African Leadership Excellence Academy
2.13K subscribers
2.38K photos
89 videos
6 files
104 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ እና #የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_ኃይል #የአመራር_ልማት_ስርዓተ_ስልጠና ዝግጅትን በጋራ ገምግመዋል።
ግምገማው የተካሄደው የአካዳሚው የፕሮግራም ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ተወካይ #እሸቴ_አበበ /ዶ/ር/ እና የሪፎርም ኮሚቴ ሰብሳቢ #ሞገስ_ሎጋው /ዶ/ር/ እና የካሪኩለም ዝግጅት ቡድን ባሉበት ሲሆን፣ በግምገማውም በአፍሌክስና በኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል በትብብር የተዘጋጀው የአመራር ልማት ስርዓተ ስልጠና ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት የተከናወነ መሆኑ ተጠቅሷል።
#ወንድወሰን_ካሳ ዶ/ር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል #የሰው_ኃይል_ልማት_ዳይሬክተር እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅት የስርዓተ ስልጠና ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ለቫሊዴሽን ግምገማ /Validation Workshop/ የማዘጋጀት ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ በቀጣይ ከቫሊዴሽን/ የሚገኘውን ግብዓት በማካተት ስርዓተ ስልጠናውን በበላይ ሃላፊዎች በማስጸደቅና ሞጁል በማዘጋጀት የአመራር ልማት ፕሮግራም ለማስጀመር የሚያስችል ስራዎች ማጠናቀቅ እንዲሚገባ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡