African Leadership Excellence Academy
2.35K subscribers
2.56K photos
96 videos
6 files
120 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
# አሁን
*********************
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮች እና ሰራተኞች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ እየተወያዩ ነው።
ውይይቱ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን በሁለት አበይት ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር የአፍሌክስ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ምክትል ርዕሰ አካዳሚው ውይይቱ የተዘጋጀበትን ዋና ዓላማ ሲያብራሩም የአካዳሚው አመራር እና ባለሙያ ስለ አጠቃላይ ሀገራዊ እና ክልላዊ ከባቢያዊ፤ ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበራዊ እና የሰላም ሁኔታ ላይ በበቂ ሁኔታ ከመንግስት ጋር በመወያየት ለመፍትሔው የጋራ ርብርብ ማድረግ አስፈላ በመሆኑ ነው ብለዋል ።
ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) በውይይቱ ላይ እንዳብራሩት ሀገራችን እጅግ ከባድ ፈተናዎችን እየተጋፈጠች አንድነቷን አስጠብቃ የቀጠለች ፤ ተግዳሮቶችን ተቋቁማ በለውጥ ጎዳና ወደ ብልጽግና ለመሸጋገር ጥረት በማድረግ ላይ እንደሆነች፤ ሀገራዊ ኢኮኖሚውን ከፍጹም ቀውስ እና ከፍተኛ የእዳ ጫና ለመታደግ የሚያስችል ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ተግባራዊ መደረጉን እና የተጀመረው የለውጥ ጉዞ የኢትዮጵያውያንን ማህበራዊ መስተጋብር እና ትስስር በአዲስ ሀገራዊ ገዥ ትርክት ለመገንባት ፈር የቀደደ የለውጥ ጉዞ ላይ እንገኛለን ብለዋል።
ሀብት የመፍጠር ጉዞአችን ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች በሚል በዛሬው ዕለት ውይይቱ የተጀመረ ሲሆን በነገው ዕለትም በስልጡን ሲቪል ሰርቪስ ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግ ም/ርዕሰ አካዳሚው ጠቁመዋል።
የፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በትብብር ትላልቅ ድሎችን አስመዝግበዋል:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
****************

በፕሪቶሪያ ከተደረሰው የሰላም ስምምነት በኋላ፤ የፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በትብብር ትላልቅ ድሎችን ማስመዝገብ ችለዋል ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።

በስብሰባው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፤ በፕሪቶሪያ ከተደረሰው የሰላም ስምምነት በኋላ የተገኙት ድሎች የፌድራል መንግስቱ ለብቻው ያመጣቸው እንዳልሆኑ ገልጸው፤ ከትግራይ ክልል ጊዜያው አስተዳደር ጋር ተዳምረው የተገኙ አሙርቂ ውጤቶች ስለመሆናቸው ነው የተናገሩት።

የተገኘው ሰላም ካመጣቸው ድሎች ውስጥ የአየር ትራንስፓርት ወደ ትግራይ ክልል መጀመሩ አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለብዙዎች እፎይታ የሰጠ መሆኑንም አንስተዋል።

በክልሉ የስልክ እና የኤሌክትሪክ አገልግሎት መጀመሩን ገልጸው፤ በፌዴራል መንግስት እና በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ትብብር የትግራይ ህዝብ አገልግሎቶቹን እንዲያገኝ መደረጉን አብራርተዋል።
በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ፍላጎትን የማሳኪያ ስልት ልምምድ ሰላምን እየፈተነ ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
***************

ባለፉት 50 እና 60 ዓመታት ሃሳብ ይዞ በሃሳብ አሸንፎ ስልጣን የመያዝ ልምምዱ ያልታየ በመሆኑ እንደባህልም እየተወሰደ ያለው የፖለቲካ ፍላጎትን በጠብመንጃ የማሳካት ፍላጎት አንዱ አደገኛ ስብራት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት የሰላም ችግር መሰረቱ የፖለቲካ ፍላጎት ማሳኪያ መንገድ ላይ ያለው ልምምድ መሆኑን ተናግረዋል።

የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት በሚደረጉ ጥረቶች ውስጥም ቢሆን እንደሀገር ያለን ልምምድ በውይይት ወይም በሽምግልና ለመፍታት ያለው ልምምድ አንስተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

በእነዚህ ችግሮች ውስጥም ተሁኖ የሰላም ጅማሮዎች ሲኖሩ ደግሞ ከግራም ከቀኝም በሰላም መንገድ ላይ ወጥመድ ማስቀመጥ መኖሩ የሰላም ልምምዱ ወደ ኋላ እንዲመለስ የማድረግ ልምምዱም ከፍተኛ ነው ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ ጥር 28/2016(ኢዜአ)፦ የኢዩቤልዮ የታችኛው ቤተ- መንግሥት ዕድሳት በሶስት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ይህን ያሉት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከህዝብ ተወካዮች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ ነው። መንግስት የቱሪስት መዳረሻ ታሪካዊ ስፍራዎችን እሴት በመጨመር የኢትዮጵያን ልክና መሻት በሚያሳዩ መልኩ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

መንግስት የዳግማዊ ምኒልክ ቤተ-መንግስትን ዕዳሳት በማድረግ አንድነት ፓርክን ገንብቶ አሁን ላይ በመቶ ሚሊየኖች ገቢ እያስገኘ መሆኑን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በቀዳማዊ ኅይለሥላሴ የተገነባው ኢዩቤልዮ ቤተ- መንግሥት በጥራትና በፍጥነት እየታደሰ መሆኑን ገልፀዋል።

የታችኛው ቤተ- መንግሥት ዕድሳት ሲጠናቀቅ ከአዲስ አበባ ሊታዩና ሊጎበኙ ከሚችሉ ውብና ምርጥ የቱሪዝም መዳረሻዎች አንዱ ይሆናል ብለዋል።

በታችኛው ቤተ- መንግሥት ዕድሳት 3 ሺህ 400 ሰራተኞች የያዘ 13 ፕሮጀክት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው፤ ከሁለት ወይም ከሶስት ወራት በኋላ እንደሚጠናቀቅ ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት እና የጎንደር አብያተ መንግስታትን ጨምሮ ሌሎች ታሪካዊ ቅርሶችን ዕድሳት የማድረግ ጥረቶችንም አንስተዋል።
የዓድዋ ድል መታሰቢያ አርኪ የታሪክ ሀብት የያዘ ነው፡ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
***********************

የዓድዋ ድል መታሰቢያ በመጠኑ እጅግ የሚያኮራ እና በውስጡ አርኪ የታሪክ ሀብት የያዘ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መታሰቢያው እንኳን ኢትዮጵያዊ የትኛውም አፍሪካዊ ሀገር ዜጋ ጊዜ ወስዶ ቢመለከተው፤ በግዝፈቱ፣ በያዘው የታሪክ ሀብት እና በአካታችነቱ በዓርአያነት የሚወሰድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ለግላዊ እና ቡድናዊ ፍላጎቶች ሲባል መታሰቢያውን ለማራከስ እና ለማንኳሰስ የሚደረገው ጥረትም፤ ቀርቦ በማየት የሚቀለበስ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡
ድርቅን ለፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል የሚደረገው ጥረት ተገቢነት የለውም - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ጥር 28/2016 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ድርቅን ለፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል የሚደረገው ጥረት ተገቢነት የለውም ሲሉ ገለጹ።

ድርቅ በተለያዩ አከባቢዎች ተከስቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርቁ የሰው ሕይወት እንዳይቀጥፍ ተባብረን መስራት አለብን በማለት አሳስበዋል።

ነገር ግን ድርቁን ለፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል የሚደረገው ጥረት ግን ተገቢነት የለውም ነው ያሉት፡፡

ድርቁን ለመከላከል በሚደረገው ስራ ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው መንግስት እንደመሆኑ መጠን ድርቁን ለመከላከል ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ በማውጣት ሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እንዲሆን ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

መንግስት በቀጣይም ፕሮጀክቶችን በማጠፍም ጭምር ድርቁ በዜጎች ህይወት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የሚሰራ ይሆናል ነው ያሉት፡፡
ኢትዮጵያ በዓለም ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ካሉ አገራት አንዷ ናት፡፡ በዘንድሮው ዓመትም በኢትዮጵያ የ7 ነጥብ 9 በመቶ እድገት ይጠበቃል፡፡ በተለይ በግብርና ዘርፍ እጅግ ውጤታማ ስራ ተከናውኗል፤ በፊስካልና ሞኒተሪ ፖሊሲ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችም ከፍተኛ ለውጥ እያስመዘገቡ ነው፡፡
የጠዋቱ ውይይት እንደቀጠለ ነው። አሁን ጊዜው የጥያቄ እና የአስተያየት ነው።
አቶ ታሪኩ ተረዳ ባነሱት ሀሳብ ላይ እንደገለጹት ሀብቶቻችንን በአግባቡ መጠቀም የምንችለው ያለንን ብዝሀነት በአግባቡ ማስተናገድ ስንችል ነው። የማንነት ጥያቄዎችንም በአግባቡ ለመፍታት አሉታዊ ትርክቶችን በሚያግባባ ገዥ ትርክቶች በማስተካከል ዕድሎችን በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል። በብዝሀነት ውስጥ ያለውን አንድነት ማክበር ያስፈልጋል። አካታችነትን መሰረት ያደረጉ እንደ አድዋ ዜሮ ዜሮ ያሉ ፕሮጀክቶች አንድነትን የሚያጠናክሩ እና ብዝሀነትን የሚያከብሩ በመሆናቸው ሊበረታቱ ይገባል። በአማራ ክልል የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር በውይይት ለመፍታት ጥረት መደረጉ የሚበረታታ ነው።
የጠዋቱ ውይይት እንደቀጠለ ነው። አሁን ጊዜው የጥያቄ እና የአስተያየት ነው።
አቶ አልአዛር ፈንታው በበኩላቸው አገራችን ለውጡን ካስተናገደች በሁዋላ ተስፋ ሰጭ የነበሩ ሁኔታዎችን በአግባቡ ባለመጠበቃችን እና ባለመንከባከባችን የሀዘን እና የችግር ጊዜ እያሳለፍን ነው። በየቦታው በሚፈጠሩ ችግሮች በበርካታ ወገኖቻችንን እያጣን ነው። ይህ እስከመቼ ነው የሚቀጥለው? በሲቪሊያን ላይ የሚደርሱ ሞቶች እና ጉዳቶች ያሳስቡኛል። ችግሮቻችንን ለመፍታት ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው። የሚከፈለውን የሰላም ዋጋ በመክፈል ወደ ሰላም ለመምጣት መስራት ይገባናል። ችግሮችን መሸፋፈናችን ዋጋ እያስከፈለን ነው። ከሩዋንዳ ብዙ መማር ይገባናል። ችግራችንን ለመፍታት ከዚህ የተሻለ ጊዜ ከየትም አይመጣም። ወጥቶ ለመግባት ስጋት ላይ ነን።
የኑሮ ውድነቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። መንግስት ትኩረት መስጠት ይኖርበታል። የዲፕሎማሲ ስራው ላይ መንግስት በስፋት በመስራት የዓለምን ሀሳብ መግዛት ይኖርበታል። የባህር ወደብ እንደሚያስፈልገን ቢታመንም ልናገኝ የሄድንበት መንገድ ሁሉንም የሚያግባባ መሆን አለበት።
የጠዋቱ ውይይት እንደቀጠለ ነው። አሁን ጊዜው የጥያቄ እና የአስተያየት ነው። አቶ አማረ በበኩላቸው ከዚህ ቀደም ሀገራችን አስያውያንን እና አፍሪካውያንን ትረዳ ነበር። አሁን ግን ሀገራችን ውስጥ ያለው ሰላም አሳሳቢ በመሆኑ ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት መስራት ይገባል።
በየክልል መንግስታቱ ያለው ግንኙነት አንድነትን የሚተርክ ትርክት አላቸው ወይ? ወደ አንድነት የሚያመጡ ትርክቶች ላይ መስራት ችግሩን ሊፈታ የሚችል ይመስለኛል።
ሌብነት ዋነኛ መለያችን ሆኗል። መንግስት በሌቦች ላይ ተግባረዊ እና አስተማሪ እርምጃ ካልወሰደ በቀር ሌባ የማያፍርባት ሀገር እየፈጠርን ነው።
የጠዋቱ ውይይት እንደቀጠለ ነው። አሁን ጊዜው የጥያቄ እና የአስተያየት ነው።አቶ ሲሳይ ዘሪሁን ባነሱት ሀሳብ የግብርና ስራችን ላይ የሚመለከታቸው ሁሉ ምርታማነት ላይ ትኩረት ሰጥተው መስራት አለባቸው። ያለንን የውሀ ሀብትና የሚታረስ መሬት በአግባቡ ባለመሰራቱ የኑሮ ውድነቱ እየባሰ ነው። ምርታማነትን በሚያሳድጉ ስራዎች ላይ በመስራት የሀገራችንን ኢኮኖሚ ማሳደግ ይቻላል።
የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለመፍታትም የኢንዱስትሪው ሚና የላቀ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት ይገባል። የሰርቪስ ዘርፉም ሊሻሻል እና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ሊደግፍ በሚችል መልኩ ሊሰራበት ይገባል።
የህግ የበላይነትን ለማስከበር መንግስት መስራት አለበት። የሰላም ችግሩ ከቤተሰብ አራርቆናል። መንግሰት ጥያቄ አለን የሚሉ እና ነፍጥ አንግበው ጫካ የገቡትን ወደ ጠረጴዛ ውይይት መጋበዝ አለበት።
የጠዋቱ ውይይት እንደቀጠለ ነው። አሁን ጊዜው የጥያቄ እና የአስተያየት ነው። አቶ አዲሱ ኡርጌሳ በበኩላቸው እናታችን ችግር ውስጥ ናት ግን ደግሞ በእናት ተስፋ አይቆረጥም። ተጋግዘን ሀገራችን ከገባችበት ችግር ውስጥ እንድትወጣ መስራት ይገባል። በሀገራችን ጨለማም ብርሀንም አለ ስለ ሁሉም በሚዛን ነው ማውራት ያለብን። ሁላችንም የመፍትሔው አካል መሆን አለብን።
የጠዋቱ ውይይት እንደቀጠለ ነው። አሁን ጊዜው የጥያቄ እና የአስተያየት ነው። አቶ ሲሳይ ከፍያለው በሰጡት አስተያየት ሰላም በንግግር ብቻ አይመጣም። የኢኮኖሚ ዕድገትም በንግግር ብቻ አይመጣም። ሁላችንም ወደ ተግባራዊ ሰላም እና የኢኮኖሚ ዕድገት እንድንመጣ ከመንግስት ጎን መቆም አለብን። ከፋፋይ ሀሳቦችን እና ትርክቶችን በመታገል ሀገራዊ አንድነታችንን ማጠናከር ይገባል። በተለያዩ መንገዶች ተደራጅተው ሰላማችንነ የሚያውኩትን በመለየት ለሰላም የድርሻችንን መወጣት ይገባል።
የጠዋቱ ውይይት እንደቀጠለ ነው። አሁን ጊዜው የጥያቄ እና የአስተያየት ነው። ወ/ሮ ዘውድ እሸት በበኩላቸው ሁሉም የሚጠበቅበትን ማድረግ አለበት። ባልተገቡ ድርጊቶች እና በአፍራሽ ሀይሎች ሴራ መጠለፍ የለብንም። ያለችን ሀገር አንድ ናት ሁላችንም ተደምረን ለሀገር ዕድገት እና ሰላም መስራት ይገባል። መንግስትን ደግፈን መቆም ቢያቅተን እንኳን ለውጡን እና የለውጡን ሀይሎች ባናደናቅፍ የሚል ሀሳብ አለኝ።
በውይይቱ ማጠቃለያው ላይ ተገኝተው ሀሳብ የሰጡት የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ተወካይ አቶ ጥላሁን አረጋ በበኩላቸው መንግስት ነጠላ ትርክትን በገዥ ትርክት ለመተካት እና አካታች የሆኑ ሀገራዊ ትርክቶች ላይ እየሰራ ነው። ሀገራዊ የኩራት ምንጮቻችንን እንደ ገዥ ትርክት በመውሰድ አዎንታዊ ተግባር ላይ በመሳተፍ ለሀገራችን ሰላም በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
ፍትሀዊ የኢኮኖሚ ዕድገቱን ለማረጋገጥም በስራው ላይ የሚጠበቅብንን በማድረግ ተስፋ ሰጭ ስራዎች ወደ ዳር እንዲደርሱ መትጋት ያስፈልጋል ብለዋል። የፖለቲካ፤ የማንነት፤ እና የፍትሀዊ ሀብት ክፍፍል ጥያቄዎች የሚፈቱበትን መንገድ መንግስት እየፈጠረ ነው። ህዝቡን ማዕከል ያደረገ የሰላም ማስከበር ስራ ለመስራት መከላከያ ሰራዊታችን እየሞከረ ነው። በየትኛውም ወገን ያለ አካል ለንግግር እና ለውይይት ራሱን ማዘጋጀት አለበት። መንግስት ሆደ ሰፊ ሆኖ ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት የጀመረውን መንገድ አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
የአፍሌክስ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) በበኩላቸው ከአካዳሚው አመራሮች እና ሰራተኞች ለተነሱት ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ሰላም የሁላችንም ናት በጋራ ልንጠብቃት ይገባል። ባለፉት ዓመታት ያጋጠሙንን ችግሮች ለመፍታት መንግስት ብዙ ርቀት ሄዷል። በውስጣችን ያሉ የተዛቡ የታሪክ አረዳድ እና ትርክቶች እንዲታረሙ መንግስት ገዥ እና ታላቅ አገራዊ ትርክት እንዲኖረን እየሰራ ነው ብለዋል።
በሀገራችን ያለውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት መንግስት አሳታፊ የሰላም መንገዶችን እየፈጠረ ነው። ከታጣቂ ሀይሎች ጋር የሰላም ድርድር እና ውይይት ለማድረግ መንግስት ቁርጥ አቋም አለው። የኑሮ ውድነቱን ለመቅረፍም መንግሰት እየሰራ ነው ብለዋል።
ክላስተር አስተባባሪው እና ፕሮጀክት ዳይሬክተሩ ስለ አፍሌክስ ሪፎርም፤ ማስፋትና ሽግግር በተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው ከአፍሌክስ ጋር አብረው ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በአመራር ልማት ፕሮግራሞቹ ቀረጻ ላይ ድጋፍ እንደሚያደርጉ የጠቀሱት ክላስተር አስተባባሪው ስቴፋን ሊድስባ Stephan Lidsba, cluster coordinater for climate change ሲሆኑ በሌሎች የአፍሌክስ ፕሮጀክቶች ላይ አብሮ ለመስራት ሰፊ ውይይት እንደሚያስፈልግ ጠቁመው በተለይም የሀሳብ ማመንጫ ማዕከላት ግንባታው ላይ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በኩል ድጋፍ ማድረግ የሚቻልበት ዕድል እንዳለ ተናግረዋል።