የአካዳሚው ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ ከሚዲያ ተቋማት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ከሰጡት ምላሽና አስተያየት የተወሰደ
የአገራችን ከፍታ ማለት የአመራር ከፍታ ነው፡፡ የአመራር ከፍታ ማለት ደግሞ የአመራር የአመለካከት፣ የክህሎት እና የብቃት ከፍታ ነው ተብሎ የሚታሰበው፡፡ ምክንያቱም ብዙ ሀገሮች የተለወጡት ጠንካራ አመራር ስላላቸው ነው ለሀገር የሚያስቡ፣ የማይሰርቁ፣ Committed የሆኑና ለሀገር የሚቆርቆሩ አመራሮች ስላላቸው ከድህነት ተነስተው ተለውጠዋል፡፡ ለምሳሌ ቻይና የዛሬ 30 እና 40 አመት ከኢትዮጵያ ጋር እኩል ድህነት ተርታ ላይ የነበረች አገር ናት፤ ኮሪያ የዛሬ 50 አመት እኛ ስንደግፋት የነበረች አገር ናት ነገር ግን ዛሬ ከአለማችን ALMOST 1ኛ እና 2ኛ ከሚባሉ ደረጃ ደርሰዋል ማለት ይቻላል፡፡ የዚህ ሁሉ ሚስጥር ደግሞ አመራር ነው፤ ስለዚህ አመራርን ማብቃት፣ ማሰልጠን፣ አመራር የሚሰለጥንበት ቦታ ማደራጀት ለቀጣይ የብልፅግና ጉዛችን ትልቁ መሰረት ነው ብለን ነው የምናምነው፡፡ አካዳሚያችንም ከተሰጠው ተልዕኮ አንፃር እነዚህን ነገሮች በአግባቡ ማበልፀግ፣ ማደራጀትና ለስልጠና ምቹ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡

ለአካደሚው አመራሮች ባለሙያዎች የማናቃቂየ ስልጠና ተሰጠ ፡፡
ስልጠናውን የሰጡት ከኮርያ የመጡ የአይ ዋይ ኤፍ (IYF) ባለሙያዎች ናቸው፡፡
የመናቃቂያ ስልጠናው የኮሪያን የእድገት መንገድ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የአካዳሚው አመራሮችና ባለሙያዎች ምን ሊማሩበት እንደሚችሉና እንዴት ከአስተሳሰብና ከአመለካከት ለውጥ ጋር ማስተሳሰር እንደሚገባቸው ለማስቻል የሚረዳ መሆኑን የገለፅት የስልጠና ቡድን አባላት፤ ኢትዮጵያ ምቹ የተፈጥሮ ሃብት ያላትና ለቅኝ ገዢዎች እጀቸውን ያልሰጡ የትልቅ ህዝቦች ሃገር ሆና ሳለ ድሃ መባሏ የሚያቆጭ ነው ብለዋል፡፡ ይህን የተፈጥሮ ሃብትና ትልቅ ህዝብ ይዞ ካደጉት ሃገሮች ተርታ ለመሰለፍ የአስተሳሰብ ለውጥ እንደሚያስፈልግ ያስረዱት አባላቱ ለዚህ ደግሞ የአመራር ሚና ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አካዳሚው እያስገነባ ያለው ዘመናዊ የትምህርትና ስልጠና ማዕከል ተጎበኘ
በቻይና መንግስት ዕርዳታ እየተገነባ የሚገኘው ዘመናዊ የትምህርትና ስልጠና ማዕከል የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ በዛብህ ገብረየስ፣ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ብርሃኑ ፈይሳ እና በአካዳሚው አመራሮችና ሰራተኞች ተጎብኝቷል፡፡
የግንባታ ሂደቱ ዘጠና አምስት ፐርሰንት (95%) መጠናቀቁን የገለፁት የአካዳሚው ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ በአፍሪካ ደረጃ እጅግ ዘመናዊ የሆነ የአመራር ማብቂያ ህንፃ ኮምፕሌክስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ በዛብህ ገብረየሱስ በበኩላቸው አካዳሚው በአሁኑ ወቅት ራሱን ከሃገሪቱ ለውጥ ጋር ለማራመድ እያከሄደው ያለው ተግባር የሚበረታታ መሆኑን ገልፀው እየተገነባ ያለው ዘመናዊ የአመራር ህንፃ የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

አካዳሚው ከኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ
የኢፌዴሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ከኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት ጋር የተጀመረውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግና በጋራ በጥናትና ምርምር፤ በስልጠናና በድጋፍ፣ በአመራር አቅም ግንባታ እና በካይዘን ትግበራ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ (MoU) ተፈራርመዋል፡፡
በአካዳሚው በኩል የፊርማ ስነ ስርዓቱን ያከናወኑት የአካዳሚው ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ አገራችን የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ከግብ ለማድረስ በዘመናዊ የካይዘን አሰራር የተካነ አመራር ትልቅ ድርሻ እንዳለው በማንሳት የተጀመረውን የጋራ ስራ ወደ ተግባር በመለውጥ ውጤታማ ስራ ማከናወን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት በኩል ፊርማቸውን ያኖሩት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ያኢ በበኩላቸው ካይዘን ሂደትንና የአመለካከት ግንባታን ቀጣይነት ባለው ሁኔታ በማሻሻል የማያቋርጥ ለውጥ እውን እንዲሆን እንደሚያግዝ በተግባራዊ ልምምድ የተፈተሸና የተረጋገጠ አማራጭ የአመራር ፍልስፍና ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ለአገራችን ሁለንተናዊ ብልጽግና ግቦች መሳካት የሚረባረብ የጋራ አመራር ዘይቤ ለመፍጠር ከምንጊዜውም በላይ ያለንን እምቅ አቅም አሰባስበንና አቀናጅተን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
የአካዳሚው የትምህርትና ስልጠና ፍላጎትና ውጤታማነት ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ሞገስ ሎጋው ስለመግባቢያ ሰነዱ ሲናገሩ ችግር ፈቺ የሆነ ጠናትና ምርምር ፤ ጥራቱን የጠበቀ፣ ዘመናዊና ወጪ ቆጣቢ የሆነ የካይዘን አሰራር እና በዘመናዊ የካይዘን አሰራር የተካነ አመራር ለማፍራት እንዲሁም በሌሎች ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች በጋራ ለመስራትና ወደ ተግባር ለመግባት የመግባቢያ

የኢፌዴሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ማኔጅመንት በሁለት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
የአመራር አካዳሚው ማኔጅመንት ሚያዝያ 7ቀን 2013 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ከቻይና መንግስት በተሰጠው የሁለተኛ እና የሶስተኛ ዲግሪ የትምህርት ዕድል ላይ ተወያይቶ ከቀረቡት ተወዳዳሪዎች ውስጥ ለሦስተኛ ዲግሪ 8 ለሁለተኛ ዲግሪ 7 ኮታ የደለደለ ሲሆን መስፈርቱን የሚያሟሉ 15 የአካዳሚው ሰራተኞች የውጭ አገር የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ወስኗል፡፡
ሁለተኛው አጀንዳ የተበላሹና የማይሰሩ ንብረቶችን ማስወገጃ መንገዶችን መለየት ላይ የተደረገ ውይይት ሲሆን ለተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት በስጦታ እንዲተላለፉ መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን ይህንኑ አጥንቶ የሚያቀርብ ቴክኒካል ኮሚቴ በማቋቋም የዕለቱ ማኔጀመንት ስብሰባ ተጠናቋል፡፡

ለአካዳሚው ተማሪዎች በሙሉ
የኢፌዴሪ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን 20ኛ ዓመት ምስረታውን በማስመልከት የተማሪዎች የስነ-ምግባር ጥያቄ ውድድር በአገር አቀፍ ደረጃ የሚያካሂድ በመሆኑ ተወዳዳደሪ ተማሪዎችን እንደ አካዳሚ ለማቅረብ በአካዳሚ ደረጃ ሚያዚያ 19/2013 ዓ/ም የተማሪዎች የስነ-ምግባር ጥያቄ ውድድር ይካሄዳል፡፡
በመሆኑም መዎዳደር የምትፈልጉ አሁን በትምህርት ላይ የምትገኙ የአካዳሚው ወንድ=5 ሴት=5 ድምር=10 ተማሪዎች እስከ 14/08/2013 ዓ/ም ድረስ በአካዳሚው ሱሉልታ ካምፓስና ዋና መስሪያ ቤት እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- ለተወዳዳሪዎች በአካዳሚው ሽልማት ተዘጋጅቷል፡፡

አካዳሚው የምርምር ዎርክሾፕ በማካሄድ ላይ ይገኛል
የኢፌዴሪ መለስ ዜናዊ አማራር አካዳሚ የምርምር ዎርክሾፕ በስካይ ላይት ሆቴል በማካሄድ ላይ ነው፡፡
በምርምር ዎርክሾፑ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአካዳሚው የጥናትና ምርምር ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ደምሴ ሽቶ የምርምር ዎርክሾፑ ዓላማ የሀገራዊ ለውጥ ሂደቱን በጥናትና ምርምር በማስደገፍ ማስፋፋትና ተግባራዊ ለውጦችን ለማጎልበት፣በዎርክሾፑ ተሳታፊዎች መካከል በሚደረገው ውይይት የእውቀት ሽግግርና የልምድ ልውውጥ በማድረግ ዘላቂነት ያለው ስትራተጂያዊ ግኑኝነትና አጋርነት መመስረት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እንዲሁም የለውጥ ሂደቱን የሚደግፉ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ለማበረታታት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አካዳሚው በሳይንሳዊ የአመራር ጥበብ የተካነና የመሪነት ሚናውን የሚወጣ፣ የለውጥ አመራር በቀጣይነት የመገንባት ተልዕኮ ያለው ስትራተጅክ የፌደራል ተቋም መሆኑን የገለፁት ም/ፕሬዝዳንቱ ተቋሙ ተልዕኮውን በብቃት መወጣት ያስችለው ዘንድ የአመራር ሥልጠና፣ የከፍተኛ ትምህርት፣ የጥናትና ምርምር እና ማማከር አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን አደረጃጀት እና አሰራር ዘርግቶ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ስኬታማ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል፡፡
አያይዘውም የምርምር ዎርክሾፑ እውን እንዲሆን ሲንቀሳቀሱ ለነበሩ የዝግጅት ኮሚቴ አባላት እና ለፅሑፍ አቅራቢዎች ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በአካዳሚው ተማሪዎች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ፡፡
የፌዴራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተቋቋመበትን 20ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በአገር አቀፍ ደረጃ የተማሪዎች የሥነ ምግባር የጥያቄና መልስ ውድድር መርሃ ግብር አዘጅቷል፡፡ ይህ ውድድር በአካዳሚ ደረጃ በተማሪዎች መካከል ተደርጓል፡፡
መርሃ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የአካዳሚው የስነ ምግባር መኮንን አቶ አዲሱ ኡርጌሳ እንደተናገሩት የትውልዱ የስነ ምግባር ግንባታ ሂደትን የበለጠ አጉልተው የሚያሳዩ አስተምህሮዎችንና ምንነትን ግልጽ ለማድረግ የስነ ምግባር ጥያቄና መልስ ውድድር የራሱ ሚና አለው ብለዋል፡፡
አቶ አዲሱ አያይዘውም በአካዳሚው በሚማሩ ተማሪዎች መካከል ውድድር በማድረግ አሸናፊዎችን በመለየትና በመሸለም ተማሪዎችን በማነቃቃት በስነ ምግባር ዙሪያ የሚኖራቸውን ግንዛቤ እና ተግባራዊነት ድርሻ ማሳደግ የውድድሩ ዋና ዓላማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በውድድር መርሃ ግብሩ ላይ ሙስናና ስነምግባር በሚል ርዕስ ጽሁፍ ያቀረቡት ያሬድ አስራት(ዶ/ር) የሙስናን ምንነትና የሚያስከትለው ውጤት፣ የሙስናና የስነምግባር ግንኙነት እንዲሁም ሙስናን መግታት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ያተኮረ ጽሁፍ አቅርበው በተሳፊዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በውድድር መርሃ ግብሩ ላይ ለተወዳደሩ ተማሪዎችና በስነ ጽሁፍ ለተሳተፉ አካላት የማበረታቻ ሽልማት በመስጠት የዕለቱ መርሃ ግብር ተጠናቋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጫኑ፡፡
በፌስቡክ https://www.facebook.com/meleszenawileadershipacademy
በዩቲዩብ - FDRE Meles Zenawi Leadership Academy
በድረ-ገጽ http:// www.mzla.edu.et
በኢሜይል info@mzla.edu.e

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
አካዳሚው ከኢትዮጵያ ፖሊስ ጥናት ኢኒስቲዩት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደረገ
የኢፌዴሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ከኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢኒስቲትዩት ጋር በጋራ ለመስራት የሚየስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ለመፈራረም ከሁለቱም ተቋማት ከተውጣጡ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር የመጀመሪያ ውይይት አደረገ፡፡
በውይይቱም ሁለቱም ተቋማት የሚያከናውኗቸው ስራዎች የተዳሰሱ ሲሆን በተለዩ የጋራ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ለመፈራረምና ወደ ስራ. ለመግባት የሚያስችል ውይይት መደረጉን የአካዳሚው የግንኙነትና ዓለም አቀፍ ትብብር ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘውዱ አለምነው ገልፀዋል፡፡
ሁለቱም ተቋማት ተባብረው የተሻለ ውጤት ለማምጣት የሚስችላቸው ጉዳዮች ላይ መስራት እንደሚኖርባቸው የገለጹት የአካዳሚው የዕቅድና አስተዳደር ልማት ዘርፍ ተ/ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሰሎሞን ገ/መድህን የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለት አሳስበዋል፡፡

Workshop.mpg
231.3 MB
የጥናትና ምርምር ዎርክሾፕ ማስፈፀሚያ እቅድ ላይ ውይይት ተካሔደ
አካዳሚው ወቅቱን የሚመጥን የአመራር ስልጠና ለመስጠት በመስራት ላይ ይገኛል
ባለንበት ዘመነ ግሎባላይዜሽን ማንኛውም ሀገር በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በገበያ ውድድር ውስጥ ያለው እጣ ፋንታ የሚወሰነው ሀገሮች ባላቸው የሰለጠነ የሰው ሀይል በተለይም በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን የማያቋርጥ የለውጥ ፍላጎት በትክክለኛ አቅጣጫ መርቶ ውጤታማ ለማድረግ የሚችሉ አመራሮችን በመፍጠር እንደሆነ የተለያዩ ምሁራን ይገልፃሉ፣ የሀገሮችም ተሞክሮ ያሳያል፡፡፡፡ ለዚህ ደግሞ አንዱና ትልቁ መሳሪያ ብቃትን መሰረት ያደረገ ስልጠና (Competency - based Training) ሲሆን ስልጠናውን በተቀመጠው አግባብ ለመምራትና ለመተግበር ደግሞ የስልጠና ተቋማት ትልቁን ሚና ይጫወታሉ፡፡
አቶ አሸብር አህመድ

EMBASSY sends letter to Invitation to Sino pharm Covid-19 vaccine Inoculation
Embassy of the People’s Republic of china sends letter to invitation to Sino pharm covid-19 vaccine inoculation to FDRE Melees Zenawi Leadership Academy.
According to the letter sent by the counselor’s office, the invitation is, to support Ethiopia’s anti-pandemic efforts and as an appreciation for the esteemed Academy’s contribution to friendly relations and win-win cooperation between China and Ethiopia, The counselor’s office would like to offer Academy 40 doses (for 20 people) of Sino pharm Covid-19 vaccine which has been authorized for emergency use by the WHO. The Silk Road Hospital in Addis Ababa will provide Inoculation service.

አካዳሚው ‹‹ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለዘላቂ አገራዊ ብልፅግና›› በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት በአዳማ ከተማ እያካሔደ ነው፡፡
በፓናሉ ላይ ‹‹ነፃ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ባህርያትና ምንነት በኢትዮጵያ›› እና ‹‹ዴሞክራሲያዊ ምርጫና የባለድርሻ አካላት ሚና›› የሚሉ ፅሁፎች የቀረቡ ሲሆን የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የፓናል ውይይቱ አሁን እየተካሔደ ነው፡፡
ፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የአካዳሚው ጥናትና ምርምር ዘርፍ ምክትል ፕሬዚደንት አቶ ደምሴ ሽቶ እንደተናገሩት ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ በሳይንሳዊ ትንታኔ የታገዘ እንዲሆንና በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መረጃን ለህዝቡ ተደራሽ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ምክትል ፕሬዚደንቱ አያይዘውም በአገራችን የተጀመረውን የለውጥ ሒደት የሚደግፉ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ለመደገፍና ለማበረታታት የፓናል መድረኩ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡
በፓናል ውይይቱ ላይ የፌዴራልና የክልል የስራ ኃላፊዎች፤ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፤ የሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች፤ ሙሁራን፤ የሲቪክ ማህበራት ኃላፊዎችና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡