African Leadership Excellence Academy
2.29K subscribers
2.48K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ምህረት ደበበ (ዶ/ር) በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምበልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግቢ በመምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ስልጠና እና ውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው ቁልፍ ንግግር አድርገዋል፡፡
ርዕሰ አካዳሚው በቁልፍ ንግግራቸውም እንደገለፁት በጦርነቱ የዩንቨርስቲው የማስተማርያ ግብዓቶችና መሰረተ ልማቶች በመዘረፋቸውና በመውደማቸው ከልብ ማዘናቸውን ተናግረው የሰው ልጅ ትልቁ ሀብት የሆነው ህሊና ባለመዘረፉ ዳግም ወደስራ ለመመለስ የሚገድብ ነገር እንደሌለ ግንዛቤ በመፍጠር የዩኒቨርስቲውን ማህበረሰብ የስራ መንፈስ አነሳስተዋል፡፡
ምህረት ደበበ (ዶ/ር) የህሊና መኖርንና አለመዘረፍ ጠቀሜታ ሲተነትኑ የሰው ልጅ ትልቁ ሀብትና የሁሉ ነገር ምንጭ ህሊና ነው፡፡ ገንዘብ ማስፈጸሚያ እንጂ ከህሊና በበለጠ መልኩ ዋጋ የለውም፡፡ ይህ ሀብት አልተዘረፈም፡፡ የዚህ ሀብት ዋና ሞተር የሆነው አእምሯችን አልተዘረፈም፡፡ ማሰብ እንችላለን ሊቆስል ይችል ይሆናል ሆኖም ግን ይታከማል፡፡ ገንዘብም ይተካል የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ ለህሊናችን ዋጋ በመስጠትና በቀረው ሀብት ላይ በመመስረት ወደነበርንበት ብቻ ሳይሆን ወደተሻለ አሰራር ገብተን ዩኒቨርሲተያችንን መለወጥ እንችላለን የሚል እምነት ሊኖረን ይገባል በማለት የሰራተኛውን ሞራል ገንብተዋል፡፡
ርዕሰ አካዳሚው በዚህም ሂደት አራት መሰረታዊ መዋቅሮች አንዳሉ በማሰገንዘብ አነሱም የመሰረተ ልማት መዋቅር፣ የህግ መዋቅር፣ የልቦና መዋቅርና የህሊና መዋቅር ሲሆኑ የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ መዋቅሮች ከሰው ውጭ ያሉ ሊወድሙ ወይም ሊዘረፉ የሚችሉ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ሁለቱ ግን በሰው ውስጥ ያሉ የማይዘረፉ ለሰው ልጅ ትልቁ ሀብት እንደሆኑ አጽንኦት በመስጠት በዩኒቨርስቲው ውስጥ ታላቅ የስራ መነሳሳት ፈጥረዋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ወላጆቻቸውን በተለያዩ ምክንያቶች ላጡ ህጻናት ድጋር አደረገ
ድጋፉን ለህጻናቱ አሳዳጊዎች ያስረከቡት የአካዳሚው ርዕሰ አካዳሚ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሕይወት አለማየሁ ልጆች ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ብሎም ሀገርን የሚጠቅሙ ትልቅ ደረጃ ላይ እንዲደርሱና ታላላቅ መሪዎች እንዲሆኑ አካዳሚው የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡
የአካዳሚው የስርዓተ ጾታና ባለብዙ ዘርፍ ማስተባበር ክፍል ቡድን መሪ አቶ ምህረት አስጨ በበኩላቸው የአካዳሚው ሰራተኞች ከደመወዛቸው ላይ ተቆራጭ በማድረግ ስምንት(8) ህጻናትን በየወሩ እንደሚደግፉ በማስታወስ በቀጣይም ድጋፉን በተሸለ ሁኔታ ለማስቀጠል መታቀዱን አስታውቀዋል፡፡
ዜና ሹመት
############
ወ/ሮ ህይወት አለማየሁ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በፕሮግራም ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ እንዲሁም አቶ ወንድዬ ለገሰ በስራ አመራር ኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ሆነው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ተሹመዋል፡፡
የአካዳሚው ማህበረሰብም መልካም የስራ ዘመን ተመኝተውላቸዋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሱሉልታ ከተማ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶችና የወጣቶች ማዕከል የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
የድጋፍ ርክክቡ የተደረገው የሱሉልታ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አቡ ብርኪ እና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ሲሆን ምክትል ከንቲባው አካዳሚው የትምህርት ተቋማትንና የወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያን ለመደገፍ የወሰነውን ውሳኔ አድንቀው የተደረገው ድጋፍ ለትምህርት ጥራትና ለመማር ማስተማሩ ተግባር ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡
ምክትል ከንቲባው አያይዘው ተቋሙ በሱሉልታ ከተማ እንደመገኘቱ ለከተማዋ ዕድገትና ልማት ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረው አስታውሰው በቀጣይም ከተቋሙ ጋር ለመስራትና አካዳሚውን ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የአካዳሚው የሰልጣኞችና ተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ሔኖክ አስፋው በበኩላቸው ተቋሙ ለከተማ አስተዳደሩ ያደረገው ድጋፍ የመጀመሪያው እንዳልሆነና ከዚህ ቀደም ለከተማው ስድስት አመራሮች የሁለተኛ ዲግሪ እና አንድ የሦስተኛ ዲግሪ የትምህርት ዕድል መስጠቱን አስታውሰው አካዳሚው ከአመራሩ ልማት ባሻገር በማህበረሰባዊ አገልግሎት ላይ እየተሳተፈ እንደሆነና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
ለሁለት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና ለአንድ የወጣቶች ማዕከል ከተደረገው ድጋፍ ውስጥ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ ፕሮጀክተር፣ ፎቶ ኮፒየር፣ ቴሌቪዥን ተጠቃሾች ሲሆኑ የንብረቶቹ አጠቃላይ ግምትም 800,000.00 (ስምንት መቶ ሺህ) ብር እንደሆነ ታውቋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ 3 ሚሊዬን ብር የሚገመት የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል ድጋፍ አደረገ፡፡
የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ከበደ ይመር ከኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ህዝብና ሚዲያ ግንኙነት ቡድን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለሆስፒታሉ ከ3 ሚሊዬን ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል ብለዋል፡፡ሆስፒታሉ በትግራይ ወራሪ ኃይል ዘረፋና ውድመት ደርሶበት ስለነበር የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ የሆስፒታሉን የግብአት ጉድለት የሚያጠና ቡድን በመላክ ባጠናው ጥናት መሰረት እጅግ አስፈላጊ ግብአቶችን ለግሷል ብለዋል፡፡ የእንግዳ ማረፊያ ወንበር ፣ የባለሙያዎች ወንበር ፣ ጠረንፔዛዎች ፣ አልጋዎች ፣ ፍራሾች ፣ ኮምፒውተር ፣ እስካነር ፣ ፋክስ ወ.ዘ.ተ እቃዎችን ድጋፍ መደረጋቸውን ስራ አስኪያጅ አብራርተዋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ምህረት ደበበ /ዶ/ር/ የህውሀት አሸባሪው ቡድን ባደረሰው ጉዳት እጅግ ማዘናቸውንና ሆስፒታሉ የገጠመውን ችግር በመጋራት የአካዳሚው ማኔጅመት ኮሚቴ ሆስፒታሉን ለመደገፍ በመወሰኑ የመጀመሪያ ዙር ድጋፉን እና መልዕክት ልከዋል፡፡ ከቁሳቁስ ድጋፍ በተጨማሪ አካዳሚው ከሆስፒታሉ ጎን በመቆም በቀጣይ የአቅም ግንባታ እና ሙያዊ እገዛ እንደሚደረግ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ከበደ ይመር ሆስፒታሉ የአፋር ክልል ፣ ሰሜን ሸዋ ፣ ኦረሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን ፣ ደቡብ ወሎ ዞን ቃሉና አርጎባን ጨምሮ በርካታ አካባቢዎችን በሪፈራል ሆስፒታልነት እያገለገለ በመሆኑ ፍሰቱ በርካታ ነው ብለዋል፡፡
ሆስፒታሉ በወራሪ ቡድኑ በደረሰበት ጉዳት የግብአት እጥረቱ እንዲቀርፍ ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በተከበረው የረመዳን ፆም ወቅት የከፍተኛ አመራር ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ ሙስሊም ሰልጣኞች በአካዳሚው የረመዳን ፆም ባማረና በደመቀ ሁኔታ እንዲከናወን የአካዳሚው ርዕሰ አካዳሚና መላው የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ላበረከቱት አስተዋጽኦ የምስጋናና የምስክር ወረቀት አበርክተዋል፡፡