African Leadership Excellence Academy
2.32K subscribers
2.51K photos
96 videos
6 files
118 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
Consultative Discussion between AFLEX and Chinese Delegates

Dec 25, 2025 / ADDIS ABABA / AFLEX / A consultative discussion was held between AFLEX President, Mr. Zadig Abreha, and the Chinese delegates from CIDAC, the China Embassy in Ethiopia, the Chinese Mission to the African Union, and the National Academy of Governance at the AFLEX Head Office.
The discussion aimed to strengthen collaboration and explore potential partnerships between the two parties. It highlighted two key areas of focus: human resource development and capacity building, and infrastructural development.

Mr. Zadig Abreha shared the academy’s recent initiatives, detailing its progress and successes. The Chinese delegates were briefed on AFLEX’s ongoing and future projects, especially its ambition to expand its influence in national and African training programs.

There was a notable emphasis on forming partnerships with prestigious Chinese universities, such as Peking University and Tsinghua University, for experience-sharing and collaborative research.

Additionally, the president emphasized the importance of China’s support in expanding AFLEX’s infrastructure.
This included potential collaboration on building new facilities and enhancing existing structures to accommodate the growing demand for training and capacity-building programs.

In response, Deputy Director-General Guan Zhiyoung of CIDAC expressed a strong willingness to collaborate with AFLEX. He shared the Chinese delegation's intent to develop a comprehensive training project plan with AFLEX.

Moreover, he referenced President Xi Jinping’s leadership development initiatives across Africa. He also confirmed that China was eager to engage with AFLEX as part of the BRICS partnership, highlighting the importance of focusing on human resource development as a primary goal.

The discussion concluded with both parties expressing a shared commitment to strengthening ties and creating sustainable collaborations.
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚና ኢጋድ በጋራ ለመስራት የተፈራረሙትን ስምምነት ፋና 90 በምሽት ዜናው እንዲህ ዘግቦታል፡-
ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ.ም. (አፍሌክስ - ሱሉሉታ):- የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያዘጋጁት ለነባር ዲፕሎማቶች እና በጎ ፈቃደኛ ወጣት ካዴቶች ለአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባኤ ዝግጅት በተመለከተ እየተሰጠ የሚገኘው ሥልጠና የዛሬው የ10ኛ ቀን ውሎ በፎቶግራፍ :-
ፎቶ- ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
At AFLEX, we strive to ignite the flame,

To generate leaders who’ll rise to acclaim.

In Ethiopia and Africa, we pave the way,

Empowering minds to shine bright every day

With vision and purpose, together we stand,

Join us on social media—let’s craft a bold plan!

Your journey to leadership starts here today,

Be part of the change, come join the AFLEX way!
የአፍሌክስ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብረሃ ከቻይና ልዑካን ቡድን ጋር በነበራቸው ውይይት ላይ ካነሷቸው ሃሳቦች የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፡-

👉የአፍሌክስን የቅርብ ጊዜ ውጥኖች አጠቃላይ እይታ አካዳሚው ያስመዘገባቸውን አዎንታዊ ግስጋሴዎችን አሳይተዋል።

👉አፍሌክስ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የአመራር ልማት ፕሮግራም ላይ ያለውን ተጽእኖ ለማስፋት ከቻይና ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።

👉ስትራቴጂክ አጋርነቶችን በማጉላት በዘርፉ ልምድ ካላቸው የቻይና ተቋማት እንደ ፔኪንግ እና ፅንጉዋ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጋራ ለመማማር እና ልምድ ለመለዋወጥ የትብብር ግንኙነት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

👉የሰው ኃይል አቅም ግንባታ ላይ ሁለቱ አካላት አብረው አንደሚሰሩ አሳውቀዋል ።

👉 አፍሌክስ መሠረተ ልማትን በማስፋፋት ረገድ የቻይና ድጋፍ ያለውን ጠቀሜታ አጉልተው አሳይተዋል።

👉አዳዲስ የስልጠና ተቋማትን በመገንባት ላይ የጋራ ጥረቶች ሊኖሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

👉መሠረተ ልማትን ማሻሻልን በማጣቀስ የሥልጠናና የአቅም ግንባታ ፍላጐቶችን በተሻለ ለማርካት ነባር መዋቅሮችን በማሳደግ ረገድ ከ ቻይና ጋር በመተባበር እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።
በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የሚሰጡ ካዴቶች ስልጠና ተጠናቀቀ
ታህሳስ 18/2017 (አፍሌክስ-ሱሉሉታ)_በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለሚሰጡ ካዴቶች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።
ላለፉት 12 ቀናት ሲሰጥ የቆየው የበጎ ፍቃደኛ ካዴቶች ስልጠና ማጠናቀቂያ መርኃ ግብር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞትዮስ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።
ሰልጣኞች ከንድፈ ሀሳብ ባሻገር በተግባር የታገዘ ስልጠና መውሰዳቸው በመርኃ ግብሩ ላይ ተገልጿል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞትዮስ (ዶ/ር) ለሰልጣኞች ቀጣይ አቅጣጫ እና የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ስልጣን ከመጡ ማግስት ጀምሮ በርካታ ወጣቶች በበጎ ፍቃድ ስራዎች እያገለገሉ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
የዲፕሎማሲ ስራ ንቃት ዝግጁነትና ብልሃትን የሚጠይቅ መሆኑን በመጠቆም ኢትዮጵያ መርህን መሰረት ያደረገ የዲፕሎማሲ ስልት በመከተል ስኬታማ ስራ ማከናወኗን አስታውቀዋል።
በዚህ ረገድ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ማህበራዊ ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ለዚህም ሰልጣኞች ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
ሰልጣኞች የጉባኤውን ትልቅነት ተገንዝበው በፍጹም አገራዊ ስሜት የተጣለባቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል።
መሪዎች የሚኖራቸው ቆይታ ስኬታማ እንዲሆን በተግባር እና በንድፈ ሀሳብ የተሰጡ ስልጠናዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን በአይበገሬ ህዝቦቿ ያስከበረች የአኩሪ ታሪክ ባለቤት መሆኗን የጠቀሱት ሚኒስትሩ እነዚህን ወረቶች በሚገባ መጠቀም ይገባል ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በበኩላቸው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ከፍ ባለ ሁኔታ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
የተሰጠው ስልጠና ጉባዔውን በተሳካ መልኩ ለማካሄድ ያለመ መሆኑን ጠቁመው ለካዴቶቹ ከ 10 በላይ በሆኑ ርእሰ ጉዳዮች የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል።
ስልጠናው በታቀደለት መልኩ መከናወኑን ገልጸው ስኬታማ እንዲሆን ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
ካዴቶቹ ያገኙት ስልጠና ለጉባኤው ብቻ ሳይሆን ለእለት ተእለት ስራዎችም ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን አንስተዋል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሀሳብ የሃይል ምንጭ ነው!

ኤሎን ማስክን ከስደተኝነት አሜሪካን ወደመቆጣጠር ያሸጋገረው የሃሳብ ሃይል።

የአፍሌክስ ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ዛዲግ አብርሃ እንዲህ ይላሉ!
#The_power_of_idea
#AFLEX
ታኀሳስ 21፣2017 ዓ.ም (ሱሉልታ - አፍሌክስ ):- የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አመራሮችን በማብቃት የባህል የስፖርትና የኪነጥበብ ዘርፍ ለሀገር አንድነትና ብልፅግና ያለውን ሚና አጠናክሮ ለማስቀጠል በአፍሌክስ ስልጠና መስጠት ጀመረ።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ሸዊት ሻንካ የስልጠናውን ማስጀመሪያ መርሀ ግብር አስመልክቶ ንግግር አድርገዋል።
ክብርት ሸዊት ሻንካ እንደተናገሩት በዓለም ላይ ባህል፣ ኪነጥበብ፣ ፈጠራ እና ስፖርት ሕዝቦችን በማስተሳሰር፣ ኢኮኖሚ በማመነጨት፣ ለብዙ ሰዎች የሥራ እድልን በመፍጠር፣ ማኅበራዊ ትስስርን እና ትብብርን በማጎልበት የአንድን አገር ጠንካራ መሰረት የሚጥሉ ዘርፎች እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡
መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት ሴክተሩ ለሀገር ገፅታ ግንባታ እና ለኢኮኖሚ እድገት ሚያበረክተውን አስተዋኦ ለማበርከት የተሰጠንን ታላቅ ሀገራዊ ሀላፊነት ለመወጣት እንዲህ አይነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ለዘርፉ ተዋንያኖች መስጠት ወሳኝ መሆኑን ክብርት ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡
በንግግራቸው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ብቁ አመራሮችን ማፍራት የሚያስችል መሰረተ ልማት እንዲሁም ብቁ አመራር እና ባለሞያዎች ያሉት ሃገራዊ ተቋም መሆኑን ጠቅሰው፤ የሚሰጡ ስልጠናዎችም አሁን ያለንበት ደረጃ እና የወደፊት አዝማሚያዎችን ለማሟላት ታስበው የተዘጋጁ በመሆናቸው የስልጠናው ተሳታፊዎች በቆይታችሁ ተፈላጊውን ችሎታ በመቅሰም ከምትሠሩት የዕለት ከዕለት ተግባር ጋር በማዛመድ ተግባራዊ ልታደርጉ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የአመራር ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ መሰረት ደስታ በመክፈቻ ስነ ስርዐቱ ላይ ተገኝተው ስለአካዳሚው ገለጻ አድርገዋል።