"መሪዎች ምሳሌ ሆነው መምራት ካልቻሉ ተቀባይነት አይኖራቸውም።" - ዛዲግ አብርሃ፣ የአፍሌክስ ፕሬዝደንት
የአፍሌክስ አመራር እና ሰራተኞች የሚወስዱት ስልጠና ቀጥሏል።
ሱሉልታ - መጋቢት 10/2017 (አፍሌክስ) - ሁለተኛ ቀኑን ባስቆጠረው ስልጠና ‘በምሳሌነት መምራት’፣ ‘ቃልን መጠበቅ’፣ ‘ታማኝነት’ እና ‘የሃሳብ ሃያልነት’ በሚሉ እሳቤዎች ዙሪያ በአካዳሚው ፕሬዝደን አቶ ዛዲግ አብርሃ ሰፊ ገለጻ ሲደረግ ውሏል።
“አፍሌክስ እንደ አመራር ልህቀት አካዳሚነቱ፣ ራሱን የብቁ አመራር ምሳሌ አድርጎ ለሌሎች ማሳየት አለበት።” ብለዋል አቶ ዛዲግ።
በመሪነት ውስጥ የገቡትን ቃል መፈጸም እና ታማኝነት ስለሚጫወቱት ወሳኝ ሚና ያብራሩት ፕሬዝደንቱ "መሪዎች ምሳሌ ሆነው መምራት ካልቻሉ ተቀባይነት አይኖራቸውም።" ሲሉ አሳስበዋል።
ታላላቅ ሃሳቦች አለማችንን እንዴት እንደቀየሩ ተግባራዊ ምሳሌዎችን በማንሳት የሃሳብን ሃያልነት በሰፊው አስረድተዋል።
በርካታ በጎ እንዲሁም መጥፎ ክስተቶችን ያስከተሉ ታላላቅ እሳቤዎችን አንስተዋል። በንግግራቸውም “ሃሳብ የማይሻገረው ወሰን እና ድንበር የለም!” ሲሉ ተደምጠዋል።
“ሃሳብ የግለሰቦችን ህይወት ከመቀየር ህብረተሰብን እስከማሻገር የሚደርስ ሃይል አለው።” ብለዋል።
ስልጠናው የአመራር ልማት እና የአመራር ልማት የሚሰጡ ተቋማት ላይ ትኩረት ባደረጉ ርዕሶች ነገም ቀጥሎ የሚካሄድ ይሆናል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያቀረቡት ጥያቄዎች
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በስብሰባው ላይ የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎችን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡
👉 በትግራይ ክልል እየታየ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ወደግጭት እንዳያመራ ምን እየተሰራ ይገኛል
👉 የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ያስገኘው ሰላም እፎያታ አስገኝቷል
👉 በስምምነቱ መሰረት ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የስምምነት ነጥቦቹ በምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ
👉 መገዳደል፣ መጠፋፋት እና የፖለቲካ ተቃርኖ ዛሬም ዋጋ እያስከፈለን በመሆኑ መንግስትና መሪው ፓርቲ ችግሮችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተነጋግሮ የመፍታት ባህል ማጎልበት ላይ በተሰሩ ስራች የተገኘ ውጤት ቢብራር
👉 የመልሶ ማደረጃት ስራስ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል
👉 ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ከአሥር ዓመቱ ስትራቴጅክ እቅዱ አንፃር ያላቸው አፈፃጸም፣
👉 በስድስት ወር ውስጥ የመንግስት ወጪና ገቢ ምን እንደሚመስል ቢብራራ፣
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡም ይጠበቃል፡፡

👉 ጫካ ከገቡ የታጣቂ ቡድኖች ጋር ችግሩን በሰላማዊ መንገድ በአጭር ጊዜ ለመፍታት መንግስት እየሰራ እንደሆነ ገልጿል ፡፡ በዚህም ተጨባች ውጤት እየተመዘገበ ነው፡፡ ሆኖም ከችግሩ ውስብስብነት አንጻር አሁንም በአማራና ኦሮሚያ ክልል ከችግሩ ያለተላቀቁ አካባዎች አሉ፡፡ ችግሩን ከስር መሰረቱ ለመፍታት ምን እየተሰሩ ነው ፤
👉እንደሀገር የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነትን ከመከላከል አኳያ መንግስት እየሰራ ያለው ስራ አበረታች ነው፤ የመንግስት የስድስት ወር አፈጻጸም ላይ ባለፈው 2016 ዓ.ም የዋጋ ግሽበት 23 ነጥብ 7 በመቶ የነበረ ሲሆን፤ በ2017 ዓ.ም በታህሳስ ወር ወደ 17 በመቶ ዝቅ ብሏል፡፡
👉 የምግብ ዋጋ ግሽበት በ2016 ዓ.ም በታህሳስ ወር 18 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ ብሎ ተመዝግቧል፡፡ ምግብ ነክ ያልሆነው የዋጋ ግሽበት 2016 ዓ.ም ታህሳስ ወር 26 ነጥብ 1 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2017 ዓ.ም በታህሳስ ወር ወደ
👉 14 ነጥብ 4 በመቶ ዝቅ ብሎ እንደተመዘገበ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡ ነገር ግን፤ በአሁን ወቅት የመንግስት ሰራተኛውን ጨምሮ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የኑሮ ውድነትን እየተጎዱ ባሉበት ወቅት እንዴት የዋጋ ንረት ቀንሷል ሊባል ቻለ?
👉 ኢትዮጵያ ከቡና ምርት ከአፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን አረቢካቡና ለአለም በማቅረብ አምስተኛ መሆኗ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ አሁንም በያዝነው ወር በቡና የውጭ ንግድ በአማካይ የ ሶስትነጥብ አምስት ጭማሪ ታይቷል፡፡
👉 በየጊዜውና በየወሩ እየጨመረ የመጣውን የነዳጅ ምርት ዋጋ መጨመር መንስኤው ምንድን ነው?
👉 ህገወጥነትን ለመከላከል፣ ነዳጅን ያለእንግልት ለህብረተሰብ ለማድረስ ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት ተዘርግቶ ችግሩን ለመቅረፍ መንግስት ምን እየሰራ ይገኛል?
👉 በህዝቡ ዘንድ እየተነሱ ያሉ የፍትህ ተደራሽነት ችግር ፣የመልካም አስተዳደርና ብልሹ አሰራሮች ለማረም መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ምን እየተሰራ ነው፣
👉 በበርካታ የሀገሪቱ አካባቢዎች በታጣቂ ሀይሎች በጽንፈኞች ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ይገደላሉ፣ የሰላም እጦት ችግር በዘላቂነት ለመፍጣት ምን እየተሰራ ነው

#የጠሚሩምላሾች
ገቢን በተመለከተ
ባለፉት ስምንት ወራት 580 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል። ነገር ግን መንግስት የሚሰበስበው ገቢ ከጥቅል ሀገራዊ ምርት አንጻር ከ7 በመቶ አይበልጥም። ይህን ማሻሻል አለብን። በየአከባቢው የሚቀርቡ የልማት ጥያቄዎችን መመለስ የምንችለው ገቢያችንን በበቂ ሁኔታ ማሳደግ ስንችል ብቻ ነው።
አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ
መንግስት የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ሁለት ዋና ዋና ስራዎች መከናወን አለባቸው። አንደኛው በቀበሌ ደረጃ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ሲሆን፤ እያንዳንዱ ቀበሌ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የሚያስችሉ አቅሞችን መገንባት ነው። በዚህም ሁሉም ቀበሌዎች ያላቸውን ሃብት በቁጥር ለይተው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው። ይህ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ሁለተኛው መሶብ የተሰኘ አገልግሎት ሲሆን በሙከራ ደረጃ በሲቪል ሰርቪስና በፕላንና ልማት ሚኒስትር በሲስተም ይጀመራል። አገልግሎቱም በአንድ መስኮት ሁሉንም አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው።
ኢንዱስትሪን በተመለከተ
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ስትሪንግ ኮሚቴ ተቋቁሞ በኢንዱስትሪ ዘርፉ ላይ ያሉ ማነቆዎችን የመፍታት ስራ ሲከናወን ቆይቷል። በዚህም የውጭ ምንዛሬ፣ የኃይል አቅርቦትና ሌሎች ችግሮች የተለዩ ሲሆን ችግሮቹን ለመቅረፍም እየተሰራ ነው። ለአብነትም በዘንድሮው ዓመት ብቻ ለኢንዱስትሪ ዘርፉ የቀረበው የኃይል አቅርቦት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር የ50 በመቶ ብልጫ አለው። ከጥቂት ዓመት በፊት የአቅርቦት ጥያቄ የነበረበት የሲሚንቶ ምርትም አሁን ላይ ለውጭ ገበያ ጭምር ማቅረብ የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ ነው። የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም 61 በመቶ የደረሰ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ብቻ 55 አዳዲስ ፋብሪካዎች ስራ ጀምረዋል።
ግብርናን በተመለከተ
"በግብርና ምርት የአነስተኛ አርሶ አደሮች የሰብል ሽፋን 20 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር ደርሷል። በስንዴ ልማትም በመኸር 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር እንዲሁም በበጋ መስኖ ልማት 3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በስንዴ የተሸፈነ ሲሆን፤ በዚህም ከ300 ሚሊየን ኩንታል ያላነሰ ምርት ይስበሰባል ተብሎ ይጠበቃል። በቡና እና ሻይ ምርትም የተሻለ ስኬት እየተመዘገበ ነው። ለአብነትም ባለፉት ስምት ወራት ብቻ ከቡና ወጪ ንግድ 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።"
ኢኮኖሚን በተመለከተ
ባለፉት ስምንት ወራት በዋና ዋና የኢኮኖሚ አመላካቾች ታላላቅ ስኬቶች ተመዝግበዋል። በቀጣይ የበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት ይህን ስኬት ማጠናከር ከተቻለ ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት ከ8 ነጥብ 4 በመቶ በላይ የኢኮኖሚ እድገት ታስመዘግባለች።
የዋጋ ንረትን በተመለከተ
መንግስት በከፍተኛ ሁኔታ ድጎማ በማድረግ የዋጋ ንረቱ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች እንዳይጎዳ በጥንቃቄ እየሰራ ነው። ለአብነትም መንግስት በአንድ ኩንታል ማዳበሪያ 3 ሺህ 700 ብር ይደጉማል። ለነዳጅም 72 ቢሊዮን ብር ተደጉሟል። በዚህም በሊትር 28 ብር እንደጉማለን። የደሞዝ ጭማሪ በማድርግም ቋሚ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ገቢያቸው እንዲያድግ እየተሰራ ነው። ይህ ስራም ተጠናክሮ ይቀጥላል።
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህልን በተመለከተ
“በኢትዮጵያ ሁለት መሰረታዊ ስብራቶች አሉ፤ አንደኛው የመጠፋፋት ባህል ነው። መንግስታት ወደ ኃላፊነት ሲመጡ ሳይደራጁ ለማጥፋት የሚደረግ ሙከራ ማለት ነው። ይህ በበርካታ የኢትዮጵያ መንግስታት ታሪክ ተሞክሯል።
ሁለተኛው ከሶሻሊስት እሳቤ ጋር በስፋት ወደ ኢትዮጵያ የገባው በሽታ ነው። ይህ በኢትዮጵያ ያመጣው ችግር ፍረጃ ነው። የጠላትና የወዳጅ ፍረጃ ማለት ነው። ይህም ለሰላማዊ ድርድር ቦታ አይሰጥም። ይህም በኃይል ስልጣን የመያዝ አባዜን አምጥቷል።ኢትዮጵያ ውስጥ እየተስተዋለ ያለውም ችግር ይህ ነው። በምርጫ የተመረጠን መንግስት በኃይል ለመጣል የሚሞክሩ ኃይሎች አሉ። የሚገርመው ነገር ግን የሚያሰቃዩት እንታገልልሃለን የሚሉትን ህዝብ ነው።”
ህዳሴ ግድብን በተመለከተ
“ህዳሴ ግድብን ለመጨረስ በርካታ ችግሮች ታልፈዋል። በሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ አካባቢ በጋራ ሪቫን በመቁረጥ ታሪክ እናደርገዋለን። ግድቡ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጭምር ፋይዳው የጎላ ነው። ግድቡ በመሞላቱ ምክንያት አሰዋን ግድብ ላይ የጎደለ ውሃ የለም። እኛም ቃል የገባነው ይህ እንዲፈጸም ነበር። ይህም በተግባር ተሳክቷል። ግድቡ የአፍሪካ ኩራት ነው። ኢትዮጵያ መቻልን ያሳየችበት፤ ስህተታችንን ያረምንበትም ጭምር ነው።”
ሰላምን በተመለከተ
መንግስት ለትችት ክፍት ነው። በሚያነሳው ሃሳብ ምክንያት የታሰረ አንድም ሰው የለም። ነገር ግን በአንድ እጅ ሰላማዊ ትግል፤ በሌላ እጅ በጦርነት መንግስት ለመጣል የሚሞክሩ ኃይሎች አሉ። ይህ ህግን መጣስ ነው። ነጻነትን በአግባቡ የማስተዳደር ችግር አለ። ነገር ግን መንግስት አሁንም ለሰላም ጽኑ አቋም አለው። ችግሮች በድርድር እንዲፈቱ ነው የምንሻው። ባለፉት 7 ዓመታት ከየትኛውም የጎረቤት ሀገራት ጋር ጦርነት ያላካሄደ መንግስት አሁን ያለው መንግስት ነው። ይህም ከሀገር ባለፈ ለቀጣናው ሰላም ያለንን አቋም የሚያሳይ ነው።
የኮሪደር ልማትን በተመለከተ
"የኮሪደር ልማት ከዛሬ ባሻገር ቀጣዩ ትውልድን መሰረት ያደረገ ነው። በአዲስ አበባ ብቻ በኮሪደር ልማት አማካኝነት ከ200 ኪሎሜትር በላይ መንገድ ተሰርቷል። ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶችም ተከናውነዋል። በኮሪደር ልማቱ ለተነሱ ዜጎችም በቂ ካሳ ተከፍሏል። እስካሁን ባለው ሂደትም ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ ካሳ ተከፍሏል። በሁሉም የክልል ከተሞችም አስደማሚ ስራ እየተከናወነ ነው፤ ለአብነትም በሐረር ከተማ በዜጎች ተሳትፎ የተከናወነው ስራ ለሀሉም ከተሞች ምሳሌ የሚሆን ነው።"
የፕሪቶሪያ ስምምነትን በተመለከተ
“የፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረተ ልማቶችን በመመለስ የትግራይ ህዝብ አገልግሎት እንዲያገኝ አድርጓል። ያም ሆኖ አሁንም በበቂ ሁኔታ ያልተፈጸሙ ጉዳዮች አሉ። ከዚህም አንደኛው የታጣቂዎች ተሃድሶ (ዲዲአር) ስራ ነው። ይህ በዋናነት የሚጎዳው የትግራይ ህዝብን ነው። ወጣቶች በታጣቂ ስም ከመቀመጥ ወደ ልማት መሰማራት አለባቸው። በየወሩ ለልማት መዋል የነበረበት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለዚህ ስራ ይወጣል።
ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው በመመለስ ረገድም በራያና ጸለምት ጥሩ ስራ ተከናውኗል። በሌሎች አከባቢዎች ግን በተፈለገው ልክ አልሆነም። ይህ የሆነውም ሰብዓዊ ስራ እና ፖለቲካ የሚቀላቅሉ ኃይሎች በመኖራቸው ነው። ነገር ግን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለፉት ሁለት ዓመታት ተጨማሪ ጦርነትን በማስቀረት ረገድ ከፍተኛ ስራ አከናውነዋል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሰጠው የሁለት ዓመት ጊዜ በማለቁ የህግ ማሻሻያ የሚፈልግ ጉዳይ አለ።ህግ ሲሻሻል ደግሞ የነበሩ አፈጻጸሞች መገምገም አለባቸው። በዚህም የፕሪቶሪያውን ስምምነት ባከበረ መልኩ መጠነኛ ለውጥ ከተካሄደ በኋላ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ስራውን እያከናወነ ህዝቡን ለምርጫ የሚያዘጋጅ ይሆናል። ይህን በተመለከተም ከጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶች እየተደረጉ ነው። በዚህ ሂደት ስራዎች ተገምግመው የግለሰቦች መቀያየር ሊኖር ይችላል።”

በአፍሌክስ የለውጥ ጉዞ ላይ ውይይት ተካሄደ
ሱሉልታ መጋቢት 11/2017 (አፍሌክስ) - በስልጠና ላይ የሚገኙት የአፍሌክስ አመራር እና ሰራተኞች በሶስተኛ ቀን ውሎአቸው አካዳሚው እየሄደበት ካለው የለውጥ ፣የማስፋት እና መሰረታዊ እመርታ ጉዞ ጋር በተያያዙ ሃሳቦች እና ተግባራት ላይ ጥልቅ ውይይቶችን አድርገዋል።
ውይይቶቹ የለውጥ፣ ማስፋት እና መሰረታዊ እመርታ ፕሮግራም ላይ ጥልቅ መረዳትን መፍጠር፣ ብሎም የለውጥ ጉዞውን ለማፋጠን የሚያስችሉ ሃሳቦችን የማፍለቅ አላማን ያነገቡ ናቸው።
ተሳታፊዎች የለውጥ ሂደቱን፣ የራሳቸውን አፈጻጸም፣ የአመራር ሂደቱን እንዲሁም ተቋሙን እንዲገመግሙ እና ገንቢ ሀሳቦችን እንዲሰጡ አሳታፊ በሆነ መልኩ ተካሂደዋል።
በቡድን በመከፋፈል የተካሄዱት ውይይቶች ተሳታፊዎች ባለፉት ሁለት ቀናት የአካዳሚው ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ያካፈሏቸውን ሃሳቦች ከአካዳሚው የለውጥ ጉዞ ጋር በማስተሳሰር ለተሻለ አፈፃጸም እንዲተጉ ያነሳሱ ናቸው።
ሁሉም ሰራተኛ በታቀዱ ፕሮጀክቶች እና ፕሮግራሞች ላይ ጥልቅ እና የተሟላ ግንዛቤ ማግኘት አለበት፣ ሁሉም ለተቋሙ ስኬት እና ውድቀት በግልም በጋራም ሃላፊነት መውሰድ መቻል አለበት እናም ለስራ አፈጻጸም ማነቆ የሆኑ ችግሮች በፍጥነት ተለይተው መፍትሄ ሊበጅላቸው ይገባል የሚሉት ሃሳቦች በውይይቶቹ ወቅት ጎልተው ተነስተዋል።

"አፍሌክስ የሃሳብ ማመንጫ፣ ማከማቻ እና ማሰራጫ ማዕከል ሆኖ የማገልገል ራዕይ አለው!” ዛዲግ አብርሃ የአፍሌክስ ፕሬዝደንት
አቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሌክስን የሃሳብ ማዕከል የመሆን ራዕይ እና ለዚህም ከአመራሩ እና ከሰራተኛው የሚጠበቀውን ሃላፊነት የተመለከተ ገለጻ አደረጉ።
ሱሉልታ መጋቢት 12/2017 (አፍሌክስ) - ፕሬዝደንቱ አካዳሚው የሃሳብ ማመንጫ፣ ማከማቻ እና ማሰራጫ ማዕከል የመሆን ራዕዩን ከግብ ለማድረስ የጀመረውን የለውጥ ጉዞ በብቃት ለመምራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።
ገለጻው የተደረገው አራተኛ ቀኑን በያዘው ስልጠና ላይ ሲሆን በቀደሙት የስልጠናው ቀናት የሃሳብን ሃያልነት አጽንዖት ሰጥተው ሲናገሩ የቆዩት አቶ ዛዲግ፣ ዛሬ የአፍሌክስን የሃሳብ ማዕከልነት የንንግራቸው ትኩረት አድርገዋል።
ስለ-አይዲዬሽን ስፔስ (Ideation Space) /የሃሳብ ማመንጫ፣ ማከማቻ እና ማሰራጫ ስርዐት በሰፊው ያብራሩት ፕሬዝደንቱ፣ ይህ ስርዐት በግለሰብ፣ በቡድን፣ በተቋም እና በሃገር ደረጃ የሚለካባቸውን መስፈርቶች ገልጸው በስርዐቱ ላይ አዎንታዊ እና አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ሁነቶችን በዝርዝር አስረድተዋል።
በሃገራችን ብሎም በአፍሪካ ይህ ስርዐት በእጅጉ እንደሚያስፈልግ አሳስበው ስለአፍሌክስ ሲናገሩ “አፍሌክስ የሃሳብ ማመንጫ፣ ማከማቻ እና ማሰራጫ ማዕከል ሆኖ የማገልገል ራዕይ አለው! ይህንን ራዕዩን ከግብ ለማድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሃላፊነታቸውን በብቃት ሊወጡ ይገባል።” ብለዋል።