African Leadership Excellence Academy
2.37K subscribers
2.58K photos
97 videos
6 files
120 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
አቶ ዛዲግ አብርሃ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ጋር ተወያዩ።
ለዋና ዳይሬክተሩ እና ለም/ል ዋና ዳይሬክተሩ ስለ አፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ሪፎርም፤ ማስፋትና ሽግግር በርዕሰ አካዳሚው ሰፊ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
አፍሌክስ አፍሪካዊ ስያሜ እና ተልዕኮ ቢኖረውም የሚጠበቅበትን ያህል እየሰራ እንዳልሆነ የጠቀሱት ርዕሰ አካዳሚው በሪፎርም፤ ማስፋት እና ሽግግር ስራዎቹ ውስጥ ተቋሙ አፍሪካዊ መልክና ይዘት እንዲኖረው እየሰራን ነው ብለዋል።
አቶ ዛዲግ አያይዘውም አፍሌክስን የአፍሪካ የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ ሱሉሉታን እንደ ዳቮስ የሚል ፕሮጀክት መቀረጹን ጠቁመው ሸገር ሲቲን ከዳቮስ ከተማ ጋር በእህትማማች ለማስተሳሰር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ስራ መጀመሩን ተናግረዋል። ባለስልጣኑ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን፤ ወርክሾፖችን፤ ሲምፖዚየሞችን እና ስብሰባዎችን በአፍሌክስ ውስጥ እንዲያደርግም ጋብዘዋል።
ለሲቪል ማህበረሰቡ የሚያገለግል የሀሳብ ማመንጫ ማዕከልም በአፍሌክስ ውስጥ በመገንባት የተሻለ ሀሳብ እንዲፈልቅ እና ችግሮችን ሊፈቱ የሚችሉ ጥናት እና ምርምሮች እንዲደረጉ አቶ ዛዲግ ግብዣ አቅርበዋል።
ባለስልጣኑ የሚመራቸውን እና የሚቆጣጠራቸውን የማህበረሰብ ድርጅቶችን በማስተባበር በአመራር ልማት ፕሮግራሞች በዲዛይን ቀረጻ፤ በአሰልጣኝነት እና በተመራማሪነት አፍሌክስን እንዲደግፍ አቶ ዛዲግ ጥሪ አቅርበዋል።
አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት የተሰጠው ሹመት የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ሲመክሩበት ቆይተው የወሰኑት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ሹመቶችን ባጸደቀበት ወቅት ነው፡፡

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)÷ ፓርቲው ከበርካታ እጩዎች ውስጥ ባላቸው ልምድ ኢትዮጵያን ማገልገል የሚችሉ እጩዎችን ወደ ፊት ለማምጣት የወሰነበት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በተለይም ከተሿሚዎች ውስጥ ሁለቱ ከብልጽግና ፓርቲ አባል ውጪ መሆናቸው ለኢትዮጵያ ቅድሚያ የተሰጠበት እና ልምድ እና እውቀት ብቻ መስፈርት የሆነበት መሆኑን አውስተዋል፡፡

ከየትኛውም ፓርቲ ቢሆን ልምድና እውቀት ያላቸውን ወደፊት ማምጣቱ እንደሚቀጥልም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ባለው የመተካካት ባህል የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሥራ አስፈፃሚነታቸው በክብር መሸኘታቸውን ተናግረዋል።

ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር ሆነው እንዲሾሙ የቀረበለትን ሹመት መርምሮ አጽድቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ
*********************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

1. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን – የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር
2. ትዕግስት ሃሚድ – የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከ UN Women ለመጡ የስራ ሀላፊዎች ስለ አፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ሪፎርም፤ ማስፋትና ሽግግር ሰፊ ገለጻ ተደረገላቸው።
ገለጻውን ያደረጉት የአፍሌክስ ፕሮግራም ዘርፍ ም/ል ርዕሰ አካዳሚ ተወካይ አቶ ጥላሁን አረጋ ሲሆኑ አፍሌክስ አስራ ሶስት ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ወደ ስራ እየገባ እንደሆነ እና በሀገራችን የነበረውን የስልጠና ስርአት ወደ አመራር ልማት ፕሮግራም ለማሳደግ የሶስት ዓመት ስትራቴጂ ቀርጾ እየሰራ ነው ብለዋል።
አካዳሚው የአፍሪካን እና የኢትዮጵያን አመራር ለማብቃት በሀገር ውስጥ ካሉ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር እየሰራ እንደሆነ የጠቀሱት አቶ ጥላሁን የሴቶችን አቅም በአመራር ልማት ፕሮግራም ለማጎልበትም ከሜሊንዳ እና ቢል ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በመሆን እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
ከ UN Women ጋር በመስራትም የአካዳሚውን ስትራቴጂያዊ የግንኙነት አድማስ ማስፋት እንደሚያስፈልግ እና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ትብብር ለመመስረት እንደሚፈልጉ የጠቆሙት አቶ ጥላሁን በቴክኒካል፤ በፕሮግራም እና በመሰረተ ልማት አብረው እንዲሰሩ ጥያቄ አቅርበዋል።
ከ UN Women የመጡት የልፍኝ አበጋዝ በበኩላቸው አፍሌክስ በሶስት ዓመት ውስጥ ሊተገብራቸው ያቀዳቸውን ፕሮጀክቶች አድንቀው በገለጻው ያገኙትን ግንዛቤ ለ UN Women ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በማጋራት እና በመነጋገር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር የሚቻልበትን ሁኔታ እንደሚያመቻቹ ተናግረዋል።
ከ UN Women የመጡት የስራ ሀላፊዎችም ለአፍሌክስ ግምታቸው ከሰባ ሺህ ብር በላይ የሆኑ መጽሀፍት በስጦታ ያበረከቱ ሲሆን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን ፋሲሊቲም ጎብኝተዋል።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከሲቪል ሶሳይቲ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ።
አቶ ዛዲግ አብርሃ በአፍሌክስ ሪፎርም(Reform)፤ ማስፋት (Scaling Up) እና ሽግግር (Transformation) ለሲቪል ሶሳይቲ ከፍተኛ አመራሮች ገለጻ አድርገዋል።
አፍሌክስ የጀመረውን የአመራር ልማት ፕሮግራም ለማሳካት የሲቪል ሶሳይቲ ድርጅቶች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ርዕሰ አካዳሚው ተናግረዋል።
አካዳሚው ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካውያን የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ እንደሆነ እና ይህንን ዓላማውን ለማሳካትም አራት የጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ቀርጾ በሶሰት ዓመት ውስጥ ለመፈጸም በመስራት ላይ እንደሆነም አቶ ዛዲግ ገልጸዋል።
ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ጋር በመሆንም በአመራር ልማት ፕሮግራም፤ በሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ግንባታ እና በአፍሌክስ ሽልማት ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ለመፈራረም መስማማታቸውንም አቶ ዛዲግ አብርሃ ጠቅሰዋል።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በበኩላቸው አፍሌክስ ይዞ የተነሳውን ራዕይ ለማሳካት ተቋማቸው ዝግጁ እንደሆነ ጠቁመው፤ ባለስልጣኑ የሚቆጣጠራቸው ሲቪል ሶሳይቲ ድርጅቶችም ከአፍሌክስ ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።
የሲቪል ሶሳይቲ ከፍተኛ አመራሮች ስለ አፍሌክስ ፕሮጀክቶች እና የአመራር ልማት ፕሮግራሞች በተደረገላቸው ማብራሪያ መደሰታቸውን ጠቅሰው፤ ለአካዳሚው የሚጠቅሙ ሀሳቦችን እና አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን እንዲብራሩላቸው ባነሷቸው ጥያቄዎች ላይም ርዕሰ አካዳሚው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።