African Leadership Excellence Academy
2.34K subscribers
2.55K photos
96 videos
6 files
119 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) አካዳሚውን ወክለው ከሸገር ሲቲ መና አብቹ ክፍለ ከተማ አመራሮችና ሰራተኞች ጋር በመሆን ነሐሴ 17፣ 2016 ዓ.ም አረንጓዴ ዓሻራቸውን አኑረዋል::

በአንድ መንፈስ በመላው ኢትዮጵያ ዓሻራችንን እናኑር፡፡ አንድ ከሆን ከዚህም በላይ እንችላለን!
👍2
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ አመራሮች እና ሰራተኞች ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) በተገኙበት ነሐሴ 17፣ 2016 ዓ.ም አረንጓዴ ዓሻራቸውን አኑረዋል::

በአንድ መንፈስ በመላው ኢትዮጵያ ዓሻራችንን እናኑር፡፡ አንድ ከሆን ከዚህም በላይ እንችላለን!
👍3
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የአንድ ጀምበር የአረጓዴ አሻራ መርሐ ግብር  አከናወነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 ዓ.ም ሱሉልታ (አፍሌክስ)  የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮችና ሠራተኞች ሁሉም በነቂስ ወጥቶ  የአንድ ጀምበር የአረጓዴ አሻራ መርሐ ግብር  አከናወኑ ።

በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ዓሻራችንን እናኑር “በአንድ መንፈስ በመላው ኢትዮጵያ ዓሻራችንን እናኑር” “አንድ ከሆን ከዚህም በላይ እንችላለን!” የሚለውን የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ /ዶ/ር/ መልዕክትን ተከትሎ የአንድ ጀምበር የአረጓዴ አሻራ ችግኝ ተካለ መርሐ-ግብር አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቆ ለዛሬው ቀን መደረሱን በአፍሪካ አመራር ልህቀት  አካዳሚ የኦፕሬሽን  ዘርፍ  ም/ል ርዕሰ  አካዳሚ (ዶ/ር)  ወንድዬ ለገሰ አስታወቀዋል ፡፡
የዘንድሮ  ተከላ ለየት የሚያደርገው መንገዱን ተከትሎ የተደረገ ተከላና የአካባቢው ሰዎች ሲያልፉ  እየተዝናኑ  እንዲያልፉ  ታሳቢ ተደርጎ መሆኑን ተናግረዋል ።

ለችግኝ ተከላው የሚውሉ ችግኞች በቅርብ ሥፍራ ዝግጁ መደረጋቸውን ተናግርዋል ፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ በፈጠራቸው የተለያዩ አደጋዎች እየተቸገረች የምትገኘውን ዓለም እፎይታን የሚያጎናፅፍ ተግባር እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በተያዘው እቅድ መሰረት እንደሀገር 600 ሚለየን ችግኝ ለመትከል ሁሉም ዜጋ በንቃት እንደሚሳተፍም አስታወቀዋል ፡፡
👍2
402 ሚሊየን
"የምትተክል ሃገር የሚያጸና ትውልድ" የ600 ሚሊዮን ችግኞች የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከማለዳው12 ሰአት ጀምሮ እስከ ቀኑ 8 ሰአት ከ30 ደቂቃ ባለው ጊዜ 402 ሚሊየን ችግኞች ተተክለዋል፡
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ_ፕሬዚደንት_ዛዲግ_አብርሃ የእንኳን ደስ አለን መልዕክት አስተላለፉ::

የዛሬ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ስድስት መቶ ሚሊዮን ችግኞችን ልንተክል ኢትዮጵያውያን ሁሉ አቅደን ነበር። ያሰብነውን ሳናሳካ ጀምበር የሚጠልቅብን አይደለንምና በአንድ ጀምበር 615.7 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል ችለናል።

ፎቶ:- ከአፍሌክስ ክምችት
👍3