሃ ተናግረዋል።

ከለውጡ ወዲህ የአገልጋይነት ስሜትን የተላበሰ ተወዳዳሪና ብቃት ያለው አመራርን ለማፍራት በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው ብለዋል።

አመራሩ በተከታታይ የሚሰጡ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ወደ ተግባር በመቀየር የመምራት ክህሎቱን ማሳደግ እንደሚገባ የገለጹት አቶ ዛዲግ አብርሃ ፤በንድፍ ሃሳብ ደረጃ ያለውን በእውቀት ወደ ተግባር መቀየር እንደሚጠበቅ ፕሬዚደንቱ ገልጸዋል።

በሁለተኛ ቀኑ እየተሰጠ በሚገኘው የአቅም ግንባታ ስልጠና ላይም የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ መካከለኛ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛል።
Public Leaders 4 Gender Equality Launches the 2nd Cohort for a Mixed Group of High Level Policy Makers From the 5 Selected Ministries

Sululta, 18 June, 2025, (AFLEX) – The PL4GE initiative has kicked off its transformative 3-day workshop focused on advancing gender equality in policy making, featuring the second cohort of participants from various ministries.

This session brings together 22 high-level leaders from the Ministry of Finance, Ministry of Labor and Skills, Ministry of Industry, Ministry of Trade and Regional Integration, and the Ministry of Planning and Development.

The workshop held at the AFLEX Sululta Leadership Development Center, aims to equip high level officials with practical tools and insights for integrating gender equality concepts into their policy making processes.
Facilitated by certified experts from AFLEX, MoWSA, and the Global Center for Gender Equality, the program emphasizes experiential learning and active engagement.

Participants are urged to challenge traditional obstacles and apply their learning directly to decision-making and policy contributions in their respective sectors.

This second cohort follows the successful delivery of the first, reinforcing PL4GE's commitment to fostering gender transformational concepts and goals in governmental policies and practices throughout Ethiopia.
በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ገለፁ።

ፕሬዝዳንቱ "በእውቀትና በክህሎት የተገነባ አመራር ለላቀ ውጤት " በሚል መሪ ቃል ለክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት ላይ ናቸው።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ እንዳሉት ድህነት የሀገርን እና የዜጎችን ክብር ዝቅ የሚያደርግ መሆኑን መረዳት እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

የአመራሮች የመሪነት ጥበብና የዜጎች የስራ ትጋት እምቅ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ሀብት ጋር ተደምሮ ከተሰራ ድህነትን መሻገር ይቻላል ብለዋል ።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የድህነት መጥፎ የታሪክ ገፅን መቀየር የሚያስችሉና በምሳሌነት የሚጠቀሱ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አሳውቀዋል ።

እናም በመከናወን ላይ ያሉ ሁሉን አቀፍ ስራዎች ቀጣይነት ባለው መልኩ ሁለንተናዊ ልዕልና እውን እንዲሆን የአመራሮችን ቁርጠኝነት ያስፈልጋል ብለዋል ።