African Leadership Excellence Academy
2.33K subscribers
2.53K photos
96 videos
6 files
119 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
በሰላም እና ደህንነት መስክ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት (MoU) #በአፍሌክስ እና #በኢፌዴሪ_መከላከያ_ዋር_ኮሌጅ መካከል ተፈርሟል።

ዛሬ በተከናወነው የጋራ መግባቢያ ስምምነት ላይ የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን፣ አፍሌክስን በመወከል የአካዳሚው #ፕሬዝደንት_አቶ_ዛዲግ_አብርሃ፣ በመከላከያ ዋር ኮሌጅ በኩል የኮሌጁ ዋና አዛዥ #ብርጋዴር_ጄኔራል #ቡልቲ_ታደሰ ስምምነቱን ፈርመዋል።

አቶ ዛዲግ ስምምነቱን ወደ ተግባር የመለወጥ ስራ በአስቸኳይ የሚከናወን መሆኑን ጠቅሰው፤ ስምምነቱ የመግባቢያ ብቻ ሳይሆን የትግበራ ሰነድም እንደሆነ ተናግረዋል። በተጨማሪም “ የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ከተቋቋመ ጀምሮ ብቁ ወታደራዊ አመራር በማፍራት ረገድ ለሃገር እያበረከተ ላለው አስተዋጽዖ ምስጋና ይገባዋል” ብለዋል።

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ዋና አዛዥ ብ/ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ በበኩላቸው “የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ዋነኛ ተልዕኮ በጦርነት ጊዜ ብቻ ሳይሆን በሰላም ጊዜ ጭምር ስለጦርነት ማወቅ እና መረዳት የሚችል ወታደራዊ አመራር ማፍራት ነው፣ ይህ አመራር ደግሞ በስትራቴጂያዊ ደህንነት መስክ ጥልቅ እውቀት ሊኖረው ይገባል። ይህንን ለማስቻል በአመራር ልማት ዘርፍ ትልቅ ስራ እያከናወነ ካለው አፍሌክስ ጋር መስራት እንደሚገባን እናምናለን” ሲሉ የስምምነቱን አስፈላጊነት ገልጸዋል።

በንግግራቸውም በሰላም እና ደህንነት ዘርፉ ውጤታማ ስራን ለማስመዝገብ የሲቪል እና ወታደራዊ ትብብር በእጅጉ እንደሚያስፈልግ አጽንዖት ሰጥተዋል።

ዛሬ የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ሁለቱ ተቋማት የሚተባበሩባቸውን መስኮች ያካተተ ሲሆን፣ ከነዚህም መካከል; በሰላም እና ደህንነት እንዲሁም በወታደራዊ አመራር መስክ ስልጠና እና ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ካሪኩለም ማበልጸግ፣ በጋራ ጥናታዊ ጽሁፎችን ማዘጋጀት እንዲሁም የባለሙያዎች ልውውጥ ማድረግ ተጠቃሽ ናቸው።

ሁለቱም ተቋማት ያላቸውን አቅም በጋራ በመጠቀም በሰላም እና ደህንነት መስክ የአመራር ልህቀት ለማስመዝገብ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
👍12