African Leadership Excellence Academy
2.32K subscribers
2.51K photos
96 videos
6 files
118 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የባህልና ስፖርት ዘርፍ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ያለው ሚና፣ ተግዳሮቶችና መልካም አጋጣሚዎች በሚል ርዕስ በአፍሌክስ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

ታኅሳስ 22፣ 2017ዓ.ም (ሱሉልታ- አፍሌክስ)- በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እየተሰጠ የሚገኘው አመራሮችን በማብቃት የባህል፣ የስፖርት እና የኪነ ጥበብ ዘርፍ ለሀገር አንድነትና ብልፅግና ያለውን ሚና አጠናክሮ የማስቀጠል ስልጠና በሁለተኛው ቀን ውሎ የባህልና ስፖርት ዘርፍ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ያለው ሚና፣ ተግዳሮቶች እና መልካም አጋጣሚዎች በሚል ርዕስ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

የስልጠናውን ሰነድ አዳነ ካሴ (ዶ/ር ) ባቀረቡበት ወቅት ኢትዮጵያ የብዝሀ ባህል እና ቋንቋ ባለቤት፤ የልዩ ልዩ ዕይታዊ፣ ትዕይንታዊ እና ሥነ-ፅሁፋዊ እሴቶችም ባለቤት እንደመሆኗ መጠን ለሀገር ኢኮኖሚ ልማት ያለው እምቅ አቅም ከፍተኛ ድርሻ ያለው እና ያልተነካ እምቅ ሀብት ያለበት ዘርፍ ነው። በቀጣይም መንግስት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም በሰጠው ትኩረት ልክ ዘርፉ ለዚህ ዕቅድ ስኬት የዕቅዱ አካል አድርጎ ሊሠራ ይገባል ብለዋል።

አክለውም በስፖርት ዘርፉም ልዩ የሆኑ ባህላዊ ስፖርቶች መገኛ ከመሆኗም ባሻገር ዘመናዊ ስፖርቶች የሚከናወኑባት እና ስፖርት ወዳድ የሆነ ህዝብ ያለባት ሀገር እንደመሆኗ ይህንን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የኢኮኖሚ ምንጭ ማድረግ ይገባል።

ሙሉጌታ ጌጡ (ዶ/ር) በበኩላቸው ብሔራዊ የህግ ማዕቀፎችና ዘርፉ ለኢኮኖሚ ያለው አስተዋፅኦ ከሀገሪቱ የልማት ዕቅድ አኳያ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን የባህል፣ የስፖርት እና የኪነ ጥበብ ዘርፍን በህግ ማቀፍ ከህገ መንግስት፣ ከስትራቴጂክ ፖሊሲ፣ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ የየዘርፉ ፖሊሲዎችንና ከዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች አንፃር ገለፃ አድርገዋል።
ሙሉጌታ ጌጡ (ዶ/ር) የስልጠናውን ዓላማ ሲያብራሩ፦ ህጎች የተቋማት ግብ ተገማች ለማድረግ፤ ለባለድርሻ አካላት መተማመኛን ለመፍጠር፤ ለሚፈለገው ግብ መዳረሻ መሳሪያ እንዲሆን፤ ቅንጅታዊ አሰራርን ለማሳለጥ፤ ለተለያዩ አካላት ሚናና ኃላፊነት ለመደልደል የሚያግዝ መሣሪያ ነው ብለዋል።

የባህል፣ ስፖርት እና የኪነ ጥበብ ዘርፍ የሀገሪቱን ህጎች የተቋሙን ፖሊሲዎች መመሪያዎችን እና ዓለማ አቀፋዊ ተሞክሮዎችን በመቀመር ለ17ቱ የሀገሪቱ የዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት ጠንክሮ መስራት ይገባል ብለዋል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጥቂት ሰዎች ሃገር ይቀይራሉ!

"ሁላችንም በአንዴ ሃብታም ልንሆን አንችልም። ነገር ግን ከህዝባችን መካከል ጥቂቱ እንኳን ስኬታማ ስራ ፈጣሪ መሆን ከቻለ ኢትዮጵያ የመለወጥ እድሏ ሰፊ ነው።
ችግሩ ጥቂቶች እንኳን ስኬታማ የሚሆኑበትን እድል የሚፈጥር ሃገራዊ ስነ-ምህዳር አለን ወይ ነው?"

አቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሌክስ ፕሬዝደንት
#AFLEX
#የአካል_ብቃት_እንቅስቃሴ_በአፍሌክስ

ታህሳስ 23፣ 2017ዓ.ም (ሱሉልታ- ኤፍሌክስ)

ብቁ፣ ንቁ እና አሸናፊ ትውልድን ለመፍጠር የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ልማድ ማድረግ አስፈላጊ ነው።

ዛሬ ማለዳ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተከናውኗል።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህል በማድረግ ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች እራሳችንን እንጠብቅ።
#UPCOMINGEVENT

WHAT: Signing of Letter of Intent for Cooperation between Africa Leadership Excellence Academy (AFLEX) and Ministry of Culture and Sport

Participant: AFLEX Management and Ministry of Culture and Sport Management team

When: Thursday 2 January 2025 at 2:00 pm

WHERE: Sululuta, AFLEX

#Partnership #LeadershipDevelopmentProgram #Collaboration

#AFLEX

#Ministry_of_Culture_and_Sport
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የራሳችን ተረቶች የሉንም። ካሉም የሚነግሩን ስለ ዝናብና ስለ ግብርና ነው።

ተረት መናገርን ካለመሰልጠን ጋር አገናኝተነዋል።

ለአገር በቀል ዕውቀቶች የሰጠነው ቦታ አነስተኛ ነው።

ከራሳችን ጋር ተጣልተናል። እንዴት እንታረቅ?

"ከውጭ ለመኮረጅ ብዙ ሞክረናል ብዙም አልተሳካልንም። ወደራሳችን እንመልከት ሃገር በቀል እውቀት ጠቃሚ ነው ይሉናል።" አቶ ዛዲግ አብርሃ :-