African Leadership Excellence Academy
2.15K subscribers
2.38K photos
90 videos
6 files
105 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
African Leadership Excellence Academy pinned «የአፍሌክስ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ #የኮሙኒኬሽን_ኃይል_እና_የአመራር_ጥበብ በሚል ርዕስ ለከፍተኛ አመራሮች የሰጡትን #ክፍል_2 ስልጠና በአካዳሚው የዩቱዩብ ቻናል ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://youtu.be/hv3Q0klclPg»
"ለውጥን የምንመራበትን መንገድ መወሰን እንጂ ከለውጥ መሸሽ አንችልም" የአፍሌክስ ፕሬዝደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ

የአፍሌክስ አስተዳደር እና ሰራተኞች የአመራር ልማት ስልጠና መውሰድ ጀመሩ

ሱሉልታ፣ መጋቢት 9/2017 (አፍሌክስ)
– የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃ ለተቋሙ አመራር እና ሰራተኞች 'ለውጥ እና የሀገራት ዕጣ ፈንታ' በሚል ርዕስ ስልጠና ሰጥተዋል።

ዛሬ ጅማሮውን ያደረገው ለ6 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው በዚህ ስልጠና የመጀመሪያ ቀን ውሎ የአላማ ግልጽነት፣ የአመራር ልማት አስፈላጊነት፣ ለውጥ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በአካዳሚው ፕሬዝደንት ሰፊ ማብራርያ ተሰጥቷል።

አቶ ዛዲግ “የአላማ ግልጽነት በተቋም ውስጥ ከፉክክር ይልቅ ትብብር እንዲመጣ ያስችላል” ሲሉ ተናግረው ስለመሪነት እና የሃገራት እጣ ፈንታ ሲያስረዱ “የሃገራት ስኬትና ውድቀት ምክንያት ምንድነው ቢባል? ከምንም በላይ አመራር ነው” ብለዋል።

የትምህርት ስርዐታችን ሁሉንም ሰው ለመሪነት የሚያበቃ ሁሉን አቀፍ ባህርይ ስለሚጎድለው እንደአፍሌክስ ያሉ የአመራር ልማት ተቁማት አስፈላጊነት በእጅጉ የላቀ መሆኑንም አንስተዋል።

በማብራርያቸው የለውጥን አይቀሬነት ሲናገሩ "ለውጥን የምንመራበትን መንገድ መወሰን እንጂ ከለውጥ መሸሽ አንችልም" በማለት ገልጸዋል።

ስልጠናው አካዳሚው እያካሄደ ያለውን የለውጥ ጉዞ በብቃት ለመምራት የሚያስችሉ ክህሎቶችን ለሰራተኞቹ ለማስጨበጥ ያለመ መሆኑ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል።

መርሃ ግብሩ ቀጥሎ ሲካሄድ በነገው እለት አቶ ዛዲግ በለውጥ አመራር እና ተያያዥ ርዕሶች ላይ አሳታፊ ስልጠና ይሰጣሉ