African Leadership Excellence Academy
2.15K subscribers
2.38K photos
90 videos
6 files
107 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
"ኮሚዩኒኬሽን ግጭትን ለማለዘብ ያገለግላል።"

አቶ ዛዲግ አብርሃ: የአፍሌክስ ፕሬዝደንት

በኮሚዩኒኬሽን እና የአመራር ልማት ላይ ስልጠና ተሰጠ

ሱሉልታ መጋቢት 17/2027 (አፍሌክስ) - የአፍሌክስ ፕሬዝደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ የኮሚዩኒኬሽንን እና የአመራር ልማት ስርዐትን ዘርፈ ብዙ ሚና ለአፍሌክስ አመራር እና ሰራተኞች በጥልቀት አብራርተዋል።

ኮሚዩኒኬሽን በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ በሁሉም መስክ የሚጫወተውን ዘርፈ ብዙ ሚና ሲያብራሩ በግጭት ውስጥ የሚኖረውን አሉታዊ እና አዎንታዊ አስተዋጽዖ ላይ ትኩረት አድርገዋል።

"ኮሚዩኒኬሽን ዋነኛ የግጭት አባባሽ ሁነት እንደሆነው ሁሉ፣ ዋነኛ የግጭት መፍቻ መሳሪያም ነው!" ብለዋል።

"ከገጽ ለገጽ ኮሚዩኒኬሽን ይልቅ ዲጂታል ኮሚዩኒኬሽን ለተዛባ አረዳድ የተጋለጠ በመሆኑ ግጭት በመቀስቀስ እና በማባባስ ረገድ ጉልህ ሚና ይጫወታል።"

"ኮሚዩኒኬሽን ግጭትን ለማለዘብ ያገለግላል።" ብለው፣ ግጭትን በኮሚዩኒኬሽን ለማብረድ የሚረዱ ቁልፍ መንገዶችን ዘርዝረዋል።

ስለአመራር ልማት ስርዐት ሲያስረዱ "በአመራር ልማት ላይ የሚሰራው እያንዳንዱ ተግባር ድምር ውጤቱ ትውልድ ተሻጋሪ ትሩፋት ነው።" ሲሉ ተደምጠዋል።

የአመራር ልማት ስርዐት አስፈላጊነት፣ ትላንት የነበረበት፣ ዛሬ ያለበት እና የወደፊት ጉዞ በፕሬዝደንቱ ማብራርያ ተዳስሠዋል።

የስኬታማ አመራር ልማት ስርዐት መገለጫዎችና የውጤታማ አመራር ልማት ማነቆዎችን ዘርዝረው፣ አፍሌክስ እንደአመራር ልማት ማዕከልነቱ እነዚህን በመለየት በአፍሪካ ሁነኛ የአመራር ልማት ስርዐት የመዘርጋት ሃላፊነት እንዳለበት አሳስበዋል።
"ዋነኛው የአመራር መለኪያ የመፈጸም አቅም ነው!" ዛዲግ አብርሃ የአፍሌክስ ፕሬዝደንት

የግለሰብ፣ የቡድን፣የተቋም እየሃገር ስኬት የሚወሰነው በመፈጸም አቅማቸው ልክ መሆኑን የአፍሌክስ ፕሬዝደንት ገለጹ።

ሱሉልታ መጋቢት 18/2017 (አፍሌክስ) -
የመፈጸም እና የመጨረስ ሃይል ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና የሰጡት ፕሬዝደንቱ "ያለመፈጸም አቅም ስኬት አይታሰብም!" ብለዋል።

"ዋነኛው የአመራር መለኪያ የመፈጸም አቅም ነው!"

"ከፍተኛ የመፈጸም አቅም በተለዩ ግቦች እና ተግባራት ላይ ልዩ ትኩረት ማድረግ ይጠይቃል።" ብለው፣ የመፈጸም አቅምን ለማሳደግ የሚረዱ ነጥቦችን አንስተዋል።

የመፈጸም ሃያልነት እውነታዎች፣ የአፈጻጸም ክፍተት ምንነት እና የከፍተኛ አፈጻጸም ሳይንስ በስልጠናው ተብራርተዋል።

"የአለማችን ታላላቅ ግለሰቦች እና ተቋማት የስኬት ምስጢር የጀመሩትን መጨረሳቸው ላይ ነው!" ሲሉ የጀመሩትን የመጨረስን ሃይል ገልጸዋል።

"የታላላቅ ጅምሮች እና ተቋርጦዎች ሃገር በሚል የምትታወቀው ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ ከዳር በማድረስ ይህንን የጀመሩትን ያለመጨረስ ታሪክ በዚህ ትውልድ ለመቀየር ጉዞ ላይ ነች።" ሲሉ ተናግረዋል።

የጀመሩትን የመጨረስ ትሩፋቶች እና ያለመጨረስን ኪሳራዎች ዘርዝረው አስረድተዋል።

"በተቋም ውስጥ የጀመሩትን ለመጨረስ ግልጽ የሆነ ግብ ማስቀመጥ እና የተጠያቂነት ስርዐት መዘርጋት ያስፈልጋል።" ብለዋል።
እንኳን ለ1446ተኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ዒድ ሙባረክ!
ዛዲግ አብርሃ
የአፍሌክስ ፕሬዝዳንት

#africanleadershipexcellence የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ African Leadership Excellence Academy