African Leadership Excellence Academy
2.33K subscribers
2.53K photos
96 videos
6 files
119 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው
*****************

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በስብሰባው ላይ የምክር ቤት አባላት ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ለህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡

ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥያቄዎቹ ላይ የሚሰጡትን የመንግሥትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡
👍11
ከዚህ ዓመት ጀምሮ ለኢትዮጵያ እንደ ሀገር ሀገራዊ ማንሰራራት የምንጀምርበት ዓመት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
👍13
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ካነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፡-
👉በ2016 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ 8 ነጥብ 1 በመቶ እድገት ተመዝግቧል፤
👉 ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃም ትልቅ ስኬት ነው፡፡ በዘንድሮው በጀት ዓመትም 8 ነጥብ 4 በመቶ እድገት እንደሚመዘገብ ይጠበቃል፤
👉 ከዚህም ውስጥ ግብርና 6 ነጥብ 1 በመቶ እንደሚያደግ የሚጠበቅ ሲሆን፤ 30 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማረስ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ኩንታል ምርት ይጠበቃል፤
👉 በተለያዩ ዘርፎች ሲከናወኑ የነበሩ ሪፎርሞችን አጠናቀን ሀገራዊ ማንሰራራት የምንጀምርበት ዘመን የመጀመሪያ ምእራፍ ላይ ተገኝተናል፤
👉 በመሆኑም በ2017 በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ለውጥ የምናስመዘግብ ይሆናል፤
👉 ከዚህ አኳያ ከትናንት እሳቤ ወጥተን በጋራ ወደ ነገ መሻገር አለብን፡፡
👍14
በዚህ ዓመት የግብርናው ዘርፍ 6 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት ያስመዘግባል - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጥቅምት 21/2017 (አዲስ ዋልታ) በተያዘው በጀት ዓመት የግብርናው ዘርፍ 6 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት ያስመዘግባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እየተካሄደ ባለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛል።

በማብራሪያቸውም በ2017 በጀት ዓመት 8 ነጥብ 4 በመቶ ዕድገት ለማስመዝገብ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም በግብርናው ዘርፍ ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ መነቃቃት መፈጠሩን ገልጸው በዚህ ዓመት በተሰራው ሰፊ ስራ 6 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት ያስመዘግባል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል።
👍14
በበጀት ዓመቱ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ 72 ትላልቅ ፋብሪካዎች ሥራ ይጀምራሉ -ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው በጀት ዓመት በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ 72 ትላልቅ ፋብሪካዎች ሥራ እንደሚጀምሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የኢንዱስትሪ ዘርፍን በሚመለከት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ÷በዘርፉ በተያዘው በጀት ዓመት 12 ነጥብ 8 በመቶ እድገት ይጠበቃል ብለዋል፡፡
ማኑፋክቸሪንግ ላይ 12 በመቶ እድገት እንደሚጠበቅ ጠቅሰው÷ኮንስትራክሽን ላይ ደግሞ 12 ነጥብ 3 በመቶ ገደማ እድገት ይጠበቃል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ኢንዱስትሪ በዚህ ዓመት ከፍተኛ እድገት እንደሚያመጣ የተጠበቀበት ዋናው ምክንያትም ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ ታምርት በሚል ንቅናቄ የጀመርነው ሥራ የሚጨበጥ ፍሬ እንደሚያመጣ ስለሚጠበቅ ነው ብለዋል፡፡
እንዲሁም ኢንዱስትሪን ባለፈው ዓመትና በዚህ ዓመት መጀመሪያ በእቅድ ደረጃ እያንዳንዱ ፋብሪካ ምን ችግር እንዳለው፤ ምን ብናግዘው ምርታማነቱ እንደሚያድግ በጋራ ለመስራት ጥረት ተደርጓልም ነው ያሉት፡፡
ከፋብሪካዎች ጋር የሚያያዝ መብራት ከሞላ ጎደል ተፈትቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ከቴሌና ከባንክ ጋር የሚያያዝ ችግርም ከሞላ ጎደል መፈታቱን አንስተዋል፡፡
በተያዘው በጀት ዓመትም በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ 72 ትላልቅ ፋብሪካዎች ሥራ ይጀምራሉ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው፡፡
ከመሬት አቅርቦትና ከእኛ አሰራር ጋር የሚያያዙ በርካታ ችግሮች መፍትሔ እያገኙ መጥተዋል ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ተጨማሪ ስራ የሚያስፈልገውና ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ የሚፈልጉት ከጉምሩክ ጋር የሚያያዝ ስራ እንደሆነም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
👍14
በተያዘው በጀት ዓመት፡-

👉የኢንዱስትሪ ዘርፉ 12 ነጥብ 8 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል

👉 የሌማት ትሩፋት ምርቶች የ5 ነጥብ 4 በመቶ እድገት ያስመዘግባሉ

👉 በዓመቱ 12 ቢሊዮን ሊትር የወተት ምርት ይጠበቃል

👉 8 ቢሊዮን የዶሮ እንቁላል ለማግኘት ታቅዷል

👉 218 ሺሕ ቶን ስጋ እና 297 ሺሕ ቶን የማር ምርት ለማምረት እቅድ ተይዟል

👉 በዘንድሮው በጀት ዓመት 8 ነጥብ 4 በመቶ እድገት እንደሚመዘገብ ይጠበቃል

👉 30 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማረስ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ኩንታል ምርት ይጠበቃል

👉72 ትልልቅ ፕሮጀክቶች ስራ ይጀምራሉ

👉 በኢንዱስትሪ ሴክተር 12 ነጥብ 8 በመቶ እድገት ይጠበቃል

👉 በማኑፋክቸሪንግ 12 በመቶ በኮንስትራክሽን ደግሞ 12 ነጥብ 3 በመቶ እድገት ለማስመዝገብ ታቅዷል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ከሰጡት ምላሽና ማብራሪያ የተወሰደ።
👍14
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ካነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፡-
👉 ባለፉት ሦስት ወራት 180 ቢሊየን ብር ገቢ ሰብስበናል፡፡ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት 109 ቢሊየን ብር ነበር የተሰበሰበው፡፡ የልዩነቱ ስፋት ለውጥ እንዳለ እና መንገዳችን ትክክል እንደሆነ አመላክች ነው፡፡
👉 በፌደራል መንግሥት 900 ቢሊየን ብር በክልሎች ደግሞ 600 ቢሊየን ብር ገቢ መሠብሰብ ከተቻለ በአጠቃላይ 1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ገደማ እንሰበስባለን ማት ነው፡፡ ይህም በቂ ባይሆንም ትልቅ እመርታ ነው፡፡
👉 ሪዘርቭን በተመለከተ ደግሞ የብሔራዊ ባንክ ሪዘርቭ 161 በመቶ አድጓል፡፡
👉 የግል ባንኮች ሪዘርቭ 29 በመቶ አድጓል፡፡
👉 ሬሚታንስን በተመለከተም ባለፉት ሦስት ወራት 24 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡
👉 ባንኮች 652 ሚሊየን ዶላር ገዝተው 1 ቢሊየን ገደማ ዶላር ሸጠዋል፡፡
👉 ባለፉት ሦስት ወራት ከኤክስፖርት ምርቶች 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ለማግኘት አቅደን፤ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር አግኝተናል፡፡ ይህ ትልቅ ስኬት ነው፡፡
👍12
በዚህ ዓመት 72 ትላልቅ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች ስራ እንደሚጀምሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ፤ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ከኢንዱስትሪው በዚህ ዓመት 12 ነጥብ 8 በመቶ እድገት ይጠበቃል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ እያንዳንዱ ፋብሪካ ችግሩ እንዲፈታ ከፍተኛ ስራ መከናወኑን ገልጸዋል።

በዚህም የኤሌክትሪክ፣ የቴሌኮም፣ የባንክና ሌሎች አገልግሎቶች መቀረፋቸውን ተናግረዋል።

ከመሬት አቅርቦት፣ ከመንግሥታዊ አገልግሎትና ከጉምሩክ ጋር የተያያዙ በርካታ ችግሮች እየተፈቱ ነው ብለዋል።

በዚህ ዓመትም 72 አዳዲስ ከፋብሪካ በላይ የሆኑ ኢንዱስትሪዎች ሥራ እንደሚጀምሩ ጠቅሰዋል።

ሥራ የሚጀምሩትም 9 የጨርቃጨርቅ፣ 41 የምግብና መጠጥ፣ አራት የኮንስትራክሽንና ኬሚካል፣ 15 የቴክኖሎጂ ና ሦስት የሚሊተሪ ኢንዱስትሪዎች ናቸው ብለዋል።

ከመከላከያ ጋር ተያይዞ ከውጭ ይመጡ የነበሩ ምርቶችን ከመተካት ባለፈ ለአፍሪካ ገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ገቢ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።

እነዚህ 72 ፋብሪካዎችች ሥራ ሲጀምሩ ቀድመው ከነበሩት ተጨማሪ ኃብት ያመጣሉ ነው ያሉት።

በአገራዊ ለውጡ 50 በመቶ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በሀገር ውስጥ ባለኃብቶች እንዲያዙ በማድረግ በተኪ ምርትም ከፍተኛ እመርታ መምጣቱን ጠቅሰዋል።

በጥቅሉ በዚህ ዓመት የኢንዱስትሪዎች የምርት አቅም ከ59 በመቶ ወደ 67 በመቶ ዕድገት ይጠበቃል ብለዋል።
👍12
ባለፉት ሦሥት ወራት ከ180 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አግኝተናል፡፡ በዚህ ሦሥት ወራት ያገኘነው ገቢ በ2010 ዓ.ም ዓመቱን ሙሉ ካገኘነው ይልቃል፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍13
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ካነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፡-

👉 የዋጋ ግሽበት ባለፉት ዓመታት በርካታ ሀገራትን ፈትኗል ፤ ኢትዮጵያም የዋጋ ግሽበትን ለመቅረፍ በርካታ ስራዎችን እያከናወነች ነው፤ በተለይም ምርት ማምረት ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

👉 በሀገሪቱ የሚስተዋለውን የዋጋ ግሽበት ለመቅረፍም ከ300 እስከ 400 ቢሊየን ዶላር ለድጎማ ተይዟል፡፡

👉 ባለፉት 3 ወራት ለነዳጅ ዘርፍ 35 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ተደጉሟል፤ በበጀት ዓመቱ ለሴፍቲነት 80 ቢሊየን ብር፣ ለዘይት 9 ቢሊየን ብር፣ ለማዳበሪያ 53 ቢሊየን ብር ለድጎማ ተመድቧል፡፡

👉 የደመወዝ ጭማሪውን በተመለከተ ከፍተኛ የዳታ ችግር ተፈጥሯል፤ ይህን ዳታ ለማጥራት ከፍተኛ ሥራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡

👉 ለደመወዝ ጭማሪ 91 ቢሊየን ብር ተመድቧል፤ ጭማሪውም በተያዘው ጥቅምትር ወር ጀምሮ ተግባረዊ ይደረጋል፡፡

👉 በተያዘው በጀት ዓመት የዋጋ ግሽበት 17 በመቶ ሆኗል፤ ይህም ካለፉት ዓመታት አንጻር የተሻለ ሥራ መሰራቱን ያመላክታል፡፡

👉 ኢንዱስት ፓርኮች 50 በመቶ በሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ተይዘዋል፡፡

👉 ከነበሩበት 59 በመቶ የማምረት ዐቅም በዚህ ዓመት 67 በመቶ የምርት ዕድገት ይጠበቅባቸዋል ኢንዱስትሪ ፓርኮች፡፡

👉 124 አዳዲስ አውሮፕላኖች አዝዘናል፡፡ በኢትዮጵያ ሁለተኛ የሆነውን አውሮፕላን በእጥፍ ለመብለጥ እየተሠራ ነው፡፡

👉 በአፍሪካ ትልቁን የአውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት እየሠራን ነው፡፡

👉 ከነበሩበት 59 በመቶ የማምረት ዐቅም በዚህ ዓመት 67 በመቶ የምርት ዕድገት ይጠበቅባቸዋል ኢንዱስትሪ ፓርኮች፡፡

👉 124 አዳዲስ አውሮፕላኖች አዝዘናል፡፡ በኢትዮጵያ ሁለተኛ የሆነውን አውሮፕላን በእጥፍ ለመብለጥ እየተሠራ ነው፡፡
👍13
“ብልፅግና ድሃን ይወዳል፤ ለድሃ ይራራል ድህነትን ግን አብዝቶ ይጠላል። ድህነትን እንበቀላለን፤ ድሃን ግን እናግዛለን” - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
👍12
አትዮ ቴሌኮም ለኢትዮጵያ የኤክትሮኒክ ግብይት ዕድገት የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*************************

አትዮ ቴሌኮም ለኢትዮጵያ የኤክትሮኒክ ግብይት ዕድገት የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “አትዮ ቴሌኮም ሰዎችን በስልክ ከማገናኘት አልፎ ኢ-ኮሜርስ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲያድግ ከፍተኛ ድርሻ እየተጫወተ ይገኛል“ ብለዋል

ተቋሙ የኤክትሮኒክ ግብይት ላይ በትኩረት በመሥራቱ በሀገሪቱ በሞባይል ስልክ የሚፈጸም የግብይት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን አንስተዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች እያስፋፋው የሚገኘው የ5ጂ ቴክኖሎጂም ለዘርፉ ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ጠቁመዋል፡፡

ተቋሙ በቅርቡ ያካሄደው የ10 በመቶ የአክስዮን ሽያጭ የተቋሙን አቅም ይበልጥ እንደሚሳድገውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አመላክተዋል፡፡
👍13
የኢትዮጵያን ዕዳ ከ10 በመቶ በታች ለማድረግ ይሰራል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*********************

በሚቀጥሉት ዓመታት የኢትዮጵያን ዕዳ ከ10 በመቶ በታች ለማድረግ እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የብድር ጫና ከአጠቃላይ ሀገራዊ ጥቅል ምርት አንጻር ከነበረበት ከ30 ነጥብ 6 በመቶ ወደ 13 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ ማድረግ መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡

በሚቀጥሉት ዓመታት ይህን አሃዝ ከ10 በመቶ በታች ለማድረግ እንደሚሰራም አስታውቀዋል፡፡

ባለፉት ስድስት ዓመታት መንግስት ምንም አይነት የንግድ ብድር አለመውሰዱን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በተጠቀሰው ጊዜ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮ ቴሌኮምን ሳይጨምር 13 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ መክፈሉን ገልጸዋል፡፡

“ይህም ለትውልዱ ዕዳን ሳይሆን ምንዳን ለማውረስ የምናደርገውን ሥራ የሚያግዝ ነው” ብለዋል፡፡
👍13
ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ከመሞትና ከመግደል በሰላማዊ መንገድ መታገል ውጤቱ የተሻለ ነው - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ከመሞትና ከመግደል በሰላማዊ መንገድ መታገል ውጤቱ የተሻለ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኃይል አማራጭ ይልቅ የሰላም አማራጭ ውጤቱ ከፍተኛ እና ተመራጭ መሆኑን አንስተዋል።

ሰላም ፈላጊ ብዙዎች ቢሆኑም ጥቂት ሰላም የማይፈልጉ ኃይሎች እንዳሉ በመጥቀስም በዓለም ላይ የሚገኙ መንግስታት ለዜጎች መኖሪያ ቤትም ማረሚያ ቤትም የሚገነቡት ለዚሁ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

“እኛ ከማንም በላይ ሰላም እንፈልጋለን፤ ክላሽ መሸከም ምን ያህል ጉዳት እንዳለው ይገባናል” ብለዋል።

በዚህች ሀገር ላይ የሚጨበጥ ለውጥ ማምጣት እንፈልጋለን፣ ያን ለማድረግ ደግሞ ሰላም በእግጁ ያስፈልጋል ነው ያሉት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሰላምን በተሟላ ሁኔታ ማረጋገጥ ካልተቻለ የምናስበውን እድገት ማምጣት እንቸገራለን ብለዋል።

ከአማራ እና በኦሮሚያ አካባቢ ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች ጋር ንግግር እንዳለ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሁን እንጂ ንግግር እና ሰላም የሚፈልጉትን ኃይሎች እንዴት ከመንግስት ጋር ትነጋገራላችሁ ብለው የሚወቅሱ ሰዎች መኖራቸውን አንስተዋል።

መንግስት ግጭቶች በሰላም እንዲፈቱ ቅድሚያ ሰጥቶ መስራቱን በመግለጽ አሁንም ያለን አቋም የትኛውም አይነት አለመግባባት በሰላም እንዲፈታ ነው ብለዋል፡፡

የትኛውም አካል በኃይል እና ጥላቻ መጠፋፋትን እንጂ ዓላማውን ማሳካት አይችልም፤ ሰከን ብሎ ማሰብ ይገባል ሲሉም ገልጸዋል፡፡
👍14
“አማራ ክልልን ባለፉት ዓመታት የኢንዱስትሪ ማዕከል አድረገነዋል”- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
**
(ኢ ፕ ድ)
አማራ ክልልን ባለፉት ዓመታት የኢንዱስትሪ ማእከል አድረገነዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከሕዝብ እንደራሴዎች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡

ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራሪያ አማራ ክልልን ባለፉት ዓመታት የኢንዱስትሪ ማዕከል መሆን መቻሉን ጠቅሰው፤ ባለፉት ዓመታት በክልሉ የጨርቃ ጨርቅ፣ የዘይት፣ የሲሚንቶ እና ሌሎች ፋብሪካዎችን መገንባታቸውን በአስረጂነት ጠቀሰዋል፡፡

የክልሉን የመንገድ ግንባታ ችግርም ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት መደረጉን እንዲሁም በባህር ዳር ከተማ በኢትዮጵያ ተሠርቶ በማያውቅ መልኩ ድልድይ መገንባቱን አንስተዋል፡፡

የኮሪደር ልማት፣ የመገጭ ግድብ፣ የፋሲል ቤተ መንግስት እድሳት እና ሌሎች የልማት ስራዎች በክልሉ እየተከናወነ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

አማራ ክልል ካልተቀየረ ኢትዮጵያ ስለማትቀየር አማራ ክልል እንዲቀየር ተባብረን እንስራ ብለዋል፡፡
👍13