African Leadership Excellence Academy
2.36K subscribers
2.56K photos
96 videos
6 files
120 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
'22ኛውን ክፍለ ዘመን ለአፍሪካውያን ለመዋጀት ከአፍሪካውያን ወጣቶች ብዙ ይጠበቃል። ወጣቱ አቅሙን ገንብቶ የአፍሪካን ህዳሴ የሚያረጋግጥበት ጊዜው ደርሷል።
አፍሌክስ በወጣቶች አመራር ልማት ከአፍሪካውያን ጋር አብሮ ይሰራል። '
አቶ ዛዲግ አብርሃ በፓን አፍሪካን ወጣቶች ዩኒየን ጉባኤ መክፈቻ ላይ ከተናገሩት የተወሰደ
'የቅኝ ግዛት አስተሳሰቦች አሁንም ድረስ በአፍሪካ የትምህርት ስርዓት ውስጥ አሉታዊ ጥላቸውን እንዳጠሉ ነው። የአፍሪካ የትምህርት ስርዓት ከእጅ አዙር የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ እና አመለካከት ነጻ እንዲወጣ ወጣቶች ዘመኑ የሚፈልገውን ጥናት እና ምርምር በማድረግ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ መፈለግ ይኖርባቸዋል።'
አቶ ዛዲግ አብርሃ በፓን አፍሪካን ወጣቶች ዩኒየን የመክፈቻ ጉባኤ ላይ የተናገሩት
# አሁን
አቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሪካ አቅም ግንባታ ፋውንዴሽን ( African Capacity Building Foundation) በአፍሪካ ህብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ባዘጋጀው ስልጠና ላይ እየተሳተፉ ነው::
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን ሪፎርም: ማስፋት እና ሽግግር ለተሳታፊዎቹ እንዲያብራሩም በአዘጋጁ አካል መድረኩ ተመቻቶላቸዋል::
የከተማ እና መሰረት ልማት ሚኒስቴር ለ 9ኛ ግዜ የዘመኑ ከተሞች ለኢትዮጵያ ብልጽግና በሚል መሪ ቃል የከተሞች ፎረም በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሄዷል::
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ በመድረኩ ላይ ተገኝተው በከተማ አመራር ልማት ፕሮግራም ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበዋል::
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ እየተሳተፉበት ያለውን እና የአፍሪካ አቅም ግንባታ ፋውንዴሽን ያዘጋጀውን ስልጠና ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዲህ ዘግቦታል:-
የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ትግበራ ማፋጠን ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ነው
On Feb 20, 2024 77
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ትግበራን ማፋጠን እና የአፍሪካ የንግድ እና የኢኮኖሚ ትስስርን ማሳደግ በሚል መሪ ሃሳብ ለአምባሳደሮች እና ለዲፕሎማቶች ስልጠና እየተሰጠ ነው።
በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ እየተሰጠ ባለው ስልጠና አምባሳደሮች፣ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ዛዲግ አብርሃ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ስልጠናው በአፍሪካ ሀገራት መካከል የሚደረገውን የግብይት መጠን እና የንግድ ትስስር ለማሳደግ ያለመ ሲሆን÷ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት እንደሚሰጥ ተመላክቷል፡፡
በለይኩን ዓለም
አፍሪካ እና የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ #2
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን እና አፍሪካን የሚያስተሳስሩ ፕሮጀክቶችን ማስተዋወቃችንን ቀጥለናል።
አካዳሚው አፍሪካዊ ቅርጽ እና ይዘት እንዲኖረው ከሚያግዙ እና በአፍሪካውያን ወንድሞች እና እህቶች ዘንድ የእኔነትና የባለቤትነት ስሜት ከሚፈጥሩ ፕሮጀክቶች መካከል አፍሪካዊ መዋቅር እንዲኖር ማድረግ አንዱ ነው።
አካዳሚው በሪፎርም ማስፋት እና ሽግግር ስራው ውስጥ የአፍሌክስን መዋቅራዊ አደረጃጀት በመከለስ እና በማስፋት ከኢትዮጵያ ውጭ በሆነ/ች አፍሪካዊ/ት ምክትል ፕሬዚደንት የሚመራ ዘርፍ የመዋቅሩ አካል እንዲሆን አጽድቋል።
በአፍሪካውያን የሚመራው እና ለአፍሪካውያን የሚሰራው የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት ዘርፍ፤ አፍሌክስን ከአፍሪካ ጋር ከማገናኘቱ ባሻገር አፍሪካውያንን በማስተባበር ያላቸውን እምቅ አቅም እና ችሎታ የአፍሪካን ብልጽግና ለማረጋገጥ እንዲጠቀሙበት ለማድረግ ያስችላል።
የፓን አፍሪካን አስተሳሰብ እና ፍልስፍና ለአፍሪካውያን እና ለተቀረው ዓለም ተደራሽ በማድረግም አፍሪካውያን እርስ በእርስ የሚገናኙበትን መድረክ በመፍጠር የስራ ልምዳቸውን ከተሞክሮአቸው ጋር እያዋሀዱ የአህጉሪቷን የሰው እና የተፈጥሮ ሀብት ለሚታለመው ተግባር እንዲውል ለመስራት ዘርፉ ትልቅ ሚና ይኖረዋል።
የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት ዘርፍ የሰው ሀይሉን ከሁሉም የአፍሪካ ሀገራት በመመልመል፤ በመቅጠር እና ወደ ስራ በማስገባት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን ከመላው አፍሪካ ጋር ለማስተሳሰር እና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ለመመስረት ቁልፍ ሚና ይኖረዋል። ከሁሉ በላይ ግን አፍሌክስ የአፍሪካውያን ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማህተም ሆኖም ያገለግላል።
አፍሪካ እና የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ #3
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እንደ ስሙ እና ተልዕኮው አፍሪካዊ ሆኖ፤ በሀገራችን እና በአፍሪካ መካከል ያለውን የግንኙነት መስመር በላቀ መንገድ ለማገናኘት እና እንደ ድልድይ ሆኖ ለማገልገል የቀረጻቸውን የሪፎርም፤ የማስፋት እና የሽግግር ስራዎችንና ስትራቴጂዎችን ማስተዋወቃችንን ቀጥለናል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 484/2013 ሲቋቋም ከተሰጡት ተልዕኮዎች መካከል የኢትዮጵያን፤ የአፍሪካ ቀንድን እና የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችን በአመራር ልማት ፕሮግራሞች አቅማቸውን መገንባት፤ ጥናትና ምርምር በማድረግ ለፖሊሲ አውጭዎች ግብዓት ማቅረብ እና የማማከር አገልግሎት መስጠት ተጠቃሾቹ ናቸው።
አካዳሚው በተሰጠው ተልዕኮና ወሰን ልክ ለመስራት የነበሩበትን ውስንነቶች ቀርፎ፤ በተለይም በ2016 ዓ.ም የአመራር ለውጥ ሲደረግ ሰፋፊ የሪፎርም፤ የማስፋት እና የሽግግር ስራዎች ውስጥ ገብቶ፤ ከአፍሪካውያን ጋር የሚያስተሳስሩ እና ወንድማማችነትን የሚያጎለብቱ ፕሮጀክቶችን ቀርጿል።
የአፍሪካ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን መቅረጽ ከአፍሪካውያን ጋር እንደ ድልድይ ሆኖ የሚያገናኝ ስትራቴጂ እንደሆነ ስለታመነበት፤ አካዳሚው አራት ጠቅላላ (General LDP) (Executive Level Leadership Development Program, Emerging Leaders Development Program, Women Leadership Development Program and Public Leadership Development Program) እና ሰላሳ ስምንት ልዩ (Specialized LDP) የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ለይቶ ወደ ስራ ገብቷል። እነዚህ የአመራር ልማት ፕሮግራሞች በአፍሪካ ውስጥ ለሚገኙ አመራሮች በሙሉ የሚሰጡ ሲሆኑ፤ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች ገለጻ ተደርጎላቸው የተገኘው ግብረ መልስ የሚያመላክተው ፕሮግራሞቹ ለአህጉሪቷ አመራሮች አቅም ግንባታ የሚኖራቸው ጥቅም የጎላ እንደሆነ ነው።
አፍሌክስ የጀመራቸው የሪፎርም፤ የማስፋት እና የሽግግር ስራዎች አፍሪካውያንን ወደ አንድ ጥላ የሚያሰባስቡ፤ ስብራትን የሚጠግኑ፤ እና የጋራ አፍሪካዊ ትርክትን ለመፍጠር የሚያግዙ እንደሆኑም ይታመናል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላም እና ደህንነት ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ለሆኑት ፋና ገብረሰንበት (ዶ/ር) ስለ አፍሌክስ የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች ገለጻ ተደረገላቸው::
ገለፃውን ያደረጉት አቶ መስፍን በሀይሉ በአካዳሚው የሴቶች አመራር ልማት ፕሮግራም ፕሮጀክት ሀላፊ ሲሆኑ አፍሌክስ አስራ ሶስት ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ወደ ስራ እንደገባ እና ለስምንቱ ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ ጠቅሰው አራት የጠቅላላ እና ሰላሳ ስምንት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ለሀገራችን እና ለአፍሪካ መሪዎች እንደተቀረጸ ገልፀዋል።
ፋና ገብረሰንበት (ዶ/ር) ለተደረገላቸው ገለፃ አመስግነው ኢንስቲትዩቱ ከአፍሌክስ ጋር በቅንጅት ሊሰራ የሚችልባቸው መስኮች እንዳሉ ገልጸዋል:: በተለይም አካዳሚው ለአፍሪካውያን ከሚከፍታቸው ሶስት ትምህርት ቤቶች ጋር በተያያዘ በትብብር መስራት የሚቻልባቸው መንገዶች እንዳሉ ጠቁመው በቀጣይ በሚኖሩ ውይይቶች የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ የአፍሌክስ ሪፎርም ማስፋት እና ሽግግር እንዲሳካ ኢንስቲትዩቱ ያግዛል ብለዋል::
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና የአሜሪካ ኤምባሲ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከአሜሪካ ምክትል አምባሳደር GWENDOLYN “WENDY” GREEN, Deputy Chief of Mission እና ከባህል ጉዳዮች ሀላፊ RYAN BRADEEN, Cultural Affairs Officer ጋር ተወያይተዋል።
አቶ ዛዲግ አብርሃ በውይይቱ ላይ ስለ አፍሌክስ ሪፎርም፤ ማስፋት እና ሽግግር ገለጻ አድርገዋል።
የኢትዮጵያን እና የአፍሪካን መሪዎች አቅም ለመገንባት እና ተተኪ አመራሮችን ለማፍራት አፍሌክስ አስራ ሶስት ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ወደ ስራ እንደገባ የጠቀሱት ርዕሰ አካዳሚው፤ ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት ስርዓት በመዘርጋት ሂደት ውስጥ የአሜሪካ መንግስት ድጋፍ እና እገዛ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
በተለይም በሁሉን አቀፍ የአመራር ስርዓት ፕሮግራም ቀረጻ፤ በአፍሪካ የአመራር ልማት እና ትምህርት ፕሮግራሞች ትግበራ፤ እንዲሁም አፍሌክስ ራሱን ለመላው ዓለም እንዲያስተዋውቅ የሚረዱ የብራንዲንግ እና የኮሙዩኒኬሽን ስትራቴጂ ቀረጻዎች ላይ ኤምባሲው የቴክኒክ እና የመሰረተ ልማት ድጋፍ እንዲያደርግ ግብዣ አቅርበዋል።
ምክትል አምባሳደሯ GWENDOLYN “WENDY” GREEN, Deputy Chief of Mission በበኩላቸው ከአፍሌክስ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ መስኮች መኖራቸውን ጠቁመው፤ በተለይም በአሜሪካን ሀገር ከሚገኙ የስልጠና እና የትምህርት ተቋማት ጋር በመሆን የአካዳሚውን የአመራር ልማት ፕሮግራሞች መደገፍ እንደሚቻል ተናግረዋል።
በአሜሪካ ኤምባሲ የባህል ጉዳዮች ሀላፊ RYAN BRADEEN, Cultural Affairs Officer እንደገለጹት አፍሌክስ ሊሰራ ባቀዳቸው ፕሮጀክቶች ዙሪያ በአሜሪካን ሀገር ከፍተኛ አቅም እና ልምድ ያላቸው ተቋማት እንዳሉ ጠቅሰው፤ ወደ ፊት በሚደረጉ ውይይቶች ላይ በዝርዝር በመነጋገር የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን መደገፍ ይቻላል ብለዋል።
ምክትል አምባሳደሯ GWENDOLYN “WENDY” GREEN, Deputy Chief of Mission የአሜሪካው አምባሳደር Ervin Massinga ባጋጠማቸው አስቸኳይ ስራ ምክንያት በውይይቱ ላይ ባለመገኘታቸውም ይቅርታ ጠይቀዋል።
አቶ ዛዲግ አብርሃ ከ UNIDO ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ተወያዩ።
ርዕሰ አካዳሚው የተወያዩት ከአኡሬሊአ ፓትሪዚአ (Aurelia Patrizia Calabro, UNIDO Representative and Director of the Regional Office) እና አሰግድ አዳነ የ UNIDO ምክትል ተወካይ (Deputy UNIDO Representative) ጋር ነው ።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከከፍተኛ የስረ ሃላፊዎች ጋር በአፍሌክስ ሪፎርም፤ ሽግግር እና ማስፋት ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች ለሀላፊዎቹ አብራርተዋል።
ርዕሰ አካዳሚው አቶ ዛዲግ በገለጻቸው ላይ እንዳብራሩት አካዳሚው ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካውያን የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ እንደሆነ እና ይህንን ዓላማውን ለማሳካትም አራት የጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ቀርጾ በሶሰት ዓመት ውስጥ ለመፈጸም እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።
በተለይም ልዩ የኢንዱስትሪ አመራር ልማት ፕሮግራም መቀረጹን የጠቀሱት አቶ ዛዲግ ከUNIDO ጋር በመሆን የኢንዱስትሪውን ዘርፍ አመራር ለማብቃት እንሰራለን ብለዋል።
አቶ ዛዲግ አያይዘውም UNIDO በአመራር ልማት ፕሮግራሞች ቀረጻ፤ በአፍሌክስ አመራር ሽልማት እና በሀሳብ ማመንጫ ማዕከላት ግንባታ ላይ ከአፍሌክስ ጋር አብሮ እንዲሰራ ግብዣ አቅርበዋል።
አኡሬሊአ ፓትሪዚአ (Aurelia Patrizia Calabro, UNIDO Representative and Director of the Regional Office) በበኩላቸው በኢንዱስትሪ አመራር ልማት ፕሮግራም፤ በአፍሌክስ ሽልማት እና በሀሳብ ማመንጫ ማዕከላት ላይ የአፍሌክስ ፕሮጀክቶችን በቴክኒክ እና በባለሙያ መደገፍ እንደሚቻል ገልጸው፤ ለዚሁ የሚረዳ ዝርዝር ሀሳቦችን የሚያሳይ ፕሮፖዛል ለ UNIDO እንዲቀርብ ጠይቀዋል።
ዝርዝር የድጋፍ እና እገዛ ፍላጎቶችን የሚገልጽ ፕሮፖዛል ተዘጋጅቶ ለ UNIDO እንዲቀርብ በመስማማትም ውይይቱ ተጠናቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድን የሰባ አምስት ዓመታት ስኬታማ ጉዞ የሚያሳይ የመጀመሪያ ደረጃ የጥናት ምርምር ሪፖርት ቀረበ። ጥናቱን ያካሔደው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ሲሆን የአየር መንገዱ ስራ አመራር አባላት ተገኝተው ሪፖርቱን ገምግመዋል።
የጥናቱ ዋና ዓላማም የአየር መንገዱን የስኬት ምስጢር በሳይንሳዊ ጥናት እና ምርምር ማረጋገጥና ለሌሎች ተቋማት እንደ ግብዓት የሚሆን የጥናት ሪፖርት ማቅረብ እንደሆነ በመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ላይ ተመላክቷል።
የመጀመሪያ ደረጃ የጥናት ሪፖርት ሲገመገም በመድረኩ የተገኙት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ እንደተናገሩት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስኬት ታሪክ ለሀገራችን ስኬታማ ጉዞ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ቀላል እንዳልሆነ ጠቅሰው፤ አካዳሚው እንደ ኬዝ ጥናት ወስዶ ማጥናቱ ለአመራር ልማት ፕሮግራሞቹ ግብዓት ከመሆኑም በላይ ለሌሎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት የስኬት መንገድ ማሳያ ሊሆን እንደሚችል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
አቶ ዛዲግ አያይዘውም የተገኘው የጥናት ውጤት እንዴት እንደሚሰፋ እና በስራ ላይ እንደሚውል ሀሳብ የሰጡ ሲሆን፤ ከመድረኩ የተገኘውን ግብዓት በማካተት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ባለድርሻ አካላት ሊጠቀሙበት የሚችል ውጤታማና ተግባራዊ የጥናት ውጤት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።