በአፍሌክስ የለውጥ ጉዞ ላይ ውይይት ተካሄደ
ሱሉልታ መጋቢት 11/2017 (አፍሌክስ) - በስልጠና ላይ የሚገኙት የአፍሌክስ አመራር እና ሰራተኞች በሶስተኛ ቀን ውሎአቸው አካዳሚው እየሄደበት ካለው የለውጥ ፣የማስፋት እና መሰረታዊ እመርታ ጉዞ ጋር በተያያዙ ሃሳቦች እና ተግባራት ላይ ጥልቅ ውይይቶችን አድርገዋል።
ውይይቶቹ የለውጥ፣ ማስፋት እና መሰረታዊ እመርታ ፕሮግራም ላይ ጥልቅ መረዳትን መፍጠር፣ ብሎም የለውጥ ጉዞውን ለማፋጠን የሚያስችሉ ሃሳቦችን የማፍለቅ አላማን ያነገቡ ናቸው።
ተሳታፊዎች የለውጥ ሂደቱን፣ የራሳቸውን አፈጻጸም፣ የአመራር ሂደቱን እንዲሁም ተቋሙን እንዲገመግሙ እና ገንቢ ሀሳቦችን እንዲሰጡ አሳታፊ በሆነ መልኩ ተካሂደዋል።
በቡድን በመከፋፈል የተካሄዱት ውይይቶች ተሳታፊዎች ባለፉት ሁለት ቀናት የአካዳሚው ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ያካፈሏቸውን ሃሳቦች ከአካዳሚው የለውጥ ጉዞ ጋር በማስተሳሰር ለተሻለ አፈፃጸም እንዲተጉ ያነሳሱ ናቸው።
ሁሉም ሰራተኛ በታቀዱ ፕሮጀክቶች እና ፕሮግራሞች ላይ ጥልቅ እና የተሟላ ግንዛቤ ማግኘት አለበት፣ ሁሉም ለተቋሙ ስኬት እና ውድቀት በግልም በጋራም ሃላፊነት መውሰድ መቻል አለበት እናም ለስራ አፈጻጸም ማነቆ የሆኑ ችግሮች በፍጥነት ተለይተው መፍትሄ ሊበጅላቸው ይገባል የሚሉት ሃሳቦች በውይይቶቹ ወቅት ጎልተው ተነስተዋል።

"አፍሌክስ የሃሳብ ማመንጫ፣ ማከማቻ እና ማሰራጫ ማዕከል ሆኖ የማገልገል ራዕይ አለው!” ዛዲግ አብርሃ የአፍሌክስ ፕሬዝደንት
አቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሌክስን የሃሳብ ማዕከል የመሆን ራዕይ እና ለዚህም ከአመራሩ እና ከሰራተኛው የሚጠበቀውን ሃላፊነት የተመለከተ ገለጻ አደረጉ።
ሱሉልታ መጋቢት 12/2017 (አፍሌክስ) - ፕሬዝደንቱ አካዳሚው የሃሳብ ማመንጫ፣ ማከማቻ እና ማሰራጫ ማዕከል የመሆን ራዕዩን ከግብ ለማድረስ የጀመረውን የለውጥ ጉዞ በብቃት ለመምራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።
ገለጻው የተደረገው አራተኛ ቀኑን በያዘው ስልጠና ላይ ሲሆን በቀደሙት የስልጠናው ቀናት የሃሳብን ሃያልነት አጽንዖት ሰጥተው ሲናገሩ የቆዩት አቶ ዛዲግ፣ ዛሬ የአፍሌክስን የሃሳብ ማዕከልነት የንንግራቸው ትኩረት አድርገዋል።
ስለ-አይዲዬሽን ስፔስ (Ideation Space) /የሃሳብ ማመንጫ፣ ማከማቻ እና ማሰራጫ ስርዐት በሰፊው ያብራሩት ፕሬዝደንቱ፣ ይህ ስርዐት በግለሰብ፣ በቡድን፣ በተቋም እና በሃገር ደረጃ የሚለካባቸውን መስፈርቶች ገልጸው በስርዐቱ ላይ አዎንታዊ እና አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ሁነቶችን በዝርዝር አስረድተዋል።
በሃገራችን ብሎም በአፍሪካ ይህ ስርዐት በእጅጉ እንደሚያስፈልግ አሳስበው ስለአፍሌክስ ሲናገሩ “አፍሌክስ የሃሳብ ማመንጫ፣ ማከማቻ እና ማሰራጫ ማዕከል ሆኖ የማገልገል ራዕይ አለው! ይህንን ራዕዩን ከግብ ለማድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሃላፊነታቸውን በብቃት ሊወጡ ይገባል።” ብለዋል።

በሃሳብ እና በፈጠራ ወይም ግኝቶች መካከል ንጽጽራዊ መረጃ አቅርበው ሃሳብ በሁሉም ነገር ላይ ፍጹም የበላይነት እንዳለው አሳይተዋል። “አሁን ላይ መሪ የሚባለው በጉልበት ሳይሆን በሃሳብ ልቆ የተገኘ ነው!” ብለዋል በገለጻቸው።
“እድገት ማስመዝገብ ከፈለግን የት ነበርን፣ አሁን የት ነን፣ ወዴት መሄድስ እንፈልጋለን? የሚሉትን ጉዳዮች ጠንቅቀን ልናውቅ እና ልንመልስ ይገባል።” ብለዋል።
“እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ ስለ ጉዞአችን እና ስለሚገጥሙን ፈተናዎች ጥልቅ መረዳት እንዲኖረን እናም ሁሉን አቀፍ እድገት ማስመዝገብ እንድንችል ይረዳናል።” ሲሉም ተናግረዋል።
አመራር እና ሰራተኛው የአካዳሚውን የለውጥ ጉዞ በብቃት እንዲመራ ክህሎቶችን የማስታጠቅ አላማን የሰነቀው ስልጠና አሁንም መካሄዱን ቀጥሏል።