African Leadership Excellence Academy
2.32K subscribers
2.51K photos
96 videos
6 files
118 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
አፍሌክስ ለጤና ሚኒስቴር እና ለተጠሪ ተቋማት አመራሮች ስልጠና መስጠት ጀመረ

ሱሉልታ የካቲት 10/2017 ዓ.ም (አፍሌክስ)-በአመራር መስኩ የጾታ እኩልነትን የማረጋገጥ አላማ ያለው የፐብሊክ ሊደሺፕ ፎር ጀንደር ኢኳሊቲ (PL4GE) ፕሮጀክት ለጤና ሚኒስቴር እና በስሩ ለሚገኙ ተጠሪ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች በአፍሌክስ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

የአፍሌክስ፣ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር እና የግሎባል ሴንተር ፎር ጀንደር ኢኳሊቲ ትብብር ውጤት የሆነው ይህ ፕሮጀክት በአመራር ዘርፍ የጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ በመስራት ላይ ይገኛል።

ዛሬ ሱሉልታ በሚገኘው የአፍሌክስ የአመራር ልማት ማዕከል የተጀመረው ስልጠናም የዚሁ አካል ሲሆን የጤና ሚኒስቴር አመራሮችን እንዲሁም በስሩ የሚገኙ ተጠሪ ተቋማትን የስራ ሃላፊዎች ያሳተፈ ነው።

የጤና ሚኒስቴርን ወክለው ስልጠናውን በንንግር ያስጀመሩት ዶ/ር አስናቀ ዋቅጅራ በጤናው አመራር ዘርፍ የጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አበክሮ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር በመክፈቻው ላይ ንግግር ያደረጉት ትፍስሂት ሰለሞን (ዶ/ር) በሃገራችን በየመስኩ ባለው አመራር ዘንድ የጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ የሚሰራው ስራ አካል የሆነው ይህ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ወደትግበራ መግባቱ ደስ የሚያሰኝ መሆኑን ገልጸው፣ በጤናውም ሆነ በሌላው መስክ የጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የፕሮጀክቱ የስራ ሃላፊ ኢሳያስ ታዬ (ዶ/ር) PL4GE በርካታ ሂደቶችን አልፎ ለዚህ በቅቷል ብለው፣ ለዚህም ጉልህ አስተዋጽዖ ላበረከቱ የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።

ስልጠናው ከየካቲት 10 እስከ 12 እንደሚቆይ ተገልጿል።
የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አመራሮች እና ባለሞያዎች በአፍሌክስ ስልጠና መውሰድ ጀመሩ

ሱሉልታ የካቲት 10/2017 ዓ.ም (አፍሌክስ)- አፍሌክስ ለባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር አመራሮች እና ባለሞያዎች መስጠት በጀመረው 2ተኛ ዙር የአመራር ልማት ስልጠና 270 የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮች እና ባለሞያዎች ተሳታፊ መሆን ችለዋል።

የሃገሪቱን ተቋማት የአመራር ብቃት ለማሳደግ በመስራት ላይ የሚገኘው አፍሌክስ ከባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ፤ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮች እና ባለሞያዎች 2ተኛ ዙር ስልጠና በአመራር ልማት ማዕከሉ መስጠት ጀምሯል።

ስልጠናው የአመራሩን ብቃት በማጠናከር ኪነ ጥበብ፣ ባህል፣ እና ስፖርት ለሃገር አንድነት እና ብልጽግና ያላቸውን ሚና አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።

በመክፈቻ ስነ ስርዐቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የባህልና ስፖርት ሚኒስትሯ ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ “የዚህ ስልጠና ዋነኛ አላማ ባህልና ስፖርትን ለሃገረ መንግስት ግንባታ ለማዋል የሚያችለንን አቅም ማሳደግ ነው።” ብለዋል።

አያይዘውም ያደጉ ሃገራት ገጽታቸውን ለመገንባት ከተጠቀሙባቸው መሳሪያዎች መካከል ባህልና ስፖርት ዋነኞቹ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ “ኢትዮጵያ ያሏትን ቱባ ባህሎችም ሆነ የስፖርቱን ዘርፍ ለሃገራዊ አንድነት እና ገጽታ ግንባታ ለማዋል ሃላፊነታችንን እየተወጣን ነው ወይ? ብለን ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል።” ሲሉ ተናግረዋል።
የአፍሌክስን የሪፎርም ስራዎች በተመለከተ ገለጻ ያደረጉት እሸቴ አበበ (ዶ/ር) ተቋሙ ከምን ተነስቶ ወደየት እየሄደ እንዳለ፣ እየከወናቸው የሚገኙትን ትልልቅ ስራዎች እንዲሁም ስለሱሉልታ ዳቮስ ፕሮጀክት አብራርተዋል።

ስልጠናው ለ4 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ዛሬ በመጀመሪያው ቀን የኢቢሲ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ፣ ኪነ ጥበብ፣ ባህል እና ስፖርት ለሃገረ መንግስት ግንባታ በሚኖራቸው ሚና ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ አቅርበዋል።

ከዚህ ቀደም የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በመጀመሪያ ዙር ከፌዴራል፤ ከክልሎችና ከሁለቱም የከተማ አስተዳደሮች ለተወጣጡ 250 የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አመራርና ባለሞያዎች ተመሳሳይ አላማ ያለው የአመራር ልማት ስልጠና መስጠቱ ይታወሳል።
🎉አፍሌክስ በኢትዮጵያ🇪🇹 ብሎም በአፍሪካ🌍 የመጀመሪያ በሆነው የሴቶች የአመራር ልማት መርሃ-ግብር ያበቃቸውን ሴት አመራሮች ሊያስመርቅ 2ቀናት ብቻ ቀርተዋል🎉
The 10% Rule of Leadership

The 10% Rule of Leadership emphasizes that our most valuable asset as leaders is not merely our expertise or vision, but our people.

This rule encourages us to invest at least 10% of our time and resources into developing our teams, a commitment that can transform workplaces and empower employees to reach their full potential.

By dedicating time to mentorship and coaching, we enable team members to take ownership of their roles and grow professionally.

Open communication through regular feedback fosters a culture of trust and collaboration, allowing individuals to thrive and innovate.

Additionally, investing in a supportive work environment boosts morale and retention, leading to greater productivity.

Ensuring that every team member understands their role in achieving organizational goals creates a sense of purpose and direction. Leadership is also a journey of continuous growth, by focusing on our own development, we set a powerful example for our teams.
Embracing the 10% Rule allows us to cultivate a thriving, engaged workforce ready to tackle challenges and drive our organization forward, reinforcing the importance of investing in our most crucial resource—our people.
Think, Behave, and Communicate Like a Leader
Leadership is a mindset and a set of behaviors that can be cultivated.
To think, behave, and communicate like a leader, adopt a long-term vision and analyze situations critically, embracing challenges as opportunities for innovation.
Exhibit confidence to inspire trust and motivate your team, while consistently acting with integrity to build credibility and foster a culture of trust.
Cultivate empathy by actively listening and showing genuine concern for your team’s well-being, which creates a supportive environment.
Communicate effectively by sharing your vision, encouraging feedback, and ensuring everyone feels heard.
Lead by example, demonstrating the work ethic and professionalism you expect from others, while also investing in your team’s growth through learning opportunities and recognition of achievements.
By embodying these principles, you can inspire your team, drive success, and make a positive impact within your organization.
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🎉አፍሌክስ በኢትዮጵያ🇪🇹 ብሎም በአፍሪካ🌍 የመጀመሪያ በሆነው የሴቶች የአመራር ልማት መርሃ-ግብር ያበቃቸውን ሴት አመራሮች ሊያስመርቅ 2ቀናት ብቻ ቀርተዋል🎉
የኢትዮጵያ የማንሠራራት ጉዞ የሚሳካው በተቋሞቻችን ጥንካሬ ነው - ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የማንሠራራት ጉዞ የሚሳካው በተቋሞቻችን ጥንካሬ ነው¬ ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑ አስፈጻሚ አካላትን የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት አፈጻጸም፣ ዛሬ ገምግመናል ብለዋል፡፡
ባለፉት ስድስት ዓመታት መንግሥታችን ለጠንካራ ተቋማት ግንባታ በልዩ ትኩረት ሠርቷል በማለት ገልጸው፤ በተለይም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት ራሳቸውን በአግባቡ በማደራጀት ለሀገር ግንባታ የሚቆጠር አስተዋፅዖ በማበርከት ላይ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።
በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ መስኮች ባለፉት ስድስት ወራት የተመዘገቡ ስኬቶች የተቋሞቻችን የመፈጸም አቅም ማሳያ ናቸው ሲሉም አመልክተዋል።
በቀጣይም ተቋማቱ የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ ለማሳካት አገልግሎት አሰጣጣችንን ማዘመን፣ ወጪ ቆጣቢ አሰራርን መከተል፣ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እና በተሰጠን ተልዕኮ የምንፈጥረውን በጎ ተፅዕኖ እንዲሁም የተገኙ ውጤቶችን በቀጣይነት እየገመገሙ መሄድ አስፈላጊ መሆኑን አቅጣጫ አስቀምጠናል ብለዋል በመልዕክታቸው።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚም ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ተጠሪ ከሆኑ ተቋማት አንዱ በመሆኑ የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን አቅርቧል።
How Character is Created and Leadership is learned
Character is the foundation of effective leadership, shaped by experiences, values, and choices. It is often forged through overcoming life challenges, which build resilience, empathy, and integrity—essential traits for leaders.
Strong leadership is rooted in clear values such as honesty and responsibility, inspiring trust and loyalty in teams. Learning from mentors and observing effective leaders helps individuals cultivate their own leadership style.
Leadership is also a continuous journey of learning through education, self-reflection, and ethical decision-making. Building strong relationships based on trust fosters an environment of support and accountability.
Ultimately, by focusing on character development, individuals can become influential leaders who inspire and uplift others.
#upcomingevent

WHAT: Signing of Letter of Intent for Cooperation between Africa Leadership Excellence Academy (AFLEX) and Ethiopian Youth Council

Participant: AFLEX Management and Ethiopian Youth Council Management team

When: Wednesday 19 February 2025 at 11:00 am

WHERE: AFLEX Leadership Development Center, Sululuta

#Partnership #LeadershipDevelopmentProgram
#Collaboration #emergingleadership #AFLEX #africanleadershipexcellenceacademy #ethiopianyouthcouncil
#EYC