African Leadership Excellence Academy
2.33K subscribers
2.52K photos
96 videos
6 files
118 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
As a Leadership Institution, We Honor Our Commitments

We understand that our credibility depends on the promises we make and the trust we nurture.

Upholding our commitments goes beyond being a policy; it is a fundamental value that shapes our leadership approach.

We aim to foster an environment where transparency and accountability flourish, ensuring that everyone we interact with feels valued and respected.

By honoring our commitments, we strengthen the trust placed in us and lay the groundwork for enduring partnerships based on mutual respect and shared objectives
👍7

👍5
በየደረጃው የሚገኝ አመራር ብልሹ አሰራሮችን በመታገል የጸረ-ሙስና ትግሉን እንዲያግዝ ጥሪ ቀረበ።
ሱሉሉታ ጥር 24/2017 ዓ.ም (አፍሌክስ)- በየደረጃው የሚገኝ አመራር ብልሹ አሰራሮችን በመታገል የጸረ-ሙስና ትግሉን እንዲያግዝ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ጥሪ አቀረቡ።
በአካዳሚው የአስተዳደር እና ቢዝነስ ልማት ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒሰቴር ጽ/ቤት ተጠሪ ከሆኑ አምስት ተቋማት ለተውጣጡ አመራሮች በተዘጋጀው የስነ ምግባር እና ጸረ-ሙስና ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት፤ በየተቋማቱ የሚታየውን የብልሹ አሰራር ዝንባሌዎችና ተግባር ለመከላከል በየደረጃው የሚገኙ የስራ መሪዎች ድርሻ የላቀ መሆኑን ጠቁመው፤ የስነ ምግባር ችግር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል ብለዋል።
ብልሹ አሰራር እና ሙስና የሀገር ሀብት እንዲባክን፣ ፍትሀዊ ያልሆነ የገቢ ልዩነትን እንዲፈጠር፣ የውጭ ኢንቨስትመንት እንዲቀንስ፣ የሕግ የበላይነት እንዳይኖር፣ የማህበራዊ ኑሮ እንዲደበዝዝ፣ እና የሰራተኞች የስራ ተነሳሽነት እና ምርታማነት እንዲቀንስ ያደርጋል ያሉት ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር)፤ የጀመርነውን የልማት እና የብልጽግና ጉዞ ከጫፍ ለማድረስ በየደረጃው የሚገኝ አመራር የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
👍4
የፌዴራል የስነ-ምግባር እና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው፤ ሙስና የህሊና እና የሞራል ዝቅጠት ውጤት በመሆኑ በመጸየፍ፤ ህዝብና መንግስት የጣለብንን ሀላፊነት በአግባቡ በመወጣት፤ ሰልጣኞች ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት በጋራ መስራት እንደሚገባቸው ጠቅሰው፤ ስልጠናው ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች በአስተሳሰብ እና በአመለካከት ምሳሌ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።
ሥልጠናው ‘”ስነ ምግባራዊ አመራር፤ ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት” በሚል መሪ ሀሳብ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ፤ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት፤ ከፕሬዚደንት ጽ/ቤት፤ ከቤተመንግስት አስተዳደር እና ከአንድነት ፓርክ ኮርፖሬሽን የተውጣጡ የስራ መሪዎች ተሳትፈዋል።
የሙስና ወንጀል ምንነቶች፣ የሙስና ወንጀል ልዩ ባህሪያት፣ ዘርፉ ለሙስና እና ብልሹ አሠራሮች ያለው ተጋላጭነት፣ እንዲሁም ሙስና እና ብልሹ አሠራሮች የሚያስከትሉት ጉዳትና መከላከያ ስልቶች ላይ እንደሚያተኩርም ተገልጿል።
👍5